👆በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
እንዴትሰነበታችሁ የልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቦች እንዴትሰነበታችሁ በየአላችሁበት የእግዚአብሔር ሠላም ከእናንተ ጋር ይሁን። እግዚአብሔር ፈቃዱ ይሁንልና ሰሞኑንን አንድ የዩቲዩብ ቻናል ላይ የተለቀቀ የሚዘዋወር ቪዲዮ አለ ስለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ተናገሩ ከበረሃ አባቶች የሚል ነገር እየተዘዋወረ ነው ግን ይኼን መልዕክት በደንብ ከሰማችሁት መልካም የሚመስል ነገር ግን በማር የተለወሰ መርዝ ስለሆነ ባታጋሩ መልካም ነው።እስኪ አንዳንድ ነገሮችን እናንሳ የሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ውግዘት ውግዘቱ የተካሄደው በአባ ጳውሎስና በሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው መካከል ብቻ እንደሆነ ይናገሩ ።ግን ውግዘቱ እንደዚያ ነው የሚለው? አይደለም በተዋረድ ከሲኖዶስ ጀምሮ እስከ ምዕመን የሚመጣ ነው እናንተም እንደምታውቁት በድምጽ አለ ተመልሳችሁ ስሙት ለማስታወስ ያክል በራሳችሁ በሊቀ ሊቃውንት አያሌው አንደበት ።
ሁለተኛ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ገና አልተቀባም አሉ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ከተቀባ ሌሎች በንጉሥ ማዕረግ ያሉ ሁሉ አብረው ያሉ እንደተሾሙ ነው እኛ ከእግዚአብሔር በእግዚአብሔር ባሮች በራሳቸው አንደበት የተነገረን ወደዱም ጠሉም ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ከተቀቡ ቆዩ ጊዜያትም አልፈዋል። እነዚህ ሰዎች አሁን ካለው ከአጥፊው ከቤተክህነት መዋቅር ያልተላቀቁ ናቸው ብዙ ነገር ስለአለው ጥንቃቄ ብናደርግና አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ የተናገረ ሁሉ እውነተኛ አይደለምና ጥንቃቄ አድርጉ።በአደባባይ ይውጡ እንወቃቸው ይላሉ እንነጋገር ይላሉ እኛ በአባቶች በኩል የተነገረን የክርክር ጊዜ እንዳበቃ ነው። ስለዚህ እባካችሁ ሁሌም አንድ ሰው እየመጣ ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ እየመጡ በተናገሩ ቁጥር የነሱን ንግግር የምናስተጋ አንሁን።ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ እነ መምህር ዶ/ር ዘበነ ፣እነ መምህር መስፍን፣ይኼ ዘመድኩን የሚባል የኢትዮጵያ ትንሳኤ በ2015 ዓ.ም ይሆናል ንጉሡ በ2015 ይመጣል እያለ ብዙውን ሰው ጊዜ እየገደበ ሲያሰናክል የቆየ ፣ይቺ ስንዱ የምትባል ሳይቀር የዛር መንፈስ የሚጫወትባት ጭምር ፣ባህታዊ ነኝ የሚሉ መምህር ገብረ መስቀል የሚባሉት ፣ ሌሎችም ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ይናገራሉ ዳር ዳር ይዞራሉ ግን እውነተኛ አይደሉም በጎን የእግዚአብሔርን እውነት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክትን የሚነቅፉ የሚተቹ በተቃራኒ የቆሙ ናቸው።ስለዚህ እነዚህ ትምህርት ሊሆኑን ይገባል አብዛኛዎቹ የራሳቸውን ፈቃድ እንጅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ አይደለም የሚናገሩት። የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ስለኢትዮጵያ ትንሳኤ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ከእናንተ የበለጠ እግዚአብሔር ስለሚያደርገው ነገር በአባቶች በባሮቹ በኩል ምስጢር የገለጸለት እንዲያውቅም ያደረገው የለም።
ትናንት ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሚባል የለም የጅል ስብስብ ነው እያሉ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው ሲሉ የነበሩ እኛ ቸሩ መድኃኔዓለም ክብር ይግባናው የዓለም ብርሃን አይደለም ያልን ይመስል ለምን እንዲህ እንደተባለ ሳይረዱ በራሳቸው በሥጋ ስሜት እየተነዱ የፈለጋቸውን እየተናገሩ ሲያስቱ ቆዩ ዛሬ ያኔ የተናገሩትን እያስተጋቡ እንደ አዲስ ያሉ አሉ።አንዳንዶች ደግሞ ዛሬ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ልክ ነው እያሉ መጠዋል ግን ደግሞ እኛን የሚተች ነገር በአባቶቻችንን እውነተኛዎቹ የዚህ መልዕክት አስተላላፊ አይደሉም የማለት ያክል የሚመስል ንግግር እየተናገሩ ነው።ልብ በሉ በፊት መልእክቱን አዲስ ሃይማኖት :አሁን ደግሞ መልዕክት እንደሆነ እና ትክክል እንደሆነ ግን አስተላላፊዎች ትክክለኛ እንዳልሆኑ የሚመስል እየተናገሩ ነው ።አንዱ አልሳካ ሲል ሌላ ሊበሏት ያሰቧትን ምን እንደሚባለው...
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት አባቶቻችን ማስተላለፍ የጀመሩት በ1998 ዓ.ም ነው የተላለፈውም ለአዳም ዘር በሙሉ ነው ዛሬ አዲስ የመጣ ይመስል ሥራቻችን አጓተቱ ይላሉ።እኛ ዛሬ ሰምተን እንዲህ የገረመን ቀዳይ የሥላሴ ባሮች ምን ይሰማቸው ይሆን እጅግ የሚገርም እኮ ነው።
ስለዚህ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች አዲስ ነገር በመጣ ቁጥር የምንሮጥ አንሁን።ይሄን የምለው በየማህበራዊ ሚዲያው ስታጋሩ ስታሸራሽሩ ስለምናይ ነው።
ልታውቁት የሚገባ ነገር እዚህ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ገጽ ላይ ተሰግስገው ተደብቀው የሚሰሙና እዚህ እየወሰዱ የሚመቻቸውን ብቻ እየወሰዱ የሚናገሩ አሉ ።እኛ የምንጠቀምባቸው ምስሎች ሁሉ እየወሰዱ የሚጠቀሙ አሉ። ወደ ፊት የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክትን በገሃድ እየተናገሩ የሚመጡ ይኖራሉ ጥንቃቄ አድርጉ። አንዳንዶች ደግሞ ተሰንገው ተገደው የሚናገሩ ይመጣሉ አምነውበት አይደለም ተገደው በየሚያዲያ ጣቢያው ሁሉ ይለፈልፋሉ ያን ካላደረጉ እረፍት እንቅልፍ ስለማያገኙ ይኼ ደግሞ በመልዕክታቱ ተነግሯል ይሄን ከወዲሁ ተረዱ።የሚገርመው ደግሞ የእግዚአብሔር ፍርድ ሲጀምር ሁሉ በየአፉ ብለን ነበር ተናገረን ነበር ማለት ጀምሯል መናፍቃን እንኳ ሳይቀር ተናግረን ነበር እያሉ ማለት ጀምረዋል እነሱን ብሎ ትንቢት ተናጋሪ።
ስለዚህ ወገኖቼ ጊዜ ካላችሁ የማንም ነገር እያያችሁ ጊዜ ከምታጠፉ የእግዚአብሔርን እውነት ተመልሳችሁ ስሙ እራሳችሁን ለእግዚአብሔር አገልግሎት አዘጋጁ ለዚያ የሚገባ ሰው እንድትሆኑ እግዚአብሔርን ጠይቁ እንጠይቅ እንለምን።ወርቅ እጃችን ላይ እያለ ሌላ ፍለጋ አንሂድ የእግዚአብሔር እውነት አንድ የቤተ-ክህነት ሰው ነኝ ባይ ስለተናገረ ስለአልተናገረ አይደለም እውነትነቱ የሚጸናው የእግዚአብሔር እውነት እውነት ነው ማንም ሊቀይረው አይችልምና ነው።
ቀዳማዊ የእግዚአብሔር ባሮችና እኛም የመንፈስ ልጆቻቸው ቤተሰቦቼ የሚሉን በስሜታዊነት ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ በገሃድ እንድንገለጥና ለማወቅ የሚደረግ ጥረት ይመስላልና ጥንቃቄ አድርጉ በገሃድ ራሳችሁን ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ አታጋልጡ ።
"ጥንቃቄ ይጠብቅሃል ማስተዋል ይጋርድሃል ይላል የእግዚአብሔር ቃል " ይሄን ደግሞ አስተምረውናል የእግዚአብሔር ባሮች።
ስለዚህ ከእኛ የሚጠበቀው የነገሩንን መታዘዝና ወደ ተግባር መለወጥ ነው።
ሌላው ከላይ በፎቶ የተጠቀሱትን የእግዚአብሔር ቃሎች እዩአቸው።
ከእኛ የሚለዩም ካሉ አትገረሙ የተጠራው ሁሉ የተመረጠ አይደለምና።ስለዚህ "ከእኛ ዘንድ ወጡ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢኾኑ አለ አያችሁ ከእኛ ጋራ ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነግር ግን አለ ተመልከቱ ኹሉ ከእኛ ወገን እንዳልኾነ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።ይላል የእግዚአብሔር ቃል በ1ኛ ዮሐንስ መልእክት ምዕ 2:19 ላይ ስለዚህ አብረውን የነበሩ የሚመስሉ ግን ያልነበሩ ሲወጡ ይሄን የእግዚአብሔር ቃል ማሰብ ነው።እንደ አንድ መንፈሳዊ ቤተሰብ እግዚአብሔር ሁሉን ይችላልና በጸሎት ማሰብ ነው።ከዚህ ውጪ ምን ማድረግ ይቻላል እንደ ፈቃድህ ይሁን ብቻ ነው።
ይቺን ለማስተላለፍ ነው ስለዚህ ዝምብላችሁ የአገኛችሁት ሁሉ ከማጋራትና ከመስማት ይልቅ የያዛችሁን ጠበቅ አድርጋችሁ ያዙ ተረዱት ገና አልተረዳነውም።ቀዳማዊ የሥላሴ ባሪያ አባታችን ገብረ መድህንም እንዲገባችሁ የእግዚአብሔርን ፈቃድ በጸሎት እየጠየቅን እንድናነበው እንድንሰማው መክረውናል።
ሠላም እግዚአብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።
ኢትዮጵያ የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር።
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም።
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን።
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ።
አሜን!
15/05/2017