በ2017 የትምህርት ዘመን ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደቡ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች አጠቃላይ ገለፃ እና የህይወት ክህሎት ስልጠና ተሰጠ፡፡
ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው የሚኖራቸው ቆይታ ጊዜን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተነገራቸው፡፡
****
በስልጠና መርሃ ግብር ላይ የተገኙት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተለለፉት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር አክበር ጩፎ ዩኒቨርሲቲው ተማሪዎችን በሚያስፈልጋቸው የትምህርት ሥራዎች ሁሉ ለማገዝ ብቁ መምህራን የተዘጋጁ መሆኑን ጠቁመው ተማሪዎቹም ከራሳቸው የሚጠበቀውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡
የዘንድሮ የፈተና አሰጣጥ ሙሉ በሙሉ (100%) ከትምህርት ሚኒስቴር በሚወጣው ጥያቄ መሰረት እንደሚሆን የገለጹት ዶ/ር አክበር የማለፊያ ውጤት ለማምጣት ተማሪዎች፣ መምህራን እንዲሁም ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ጥራት ያለው ትምህርት እንዲሰጥና የተማሪዎች አገልግሎት አሰጣጥ የተሳለጠ እንዲሆን ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
ዶ/ር አክበር አክለውም ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው በሚኖራቸው ቆይታ ሳይረበሹ ጊዜያቸውን በአግባቡ በመጠቀም የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዳለባቸው ተናግረው በተማሪዎቹ አመርቂ ውጤት አስመዝግበው የተሳካ ጊዜን እንዲያሳልፉ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል፡፡
በዩኒቨርሰቲው የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት ተማሪ ተስፋጽዮን መድኅን ዩኒቨርሲቲ ዕውቀት የሚጋራበት እና ተማሪዎች ራሳቸውንና ሕይወታቸውን በአግባቡ ለመምራት ክህሎት የሚያገኙበት ተቋም መሆኑን ጠቅሶ አዲስ ወደ ዩኒቨርሲቲው የተመደቡ ተማሪዎች በመልካም ድስፕሊን ታንፀው ጥሩ ዉጤት ለማስመዝገብ መስራት እንዳለባቸው መክሯቸዋል፡፡