Addis Ababa Education Bureau

Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan

ይህ ቻናል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቴሌግራም ቻናል ሲሆን በከተማ አስተዳደሩ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የተከናወኑ እንዲሁም ሀገራዊ ፣ አህጉራዊ እና አለማቀፋዊ የትምህርት መረጃዎች ተደራሽ የሚደረጉበት ነው፡፡

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri

በትምህርት ቤቱ በነበረው የማስጀመሪያ መርሀ ግብር የአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አስፋው ኩማን ጨምሮ የአራዳ ክፍለ ከተማ ዋና አፈጉባኤ አቶ ደሳለኝ አገኘው እና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ ደበሌ የተገኙ ሲሆን ለተማሪዎች ደብተር እና ዩኒፎርምን ጨምሮ ሌሎች ቁሳቁሶች ተሰራጭቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: @addisababaeducationbureau9728' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- @aaeducationbureau' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በዛሬው እለት በይፋ ተጀመረ።

(መስከረም 6/2017 ዓ.ም) ትምህርቱ በሁሉም የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች የተጀመረ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች ጋር በመሆን የመማር ማስተማር ሂደቱን በድምቀት አስጀምረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በዳግማዊ ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርቱን ባስጀመሩበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ ለሚገኙ አጠቃላይ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ለ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እንኳን በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት በ2016 ዓ.ም የነበሩንን ጠንካራ ጎኖች በማስቀጠል ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ አክለውም በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት ተማሪዎች ለትምህርት አገልግሎት ከሚጠቀሙባቸው የመማሪያ ቁሳቁሶች ባሻገር የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን ይዘው መምጣት እንደማይችሉ ጠቁመው ቢሮው በ2017 ዓ.ም የትምህርት አመት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አመላክተዋል።

የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

(መስከረም 6/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ማድረግ የሚኖረዉን ጠቀሜታ እና በቀላሉ በሰራተኞች ሊተገቡ የሚችሉ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ሰነድ በወ/ት ኤልሳቤት በዮራ በቢሮ የስፖርት ባለሙያ አማካኝነት ከቀረበ እና ሰራተኞች ቀላል የሚባሉ የስፖርት እንቅስቃሴዎችን በተግባር እንዲያሳዩ ተደረጋል፡፡

በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ምግባርና ጸረ ሙሰና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አስራት ሽፈራው በተግባር የተገለጸ እና ብቁና ንቁ እንዲሁም ጤናማ ለመሆን የሚያግዝ እውቀት መሸመት የተቻለበት የዕውቀት ሽግግር መድረክ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም እንኳን ለመውሊድ በዓል  አደረሳችሁ እያልኩ በዓሉ   የሰላም ፣ የፍቅር ፣ የጤና  እና የመረዳዳት እንዲሆን  እመኛለሁ፡፡

                                                                                                 አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: @addisababaeducationbureau9728' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- @aaeducationbureau' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1 ሺህ 499ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

(መስከረም 5/2017 ዓ.ም) በዓሉን ስናከብር የነብዩ መሐመድ የፍቅርና የአብሮነት አስተምሮትን በመተግበር ምንጊዜም እንደምናደርገው ለወገኖቻችን ያለንን ፍቅር የምንገልፅባቸውን የበጎነት ፣ የልግስናና የቸርነት ተግባራትን በማከናወን ፤ አብሮነትን ፣ ወንድማማችነትንና መተሳሰብን በማጠናከር ሊሆን ይገባል።

ከዚህም ጎን ለጎን በከተማ አስተዳደሩ የፊታችን ሰኞ የምንጀምረውን የ2017 የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ስራ ውጤታማ እንዲሆን የሚጠበቅብንን ሁሉ በማድረግና እጅ ለእጅ ተያይዘን ለላቀ አፈጻጸም በመትጋትም ጭምር መሆን ይኖርበታል፡፡

በ2016 የትምህርት ዘመን ካስመዘገብናቸው አፈጻጸሞች በመነሳት በ2017 የትምህርት ዘመንም በቅንጅታዊ አስራር ፤ በመሰናሰልና በትጋት በመስራት የላቀ አፈጻጸም እንዲመዘገብ እንደምናደርግ ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡

የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሰኞ መስከረም 6/1/2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

(መስከረም 4/2017 ዓ.ም) ለትምህርት ባለድርሻ አካላት በሙሉ እንኳን ለ2017 የትምህርት ዘመን አደረሳችሁ እያልን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን ትምህርት ሰኞ መስከረም 6/1/2017 ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ቤቶች የሚጀመር መሆኑን እንገልጻለን፡፡

መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን እንመኛለን፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: @addisababaeducationbureau9728' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- @aaeducationbureau' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

43.1k 1 831 36 316

በስትራቴጂክ እቅዱ የሁሉም ባለድርሻ ተግባርና ኃላፊነት በዝርዝር በመቀመጡ የውይይቱ ተሳታፊዎች በተቀመጠላቸው ተግባር መሰረት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ በመወጣት ተማሪዎችን በሁለቱ የትምህርት አይነቶቹ ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ የተዘጋጀ ስትራቴጂክ እቅድ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በሆኑት በዶክተር ቢኒያም አወቀ አማካይነት በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ከመካሄዱ ባሻገር የተለያዩ አስተያየቶችና ጥያቄዎች የተነሱ ሲሆን ለቀረቡ ጥያቄዎች በኃላፊዎች ምላሽ ተሰቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: @addisababaeducationbureau9728' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- @aaeducationbureau' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ በተዘጋጀው ስትራቴጂክ እቅድ ዙሪያ የሚደረገው ውይይት ዛሬም ቀጥሎ ተካሂዷል።

(መስከረም 4/2017ዓ.ም) በዛሬው ውይይት የክፍለ ከተማ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎችን ጨምሮ የወረዳ ስርአተ ትምህርት ቡድን መሪዎች እና በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የተማሪዎች ውጤት ከጊዜ ወደ ጊዜ መሻሻል እያሳየ እንደሚገኝ እና ዘንድሮ በ12ኛ ክፍል ውጤትም በአዲስ አበባ ደረጃ 21.4% ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ከማስመዝገባቸው ባሻገር በ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተስፋ ሰጪ ውጤት መመዝገቡን አስታውቀዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊው አያይዘውም የተማሪዎች ውጤት መሻሻል እያሳየ ቢገኝም በሒሳብና እንግሊዘኛ የትምህርት አይነቶች የሚፈለገው ውጤት እየተመዘገበ ባለመሆኑ ቢሮው ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ እንዲሆኑ ስትራቴጂ ነድፎ ወደ ተግባር መግባቱን ጠቁመው ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ መሆን ከቻሉ በሌሎች የትምህርት አይነቶች የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ በስትራቴጂክ ዕቅዱ የተቀመጡ ዝርዝር ጉዳዮችን መሰረት በማድረግ ወደተግባር መግባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በበኩላቸው ስትራቴጂው በ2016 ዓ.ም በየትምህርት አይነቱ የነበረውን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ውጤት ትንተና መነሻ አድርጎ መዘጋጀቱን ገልጸው

የቢሮው የአፋን ኦሮሞ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ባለሙያ አቶ ፍሰሀ አለማየሁ በበኩላቸው የመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች በትምህርት አይነቱ በተዘጋጀው የተማሪዎች የመለማመጃ ደብተርም ሆነ በመምህር መምሪያ ይዘት ላይ በቂ ግንዛቤ ይዘው በየትምህርት ቤቱ በተመሳሳይ ሁኔታ የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩ ገልጸው ቢሮው በቀጣይ በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመገኘት አተገባበሩን የሚከታተል መሆኑን አስገንዝበዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

Imo: - https://s.channelcom.tech/vlWdNr?from=TG
What Sapp: - https://whatsapp.com/channel/0029VaHFiBpA2pLF0lLslK2D
flickr :- https://www.flickr.com/photos/197652854@N04/
You Tube: @addisababaeducationbureau9728' rel='nofollow'>https://www.youtube.com/@addisababaeducationbureau9728
TikTok፡- @aaeducationbureau' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@aaeducationbureau
Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau
Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc
Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication
Blog: - http://www.aacaebc.wordpress.com/
Instagram: - https://www.instagram.com/aacaeb/
Website: - aaceb.gov.et
Email;- aacaebc@gmail.com

12 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.