#መንትዮቹ
#ክፍል_2
#እውነተኛ_ታሪክ
በዚህ ጊዜ ነበር ዛሬም ድረስ በፀፀት ጅራፍ ስገረፍ
እንድኖር ያደረገኝ ነገር የተፈጠረው ..... ጊዜው
ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ነው አስረኛ ክፍልን ገና
መጀመራችን ነበር። በእረፍት ሰዓት እህቴን ለመጥራት
ወደ ክፍሏ አመራሁ ክፍሏ በር ላይ ደርሼ ወደ ውስጥ
ልገባ ስል ከውስጥ እየወጣ ከነበረ ልጅ ጋር ተጋጨን
ይቅርታ ጠይቆኝ አልፎኝ ሄደ እየተጣደፈ ስለነበር ልብ
ብሎም አላየኝም እኔ ግን በጣም ነበር ያየሁት ረጅም
ነው ሁሉ ነገሩ ደስ የሚል .... ልቤ ለምን እንደዛ
እንደመታ አላውቅም ብቻ የማላውቀው ስሜት ነበር
የተሰማኝ ካይኔ እስኪጠፋ ድረስ ቆሜ ካየሁት በኃላ
ወደ ውስጥ ገባሁና እህቴ ቁጭ ብላ ስትፅፍ አገኘኃት
.... ከዛን ቀን በኃላ ግን ልጁን ፍለጋ እህቴ ክፍል
መመላለሱን ተያያዝኩት ኤርሚያስ ይባላል።
ተጫዋችና ከሰው ለመግባባት ፈጣን ስለነበረ ከእህቴ
ጋር ባጭር ጊዜ ተቀራርበዋል። ከኔም ጋር
አስተዋውቃኝ እኔ እህቴ እሱ ሜሮን አይናለም
አምስታችንም ምርጥ ጓደኛሞች ሆንን በእረፍት ሰዓት
ተሰብስበን እናሳልፋለን ወደቤት ስንለቀቅ አብረን
እንሄዳለን በቃ ጥሩ ቅርበት ፈጠርን።
እኔ ግን በጣም እየወደድኩት መጣሁ እሱ መሳቅ
መጫወት እዛም እዚም ወከባ መፍጠር መዝናናት
እንጂ ለማናችንም የተለየ ስሜት አያሳየንም
አራታችንንም በእኩል መንገድ ነው የሚያየን ......ብቻ
አንዳንድ ጊዜ እህቴን ነይ ብቻችንን እንሁን እያለ
ይዟት እራቅ ብለው ይቀመጡና ያወራሉ ይሳሳቃሉ
ምን እንደሚያወራት በምን እንደሚስቁ አላውቅም ግን
ለብቻቸው ሲሆኑ በጣም እናደድ ነበር። እኔና እህቴ
ጓደኞቻችንም አስተማሪዎቻችንም
እየተመሳሰልንባቸው ስለተቸገሩ እንዲለዩን በማለት
የዩኒፎርማችንን ሸሚዝ እኔ እጀ ጉርድ እሷ ደግሞ እጀ
ሙሉ መልበስ ጀመርን የፀጉር እስታይላችንንም እሷ
ብዙ ጊዜ ሹሩባ ስለምትሰራው እኔ ደግሞ
አስይዘዋለሁ በዛ በዛ በቀላሉ ማን ትህትና ማን
ልእልና እንደሆንን መለየት ጀመሩ። ..... በዚህ መልኩ
እኔም የኤርሚ ፍቅር እየባሰብኝ ሲመጣ ፀባዬ
መቀያየር ጀመረ እቤት ውስጥ መነጫነጭ የዘውትር
ስራዬ ሆነ እናቴ ሁሉ ነገሬን ስታስተውል ልክ አልሆን
ቢላት ምን እንደሆንኩ እንድነግራት ትገፋፋኝ ጀመር
እንደነገርኳቹ እናታችን ግልፅ ሆና ስላሳደገችን
እንደጓደኛችን ነበር የምንቀርባት ብዙም ሳልጨነቅ
እነትህትና ክፍል የሚማር ኤርሚያስ የሚባል ልጅ
እንደወደድኩ ነገርኳት መጀመሪያ ትንሽ ብትደነግጥም
ወደመኝታ ክፍሏ ይዛኝ ገብታ
"ልጄ ለኔ ሁሌም ህፃን ሆናችሁ ስለምትታዩኝ ነው
የደነገጥኩት እንጂ አሁን እድሜያቹ መሆኑን
አላጣውም አሁን ላይ ትምህርታቹን ብቻ ጠንክራቹ
ብትማሩልኝ ደስ ይለኝ ነበር ሆኖም ግን ፍቅር
ባልፈለጉት ጊዜ አሽሽተው በፈለጉት ጊዜ
የሚያመጡት ነገር አይደለም። ለመሆኑ ልጁ ላንቺ
ምን አይነት ስሜት አለው?" ብላ ጠየቀችኝ እኔም
ምንም የተለየ ስሜት እንደሌለውና እንደውም ከኔ
በላይ ትህትናን እንደሚቀርባት ብቻቸውን ሆነው
እንደሚያወሩ ነገርኳት። እናቴ ብዙ ከመከረችኝ በኃላ
ለጊዜው የእህቴን ስሜት እስከምናውቅ ድረስ ምንም
ነገር ለእህቴ እንዳንነግራት ተነጋገርን።
ምናልባት እህቴስ ወዳው ቢሆን?
በዚህ መልኩ ትምህርታችንን እየቀጠልን እያለ ግማሽ
ሴሚስተር ተጠናቆ ሁለኛ ሴሚስተር ከመጀመሩ በፊት
የ15 ቀን እረፍት ተሰቶን ትምህርት ሲዘጋ እኛም
እየተሰነባበትን ወደየቤታችን ስንበተን ኤርሚያስ ቻዎ
ብሎን ከሄደ በኃላ ራቅ ብሎ ትህትናን ጠርቷት
የተጠቀለለ ወረቀት ሰጣትና ጉንጯ ላይ ስሟት
እየሮጠ ሄደ። የሳማትን ጉንጯን በስስት በእጇ
እያሻሸች በፈገግታ ወደኔ መጣች
"የምን ወረቀት ነው የሰጠሽ?" አልኳት አይኔን
አፍጥጫ"
[..........ይቀጥላል........]
@yefikir_menorya
@girumneg
#ክፍል_2
#እውነተኛ_ታሪክ
በዚህ ጊዜ ነበር ዛሬም ድረስ በፀፀት ጅራፍ ስገረፍ
እንድኖር ያደረገኝ ነገር የተፈጠረው ..... ጊዜው
ጥቅምት መጀመሪያ ላይ ነው አስረኛ ክፍልን ገና
መጀመራችን ነበር። በእረፍት ሰዓት እህቴን ለመጥራት
ወደ ክፍሏ አመራሁ ክፍሏ በር ላይ ደርሼ ወደ ውስጥ
ልገባ ስል ከውስጥ እየወጣ ከነበረ ልጅ ጋር ተጋጨን
ይቅርታ ጠይቆኝ አልፎኝ ሄደ እየተጣደፈ ስለነበር ልብ
ብሎም አላየኝም እኔ ግን በጣም ነበር ያየሁት ረጅም
ነው ሁሉ ነገሩ ደስ የሚል .... ልቤ ለምን እንደዛ
እንደመታ አላውቅም ብቻ የማላውቀው ስሜት ነበር
የተሰማኝ ካይኔ እስኪጠፋ ድረስ ቆሜ ካየሁት በኃላ
ወደ ውስጥ ገባሁና እህቴ ቁጭ ብላ ስትፅፍ አገኘኃት
.... ከዛን ቀን በኃላ ግን ልጁን ፍለጋ እህቴ ክፍል
መመላለሱን ተያያዝኩት ኤርሚያስ ይባላል።
ተጫዋችና ከሰው ለመግባባት ፈጣን ስለነበረ ከእህቴ
ጋር ባጭር ጊዜ ተቀራርበዋል። ከኔም ጋር
አስተዋውቃኝ እኔ እህቴ እሱ ሜሮን አይናለም
አምስታችንም ምርጥ ጓደኛሞች ሆንን በእረፍት ሰዓት
ተሰብስበን እናሳልፋለን ወደቤት ስንለቀቅ አብረን
እንሄዳለን በቃ ጥሩ ቅርበት ፈጠርን።
እኔ ግን በጣም እየወደድኩት መጣሁ እሱ መሳቅ
መጫወት እዛም እዚም ወከባ መፍጠር መዝናናት
እንጂ ለማናችንም የተለየ ስሜት አያሳየንም
አራታችንንም በእኩል መንገድ ነው የሚያየን ......ብቻ
አንዳንድ ጊዜ እህቴን ነይ ብቻችንን እንሁን እያለ
ይዟት እራቅ ብለው ይቀመጡና ያወራሉ ይሳሳቃሉ
ምን እንደሚያወራት በምን እንደሚስቁ አላውቅም ግን
ለብቻቸው ሲሆኑ በጣም እናደድ ነበር። እኔና እህቴ
ጓደኞቻችንም አስተማሪዎቻችንም
እየተመሳሰልንባቸው ስለተቸገሩ እንዲለዩን በማለት
የዩኒፎርማችንን ሸሚዝ እኔ እጀ ጉርድ እሷ ደግሞ እጀ
ሙሉ መልበስ ጀመርን የፀጉር እስታይላችንንም እሷ
ብዙ ጊዜ ሹሩባ ስለምትሰራው እኔ ደግሞ
አስይዘዋለሁ በዛ በዛ በቀላሉ ማን ትህትና ማን
ልእልና እንደሆንን መለየት ጀመሩ። ..... በዚህ መልኩ
እኔም የኤርሚ ፍቅር እየባሰብኝ ሲመጣ ፀባዬ
መቀያየር ጀመረ እቤት ውስጥ መነጫነጭ የዘውትር
ስራዬ ሆነ እናቴ ሁሉ ነገሬን ስታስተውል ልክ አልሆን
ቢላት ምን እንደሆንኩ እንድነግራት ትገፋፋኝ ጀመር
እንደነገርኳቹ እናታችን ግልፅ ሆና ስላሳደገችን
እንደጓደኛችን ነበር የምንቀርባት ብዙም ሳልጨነቅ
እነትህትና ክፍል የሚማር ኤርሚያስ የሚባል ልጅ
እንደወደድኩ ነገርኳት መጀመሪያ ትንሽ ብትደነግጥም
ወደመኝታ ክፍሏ ይዛኝ ገብታ
"ልጄ ለኔ ሁሌም ህፃን ሆናችሁ ስለምትታዩኝ ነው
የደነገጥኩት እንጂ አሁን እድሜያቹ መሆኑን
አላጣውም አሁን ላይ ትምህርታቹን ብቻ ጠንክራቹ
ብትማሩልኝ ደስ ይለኝ ነበር ሆኖም ግን ፍቅር
ባልፈለጉት ጊዜ አሽሽተው በፈለጉት ጊዜ
የሚያመጡት ነገር አይደለም። ለመሆኑ ልጁ ላንቺ
ምን አይነት ስሜት አለው?" ብላ ጠየቀችኝ እኔም
ምንም የተለየ ስሜት እንደሌለውና እንደውም ከኔ
በላይ ትህትናን እንደሚቀርባት ብቻቸውን ሆነው
እንደሚያወሩ ነገርኳት። እናቴ ብዙ ከመከረችኝ በኃላ
ለጊዜው የእህቴን ስሜት እስከምናውቅ ድረስ ምንም
ነገር ለእህቴ እንዳንነግራት ተነጋገርን።
ምናልባት እህቴስ ወዳው ቢሆን?
በዚህ መልኩ ትምህርታችንን እየቀጠልን እያለ ግማሽ
ሴሚስተር ተጠናቆ ሁለኛ ሴሚስተር ከመጀመሩ በፊት
የ15 ቀን እረፍት ተሰቶን ትምህርት ሲዘጋ እኛም
እየተሰነባበትን ወደየቤታችን ስንበተን ኤርሚያስ ቻዎ
ብሎን ከሄደ በኃላ ራቅ ብሎ ትህትናን ጠርቷት
የተጠቀለለ ወረቀት ሰጣትና ጉንጯ ላይ ስሟት
እየሮጠ ሄደ። የሳማትን ጉንጯን በስስት በእጇ
እያሻሸች በፈገግታ ወደኔ መጣች
"የምን ወረቀት ነው የሰጠሽ?" አልኳት አይኔን
አፍጥጫ"
[..........ይቀጥላል........]
@yefikir_menorya
@girumneg