YeneTube


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: ko‘rsatilmagan


መረጃዎችን ለመላክ @Fikerassefa

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
ko‘rsatilmagan
Statistika
Postlar filtri


በዛሬው ዕለት ከአዲስ አበባ ወደ ድሬዳዋ በመጓዝ ላይ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET248 ድሬዳዋ አየር ማረፍያ ለማረፍ በዝግጅት ላይ ሳለ በአውሮፕላኑ ውስጥ ጢስ ታይቱ እንደነበር የኢትዩጲያ አየር መንገድ አሳወቀ፡፡

በዚህም ምክንያት አውሮፕላኑ በድሬዳዋ አየር ማረፍያ በሰላም እንዲያርፍ በማድረግ መንገደኞችን ከአውሮፕላኑ ማውረድ መቻሉንም ባወጣው መረጃ ገልፃል፡፡አየር መንገዱ ጢሱ የተነሳበትን ምክንያት በማጣራት ላይ ነው ብሏል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለተፈጠረው ክስተት መንገደኞቹን ከወዲሁ ይቅርታ ጠይቋል፡፡

@YeneTube @FikerAssefa


በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት “ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የጤና ችግሮች በወረርሽኝ መልክ እየመጡ ነው” ተባለ!

በአማራ ክልል በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ምክንያት የክልሉ የጤና ሥርዓቱ በአግባቡ እንዳይሠራ ኾኗል ተባለ፤ “ቀደም ሲል በቁጥጥር ስር ውለው የነበሩ የጤና ችግሮች በወረርሽኝ መልክ እየመጡ” መሆኑም ተጠቁሟል።ይህ የተገለጸው በአማራ ክልል የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፎረም ባዘጋጀው ውይይት ወቅት ነው።

መንገዶች ይዘጋሉ፣ ወገኖች ያለ ስጋት ወደ ጤና ተቋማት ሄደው መታከም አይችሉም ተብሏል፤ የታጠቁ ወገኖችን የጤና አገልግሎቱን የሚጠብቁ ሕጎችን እንዲያከብሩ ተጠይቋል፡፡ታመው መታከም የማይችሉ ወገኖች በርካቶች ናቸው፤ ስለ ምን ካሉ ሕሙማን በነጻነት ወደ ሕክምና ቦታ መሄድ አይችሉም፣ የጤና ባለሙያዎችም በነጻነት ሕክምና አይሰጡምና ነው ማለታቸውም ተካቷል።አሁን ባለው ችግር የጤና አገልግሎት ለመስጠት አስቸጋሪ መኾኑንም ተመላክቷል፡፡

[Addis Standard]
@YeneTube @FikerAssefa


በኢትዮጵያ ብሔራዊ ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ!

በኢትዮጵያ ብሔራዊ የሆነ ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት ለመዘርጋት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ እየተስተዋለ ያለውን የተበታተነ የጤና መረጃ አያያዝ ማሻሻል አስፈላጊ መሆኑ እንደታመነበት ገልጿል።

ይዘጋጃል የተባለው የመረጃ ቋት የመድኃኒት አያያዝንና ቁጥጥርን ጨምሮ የበሽታ አይነቶች የሚመዘገቡበት እንዲሆን ውጥን መያዙን የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል።

አክለውም፤ ዲጂታል የጤና መረጃ ለማደራጀት፣ ለመጠቀም እንዲሁም ወደ ዲጂታል አገልግሎቶች መግባት የሚችሉ የጤናው ዘርፍ ሥራዎችን በዲጂታል ለመተካት bጤና ሚኒስቴር በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ለአሐዱ ተናግረዋል።

ዲጂታል የጤና የመረጃ ቋት በተለያዩ ጊዜያቶች የሚፈጠሩ በሽታዎችን ለመለየት የሚያስችል መሆኑን የገለጹት ሚንስተሯ፤ የተያዘው ውጥን እንዲሳካ ከተለያዩ ተቋማት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ መሆኑን አሳስበዋል።

"የዲጂታል የጤና መረጃ ስርአት መዘርጋቱ የጤና አገልግሎት አሰጣጡን ለማቀላጠፍ ይረዳል፡፡" የተባለ ሲሆን፤ ስርዓቱ መረጃን በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ፣ እንግልትን ለመቀነስ እንዲሁም፤ ቶሎ ውሳኔ በመስጠት ወረርሽኝን ለመግታት እና ለመሳሰሉት አስፈላጊ መሆኑን ተነግሯል።በኢትዮጵያ ከጊዜ ወደ ጊዜ የሚከሰቱ በሽታዎች ዙርያ በሰነድ ደረጃ የሚያዝ መረጃ እንዳልነበረ ሲገለፅ ቆይቷል።

[Ahadu]
@YeneTube @FikerAssefa


ጀርመናዊውን አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል የእንግሊዝ የብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ መሆናቸዉ ይፋ ተደርጓል።

የእንግሊዝ ብሔራዊ ቡድንን የማሰልጠን ክብር በማግኘቴ ደስተኛ ነኝ ኩራትም ተሰምቶኛል። ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር ስኬታማ ጊዜን እንደምናሳልፍ አስባለሁ በማለት ቱሔል ተናግረዋል። አሰልጣኙ በጥር ወር ስራቸዉን የሚጀምሩ ሲሆን የ18 ወራት ኮንትራትም ተፈራርመዋል።

@YeneTube @FikerAssefa


ግብጽ ለሱማሊያ ጦር መሳሪያ መላክ ከጀመረች ወዲህ፣ ኢትዮጵያ በሱማሊያ ግዛት ውስጥ ያላትን የወታደር ብዛት ወደ 22 ሺሕ ማሳደጓን ከምንጮች መስማቱን ጠቅሶ የኢምሬቶች ጋዜጣ ዘ ናሽናል ዘግቧል።

በግብጻዊያን ወታደራዊ አማካሪዎች የሚታገዙ የሱማሊያ ወታደሮች፣ ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወታደሮችን ወደ አገሪቱ እንዳታስገባ ለመከላከል ወደ ድንበር መሠማራታቸውን ምንጮች እንደነገሩት ጋዜጣው ጠቅሷል። ግብጽ ባለፉት ሳምንታት፣ ወደ ሱማሊያ ወታደራዊ አማካሪዎችን፣ አሠልጣኞችንና የጸረ-ሽብር ኮማንዶዎችን እንደላከች የጠቀሰው ዘገባው፣ እስከ ታኅሳስ መጨረሻ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮቿን ታሠማራለች መባሉንም ገልጧል። ግብጽ፣ ሱማሊያ ውስጥ የወታደራዊ ተልዕኮዋን በማቋቋም ላይ እንደኾነችም ተነግሯል።

@YeneTube @FikerAssefa


አባ መፍቀሬ ሰብዕ ኪዳነወልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ!

በተለያዩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት በሐይማኖታዊ አስተምህሮ፣ አንድነትን በማስተማር እንዲሁም በብዝኀ ሕይወት ጥበቃ ስራ ያገለገሉት አባ መፍቀሬ ሰብዕ ኪዳነወልድ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

በ1921 ዓ.ም የተወለዱት አባ መፍቀሬ ሰብዕ በግሸን ደብረ ከርቤ ለበርካታ ዓመታት ሲያገለግሉ ቆይተው በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡አባ መፍቀሬ፤ በተለያዩ ሐይማኖት ተከታዮች እና የሕብረተሰብ ክፍሎች ዘንድ ተወዳጅ እንደነበሩ ይነገርላቸዋል፡፡

Via EBC
@YeneTube @YeneTube


🎮 ALT COMPUTER 🖥💻
አዲስ  እንዲሁም ዱባይ ዩዝድ ላፕቶፖች ከ አስተማማኝ
💯የ 1  አመት ዋስትና ጋር
እንዲሁም የተለያዩ
computer accessory’s ⌨️ 🖱🔋🔌
laptop batteries, gaming keyboard , SSD & HDD Internal and  External hard discs , frameless monitor🖥
Desktop computer
⭐️special discount for students with mouse and flash-disc 🎁

የቴሌግራም ቻናል ሊንክ
https://t.me/altcomputer
💻💻💻💻💻💻💻

አድራሻ : - 📍 መገናኛ ማራቶን የ ገበያ ማእከል  ground floor #6

Inbox @anteneh00
📞. Call 0941171815
               0960557573
✉️ @anteneh00


ጤናወ በእጀወ በቤትወ የጤና በረከት የተለያዩ መፍትሄ ያጡ ችግሮች እናም በሽታወችን እንዴት አባቶች እና እናቶች ባቆዩነን ቅመማቅመም ቅጠል ስር ፍሬ እና ጥበብ መታከም መፈወስ ከችግራችን መውጣት እንዴት እንደምንችል እምንረዳበት የምንችለው  ቻናል ነው ይቀላቀሉ በየቀኑ የምንለቃቸውን ጠቃሚ መረጃ ተካፋይ ይሑኑ ሸር ያድርጉ
    👇
https://vm.tiktok.com/ZMhNYSvDS/       ለበለጠ መረጃ
0912718883
0917040506 በቴሌግራም በውስጥ መስመር የሚፈልጉትን ያስቀምጡ
👉አድራሻችን አዲስ አበባ አየር ጤና ካራቆሬ ወደመድኀኒአለም 200ሜትር ገባ ይበሉ
ቁጥር 2ባህርዳር ቀበሌ 11ዲያስፖራ በአሮየው 
አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት ያገኙናል ይምጡ
ይፈወሱ
     https://www.tiktok.com/t/ZMhN2XcBE/

በማንኛውም አገልግሎት ውጤቱን እንዳዪ ክፍያ ይፈፅማሉ


🛍 ዲጂታል ገበያ በእጅ ስልክዎ📲

ከቤትዎ ሳይወጡ የፈለጉትን ይግዙ፣ የፈለጉትን ይሽጡ!

በሁሉማርኬት
1️⃣ከሻጮች ጋር በቀጥታ ይገናኛሉ
2️⃣ዋጋ ይደራደሩ
3️⃣ምርጥ ዕቃዎችን ያገኛሉ!

አሁኑኑ መተግበርያችንን 👉👉 DOWNLOAD ያውርዱ! በቀላሉ ይሸምቱ!


🎉50,000+ downloads!📱

A huge thank you to our community for helping us reach this milestone! Together, we’re revolutionizing education and making learning more accessible than ever. Onward to the next chapter!

👇—
DOWNLOAD NOW — 👇

https://app.gdacademy.et/app

For any updates Follow Globe Dock Academy's Official Channel :
https://t.me/globedockacademy

GlobeDock Academy


በአዲስ አበባ የህዝብ ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ጭማሪ ተደረገ!

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ለተሰማሩ ሚኒ-ባሶች፣ ሚዲ-ባስ ታክሲዎችና የከተማ አውቶብሶች ላይ የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያ አድርጓል፡፡

አዲሱ የታሪፍ ማስተካከያው ከነገ ጥቅምት 06 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ ቀድሞ አገልግሎት ሲሰጥበት የነበረው የታሪፍ ተመን ከጥቅምት 20/2016 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ የዋለ እንደነበረና ስሌቱም የነዳጅ ጭማሪ ዋጋን ብቻ ታሳቢ ያደረገ እንደነበር ቢሮው አስታውቋል።

አሁን የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ደግሞ ወቅታዊ የነዳጅ የችርቻሮ ዋጋ እና ሌሎች አስተዳደራዊ ወጪዎችን ያማከለ መሆኑን ያስታወቀው ቢሮው፤ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች አዲስ በተሻሻለው ህጋዊ የታሪፍ ተመን ብቻ አገልግሎት እንዲሰጡ  እያሳሰበ፤ ይህንን በሚተላለፉት አካላት ላይ ቢሮውና የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ አሳስቧል።

ህብረተሰቡም ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ሲያጋጥሙት በአቅራብያው ለሚገኝ የትራንስፖርት ተቆጣጣሪዎችና ለትራፊክ ፖሊስ እንዲሁም በአቅራቢያዎ ባለ የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በአካል ወይም በነፃ የስልክ መስመር 9417 ጥቆማ መስጠት የምትችሉ መሆኑን ቢሮው አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa

11.8k 0 52 16 176

ዩኤስኤድ በኢትዮጵያ በ5 ቢሊየን ብር የሚተገበር የአደጋ ሥጋት አመራር ፕሮግራም ይፋ አደረገ!

የአሜሪካ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤድ) በኢትዮጵያ 9 ክልሎች የሚተገበርና 5 ቢሊየን ብር ድጋፍ የተደረገበትን የአምስት ዓመት የአደጋ ሥጋት አመራር ፕሮግራም በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አርባምንጭ ከተማ ይፉ የተደረገው ይህ ፕሮግራም፤ በአሜሪካ መንግሥት በሚገኝ የ49 ሚሊዮን ዶላር ወይንም ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ ድጋፍ የሚተገበር ሲሆን፤ በኢትዮጵያ በሚገኙ 9 ክልሎችና 120 ወረዳዎች ላይ ከ14 ሚሊዮን በላይ ሕዝቦችን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ ተነግሯል፡፡

የድርጅቱ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ቢሮ ምክትል ዳይሬክተር ሄኖክ ሁንበላይ፤ ለፕሮግራሙ የ5 ዓመታት ጊዜ መያዙን ገልጸው፤ ሦስት መሰረታዊ ትላልቅ አላማዎች በውስጡ መያዙን ለአሐዱ ተናግረዋል፡፡

እነርሱም አንደኛ የአገሪቱ አደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ሥራዎች በተፋጠነ እና በተቀላጠፈ መልኩ በተሻለ ዝግጁነት እንዲሰሩና ከአሁን በፊት በተደረጉ ሥራዎች ላይ ተመስርቶ የተሻለ ትንበያ እንዲሁም የአደጋ ምላሽ እንዲሰጥ ማስቻል መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ሁለተኛው ደግሞ በየክልሎቹ ያሉ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ተቋማትን አቅም የማጎልበት ሥራ ነው ብለዋል፡፡

በሦስተኛው ደረጃ ደግሞ የግሉ ዘርፍ አደጋ ከተከሰተ በኋላ ሳይሆን፤ አደጋ ከመከሰቱ በፊት አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ማስቻል እና ማስተባበር የፕሮግራሙ ዋና አላማዎች መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በየክልሎቹ የሚገኙ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽኖች የተሻለ የአደጋ ትንበያ እንዲሰጡ፣ ያላቸውን ሀብትና ሌሎች ግብዓቶችን በአግባቡ እንዲጠቀሙ እንዲሁም አደጋው ችግር ከማስከተሉ በፊት ከማህህረሰቡ ጋር እንዲሰሩ የሚያደርግ የአቅም ግንባታ ሥራዎች እንደሚሰሩም አቶ ሄኖክ አስረድተዋል፡፡

በዚህም መሰረት ፕሮግራሙ የሶማሌ ክልል፣ የደቡብ ክልል፣ የአፋር ክልል፣ የኦሮሚያ ክልል፣ የአማራ ክልል፣ የትግራይ ክልል፣ የደቡብ ምእራብ እና ማዕከላዊ ደቡብ ክልሎችን ማዕከል አድርጎ እንደሚሰራ የገለጹ ሲሆን፤ በዚህም እንደየክልሎቹ የአደጋ ተጋላጭነት የክልሎቹን አቅም የመገንባት ሥራ ይሰራል ሲሉ ለአሐዱ ገልጸዋል፡፡

የአሜሪካ አለም አቀፍ የተራድኦ ድርጅት በዚህ ፕሮጀክት ከፌደራል አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን፣ ከገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም ከሌሎች የመንግሥት አካላትና የልማት አጋር ድርጅቶች ጋር በትብብር እንደሚሰራ የገለጹት ምክትል ዳይሬክተሩ፤ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበርን ጨምሮ ሦስት አለም ዓቀፍ እና የአገር ውስጠ ተቋሟት ፕሮግራሙ በማስፈጸም ደረጃ አብረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል፡፡

ይህ ድጋፍ በአደጋ ሥጋት አመራር ዘርፍ በዩኤስኤድ እስካሁን ከተደረጉ ድጋፍ ከፍተኛ መሆኑ የተነገረ ሲሆን፤ በዚህም ምክንያት ፕሮግራሙ በአግባቡ ተግባራዊ ስለመደረጉ ትልቅ አጽዕኖት ተሰጥቶበት የቁጥጥር ሥራ እንደሚሰራ ተመላክቷል፡፡

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa


ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ስልካቹን ብቻ በመጠቀም ምንም ገንዘብ ማውጣት ሳይጠበቅባቹ ::

እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉና ስለ ክሪፕቶ በዝርዝር።

ሁሉንም የONLINE ስራዎች በዝርዝር በዚ ቻናል ያገኛሉ።

በርግጠኝነት ትወዱታላቹ በዚ LINK አሁንኑ ተቀላቀሉ👇👇
https://t.me/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://t.me/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://t.me/+fzeZ2gn56UE3NTI0


ጉያ የበረንዳ ስራ

ለስራዎ ቦታዎ ይሁን ለመኖሪያ ቤትዎ የፀሃይና ዝናብ መከላከያ በረንዳ ማሰራት የሚፈልጉ ከሆነ በመረጡት ማቴሪያል በተመጣጣኝ ዋጋ ጥራት ያለው ስራ እንሰራልዎታለን።

ስልክ:
0954260423
0973007170


የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የቀድሞ ታጣቂዎችን እና ተፈናቃዮችን ለማቋቋም፤ ለዚህ ዓመት ብቻ ከ“130 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገኛል” አለ!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሰላማዊ ኑሮ የተመለሱ የቀድሞ ታጣቂዎችን እና በጸጥታ መደፍረስ ከቀያቸው ተፈናቅለው የነበሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን ለማቋቋም፤ በዚህ ዓመት ከ130 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ ማቀዱን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጸ።

▶️ ክልሉ ለመልሶ ማቋቋም ስራው የሚያስፈልገውን የገንዘብ መጠን የሚያፈላልግ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴ ማቋቋሙን አስታውቋል።

▶️ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ከትላንት በስቲያ እሁድ ጥቅምት 3፤ 2017 ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ፤ ኮሚቴው “በአጭር ጊዜ ወደ ስራ እንዲገባ” ውሳኔ አስተላልፏል።

▶️ የገቢዎች፣ የፋይናንስ፣ የንግድ፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊዎችን በውስጡ ያካተተው ኮሚቴው፤ የክልሉ ማህበረሰብ እና የተለያዩ ድርጅቶችን አስተባብሮ የሚፈለገውን የገንዘብ መጠን የማሰባሰብ ስራን በበላይነት የመምራት ኃላፊነት የተጣለበት መሆኑም ተነግሯል።

▶️ የሃብት አሰባሳቢ ኮሚቴውን ማደራጀት ያስፈለገው፤ የክልሉ መንግስት ካለው የበጀት ውስንነት አንጻር ስራውን በራሱ አቅም ብቻ ለማከናወን የማይቻል በመሆኑ ምክንያት መሆኑን የክልሉ የካቢኔ ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሻሪፍ ሃጂ አኑር ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።

▶️ ክልሉ ለመልሶ ማቋቋም በዚህ ዓመት ለመሰብሰብ ያቀደው ከ130 ሚሊየን ብር በላይ መሆኑን የገለጹት አቶ አሻሪፍ፤ ሆኖም ለአጠቃላይ ስራው ከዚህም በላይ በጀት እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

[Ethiopia Insider]
@YeneTube @FikerAssefa


የብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ ንግድ ባንክ የዶላር መሸጫ ዋጋውን በ8 ብር ቀነሰ!

ንግድ ባንክ ዛሬ ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም. ባወጣው ዕለታዊ የውጭ ምንዛሬ ግብይት የዋጋ ዝርዝር ላይ የዶላር የመሸጫ ዋጋው ከትናንቱ ጋር ሲነጻጸር የስምንት ብር ቅናሽ አሳይቷል። ባንኩ ያደረገው ይህ ማስተካከያ በአንድ ዶላር መሸጫ እና መግዣ ዋጋ መካከል ያለውን ልዩነት ወደ ሁለት በመቶ አውርዶታል።

ንግድ ባንክ ሰኞ ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም. የዶላር የመሸጫ ዋጋው 123.63 የነበረ ሲሆን መግዣው ደግሞ 112.39 ነበር። ይህም በሁለቱ ዋጋዋች መካከል የነበረው ልዩነት የ9.2 በመቶ ነበር።

የብሔራዊ ባንክ ውሳኔን ተከትሎ ንግድ ባንክ ዛሬ ማክሰኞ ባደረገው የውጭ ምንዛሪ ግብይት ዋጋ ማስተካካየ የዶላር መግዣ 113.13 ተደርጓል።መሸጫውን ደግሞ ወደ 115.39 በመውረድ የስምንት ብር ቅናሽ ታይቶበታል።ይህ የባንኩ እርምጃ ብሔራዊ ባንክ ባስቀመጠው የሁለት በመቶ ልዩነት ውስጥ የሚገኝ ነው።

ብሔራዊ ባንክ አዲሱን መመሪያ በተመለከተ በአገሪቱ ለሚገኙ ሁሉም ባንኮች በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን እስከ ረቡዕ ድረስ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉ አዟል።

@YeneTube @FikerAssefa


የእስራኤል ጦር በሊባኖስ እና ጋዛ ሰርጥ በ24 ሰዓት ውስጥ ከ230 በላይ ኢላማዎችን ደበደበ

"የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት በደቡባዊ ሊባኖስ እና ጋዛ ሰርጥ በቀጠለው ኦፕሬሽን ባለፈው ቀን ከ230 በላይ የሽብር ኢላማዎችን መቷል" ሲል ጦሩ በቴሌግራም ባሰራጨው መግለጫው አስታውቋል።

እንደ መከላከያ ሰራዊቱ ገለጻ የእስራኤል አየር ኃይል ሊባኖስ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓታት ከ200 በላይ የሺዓ ንቅናቄ ሂዝቦላ ኢላማዎችን ደብድቧል።

@Yenetube @Fikerassefa


የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ እንዳይሆን ተባለ!

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ በሚገዙበት እና በሚሸጡበት ዋጋ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ መብለጥ እንደሌለበት አሳሰበ።ብሔራዊ ባንኩ ይህንን በተመለከተ ለንግድ ባንኮች በደብዳቤ ማሳወቁን ገልጿል።

አዲሱ የምንዛሬ ተመን አሰራር ይፋ መሆኑን ተከትሎ በውጭ ምንዛሬ ገበያው ላይ ያሉ ሂደቶችን ሲከታተል መቆየቱን የገለጸው ብሔራዊ ባንኩ፤ የንግድ ባንኮች የውጭ ምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት በዓለም አቀፍ አሰራር መሰረት መሆን እንዳለበት አመልክቷል።

በመሆኑም የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ መካከል ያለው ልዩነት ከሁለት በመቶ በላይ መሆን እንደሌለበት አስታውቋል።

አሁንም ቢሆንም ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በራሳቸውና ከደንበኞቻቸው ጋር ባላቸው ስምምነት ማድረጋቸውን እንደሚቀጥሉ ጠቁሟል።

ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መግዣ እና መሸጫ ዋጋቸውን በተናጠል በየቀኑ ማሳወቃቸውን መቀጠል እንዳለባቸው ጠቅሶ፤ ባንኮች ከውጭ ምንዛሬ ሽያጭ ጋር በተያያዘ የሚጠይቋቸውን ኮሚሽኖች ከምንዛሬ መሸጫ ጋር ሳይሆን በተናጠል ለደንበኞቻቸው እንዲያሳውቁሞ አዝዟል።

እስካሁን በነበረው አሰራርም ንግድ ባንኮች የምንዛሬ መሸጫ ዋጋቸውን ከኮሚሽኑ ጋር ደምረው ያስታውቁ እንደነበር አስታውሶ፤ ንግድ ባንኮች ሁለቱን ጉዳዮች እስከነገ ባለው ባለው ጊዜ ተግባራዊ ሊያደርጉት ይገባል ብሏል።

@YeneTube @FikerAssefa


"26 ድሃ ሀገራት እአአ ከ2006 ወዲህ ባልታየ ደረጃ ዕዳ ውስጥ ተዘፍቀዋል” -የዓለም ባንክ

ከዓለም እጅግ ድሃ ህዝብ አእርባ ከመቶው የሚኖርባቸው 26 ድሃ ሀገራት እአአ ከ2006 ወዲህ ከምንጊዜውም በከፋ ከፍተኛ እዳ ውስጥ እየተዘፈቁ፣ ለተፈጥሮ አደጋዎች እና ሌሎች ቀውሶች እየተጋለጡ መሆኑን የዓለም ባንክ ጥናታዊ ዘገባ አመለከተ፡፡ትላንት የወጣው ጥናታዊ ዘገባው እንዳመለከተው ምንም እንኳ የተቀረው የዓለም ክፍል ከኮቪድ 19 ቀውስ በማገገም ጉዞውን የቀጠለ ቢሆንም፣ እነዚህ ኢኮኖሚዎች ግን ወረርሽኙ ዋዜማ ከነበሩት አንጻር ሲታዩ ዛሬ በአማካይ የበለጠ የደኸዩ ሆነዋል፡፡

በዋሽንግተን ከሚካሄዱት የዓለም ባንክ እና የዓለም የገንዘብ ድርጅት አመታዊ ስብሰባዎች በአንድ ሳምንት ቀደም ብሎ የተለቀቀው ጥናታዊ ዘገባው የከፋ ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ትልቅ ችግር መኖሩን ያረጋገጠ ነው ተብሏል፡፡እነዚህ ሀገራት በዓለም አቀፍ ልማት ማህበር (አይ ዲ ኤ) እርዳታ እና ብድር ላይ በከፍተኛ ደረጃ ጥገኛ በመሆናቸው ድህነትን ለማስወገድ በሚደረገው ጥረት ላይ ያለውን ውድቀትም ያሳየ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዓለም ባንክ በዚህ አመት በአለም እጅግ ድሃ ለሆኑት የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ 100 ቢሊዮን ዶላር ለማሰባሰብ የሚያደርገውን ጥረት አጉልቶ እንደሚያሳይም ተመልክቷል፡፡የሀገራቱ ዕዳ ከአጠቃላይ ምርት ገቢያቸው (GDP) አንጻር ሲሰላ 72 በመቶ መደረሱም በዘገባው ተጠቅሷል፡፡ ይህም በ18 ዓመታት ውስጥ ሲታይ ከፍተኛው ሲሆን ከእነዚህ ሀገሮች ውስጥ ግማሾቹ በእዳ ማጥ ውስጥ የተዘፈቁ ወይም ለከፍተኛ አደጋ የተጋለጡ ናቸው ተብሏል።

ከእነዚህ ሀገራት መካከል ሁለት ሶስተኛዎቹ በትጥቅ ግጭት ውስጥ የሚገኙ ወይም ፀጥታን የማስከበር ፈተናዎች ገጥሟቸዋል፣ ይህ ደግሞ የውጭ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ የሚያበረታታ ባለመሆኑ በርካቶች ወደ ውጭ በሚላኩ ምርቶች ላይ ብቻ እንዲተማመኑ በመገደዳቸው ለኢኮኖሚ አለመረጋጋት ተጋላጭ እንደሚያደርጋቸው ተዘግቧል፡፡

የተፈጥሮ አደጋዎች በነዚህ ሀገራት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያሳደሩ ሲሆን እኤአ በ2011 እና 2023 ባለው ጊዜ አመታዊ ኪሳራቸው በአማካይ በአጠቃላይ የሀገር ውስጥ ምርት የሁለት ከመቶ ኪሳራ ያሳደረባቸው መሆኑ ተመልክቷል፡፡የዓለም ባንክ ዋና ኢኮኖሚስት ላለፉት አምስት አመታት በተለይም ሌሎች የፋይናንስ ምንጮች እየቀነሱ በመጡበት ወቅት ዓለም አቀፍ ልማት ማህበር (አይዲኤ) ለሀገሮች ወሳኝ የሆነ የፋይናንስ ምንጭ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ዓለም አቀፉ የልማት ማሕበር በየሦስት ዓመቱ ከዓለም ባንክ አባል ሐገሮች መዋጮ ገንዘብ የሚያገኝ ሲሆን እኤአ በ2021 ከፍተኛው የሆነው የ93 ቢሊዮን ዶላር መዋጮ ሰብስቧል፡፡ የዓለም ባንክ ፕሬዚደንት ኤጄይ ባንጋ እ አ አ እስከ ታሕሳስ 6 ባለው ጊዜ ቃል የተገባውን 100 ቢሊዮን ዶላር እና ከዚያም በላይ ለመሰብሰብ አቅደዋል፡፡እነዚህ ሀገራት የግብር አሰባሰብ ስርዓቶችን በማሻሻል ፣ መንግስታዊ ወጪን የበለጠ ውጤታማ በማድረግ የውጭ ዕርዳታ ላይ ያለውን ጥገኝነት በመቀነስ ፣ የራሳቸውን ጥረት ማጠናከር እንዳለባቸው ሪፖርቱ አመልክቷል።

@YeneTube @FikerAssefa


ኢትዮቴሌኮም ከሜታ ከኩባንያ ጋር በመተባበር የደንበኞች ተሞክሮ የሚያሻሽል ፕሮግራም ተግባራዊ ሊያደርግ ነው!

ኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሬህይወት ታምሩ ከሜታ-ፌስቡክ የመካከለኛው ምስራቅና አፍሪካ የንግድ ልማትና ስትራቴጂክ አጋርነት ዳይሬክተር ቪካስ ሜኖን ጋር የደንበኞችን የዲጂታል ተሞክሮ ለማሻሻል በሚረዱ ጉዳዮች ላይ ስትራቴጂያዊ ውይይት አደረጉ።በውይይቱ ሜታ-ፌስቡክ ከኢትዮቴሌኮም ጋር በመተባበር የደንበኞችን ዳታ አጠቃቀም የሚያሻሻል ፕሮግራም በኢትዮጵያ መጀመሩ ያለውን ትብብር ወደላቀ ደረጃ እንደሚያሳድገው ተገልጿል።

ደንበኞች አካውንታቸው ውስጥ ሂሳብ ባይኖርም የሜታ-ፌስቡክ አገልግሎቶችን ለተወሰነ ጊዜ በነጻ በመጠቀም ግንኙነታቸውን እንዲያስቀጥሉ ከማስቻል ባሻገር ጤና፣ ትምህርትና የስራ ዐድሎች ጠቃሚ መረጃዎችን ከክፍያ ነጻ በማቅረብ በመረጃ የበለጸገ ንቁ ዜጋ ለመፍጠር ያስችላል፡፡የዲጂታል ሊትሬሲንና አካታችነትን ማሳደግ ለዲጂታል ኢትዮጵያ ግንባታ ወሳኝ ነው። ሀገራዊ የይዘት ፈጠራ እንዲጎለብትና የዲጂታል ስነምህዳሩን የሚያሻሽሉ ፋይዳ ያላቸው ፕሮግራሞችን መተግበር የሳይበር ደህንነትና መረጃ አያያዝን በጋራ አስተማማኝ ስለማድረግ አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

የስምምነቱ ትግበራ የዲጂታል አገልግሎት ተደራሽነትንና አካታችነትን በመጨመር የሀገራችንን ዲጂታል ሊትሬሲ በማሳደግ እንዲሁም ለደንበኞች የላቀ ተሞክሮ በማምጣት ለዲጂታል ትራንስፎርሜሽን እድገት የላቀ ሚና እንደሚኖረው ከኢትዮቴሌኮም ያገኘው መረጃ ያመለክታል።

@YeneTube @FikerAssefa

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.