እስቲ ትንሽ ወደኋላ መለስ እን በልና ስለ ዋካንዳ እና ስለ ጣና እናውራ ።
በብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በምናብ የተሳለው ዋካንዳ
ከተማ በኢትዮጵያ በዕውን ሊሰራ መሆኑ ከተገለፀ አንስቶ
የበርካቶች መነጋጋሪያ ሆኗል።
ከተማው በአንድ በኩል የአፍሪካውያን የባህልና የታሪክ
ማንነት መገለጫዎች የሚሰባበሰቡበት ፣ በሌላ በኩል
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምርምር የሚካሔድበት፣ ሮቦቶች
የሚርመሰመሱበት፣ ሮኬት የሚመጥቅበት ፣ በሌላኛው ገፅ
የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት እና የሚከናወንበት
የኢንዱስትሪ ክፍለ ከተማ፤ የሚገማሸረውን የአባይ ፏፏቴንና
ሸንተረሮቹን ጠዋት ማታ አሻግሮ ለማየት በሚያመች መልኩ
ይገነባል ተብሏል።
ይሁን እንጂ ዕቅዱን ቅዠት ነው፤የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ
ያላጋናዘበ ነው ሲሉ ያጣጣሉትም አልታጡም።
ፕሮጀክቱ ሀብ ሲቲ ላይቭ በሚባል ፕሮጀክት ስም በፊልሙ
ላይ የሚታየውን የምናብ ከተማ በእውነት ለመገንባት
ታቅዷል።
"ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች መኖሪያ፣ የቀደመ ስልጣኔ
ምንጭና መገኛ ቦታ ነች፤ ስለዚህ ምንጩ ላይ በአጠቃላይ
በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የሚጋሩትንና
በቴክኖሎጂም በባህልም የበለፀገ ከተማ እንገንባ የሚል
ሃሳብ ያለው ነው" ይላሉ በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት
ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን።
ሀብ ሲቲ ላይቭ የቴክኖሎጂ ከተማውን ዋካንዳን ካሊፎርኒያ
ውስጥ ለመገንባት የቀደመ ሃሳብ ቢኖረውም፤ እውነተኛ
ዋካንዳ ግን አፍሪካ ለዚያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው መሆን
ያለበት በሚል በደቡብ ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በባህርዳር
የሚገኙ ቦታዎችን ሲያስስ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ የሆኑት
ዶክተር ሹመቴ ግዛው ናቸው።
በመጨረሻም በአማራ ክልል የሚገኘው ጢስ አባይ በፊልሙ
በምናብ ከተሳለው የቴክኖሎጂ ከተማው (ዋካንዳ) ጋር
ተመሳስሎ በማግኘታቸው የክልሉን መንግስት ጋር ንግግር
እንደተጀመረ ይገልፃሉ።
ከክልሉ መንግስት ይሁንታ ከተገኘ በኋላ ሃሳቡ የቴክኖሎጂ
ከተማን መገንባት በመሆኑ ድርጅቱ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር ጋር መወያየት እንደጀመረ ዶክተር ሹመቴ
ይናገራሉ።
ፕሮጀክቱ ቴክኖሎጂን ከማሳደግ፣ቱሪዝምን ከማስፋፋት፣
ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ
በማለም ሃሳቡን ወደዱት፤ የመጀመሪያው የምክክር
መድረክም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተካሄደ።
በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ ሁለተኛው ውይይት ይደረጋልም
ብለዋል።
ተፈጥሮውን ከመጠበቅ ጋር የሚጋጭ ነገር እንደሌለ
የሚናገሩት ኮሚሽነር ጌታሁን መኮንን "ሌሎች የሐይድሮ
ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመዘየድ የጢስ አባይ ፏፏቴ ወደ
ቀድሞው ግርማው መመለሱ የፕሮጀክቱ አካል ነው" ሲሉ
ይገልፃሉ።
ይቀጥላል.....
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
በብላክ ፓንተር ፊልም ላይ በምናብ የተሳለው ዋካንዳ
ከተማ በኢትዮጵያ በዕውን ሊሰራ መሆኑ ከተገለፀ አንስቶ
የበርካቶች መነጋጋሪያ ሆኗል።
ከተማው በአንድ በኩል የአፍሪካውያን የባህልና የታሪክ
ማንነት መገለጫዎች የሚሰባበሰቡበት ፣ በሌላ በኩል
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ምርምር የሚካሔድበት፣ ሮቦቶች
የሚርመሰመሱበት፣ ሮኬት የሚመጥቅበት ፣ በሌላኛው ገፅ
የንግድ ልውውጥ የሚካሄድበት እና የሚከናወንበት
የኢንዱስትሪ ክፍለ ከተማ፤ የሚገማሸረውን የአባይ ፏፏቴንና
ሸንተረሮቹን ጠዋት ማታ አሻግሮ ለማየት በሚያመች መልኩ
ይገነባል ተብሏል።
ይሁን እንጂ ዕቅዱን ቅዠት ነው፤የአገሪቱን ነባራዊ ሁኔታ
ያላጋናዘበ ነው ሲሉ ያጣጣሉትም አልታጡም።
ፕሮጀክቱ ሀብ ሲቲ ላይቭ በሚባል ፕሮጀክት ስም በፊልሙ
ላይ የሚታየውን የምናብ ከተማ በእውነት ለመገንባት
ታቅዷል።
"ኢትዮጵያ የጥቁር ህዝቦች መኖሪያ፣ የቀደመ ስልጣኔ
ምንጭና መገኛ ቦታ ነች፤ ስለዚህ ምንጩ ላይ በአጠቃላይ
በዓለም ላይ የሚኖሩ ጥቁር ህዝቦች የሚጋሩትንና
በቴክኖሎጂም በባህልም የበለፀገ ከተማ እንገንባ የሚል
ሃሳብ ያለው ነው" ይላሉ በአማራ ክልል የኢንቨስትመንት
ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ጌታሁን መኮንን።
ሀብ ሲቲ ላይቭ የቴክኖሎጂ ከተማውን ዋካንዳን ካሊፎርኒያ
ውስጥ ለመገንባት የቀደመ ሃሳብ ቢኖረውም፤ እውነተኛ
ዋካንዳ ግን አፍሪካ ለዚያውም ኢትዮጵያ ውስጥ ነው መሆን
ያለበት በሚል በደቡብ ፣ በኦሮሚያ እንዲሁም በባህርዳር
የሚገኙ ቦታዎችን ሲያስስ መቆየቱን የሚናገሩት ደግሞ
በሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚንስትር ዲዔታ የሆኑት
ዶክተር ሹመቴ ግዛው ናቸው።
በመጨረሻም በአማራ ክልል የሚገኘው ጢስ አባይ በፊልሙ
በምናብ ከተሳለው የቴክኖሎጂ ከተማው (ዋካንዳ) ጋር
ተመሳስሎ በማግኘታቸው የክልሉን መንግስት ጋር ንግግር
እንደተጀመረ ይገልፃሉ።
ከክልሉ መንግስት ይሁንታ ከተገኘ በኋላ ሃሳቡ የቴክኖሎጂ
ከተማን መገንባት በመሆኑ ድርጅቱ ከሳይንስና ቴክኖሎጂ
ሚኒስቴር ጋር መወያየት እንደጀመረ ዶክተር ሹመቴ
ይናገራሉ።
ፕሮጀክቱ ቴክኖሎጂን ከማሳደግ፣ቱሪዝምን ከማስፋፋት፣
ኢንቨስትመንትን ከማበረታታቱ የሚኖረውን አስተዋጽኦ
በማለም ሃሳቡን ወደዱት፤ የመጀመሪያው የምክክር
መድረክም በሚኒስቴር መስሪያቤቱ ተካሄደ።
በቅርቡ በባህር ዳር ከተማ ሁለተኛው ውይይት ይደረጋልም
ብለዋል።
ተፈጥሮውን ከመጠበቅ ጋር የሚጋጭ ነገር እንደሌለ
የሚናገሩት ኮሚሽነር ጌታሁን መኮንን "ሌሎች የሐይድሮ
ኤሌክትሪክ ማመንጫ በመዘየድ የጢስ አባይ ፏፏቴ ወደ
ቀድሞው ግርማው መመለሱ የፕሮጀክቱ አካል ነው" ሲሉ
ይገልፃሉ።
ይቀጥላል.....
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch
@yaltenegeru_mistroch