"በውስኔና አድርጊት መሃል ያለው ርቀት ፍርሃትን ያክላል... ምናልባት በግዜና በሰውም"
"... ገመድ ዝላይ...
የገመዱ አንድ ጫፍ የስልክ እንጨት ልላይ ታስሯል... እኩያዬ አንዱን ጫፍ ይዛ ታዞራለች... "አንድ... ሁለት... ሶስት... ግቢ እንጂ..." ቀሚሴን ዳር እና ዳር ይዤ እመር ብዬ እንደቆምኩ... የገመዱን ጡዘት አጠናለው... ዘልዬ ለመግባት ግን አልደፍርም..."
"... እናሸንፋለን...
ለገላዬ ፀሃይ ላይ ያኖርኩት ውሃ ስሸሸው እሁድ ሊያልቅ አፋፍ ላይ እደርሳለው... እንደልጅነቴ ... ሜዳው ላይ ልታጠብ እቀመጣለው... ከልብሴ ስር ሙቅ ቆዳ አለ... የጠለኩትን ውሃ ይዤ እጠብቃለው... የሚሌልት ቀን የሚቀትር ይመስል... በንፋስ የያዝኩት ውሃ ይሞቅ ይመስል... ሌላ ቀን ሊላ ግዜ ሌላ መላ እጠብቃለው... " ምናባቱ ይሄ ራቁቱን ይወላገዳል" እናቴ ናት...ባገኘችው ነገር የፈራሁት ውሃ ውስጥ ትነክረኛለች... በፍቃዴ ያልገባሁበትን ህፅበት እፈፅማለው..."
|ዘካሪያስ|
°•.• @yenie_kal •.•°
@yenie_kal
○○○○○○○