...ትንፋሼን እቆጥራለው... እያንዳንዷ የሳንባዬ የመጨረሻ ትዝታ ልትሆን ትችላለች... እርምጃዬን እቆጥራለው... የፊተኛው የቀደመውን ይሽራል... አይኖቼ መድረሻዬን ለማማተር አይሹም... ይልቅ ጫማዬ ላይ ተተክለዋል... በጆሮዬ የከበበኝን ሁከት አልሰማም... የገዛ ትንፋሼን አዳምጣለው... እፍፍፍፍፍፍፍ... እንደበረሃ አውሎ ንፋስ ያፏጫል... የተረከዜን መንኳተት እስመአለው... የልብ ምቴን እሰማለው... የግርግዳው ሰአት ውስጥ ካለው ፔንዱለም ጋር ያረግዳሉ... ጀርባዬ ላይ ስለተሸከምኩት ጓዝ አላማርርም... በዝምታ እግሬን አነሳለው... በመጓዝ መሃል በሰመመንሽ አርፋለው... በስምሽ ከተከልኩት የእጣን ዛፍ ጠረንሽ ይጤሳል... በርሱ ላይ ትዝታሽ ይጫወታል... ከትዝታሽም ያን ቀን እመርጣለው... "መጣህልኝ" ድምፅሽ እንደንጋት እንዲያንሾካሹክ እጠብቃለው... ከሰመመኔ እንቅፋት ያነቃኛል... እንዳዲስ እግሬነነሳለው... ቤቴ እስክደር
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○