መዝሙር በግጥም


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


መዝሙር 147:7
ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፤ ለአምላካችንም
በመሰንቆ ምስጋና አቅርቡ።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri








♡ አሳዳጊዬ ♡


አሳዳጊዬ ማይልህ አንተ ያላሳደግከው
ማን አለ ሚካኤል ከፍ ያላደረግከው
የሕይወቱ ነህ ከፍታ ክብርና ማዕረጌ
አልረሳም ሥራህን በቤትህ አድጌ


ከልጆቹ መሐል አንዷ ምስክር ነኝ
ሚካኤል አባቴ እርሱ እየጠበቀኝ
መጠበቅን ያውቃል መሰወር ከክፉ
አለው እየረዳኝ ከልሎኝ በክንፉ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
ይሰምራል የልቤ ጠይቄው አላፍርም
እርሱ ከእኔ ጋር ነው ብቻዬን አልቆምኩም
የትላንት ታሪኬ መዝገቡ ቢከፈት
በነገሬ ሁሉ ሚካኤል አለበት
መልካምን ይደርጋል ወዳጅ ለወዳጅ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወቴ
ለኔ ያላረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጁ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለሌጁ

አዝ= = = = =
ከኔ አልተለየም ዛሬም በሕይወት
አየዋለሁ ቀድሞ ሁልጊዜ ከፊቴ
ይሄ ነው ምስጢሬ ወጥቶ የመግባቴ
ሚካኤል ይመስገኔን ኃያሉ አባቴ
መልካም ያደርል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

አዝ= = = = =
መገኛዬ ደጁ ሌላ አድራሻ የለኝ
የሚካኤል ልጅ ነኝ በፍቅሩ ያደኩኝ
በመላኩ ምልጃ አጊጧል ሕይወትቴ
ለኔ ያላደረገው ምን አለ አባቴ
መልካምን ያደርጋል ወዳጅ ለወዳጁ
ድንቅ አድርጎልኛል ሚካኤል ለልጁ

መዝሙር
ዘማሪት ሊዲያ ታደሰ

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
   @maedot_ze_orthodox
   ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ይለይብኛል ሚካኤል ✞


ጠብቆ አሳድጎ ከልጅነቴ
አባት እየሆነኝ ሚካኤል አባቴ
ይለይብኛል ሚካኤል ይለይብኛል(2)
በክንፉ ሸፍኖ በቤቱ አሳድጎኛል (2)


አያምርብኝ ብዘነጋው ታሪኬን
ሚካኤል ነው ያስጌጠልኝ ህይወቴን
አረሳብኝ እርሱ አትርሳብኝ ያልኩትን
ለካስ ሰምቶኝ ኖሯል የልጅነት ጸሎቴን

ሚካኤል ያን ሁሉ ዘመን የታገሰኝ
ሚካኤል===ፍሬ ጠብቆ ያልቆረጠኝ
ሚካኤል===የከፍታዬ መሰላል
ሚካኤል===መነሻዬ ሆነሀል

አዝ====

እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን


አዝ====
ውድቅ አረገው የጠላቴ ክፉ እቅድ
አራመደኝ በከፍታዬ መንገድ
ሊያስቀረኝ አልቻለም ሊጎትተኝ ባላጋራ
ተጥሎ ስላለ በእግዚአብሔር ድንቅ ስራ

ሚካኤል===እሳታዊ ነው ነበልባል
ሚካኤል===ጠላቴ ፊትህ ይቀልጣል
ሚካኤል===ለኔ አይኔ ነው መከታዬ
ሚካኤል===የዘለዓለም ጠባቂዬ

አዝ===
እንዳይከፋኝ እንዳልደፋ አንገቴን
እንዳላለቅስ እንዳለፈስ እንባዬን
እንዳይርቀኝ ደስታ በመንፈሴ እንዳልዝል
ካጠገቤ አይርቅም ያሳደገኝ ሚካኤል

ሚካኤል ቀኔም ቀን አይሆን ሳልጠራህ 
ሚካኤል===ና ድረስልኝ ሳልልህ
ሚካኤል===እንዳስጀመርከኝ ጅማሬዬን
ሚካኤል===አሳምረው ፍፃሜዬን


መዝሙር
ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ


♡ ብዙ ልጆች አሉት ♡

ብዙ ልጆች አሉት ለሥሙ ምሥክር
በዙሪያው ያሉትን አብቅቷል ለክብር
ስለ ፍጹም ምልጃው ለእኔ ግን ይለያል
መልዓኩ ሚካኤል ስለው ደስ ይለኛል


ከመላዕክት ክብሩ ከፍ ከፍ ብሎ
በአምላኬ ተሾመ ዘንዶውንም ጥሎ
አሳዳጊዬነው ሆኖ እናት አባቴ
ሚካኤል በአለበት ይሸሻል ጠላቴ

ከሚታየው ሁሉ ልቤ ከሚፈራው
ካላየሁት ነገር ጠላት ከሰወረው
ያድነኛል ፈጥኖ በመንገዴ ወቶ
ሚካኤል ሀያሉ ክንፎቹን ዘርግቶ

በባሕራን ታሪክ በነተላፊኖስ
በአፎምያ መትረፍ በነ ዱራታኦስ
በነብዩ ዳንኤል መች ይፈጸምና
የሚካኤል ስራ ይቀጥላል ገና

በጉዞ የረዳችሁ በባሕር በየብሱ
ፈጥኖ ደርሶላችሁ ዕንባን ስታፈሱ
ስለታችሁ ሰምሯል ቁሙ ለዝማሬ
በሚካኤል ምልጃ የቆማችሁ ዛሬ


ክብር ለሚገባው ክብርን እንሰጣለን
ንጉሥ ለወደደው አንሰግድለታለን
እንኳን ለሚካኤል ለሚቆም ጌታ ፊት
ክብርን እንሰጥ የለ ለምድር ሹማምንት

መዝሙር
በሊቀ መዘምራን ቴዎድድሮስ


ይችላል ሚካኤል

የቀደመው እባብ ከላይ የተጣለው
በዚህ በምድር ላይ ኃይል ስልጣን ካለው
የእግዚአብሔር መላእክማ
ቅዱስ ሚካኤልማ
አለልን በፊቱ አለልን በግርማ

አዝ_
ዓለምን ከያዛት ከላይ የወደቀው
ወጥመድ እየሰራ ምድሩን ካስጨነቀው
ድል ያደረጉትማ ሰፍረዋል ፊታችን
የማይደፈር ነው የእሳት ነው ቅጥራችን
     የእግዚአብሔር መላእክማ
     ቅዱስ ሚካኤልማ
      አለልን በክብር አለልን በግርማ


አዝ_
ሊውጥን ከዞረን  የወደቀው ዘንዶ
ሊያድነን ይሰፍራል ሚካኤልም ወርዶ
ወጥመድ ሊያደርግብን ዳቢሎስ ከቻለ
የሚሰብረው መልዕክ በዙሪያችን አለ
      የእግዚአብሔር መልዕክማ
      ቅዱስ ሚካኤልማ
      አለልን በክብር በግርማ


አዝ_
በሰማይ ተዋግቶ ድል የተደረገ
ሰይፍና መከራን ችሎ ካደረገ
ይችላል ሚካኤል ከእሳቱ ሊነጥቀን
የሚነካን የለም የንጉስ ልጆች ነን
     የእግዚአብሔር መልዕክማ
     ቅዱስ ሚካኤልማ
     አለልን በክብር አለልን በግርማ 


አዝ_
ከእግዚአብሔር ሊለየን ሰይጣን ከደከመ
በሀሰት ሊከሰን በፊቱ ከቆመ
ብርሃናዊ መልዕክ ሚካኤል ይደርሳል
በምልጃ በኃይሉ ክሱን ይሰርዛል
     የእግዚአብሔር መልዕክማ
     ቅዱስ ሚካኤልማ
     አለልን በክብር አለልን በግርማ



ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ


ከሚካኤል በቀር


ከሚካኤል በቀር የሚያጽናናኝ የለም
ረዳቴ እርሱ ነው በመከራዬ ቀን



ሃዘኔ እጅግ በዝቶ - ከሚካኤል በቀር፣
የየሚረዳኝ ሳይኖር በስደቴ ዘመን፣
ሰላም ከእኔ ርቆ - ከሚካኤል በቀር፣ ጭንቀት አስጠብቦኝ በዙሪያዬ ከቦኝ፣
ዛሬ ግን አጽናኜ - ከሚካኤል በቀር፣
ሚካኤል ደረሰ ጠላቴ አፈረልኝ።
ሚካኤል ነው - የዳዊት ረዳት ከጎልያድ ያዳነው፣
ሚካኤል ነው - መንፈሳዊ ብርታት ኃይልንም የሠጠው

ቃልኪዳኑ ግሩም - ከሚካኤል በቀር፣
ዝክሩን ለዘከሩት ስሙንም ለጠሩት፣
አጋንንት አይቀርቡም - ከሚካኤል በቀር፣
ስዕሉ ባለበት ድርሳኑን ቢደግሙት፣
በረከት ይገኛል - ከሚካኤል በቀር፣
በእርሱ ቢማጸኑት ከለመኑት በእውነት።
ሚካኤል ነው - በትረ መስቀል ይዞ የሚጠብቀኝ፣
ሚካኤል ነው - ከአንበሶች መንጋጋ የሚታደገኝ


በኑሮአችን ሁሉ - ከሚካኤል በቀር፣
እርሱ ይመራናል ፈጥኖ ይረዳናል፣
ፈርኦንን ድል ነስቶ - ከሚካኤል በቀር፣
ከግብጽ አውጥቶናል በብርሃን መርቶናል፣
የኤርትራን ባሕር - ከሚካኤል በቀር፣
ከፍሎ እንዳሻገረን ከነዓን ገብተናል፣
ሚካኤል ነው - ከበለአም እርግማን እስራኤልን ያዳነው፣
ሚካኤል ነው - ዛሬም በአዲስ ኪዳን ስሙ የገነነው


በሕብረት የተዘመረ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@Yemezmurgtm
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ ምድር አበራች ✞

ከመልአኩ ክብር የተነሳ ምድር አበራች[፪]
ፀጋውና ክብሩ ሆኗት የምስራች
ኃያል[፪] ከመላእክት ክብሩ የገነነ
ሊረዳኝ የመጣው ቅዱስ ሚካኤል ነው(፪)

        
ሲደግፈኝ ክንዱ በዘመኔ
ምልጃው ሲጠብቀኝ እያለፈ ቀኔ
እየመራኝ በብርሃኑ ፋና
ሚካኤል መንገዴን አቀና
   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

        
እያጽናናኝ ፍጹም ከድካሜ
ስጠራው ተፈወስኩ ዳንኩኝ ከህመሜ
ሊመግበኝ ለተራብኩት መና
ደረሰልኝ ሚካኤል ገናና
   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

        
ያሻገረኝ መልአክ ሚካኤል ነው
በምልጃው ይደርሳል ቀርቦ ለለመነው
ለነፍሴ ከለላ ሆኖላት
አተረፈኝ ከዕደ ረበናት

   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ


ዲ/ን ኪሮስ ይኄይስ
መዝሙር

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈






የቅዱስ ሚካኤል መዝሙር ስብስብ ዛሬ ይለቀቅ የምትሉ እስኪ 50 ❤️ 👈 like ከሞላ ይለቀቃል




✞ ምድር አበራች ✞

ከመልአኩ ክብር የተነሳ ምድር አበራች[፪]
ፀጋውና ክብሩ ሆኗት የምስራች
ኃያል[፪] ከመላእክት ክብሩ የገነነ
ሊረዳኝ የመጣው ቅዱስ ሚካኤል ነው(፪)

        
ሲደግፈኝ ክንዱ በዘመኔ
ምልጃው ሲጠብቀኝ እያለፈ ቀኔ
እየመራኝ በብርሃኑ ፋና
ሚካኤል መንገዴን አቀና
   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

        
እያጽናናኝ ፍጹም ከድካሜ
ስጠራው ተፈወስኩ ዳንኩኝ ከህመሜ
ሊመግበኝ ለተራብኩት መና
ደረሰልኝ ሚካኤል ገናና
   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ

        
ያሻገረኝ መልአክ ሚካኤል ነው
በምልጃው ይደርሳል ቀርቦ ለለመነው
ለነፍሴ ከለላ ሆኖላት
አተረፈኝ ከዕደ ረበናት

   ዐይኑ ዘርግብ ዐይኑ
   ኦ ሚካኤል ታየ በብርሃኑ
   ሲማልድ ሲማጸን በፊቱ
   እግዚአብሔር አየን በምሕረቱ


ዲ/ን ኪሮስ ይኄይስ
መዝሙር

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


✞ በአምሳሉ ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ ✞

በአምሣሉ ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ
በዓርአያው ለሠራኝ ለቅድስት ሥላሴ
እገዛለታለሁ በሥጋ በነፍሴ/፪/


ከድንኳኔ ገብቶ በቸርነት ያየኝ
ከሐገር ከወገን ከዘመድ የለየኝ
ሥሙን ሊያሸክመኝ ሥሜን የቀየረው
ዘሬን እንደ አሸዋ ያበዛው እርሱ ነው
ቅድስት ሥላሴ



ሥሙን እንድቀድስ ክብሩን እንድወርስ
እፍ ብሎብኛል የሕይወት እስትንፋስ
ከፍጥረቱ ሁሉ አልቆኛል ሠርቶ
መንግስቱን እንድወርስ ሕያውነት ሠጥቶ
ቅድስት ሥላሴ


ገና ሳልፈጠር ጀምሮ የሚያውቀኝ
በበረከት አጥሮ ነገን የሚያይልኝ
በእርሱ ነው መቆሜ በእርሱ ነው መኖሬ
ትናንትን አልፌ መድረሴ ለዛሬ
ቅድስት ሥላሴ




በከሐሊነቱ የአመጣኝ ከምድር
ከፍጥረት ለይቶ የሰራኝ ለክብር
የሚመሰገን ነው በአንድነት ሦስትነት
እግዚአብሔር እርሱ ነው አምላከ አማልዕክት
ቅድስት ሥላሴ

መዝሙር
ዘማሪ ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ


✝️ ሥላሴ ትትረም ✝️


"ይትባረክ እግዚአብሔር አምላከ አበዊነ ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም"

"እግዚአብሔርን በአፌ እጅግ አመሰነዋለሁ በብዙዎችም መካከል አከብረዋለሁ"

ሥላሴ ትትረመም
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር/2/
ሥላሴ ትትረመም ወትትነከር/2/

ይገባል ምስጋና ይገባል ውዳሴ
ሁሉን ለፈጠረ ለቅድስት ሥላሴ
ከዘመናት በፊት ቀድሞ የነበረ
ፍጥረቱን በሙሉ ለክብሩ ፈጠረ


ልበል ሀሌሉያ ኪሩቤልን ልምሠል
በእግረ ምስጋና ያሬድን ልከተል
ላቅርብ ምስጋናውን ዘምስለ ሡራፌል
ውዳሴ ምስጋና ነውና ለልዑል

በስም ሦስት ሲሆን እንዲሁም በአካል
በግብርም ሦስት ነው ያለመቀላቀል
ፍጥረትን በመፍጠር በአምላክነት
በባህርይና ደግሞም በመንግስት
አንድ አምላክ ነው እንጂ አይባልም ሦስት


በኪሩቤል ጀርባ ዙፋኑን ዘርግቶ
ክብሩን ጌትነቱን ከፍጥረት ለይቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግሥቱ ፀንቶ
ይኖራል ዘለዓለም በመንግስቱ ፀንቶ

ይመስክር ዮርዳኖስ ይናገር ታቦር
የአምላክን ጌትነት የሥላሴን ክብር
ይኸው በዮርዳኖስ ወልድ ተገለጠ
መንፈስ ቅዱስ ታየ አብም ቃሉን ሠጠ






♡ እንዘ ተሐቅፊዮ ♡


እንዘ ትሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ንኢ ማርያም(፪)
ንኢ (፫)ማርያም (፪)



የዋኖስ እናት ነሽ የእርግብ ወላዲቱ
ንኢ ሰናይትዬ ንኢ ናዛዚቱ
የእምነታችን ሙዳይ መንበር ለመስዋዕቱ
        
ገብርኤልም ይምጣ የደስታው አብሳሪ
ነይ ከሚካኤል ጋር ጨለማውን አብሪ
የሕግ ታቦት ሆይ በእኛ መኃል ኑሪ

        
ነጭ እና ቀይ ነው የአንቺ ፅጌሬዳ
የተዋሕዶ አክሊል መለኮት ፀአዳ
በቀይ ስጋ ደሙ አራቀን ከፍዳ
        
በሰቆቃው ሐዘን በማኅሌት ደስታ
በአንድ የሚሰማብሽ ለቅሶ እና እልልታ
የጽጌ ምሥጢር ነሽ የእጣኑ ሽታ



መዝሙር
ዘማሪት ትዕግስት ስለሺ
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈


♡ ቁስቋም ማርያም ♡



🌺ህዳር 6 - ቁስቋም
እመቤታችን ወደ ግብጽ አገር ተሰዳ ስትመለስ ቁስቋም በምትባል አገር ገብታ ያረፈችበት በዓል ነው፡፡ ከገነት የተሰደደውን አዳም ወደ ገነት ለመመለስ ሲል ወልደ እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከድንግል ማርያም ከአረጋዊው ዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ወደ ግብጽ ተሰደደ፡፡ ጌታችን ከ3 ዓመት ከ6 ወር የግብጽ ስደት በኋላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ አስቀድሞ ነቢየ ልኡል ሆሴዕ በትንቢት መነጽርነት ተመልክቶ “ልጄንም ከግብጽ ጠራሁት ” ብሎ ተናግሯል ሆሴ ፲፩፥፩

🌺 መልካም በዓል 🌺

┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
@maedot_ze_orthodox
┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.