ንስሐ ምንድን ነው?
ንስሃ- ነሐሰ ከሚል የግዕዝ ግስ የወጣ ቃል ነው። የቃሉ ፍች ሐዘን፣ፀፀት፣ ቁጭት፣ ምላሽ፣ መቀጮ፣ ቅጣት፣ ቀኖና፣ የኃጢአት ካሣ መለት ነው።አንድ ሰው ንስሃ ገባ ሲባልም ዐዘነ፣ ተጠጠተ፣ ተመለሰ፣ክፋ ዐመሉን ተወ፣ጠባዮን ለወጠ ማለት ነው። ንስሐ ማለት ደግሞ አንድ ሰው በሠራው ጥፋት፣ባደረገው ስህተት፣በፈጸመው ኃጢአት ማዘኑና መቆርቆሩ፣መፀፀቱ ዳግመኛም ያንን የመሰለ ኃጢአት ላለማድረግ የሚወስነው ውሳኔ ነው።