Wolkite University Registrar


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


It is the official telegram channel of Wolkite University Registrar Directorate.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri








የተስተካከለ የጥር 30 መውጫ ፈተና REVISED EXIT EXAM SCHEDULE (ጥር 30)


#ይነበብ

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከነገ ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ/ም ይጀምራል።

ለመሆኑ በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እንዲሁም ከፈታኞች ምን እጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

- ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

- ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

- ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን
ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

- ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

- ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

- ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

- በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

- ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

- ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

- ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

NB. ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]

- የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

- ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

- በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

- የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

- በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

- ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

- ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

- ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

- ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ: 2017 ዓ/ም






በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 አጋማሽ የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ከላይ በተያያዘው ፕሮግራም መሰረት የተመደባችሁበትን የፈተና ቀን፣ሰዓት እንዲሁም የመፈተኛ ቦታ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡ ስለዚህ ከፈተናው ሰዓት 30 ደቂቃ ቀድማችሁ እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፡ ለፈተና ስትመጡ ማንኛውንም የኤለክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ ሰዓት…) መያዝ አይፈቀድም፡፡


EXIT_EXAM_MID_Schedule_2017.pdf
168.4Kb
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የ2017 አጋማሽ የመውጫ ፈተና ፕሮግራም


ማስታወቂያ
የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመዉጫ  ፈተና (Exit Exam) ጊዜን በድጋሚ ስለማሳወቅ
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም መሆኑን ከዚህን በፊት መግለጻችን ይታወሳል፡፡ በመሆኑም ፈተናውን ለመፈተን የተመዘገባችሁ ተፈታኞች (አዲስና በድጋሚ ለመፈተን ያመለከታችሁ በሙሉ) ፈተናው የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ መኑን በድጋሚ ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር


Ministry of Education Ethiopia dan repost
በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የምዝገባ ጊዜ የሚጠናቀቀው ነገ ጥር 14/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።


Subject: Preliminary Exam Schedule for Huawei ICT Competition (Northern Africa 2024-2025 - Ethiopia)

Dear Huawei ICT Competition 2024-2025 Practice Competition Participants,

This is to inform you that the exam time for the Huawei ICT Competition (Northern Africa 2024-2025 - Ethiopia) Practice Competition (Network Track, Cloud Track, and Computing Track) is scheduled as follows:

🔔Date: Wednesday, January 22, 2025
The Exam.will be Active from:

   ➡️9:00 AM - 5:59 PM
   ➡️3:00-11:59Local time(Ethiopia)
➡️Each one has two trials for this stage

➡️Exam Place: Online
➡️Exam Duration:90Minute
🔔The National final exam will be in March,2025 and we will announce the exact exam date.
Please ensure you are prepared and ready to log in on time.


For any support, please contact your university’s Huawei ICT Academy Administrator, Huawei ICT Academy Instructors, or Huawei ICT Academy Ambassadors.

If you have further questions or require additional information, feel free to reach out.
Best regards,
Tamire Dawud.
ICT Ecosystem Development Manager.
Huawei Technologies Ethiopia.


በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።



11.4k 0 141 51 53

05/05/2017 ዓ.ም
በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለተመደባቹህ የሪሜዲያል (REMEDIAL) ተማሪዎች በሙሉ

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ለሪሜዲያል (REMEDIAL) የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 26-27/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት በአካል በመገኘት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ትምህርት የሚጀመረው ጥር 28/2017 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትመጡ የሚከተሉትን ይዛችሁ መምጣት ይጠበቅባችኃል፡፡
1ኛ. መሰናዶ ያጠናቀቃችሁበትን ሰርተፍኬት፣ ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት፣ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውን ከማይመለስ አንድ ኮፒ ጋር እና አራት 3x4 ጉርድ ፎቶ ግራፍ፡፡
2ኛ. አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ጨርቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ እናሳስባለን፡፡
3ኛ. ይህንን የመግቢያ ጊዜ አሳልፎም ሆነ ቀድሞ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው የማያስተናግድ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ዳይሬክቶሬት

9.5k 0 122 12 50

ማስታወቂያ
e-SHE ኮርስ ላይ ያልተመዘገባችሁ አንደኛ ዓመት መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ኤሌክትሮኒክ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ከቀን 23/04/2017 ዓም እስከ 25/04/2017 ዓም
ለተከታታትይ ሶስት ቀናት የተቋማዊ ኢሜል አድራሻ ማስተካከልና እና የe-SHE መስመር ላይ (SSS) ኮርስ ምዘገባ
መርሃ ግብር እንደነበር ይታወቃል። ነገር ግን አንዳንድ ተማሪዎች በተለያዩ ምክንያት እስካሁን ድረስ የተቋማዊ ኢሜል
ያላገኛችሁና ኢሜል አልሰራ ያላችሁ ተማሪዎች እስከ 06/05/2017 ዓም ድረስ ብቻ ኤሌክትሮኒክ ትምህርት
አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት በአካል በመምጣት እንድትመዘገቡ በጥብቅ እናሳስባለን። ከተጠቀሰው ቀን ውጪ
የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን።

የኤሌክትሮኒክስ ትምህርት አስተዳደር ክፍል ዳይሬክቶሬት
                 





18 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.