"ምሥጢሩን ማወቅ" ከሚለው መፅሐፍ የተቀነጨበ!
''ሁሉም ነገር አዎንታዊና አሉታዊ ጎን አለው፤ በማንኛውም ክስተት ውስጥ ሁለቱንም ማግኘት ትችላለህ፡፡ ስኬታማ የሚሆነው አስቀድሞ አዎንታዊ ጎኑን መመልከት የሚችለው ነው'' -ፒተር በርዋሽ
ቀናም ሆነ ክፉ አሳቢ ለመሆን ሙሉ ነፃነት አለህ፡፡ በውስጥህ ተደርቶ የኖረውን አሮጌ አመለካከት አውልቀህ በአዲስ ለመተካት እያንዳንዱ ቀን ያንተው ነው፡፡ ያን ያህል ቀላል ነገር ነው፡፡
''ሁሉን ነገር በአሉታዊ ጎኑ የምትመለከት ከሆነ ሕልምህን ይገድለዋል'' - አናስታዢያ ሶሬ
''ነገሮች ሲጨልሙብን እንደሰው የመናደድ የማማረር ዝንባሌ አለን፡፡ ንዴት፣ ማማረርና ማላከክ ዘመዳሞች ይመስሉኛል፡፡ ያደግኩት ከሰዎች ምንም ነገር መጠበቅ እንደሌለብኝ አምኜ ነው፡፡ ስላለህ ነገር ማመስገንን ልመድ፤ ምክንያቱም በሰከንዶች ውስጥ ሊጠፋ ይችላልና! ይህ አመለካከት ነው ሊኖርህ የሚገባው'' - ሊዝ ሙሬይ
''ፍርሃትን ምንጊዜም ልታስወግደው አትችልም፡፡ ምክንያቱም ፍርሃት ተፈጥሮአዊ ነው'' - ሊዝ ሙሬይ
''በሕይወትህ አደጋን መጋፈጥ የማትፈልግ ከሆነ ሲጀምር ጠንካራ እንደሆንክ ልታውቅ አትችልም፡፡ ሲቀጥል ደግሞ መቼም ላታድግ ትችላለህ'' -አናስታዢያ ሶሬ
''ሁሉንም ደረጃዎች አስቀድመህ ለማየት የምትፈልግ ከሆነ ተሳስተሃል፡፡ ስህተት የምንሰራው ሁሉንም ነገሮች መቆጣጠር እንደምንችል ማሰብ ስንጀምር ነው'' -ሊዝ ሙሬይ
''ሕይወት ፈተና ነች፡፡ ሕይወት ቀላልና እንከን አልባ ከመሰለችህ ተሳስተሃል፤ አልያም ቅዥት ላይ ነህ'' - ሊዝ ሙሬይ
መልካም ቀን!የሁሉም ቤት