የወደድኩት ምክር ነው ከጠቀማቹ ብዬ ነው
በቢዝነስ ፊልድ ሰልጥነህ ዲግሪ ይዘህ ወጥተህ በአንዴ የምሁር ሀብታም ለመሆን ታስብ ይሆናል:: ስትፈልግ የ ACCA ሰርቲፊኬሽን ጨምርበት:: ከባንክና ኢንሹራንስ ጀምረህ እስከ ጉሊት ግባ:: ንግዱ በኢትዮጵያ የቢዝነስ ባሕል ነው የሚመራው:: ባንክ ማለት ፎቅ ውስጥ ያለ ጣሳ-ተራና ወራባ-ተራ ነው:: ጠጅና በርጫ የለም እንጂ እቁብ ቤት ነው:: አንተ ዲግሪ የተማርከው በአሜሪካን ሀገር ሲስተም እና በእንግሊዝ ሀገር ሰርቲፊኬሽን ነው:: አጎትህ ግን ከገጠር ነው የመጣው:: እርሱ በሥራና በመከራ ሲማር አንተ አፍላው የትምህርትና የሩጫ ጊዜህ የቲየሪ ትምህርት እስር ቤት ውስጥ ነበርክ:: ከእስር ስትወጣ ኑሮና ቢዝነሱን ወድቀህ ተዋርድቀህ እንዳትማር ዲግሪ ተጭኖብሃል:: እስቲ የ4 ኪሎን ፖለቲካ አስበው? እየተመራ ያለው እዚያው 6 ኪሎ ባለ የፖለቲካል ሳይንስ ፕሮፌሰር ነው ወይስ ከጫካ በመጣ ሽፍ^ታ?
1994 ላይ የ2 ሺህ 900 ዓመታት የኢትዮጵያ ነገሥታት የሥልጣን ርክክብ መጽሐፍ ጽፌ ነበር:: ወደ ፋይናንሱ ስለነበርኩ አልታተመም:: በጥናቴ እንዳየሁት የኢትዮጵያ የሥልጣን ርክክብ የሽፍታ-ለ-ሽፍታ ነው:: በቅርብ አሥርተ ዓመታት "በምርጫ ምናምን" ፉገራ ነው:: ባሕላችንም ይሁን ታሪካችን ያንን አያሳይም:: ፖለቲካው በፖለቲካ ሳይንስ ሳይመራ ቢዝነሱ እንዴት ብሎ ነው በቢዝነስ ሳይንስ የሚመራው? You can’t never succeed in business ዊዝ ቢዝነስ ሳይንስ:: የአሜሪካ የቢዝነስ ሳይንስ ከተማርክ ለኢትዮጵያም ለአሜሪካም አትሆንም:: ተምረህና ተመርቀህ ስትወጣ በነጋዴውም በካድሬውም አትበሳጭ:: በባሕሉ ነው እየሠራና እየኖረ ያለው:: አንተ ነህ ያፈነገጥከው:: ሀገሪቷ የሌላትን ነገር ነው የተማርከው:: በበረዶ ሸርተቴ ማስተርስ የሠራ አለ:: በጂዖሎጂ ስኮላር አግኝታ አውሮፓ ሄዳ የማርስ ላይ ውኃ ማስተርስ ሠርታ የመጣች ልጅት አውቃለሁ ወላሂ::
እኛ አካውንቲንግ ከመቶዎች አልፈን ሺዎች ተጠግተን የተመረቅንበት ዓመት ላይ 4 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ 12 የፋብሪካ ኬሚስት ተመርቀው ነበር:: አንድ ዘመዳችን በዘመድ ቆዳ ፋብሪካ ተገኝቶለት ሁለት ወር ሠርቶ አቋርጦ ይኸው ለ26 ዓመታት ሳያቋርጥ እየቃመ ነው:: ባለዲግሪ ሆኖ እንዴት ከገጠር ከመጡት ጋር ቆዳ ያልፋ? እናልህ ነጋዴው በሥርዓት በንግድ ፖለቲካ ማለትም በሽፍታነት እየነገደ ነው:: አንተ ነህ ቢሮ ገብተህ አዋክበህ ብር የምትፈልጠው:: ለነገሩ ብር ሲሰጥህ የወሰደብህን ያውቀዋል:: ሒሳብ ውስጥ ከቶታል::
በአሁን ወቅት መደበኛ ትምህርት ማለትም at least ቢኤ ዲግሪ የግድ ነው:: የፈለግህ ጎበዝ "ሹፌር-ሜካኒክ" ብትሆን ያለመንጃ ፈቃድ መንዳት እንደማትችለው ሁሉ ያለዲፕሎማና ዲግሪ ብዙ ቦታ መንቀሳቀስ አትችልም:: ትክክለኛ ትምህርት ወላሂ ያሳድጋል:: የተረጋጋ ኑሮ ያኖራል:: እናልህ ይህ ከመሆኑ ጋር አሁን ላይ ቢኤ ማለት መሠረተ ትምህርት እንደመማር ነው:: በጣት መፈረም ትንሽ የተሻለ በለው:: ጥሩ ነው ግን በጣት ከመፈረም ብዙም ያልራቀ ዲግሪ ይዘህ ዲግሪው አይጫጫንህ:: በትምህርቱም በልፋቱም ግፋ:: Am an ኢንጂነር እኮ ብሎ መኮፈስ አላዋጣም:: የፊዚክስ ፎርሙላና ዲግሪ ድንጋይ ከማሞቅ አላዳነም:: በጣትህ ከመፈረም ስላልራቅህ ነው:: የሕክምና ዲግሪም የኢንጂነሮቹ ምድብ ጋር ተቀላቅሏል:: Am a ዶክተር እኮ ስትል ፈጣን ነርስህ ይቀጥርሃል:: ዶክተር እና ፕሮፌሰር ኢንጂነርና ሳይንቲስት "ደመወዝ አነሰን" ብሎ ማለቃቀስ አያምርበትም:: እና መፍትሔ ገበሬዎች ያምጡልህ? ወይስ ወዛደሮች? ኡስታዝም አለቃቅሶ ዶክተርም አለቃቅሶ ሰው ምን ይሁን? ቲክቶከር ወይስ ዩቲዩበር?
ሲጠቃለል:- እየሠራህ ተማር:: እየተማርክ ሥራ:: ተማሪ ነኝ ብለህ ሴት ስታሳድድ ማለት እኮ ቂሊንጦ እስር ቤት ሆነህ ሀሺሽ እንደማሳደድ ነው:: የዩኒቨርሲቲ ዕድሜ is እጅግ ምርጡ እድሜ ነው:: በረፍት ስትመጣ መንጃ ፈቃድ አውጣ:: የሆነ የሥራ ቦታ ተላላክ:: አጫጭር ኮርስ ተማር:: ልጄ ከውጭ ሀገር ዩኒቨርሲቲ ለ2 ወር እረፍት ሲመጣ መንጃ ፈቃድ ተምሮ ሰልጥኖ መንጃፈቃዱን ይዞ ሄደ:: ሌሎች ትላልቅ ሀጃዎችን ፈጽሞ ተመለሰ:: ማሻአላህ::