ዳጉ-ጆርናል/Dagu-Journal


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


The best fiction is far more true than any journalism
📢 ተዓማኒ የመረጃ ምንጭ ፤ ለሙያው ስነምግባር ተገዢ በሆኑ ጋዜጠኞች ብቻ
👉 በፌስቡክ ገፆቻችን https://www.facebook.com/simon.dereje.56
👉 https://www.facebook.com/mik0Man

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ስልጣን በይፋ የተረከቡት ትራምፕ "የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል" ሲሉ ተናገሩ

ዶናልድ ትራምፕ 47ኛው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ሆነው
በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ሮቱንዳ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።የአሜሪካ ወርቃማ ዘመን አሁን ይጀምራል በማለት በንግግራቸው ላይ "ሰላም እና አንድነት" በሀገሪቱ "ያብባል እናም አሜሪካ ትከበራለች ሲሉ ትራምፕ ገልፀዋል። ትራምፕ የባይደን አስተዳደርን በተመለከተ የስደተኞችን ቀውስ በመፍጠር በመንግስቷ ላይ “የመታመን” ችግር በህዝበ ዘንድ አስከትሏል ሲሉ ተናግረዋል ።

የቴክኖሎጂ ቢሊየነሮች፣ የካቢኔ ተሿሚዎች እና የቀድሞ ፕሬዚዳንቶችን ጨምረው በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል በተካሄደው የበዓለ ሲመት ሥነ ሥርዓት ላይ ተገኝተዋል። ትራምፕ ቃለ መሃላ ከመፈፀማቸው ጥቂት ደቂቃዎች በፊት ጆ ባይደን ስልጣናቸውን ተከትሎ ለቤተሰቡ አባላት ይቅርታ ሰጥተዋል። ቤተሰቤ እኔን ለመጉዳት ባለው ፍላጎት ብቻ የማያባራ ጥቃቶች እና ዛቻዎች እንዲሁም ክስ ደርሶባቸዋል ሲሉ ባይደን ተደምጠዋል። ከሁሉ የከፋው የወገንተኝነት ፖለቲካ መሆኑን ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት ባይደን በመግለጫቸው ገልፀዋል።


አክለውም እንደ አለመታደል ሆኖ እነዚህ ጥቃቶች ያበቃል ብዬ ለማመን ምንም ምክንያት የለኝም ብለዋል። የባይደን የስልጣን ዘመን የመጨረሻ የይቅርታ እድል ያገኙት የባይደን ሁለት ወንድሞች ጄምስ እና ፍራንሲስ ይገኙበታል። እንዲሁም በዝርዝሩ ውስጥ የባይደን እህት ቫለሪ እና ባለቤቷ ጆን ይገኙበታል።ሳራ የተባለችው የጄምስ ባይደን ሚስት በተመሳሳይ የይቅርታ እድሉ ተጠቃሚ ናቸው።ትራምፕ ስልጣን መረከባቸውን ተከትሎ የአስፈፃሚ ትዕዛዞች አካል በመሆን "ብሄራዊ ድንገተኛ አደጋ" ለማወጅ ተዘጋጅተዋል።


ትራምፕ ዳግም ወደ ስልጣን መመለሳቸውን ተከትሎ ለአሜሪካ ህዝብ መልዕክት አስተላልፈዋል። አንድ ነገር ማድረግ የማይቻልን ነው ብሎ ማመን እንደሌለባችሁ ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ በፊታችሁ ቆሜያለሁ ሲሉ ተደምጠዋል። በአሜሪካ ውስጥ የማይቻለውን ማድረግ እንደምንችል አሳይተናል ብለዋል ። ከዚህ ቀን ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ ሉዓላዊ እና ነጻ ሀገር ትሆናለች በማለት አክለዋል። "መጪው ጊዜ የእኛ ነው፤ እናም ወርቃማው ጊዜያችን ገና ጀምሯል ብለዋል።ተቃዋሚዎች ባነሮችን እያውለበለቡ እና የመጪውን የትራምፕ አስተዳደር ፖሊሲዎችን በማውገዝ በኋይት ሀውስ ተቃውሞ አሰምተዋል።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል




የአዲስ አበባ ፖሊስ የባለሀብቱን ገዳዮች መያዙን አስታወቀ

መሰረት ሚዲያ ከሀያ ቀን በፊት ታዋቂው የአክሰስ ኮም ኩባንያ ባለቤት እና የሸበል በረንታ ሲሚንቶ ፋብሪካ ስራ አስኪያጅ አቶ ቢረሳው ምናለ ምሽት 1:30 ላይ ቤታቸው በር ላይ በጥይት ተመትተው እንደተገደሉ መዘገቡ ይታወሳል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ዛሬ ይፋ ባረገው መረጃ የባለሀብቱን ገዳይ እና አስገዳይን ይዞ ምርመራ እያጣራ መሆኑን አስታውቋል።

ወንጀሉን በመፈፀም የተጠረጠረውን መኮንን ይዋል ይፍሩ የተባለውን ግለሰብ እና አብዩ አይተነው ፈንታ ጨምሮ ለወንጀሉ መፈፀም አካባቢውን በመቆጣጠር ተሳትፎ የነበረውን አቶ ወርቁ መለሰ ካሴ የተባሉትን ሦስቱንም ተጠርጣሪዎች በደቡብ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በጌዴዎን ዞን ይርጋ ጨፌ ከተማ ላይ በቁጥጥር ሥር በማዋል ምርመራ እያጣራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

"ምንም እንኳን ተጠርጣሪዎቹ ማንነታቸውን በመቀየር ከወንጀሉ ተጠያቂነት ለማምለጥ በሐሰተኛ ስም ሐሰተኛ መታወቂያ በማዘጋጀት ከኢትዮጵያ በሞያሌ በኩል ወደ ኬንያ ለመጥፋት ቢያስቡም በተሰራው እረፍት አልባ ፖሊሳዊ ጥበብ በታከለበት የክትትልና የምርመራ ስራ በቁጥጥር ስር ውለዋል" ያለው ፖሊስ የወንጀሉ ፍሬ የሆነው ንብረትነቱ የአቶ አብዪ አይተነው ፈንታ የውግ ቁጥር  የሌለው ማካሮቭ ሽጉጥ እና ለማምለጥ የሞከሩበት እንዲሁም ሽጉጡን የደበቁበት ላንድክሩዘር ተሽከርካሪ በኤግዚቢትነት ተይዟል ብሏል፡፡

የምስራቅ ጎጃም ቢቸና ወረዳ ተወላጅ የሆኑት እና የ 'ምናሉ ሆቴል' ባለቤት አቶ ቢረሳው ግድያ ከተፈፀመባቸው በኋላ ቀብራቸው በሳሊተ ምህረት ቤተክርስቲያን ተፈፅሟል።

ምንጭ:- መሰረት ሚዲያ

#ዳጉ_ጆርናል


ጀነራል አል ቡርሀን የአሜሪካን ማዕቀብ ውድቅ አደረጉ

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበሩ ጄኔራል አብዱልፈታህ አል-ቡርሃን አሜሪካ በእርሳቸው ላይ የጣለችውን አዲስ ማዕቀብ ምንም ተጽእኖ እንደሌለው በመግለጽ ውድቅ አድርገውታል። አል ቡርሃን ቅዳሜ ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከሆነ "የዩኤስ ውሳኔን ለማንበብ እንኳ አልጓጓሁም" ብለዋል።

በውጭ ሀገር የተከፈተ የባንክ አካውንት ወይም ሪል እስቴት የለኝም፣ በኦምዱርማን ብሔራዊ ባንክ ውስጥ ያለኝ የሀገር ውስጥ አካውንት እንኳን እንደማንኛውም የጦር ሃይል መኮንን ደሞዜን ለመቀበል ብቻ የተገደበ ነው” ያሉት አልቡርሀን የዋሽንግተን ንብረቱን ለማገድ መወሰን እንዳስገረማቸው ገልፀዋል።

ዩናይትድ ስቴትስ በአል ቡርሃን ላይ የሰላም ድርድርን በማደናቀፍ እና በሲቪሎች ላይ ጉዳት ሲደርስ መቆጣጠር አልቻሉም በሚል ባለፈው ሐሙስ ማዕቀብ መጣሏ አይዘነጋም። የዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለማዕቀቡ መንስኤ ምክንያት የጎደለው የቦምብ ጥቃት፣ በሲቪል ኢላማዎች ላይ እንደ ትምህርት ቤቶች እና ሆስፒታሎች የሚፈፀሙ ጥቃቶችን እና ከህግ አግባብ ውጭ የሆኑ ግድያዎች መሆናቸውን ጠቅሷል።

አል-ቡርሃን ግን የሱዳን ህዝብ ድል ለመጠለፍ ለሚፈልጉ ሁሉ እንደማይፈቅዱ እና ሰራዊቱን የሚደግፉ ኃይሎች ከጦርነቱ በኋላ ስልጣን እንደማይዙ በመግለጽ ሰራዊቱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ያለውን ገለልተኝነት ገልፀዋል። አክለውም ፈጣን የድጋፍ ሰጪ ኃይሎች በሀገሪቱ የወደፊት ሁኔታ ውስጥ ለሚደግፏቸው ሰዎች ምንም ቦታ የለም ብለዋል። ያለን አማራጭ መሬቱን ነፃ አውጥተን ከፖለቲካ ደጋፊዎቻቸው ጋር ለዘላለም ማባረር ነው ድል ​​ቅርብ ነው ሲሉም አክለዋል።

በአልጃዚራህ ግዛት በሲቪሎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስመልክቶ ቡርሃን እንዳሉት የአካባቢው ነዋሪዎች ምንም አይነት ችግር እንደሌለ አረጋግጠውላቸዋል። የሱዳን ጦር የመንግስት ዋና ከተማ የሆነችውን ዋድ ማዳኒን መልሶ ከተቆጣጠረ በኋላ ሰራዊቱ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል ሲሉ የተቃዋሚው የሲቪልና ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች ማስተባበሪያ (ታጋዱም) ተችቷል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል




በነቀምት ከተማ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት የፈፀመው ግለሰብ እና በቪዲዮ ቀርፆ  ለማህበራዊ ሚድያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

በነቀምት ከተማ አስተዳደር 02 ቀበሌ ውስጥ በሁለት ተማሪዎች ላይ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀም በቪዲዮ ቀርፀው ለማህበራዊ ሚዲያ ያሰራጩ ሁለት ተከሳሾች እና ደፋሪው ግለሰብ በፍጥነት ተከታትሎ ለህግ በማቅረብ ውሳኔ ማሰጠቱን የነቀምት ከተማ ፖሊስ መምሪያ ገለፀ።

የነቀምት ከተማ አስተዳር ፖሊስ መምሪያ የወንጀል ምርመራ ዋና ክፍል ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጥቄሳ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደገለፁት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የተባለው ግለሰብ በነቀምት ከተማ 02 ቀበሌ ውስጥ የ17 ዓመቷን ታዳጊ ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች እያለ መንገድ ላይ ጠብቆ ከሁለት ግብረአበሮቹ ጋር አስገድዶ ወደ ጫካ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተገልጿል። አንደኛው ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ17 ዓመቷን ልጅ በዱላ እየደበደበ የለበሰችውን ልብስ ሲያወልቅ እና የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምባት ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር እና ሶስተኛ ተከሳሽ ፍራኦል ታሪኩ የተባሉት ግለሰቦች በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ ከባህል እና ወግ ውጪ አስነዋሪ ተግባሩን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።

በተጨማሪም አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ከሁለቱ ግብረአበሮቹ ጋር በመቀናጀት የ15 አመቷን ታዳጊ ጠልፈው አንደኛ ተከሳሽ የተከራየበት በመውሰድ አንደኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃት ሲፈፅምበት ሁለተኛ እና ሶስተኛ ተከሳሽ የመድፈር ጥቃቱን በእጅ ስልካቸው በመቅረፅ ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን በማስረጃ መረጋገጡን ገልፀዋል።አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ የ15 ዓመቷን ታዳጊ ከነቀምት ከተማ አስተዳደር 01 ቀበሌ ውስጥ መስከረም 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጠልፎ በመውሰድ ከግብረአበሮቹ ጋር በማስገባት በዱላ በመደብደብ ልብሷን እንድታወልቅ በማድረግ የመድፈር ጥቃት ሲፈፀምባት ሁለቱ ግብረአበሮቹ በእጅ ስልካቸው ቪዲዮ በመቅረፅ አስነዋሪ ድርጊቱን ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸውን የነቀምት ከተማ እና የአካባቢው ነዋሪዎቹን ያስቆጣ እንደነበረ ዋና ኢኒስፔክተር ፍሮምሳ ገልፀዋል።

ፖሊስም ይህንን ከማህብረተሰቡ ባህል እና ወግ ውጪ የሆነን ድርጊት በመከታተል በጥቂት ቀናት ውስጥ የድርጊቱ ፈፃሚዎች እና ተባባሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የዚህ ድርጊት ዋነኛ ፈፃሚ እና ተባባሪዎች ላይ ምርመራ መዝገቡን በስፋት በማጣራት በሆስፒታል በተገኘ የምርመራ ውጤት እና በተጎጂዎች ቃል እንዲሁም ተከሳሾች የሰጡት የእምነት ቃል በማጠናከር የምርመራ መዝገቡን አጠናክሮ ለአቃቤ ህግ የላከ መሆኑን ተገልፆል። አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ አንቀፅ 620 ንዕስ አንቀፅ 2 እና ንዑስ አንቀፅ 4  በመጥቀስ በጭካኔ በማሰቃየት የመድፈር ጥቃት በመፈፀም እጅግ አስነዋሪ እና የማህበረሰቡን መልካም ስነምግባር እና ፀባይ በተፃረረ መልኩ የተፈፀመ ድርጊት ለማህበራዊ ሚዲያ ማጋራታቸው ክስ የተመሠረተባቸው መሆኑን ገልፀዋል።

በአቃቤ ህግ የቀረበውን ክስ ሲከታተል የነበረው የምስራቅ ወለጋ ዞን ከፍተኛው ፍርድ ቤት ጥር 5 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አንደኛ ተከሳሽ ሌሊሳ ደበላ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ 12 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሁለተኛ ተከሳሽ ጫላ ዑመር ድርጊቱን በቪዲዮ ቀርፆ በማሰራጨት እና ተጎጂዋን በመጥለፍ ተባባሪ በመሆኑ በ 4 ዓመት እስራት ሲቀጣ ሶስተኛ ተከሳሽ በድርጊቱ ያለው ተሳትፎ አነስተኛ በመሆኑ በአንድ ወር ቀላል እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ዋና ኢንስፔክተር ፍሮምሳ ጢቄሳ ጨምረው ለብስራት ገልፀዋል።

በሰመኃር አለባቸዉ
#ዳር_ጆርናል


የጥምቀት በዓል በተከበረባቸው የተለያዩ ስፍራዎች ላይ የሥርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ዋሉ።
👉ከእነዚህ መካከል በተወሰኑት ላይ የቅጣት ውሳኔ ተላልፏል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የበዓሉን ሠላማዊነት በቅርበት ለመከታተልና ለህብረተሰቡ ተደራሽ አገልግሎት ለመስጠት በተለያዩ የበዓሉ ማክበሪያ ስፍራዎች ላይ ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ በማቋቋም የምርመራ እና የክትትል ቡድን በማዋቀር ከፍትህ እንዲሁም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር ተቀናጅቶ ባከናወነው ተግባር ወንጀልን እና የወንጀል ስጋቶችን መቆጣጠር ችሏል፡፡ 

በጥምቀት በዓል አከባበር ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀሙ ከ20 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለው በእነዚሁ በጊዜያዊነት በተቋቋሙት ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ምርመራ ተጣርቶባቸዋል፡፡ ከተያዙት መካከል የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው መኖራቸውም ታውቋል፡፡

ብርሀኑ አበበ የተባለው ተከሳሽ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ልዩ ቦታው አበበ ቢቂላ ስታዲዮም በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ላይ በርካታ ሰው መሰባሰቡን እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅሞ የስርቆት ወንጀል ፈፅሟል፡፡

ከክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁመው ተከሳሹ ጥር 11 ቀን 2017 ዓ/ም ከጠዋቱ በግምት 3:00 ሰዓት ገደማ ከሁለት ግለሰቦች ኪስ ውስጥ 2 ሞባይል ስልኮችን ሰርቆ እጅ ከፍንጅ ተይዟል፡፡

ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን ካጠናቀቀና አቃቤ ህግ ክስ ከመሰረተ በኋላ በፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ ችሎት በበዓሉ ስፍራ በተቋቋመው ጊዜያዊ ፍርድ ቤት በዚያው ዕለት ተከሳሽ ብርሃኑ አበበ በ2 አመት ከ9 ወር ፅኑ እስራት እንዲቀጣ እንደተወሰነበት የፖሊስ መምሪያው መረጃ ያመለክታል። 

በተመሳሳይ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 09 ጥሩነሽ ቤጂንግ ሆስፒታል አካባቢ በነበረው የጥምቀት በዓል ማክበሪያ ስፍራ ላይ የስርቆት ወንጀል የፈፀመ ግለሰብ በእስራት ተቀጥቷል፡፡

ታዘበው ሞላ የተባለው ይኸው ተከሳሽ በበዓሉ ከታደሙ አንዲት ግለሰብ ላይ ሞባይል ስልክ ሰርቆ በድጋሚ ከሌላ ሰው ላይ ሊሰርቅ ሲሞክር በህብረተሰቡ ትብብር እጅ ከፍንጅ ተይዞ በስፍራው በተቋቋመው ጊዜያዊ ፖሊስ ጣቢያ ምርመራ ከተጣራበት በኋላ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

ዛሬ ጥር 12 ቀን 2017 ዓ/ም የተከሳሽ ታዘበው ሞላን ጉዳይ የተመለከተው የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አቃቂ ቃሊቲ  ምድብ ወንጀል ችሎት ጉዳዩን በተፋጠነ ችሎት በማየት ጥፋተኝነቱን በማስረጃ በማረጋገጥ በ6 ወር እስራት እንዲቀጣ የወሰነበት መሆኑን የክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

በሌላ በኩል በጃን ሜዳ በነበረው የጥምቀት በዓል አከባበር ስነ ስርዓት ላይ የታዳሚውን ብዛት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ተመሳስለው ገብተው ወንጀል የፈፀሙ 21 ተጠርጣሪዎች በፖሊስ እና በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ውለው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል፡፡

ከአራዳ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት፣ የቅሚያ እና የራስ ያልሆነን ንብረት ይዞ መገኘት ወንጀል የፈፀሙ ናቸው ተብሏል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ  እጅ ላይ የወንጀል ፍሬ የሆኑ እና የተለያየ አይነት ሞዴል ያላቸው ዘጠኝ ሞባይል ስልኮች በኤግዚቢትነት ተይዘዋል፡፡

#ዳጉ_ጆርናል




በ2017 በጀት ዓመት በአዊ ዞን የሚገኙ የቱሪስት መዳረሻዎች  በአስር የውጪ ዜጎች ብቻ መጎብኘታቸው ተነገረ  

በ2017 በጀት ዓመት  በአዊ ዞን የሚገኙ የቱሪዝም  ቦታዎች ለመጎብኘት የሚመጡ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱ ተገልጿል ።በአዊ ዞን  በበጀት ዓመቱ 330 ሺህ ሰው ወደ አካባቢው በመሄድ ይጎበኛል ተብሎ ቢጠበቅም  ወደ  ቦታው የሄደው 75 ሺህ ቱሪስት ብቻ መሆኑ ተገልጿል ።

በአካባቢው  ባለው    አለመረጋጋት እና  የትራንስፖርት  አገልግሎት   ምቹ አለመሆኑ በአካባቢው የሚመጡ ቱሪስቶች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት መሆኑን  የአዊ ዞን የባህል እሴቶች ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ዋለልኝ ጌቴ  በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት  በሩብ ዓመት እቅዱ  330 ሺህ ጎብኝዎች  ይጎበኛሉ ተብሎ ተጠብቆ የነበረ ቢሆንም ወደ አካባቢው የሄዱ ቱሪስቶች ቁጥር  75 ሺህ  364 ብቻ ነዉ። ይህም ከተያዘው  እቅድ በታች መሆኑን አክለዋል።

በተጨማሪም በገንዘብ ደረጃ ከቱሪስት ለማስገባት የታቀደው  131 ሚሊዮን 640 ሺህ ብር  ለማግኘት የታቀደ ሲሆን  12 ሚሊዮን  175 ሺህ ብር  ገቢ ማድረግ ተችሏል። በአካባቢው ከተገኙት ጎብኝዎች መከካል  10 ብቻ የሚሆኑት የውጪ ዜጎች መሆናቸውን እና  60 ሺህ ብር የሚሆነው ገንዘብ ገቢ የተደረገው ከአስሩ የውጪ ዜጎች  መሆኑን  አቶ ዋለልኝ ጌቴ     ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። 

በአካባቢው  በርካታ ቱሪስቶች የሚገኙበት የፈረስ ውድድር  በጥር 27 የሚከበር መሆኑ እና በዚህም በርካታ ቱሪስቶች ይገኛሉ ተብሎ  እንደሚጠበቅ  ተነግሯል ።  ይህንንም ክብረ በዓል  ለማክበር በርካታ ቅድመ ዝግጅቶች  የተደረጉ መሆኑ የተነገረ ሲሆን በበዓሉ ላይ አካባቢውን  የምትወክለዋን ቆንጆ  ለመምረጥ የቁንጅና  ውድድር ፣ ኤግዚብሽን ፣  የፈረስ ውድድሮች እና ሌሎች ስርዓቶችም በእለቱ የሚጠበቁ መሆናቸው ተጠቁሟል።ክብረ በዓሉም ጥሩ የሚባል ገቢ እና በርካታ ቱሪስቶች ይገኙበታል ተብሎ የሚጠበቅ መሆኑን አቶ ዋለልኝ ጌቴ ገልጸውልናል ።

በኤደን ሽመልስ
#ዳጉ_ጆርናል


ቻይና በደርዘን የሚቆጠሩ ሰዎችን በመኪና ገጭቶ የገደለውን ሹፌር በሞት ቀጣች

በደቡባዊ ቻይና ስታዲየም ዙርያ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ መኪናውን በመንዳት በርካቶችን የገደለው ግለሰብ በሞት መቀጣቱን፤ ቅጣቱም ተግባሪዊ መደረጉን የቻይና መንግስት ሚዲያ ዘግቧል።

የ62 አመቱ ፋን ዌይኪው ህዳር 11 ቀን በቻይና ምድር ላይ በአስር አመታት ውስጥ ከደረሱት የትራፊክ አደጋዎች አስከፊውን አደጋ ያደረሰ ሲሆን በዝሁሃይ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትራክ ላይ መኪናውን በመንዳት በትንሹ 35 ሰዎችን ገድሎ በደርዘን የሚቆጠሩ ሌሎች ደግሞ ማቁሰሉን ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።

የ62 ዓመቱ ሰው የሞት ፍርዱ ዛሬ ሰኞ ተፈፃሚ የተደረገ ሲሆን የሞት ፍርድ በተፈረደ ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ፍርዱ ተግባራዊ መደረጉ በርካቶችን አስገርሟል። ፋን በሚል መጠርያ የሚታወቀው ግለሰቡ “የሕዝብ ደህንነትን አደጋ ላይ በመጣል” ጥፋተኛ ሆኖ መገኘቱን የገለፀው ፍርድ ቤቱ ነገሩን የፈፀመው “በልዩ ሁኔታ ጭካኔ በተሞላበት ዘዴ ነው” ሲል ገልጾታል።

በሚሊዮን ሙሴ
#ዳጉ_ጆርናል


ሀማስ ሶስት ታጋቾችን መልቀቁን ተከትሎ 90 ፍልስጥኤማውያን ከእስር ተለቀቁ

የእስራኤል ባለስልጣናት ሃማስ በጦርነት ለተጎዳው የጋዛ ሰርጥ የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ መሆኑን ተከትሎ የመጀመሪያዎቹን ሶስት ሴት ምርኮኞች አሳልፎ መስጠቱን አረጋግጠዋል። የእስራኤል ወታደራዊ ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ እሁድ አመሻሹ ላይ እንደተናገሩት የ24 ዓመቷ ሮሚ ጎነን፣ የ28 ዓመቷ ኤሚሊ ዳማሪ እና የ31 ዓመቷ ዶሮን ሽታይንብሬቸር ለቀይ መስቀል ተላልፈው በእስራኤል ውስጥ “ደህንነታቸው በተጠበቀ ስፍርል ውስጥ ናቸው” ብለዋል።

በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት 90 የፍልስጤም እስረኞች ተለቀዋል። ከእስራኤል እስር ቤት የተፈቱት ፍልስጤማውያን 69 ሴቶች እና 21 ታዳጊ ወንዶች ከዌስት ባንክ እና እየሩሳሌም እንደተለቀቁ ሃማስ አስታውቋል። የሮይተርስ የዜና ወኪል እንደዘገበው ከተፈቱት ሰዎች መካከል አብዛኞቹ በቅርቡ የታሰሩ እንጂ ፍርድ ቤት አልቀረቡም ወይም አልተፈረደባቸውም ብሏል።

በመጀመርያው የእርቅ ሂደት እስራኤል ወደ 1,900 የሚጠጉ ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትፈታ ሲጠበቅ ሃማስ 33 የሚሆኑ የእስራኤል ታጋቾችን ይፈታል ተብሎ ይጠበቃል።የመከላከያ ሰራዊት ቃል አቀባይ ዳንኤል ሃጋሪ በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ እንደተናገሩት በዚህ የመጀመሪያ ስድስት ሳምንት ሂደት "በየሳምንቱ ከሦስት እስከ አራት ተጨማሪ ታጋቾች ይለቀቃሉ"። የሐማስ ባለስልጣን ለኤኤፍፒ የዜና ወኪል እንደተናገሩት ቀጣዩ የታገቱ ሰዎችን የማስፈታት እና የእስረኞች ቅያሬ ቅዳሜ ይካሄዳል።

ከ630 በላይ ሰብዓዊ ርዳታዎችን የጫኑ የጭነት ተሽከርካሪዎች እሁድ እለት ጋዛ የገቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ቢያንስ 300 ያህሉ ወደ ሰሜናዊው ጋዛ ሰርጥ አቅጣጫ ማቅናታቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ምክትል ዋና ጸሃፊ ቶም ፍሌቸር ተናግረዋል።በቅርብ ሳምንታት ውስጥ በአማካይ 40 የጭነት ተሽከርካሪዎች ብቻ እየገቡ ነበር፣ ከግጭቱ በፊት ግን በየቀኑ 500 የሚጠጉ የረድኤት ድጋፍ የያዙ ተሽከርካሪዎች ወደ ጋዛ ይገቡ ነበር። የተኩስ አቁም ስምምነቱ በየቀኑ 600 የእርዳታ ተሽከርካሪዎች እንዲገቡ የሚያስችል ነው።

በስምኦን ደረጄ
#ዳጉ_ጆርናል




ጣፋጭ ድል ለፔፕ

ኢፕስዊች 0-6 ማን ሲቲ

#ዳጉ_ጆርናል


ማንችስተር ሲቲ ወደ አራተኛ ደረጃ 😮

ፊል ፎደን ወደ ግብ አስቆጣሪነቱ የተመለሰ ሲሆን በዛሬው ጨዋታ 2ግቦች እና 1አሲስት ከወዲሁ ማበርከት ችሏል

ጎሎቹ 👉 @mikoethio
#ዳጉ_ጆርናል


⚽️ሪያል ማድሪድ ድል በማድረግ ላሊ ጋውን መምራት ጀመረ

Real Madrid claim victory and leapfrog to the top of the La Liga table! 🔝

#ዳጉ_ጆርናል


ዜና ዕረፍት

አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ አረፈ

አንጋፋው አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅአገኘሁ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል፡፡

ባደረበት ሕመም በሕክምና ሲረዳ ቆይቶ ሕይወቱ ማለፉን የአርቲስቱ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡

ከ30 በላይ ፊልሞች እና ቴአትሮች ላይ በትወና በመሳተፍ በብዙዎች ዘንድ አድናቆትን ያገኘው አርቲስት እንቁስላሴ አጋጥሞት በነበረው የኩላሊት ሕመም ጋር በተገናኘ ህክምናውን ሲከታተል እንደነበር ይታወሳል።

አርቲስቱ የእግር እሳት፣ ሥርየት፣ ሰው ለሰው፣ መንጠቆ ቴአትር እና ሌሎች የቴሌቪዥን ድራማዎች እና ፊልሞች ላይ በትወና መሳተፉን የሕይወት ታሪኩ ያስረዳል፡፡

በአዲስ አበባ ጉለሌ አካባቢ የተወለደው አርቲስት እንቁስላሴ ÷በኢትዮጵያ የሲኒማ ኢንዱስትሪ ዘርፍ የራሱን አሻራ አስቀምጧል፡፡

አርቲስት እንቁስላሴ ወርቅ አገኘሁ የአንድ ወንድ እና የሁለት ሴት ልጆች አባት ነበር።

ዳጉ ጆርናል በአርቲስት እንቁስላሴ ህልፈት ሕይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለወዳጅ ዘመዶቹ እና አድናቂዎቹ መፅናናት ይመኛል።

#ዳጉ_ጆርናል


ቲክቶክ በይፋ ከመዘጋቱ በፊት አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት መስጠት አቆመ

ቲክቶክ እንዲዘጋ የሚያዘው ሕግ ተግባራዊ ከመደረጉ ከሰዓታት በፊት መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ አገልግሎት መስጠት ማቆሙ ታውቋል።

ተጠቃሚዎች ስልካቸውን ሲከፍቱ መተግበሪያው አሜሪካ ውስጥ ጥቅም ላይ እንዳይውል በመታገዱ ምክንያት "ለጊዜው ቲክቶክን መጠቀም አትችሉም" የሚል መልዕክት ያሳያል።

አክሎ "ፕሬዝደንት ትራምፕ ሥልጣን ሲይዙ ከእኛ ጋር በመሥራት ቲክቶክ ድጋሚ ክፍት እንዲሆን መጠቆማቸው ዕድለኛ ያደርገናል" ሲል ይነበባል።

ኩባንያው የፕሬዝደንት ዳይደን አስተዳደር ቲክቶክ እንደማይታገድ ማስረገጫ ካልሰጡ ከእሑድ ጀምሮ አገልግሎት መስጠት እንደሚያቆም አስጠንቅቆ ነበር።

ተመራጩ ፕሬዝደንት ዶናልድ ትራምፕ ከዚህ ቀደም ሰኞ ሥልጣን ከያዙ በኋላ ለቲክቶክ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜ እንደሚሰጡት ተናግረው ነበር።

ትራምፕ ቅዳሜ ኤንቢሲ ኒውስ ለተሰኘው ጣቢያ "የ90 ቀናት ማራዘሚያው መካሄዱ የሚቀር አይደለም፤ ምክንያቱም ትክክለኛው እምጃ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

"ይህን ለማድረግ ከወሰንሰኩ ሰኞ ዕለት የማደርገው ይሆናል።"

ዋይት ሐውስ በሰጠው መግለጫ የቲክቶክ ዕጣ ፈንታ በመጪው አስተዳደር እርምጃ ላይ የሚወሰን ነው ብሏል።

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አርብ ዕለት ቲክቶክ ያቀረበውን ይግባኝ ውድቅ በማድረግ ባለፈው ሚያዚያ የፀደቀው ሕግ እንዲፀና ወስኗል።
ተጠቃሚዎች እንደሚሉት ቲክቶክ ከአፕል እና ጉግል መተግበሪያ ማውረጃ ቋቶች እንደተወገደ ተመልክተዋል።

በተጨማሪም መተግበሪያው ቪድዮ ማሳየት አቁሟል።

ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት ነው የአሜሪካ ሕግ አውጭዎች ቲክቶክ ከቻይና መንግሥት ጋር ግንኙነት ስላለው መታገድ አለበት ሲሉ አዋጅ ያፀደቁት።

#ዳጉ_ጆርናል


ኡናይ ኤምሪ አሁንም መድፈኞቹን ነጥብ አስጥሏል
Unai Emery's done it again

#ዳጉ_ጆርናል


22ተኛ ሳምንት የእንግሊዘ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ

        አርሰናል 2-2 አስቶን ቪላ
⚽ ማርቲኔሊ ⚽️ቲሌማንስ
⚽️ ሀቨርት ⚽️ዋትኪንስ

ጎሎች 👉 @mikoethio
#ዳጉ_ጆርናል


ጋብሪኤል ማርቲኔሊ ግብ ባስቆጠረባቸው ያለፏ 41ጨዋታዎች መድፈኞቹ አልተሸነፉም

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.