ቤተ ሊባኖስ ₃


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Din


የኢ/ ኦ/ተ/ቤ/ክርስቲያን አስተምሮ ና ስርዓት የጠበቁ
👉 መንፈሳዊ መዝሙሮች
👉 መንፈሳዊ ትምህርቶች
👉 መንፈሳዊ ግጥሞች
👉 መንፈሳዊ ታሪኮች
👉 ምንፈሳዊ ምክር ነክ ፁፎች
👉 ንግሶች ስኖሩ እናሳዊቃለን
👉ለመናፍቃለ የተለያዩ መልሶችን እንሰጣለን
ግሩፕን ለመቀላቀል @zemariwochu3
ለተለያየ ጥያቄ ና @DA121922 ካላቹ አናግሩኝ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Din
Statistika
Postlar filtri


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱




#ታላቅ_መንፈሳዊ_ጉዞ ወደ ምድረ ከብድ አቦ ገዳም

በመጀመሪያ ሰላመ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን እያልን የአያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤ/ክ ተክለ ቴዎፍሎስ ሰንበት ት/ቤት በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የታላቁን ገዳም ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓመታዊ በዓለ ንግሥ ምክንያት በማድረግ መጋቢት 4-5/2017ዓ.ም ወደ ምድረ ከብድ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም መንፈሳዊ ጉዞ አዘጋጅተናል።ስለዚህ እርስዎም የበረከቱ ተሣታፊ ይሆኑ ዘንድ በልዑል እግዚአብሔር እና በጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ስም ተጠርተዋል።

✍ መነሻ ቀን : 04|07|2017
✍ መነሻ  ⌚ : 12:00 ሰዓት
✍ መመለሻ  05|07|2017ከንግሥ በኋላ
✍ የጉዞ ዋጋ : 750 ብር መስተግዶን ምሳን ጨምሮ
✍መነሻ ቦታ : አያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቅጥር ጊቢ ዉስጥ  ና አያት አደባባይ   መገናኛ ና ጦር አይሎች
                    

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር :

+251953125078 ዳኜ
                  
+251952559464 በሱፍቃድ                    
+251941137351 ፀጋ

የጉዞ ቦታ ሳይሞላ አሁኑኑ ይመዝገቡ
በረከቱ እንዳያልፈን በቶሎ እንመዝገብ
                
     ትኬቶችን በአያት ጣፎ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን መግቢያ በሮች ና የደብሩ ሰንበት /ት/ት  ሱቁ ላይ በሁለቱም መግቢያ  በሮች ሱቁ ላይ ታገኛላችሁ                        
       #ቦታ #ያስይዙ፣#ይመዝገቡ።
  
አዘጋጅ አያት ጣፎ መካነ ብስራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ተክሌ ቴዎፍሎስ ሰንበት /ት/ት

በቴሌግራም @DA121922


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

🌿#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል7⃣

🌺#አዳምጡ መልካም ቆይታ

https://t.me/zemariwochu

ይቀጥላል.


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል6⃣


https://t.me/Abalibanos333


ዐቢይ ጾም (ጾመ 40 ዘጾመ ክርስቶስ)

ይህ ጾም ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ከርሰቶስ በተወለደ በ 30 ዓመቱ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንሰ እጅ ጥር 11 ቀን በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ ከጥር 12 ቀን እስከ የካቲት 21 ቀን ድረስ 40 መዓልትና ሌሊት ከቆመ ሳያርፍ ከዘረጋ ሳያጥፍ በትኅርምት በገዳመ ቆሮንጦስ የጾመው ጾም በመሆኑ ዐቢይ ተብሏል፡፡ [ማቴ. 4.1]፡፡ ጾሙ የተለየ፣ የከበረ፣ የተቀደሰ፣ የጸና፣ የተከለከለ እና እነዚህን የመሰሉ ተቀጽላ ስሞችን ያገኛል፡፡ እኛም ጌታ የጾመውን ለማስታወስ በረከቱን ለማግኘት በግብር እርሱን ለመምሰል የሥጋ ፈቃዳችንን ለነፍስ ፈቃዳችን ለማስገዛት እንጾመዋለን፡፡ ጌታችን የጾመው እቀደስ እከብር ወይም እነፃ ብሎ ሳይሆን ለእኛ አርአያ ለመሆን ነው፡፡ 

ለምን ጾሙን አርባ ቀንና አርባ ሌሊት አደረገው?
✓ እግዚአብሔር አምላካችን የፈጠረውን የሰው ልጆችን አባት አዳምን በልጅነት አክብሮ ገነት ያስገባው በፈጠረው በአርባ ቀኑ ነው፡፡ "ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ እግዚአብሔር ዘገብሮ ለአዳም" አዳምን የፈጠረ እግዚአብሔር ቅዱስ ነው እያሉ እያመሰገነ መላእክት ወደ ገነት አስገብተውታል፡፡ [ቀሌ 4]

✓ ለአዳም አርባ ቀን ከተፈጸመለት በኋላ ወደ ገነት አስገባው፡፡ ሔዋንንም በኹለት አርባ ማለትም በሰማኒያ ቀኑዋ ወደ ገነት አስገባት፡፡ [ኩፋ. 4:12]፡፡ 

✓ በተጨማሪም አዳም ትእዛዘ እግዚአብሔርን ካፈረሰ በኋላ ዲያቢሎስ በአቋራጭ መጥቶ አስወጣው እንጂ ሱባኤ የገባው ለአርባ ቀናት ነበር፡፡ ይህን አርባ ቀን የሰው ልጆች ከስሕተት በኋላ በቀንም ሆነ በዓመት ለጾም፣ ለሱባኤ፣ ከዚያ አልፎ ለመትነት አገልግሏል፡፡

✓ በኦሪት ዘፍጥረት እንደምናነበው የሰው ልጅ በንፍር ውኃ የተቀጣው አርባ መአልትና ሌሊት ነበር፡፡ "አርባ ቀንና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ዝናብ አዘንባለሁና የፈጠርሁትንም ፍጥረት በምድር ላይ አጠፋለሁና፡፡" [ዘፍ. 7:12]፡፡ የሰማይ መስኮቶች ተከፈቱ ዝናቡም አርባ መአልትና አርባ ሌሊት በምድር ላይ ሆነ፡፡ [ዘፍ. 7:12]፡፡

✓ በዚህ ዓይነት አርባ ቀን እግዚአብሔር ሰውን እንደ ቀጣበት እናያለን፤ መቅጣት ብቻ ሳይሆን በዚህ የአርባ መአልትና የአርባ ሌሊት ምድር በዛበት ርኲሰት አጥቧታል፡፡ ምክንያቱም የጥምቀት ምሳሌ ነውና፡፡ ማየ አይህ (የጥፋት ውኃ የጥምታት ምሳሌ ለመሆኑ ቅዱስ ጴጥሮስ እንዲህ በማለት ጽፏል "ጥቂቶች ማለት ስምንት ነፍሳት በውኃ የዳኑበት መርከብ ሲዘጋጅ የእግዚአብሔር ትዕግሥት በኖኅ ዘመን በቆየ ጊዜ ቀድሞ አልታዘዙም ይህም ውኃ ደግሞ ማለት ጥምቀት ምሳሌው ሆኖ አሁን ያድነናል፡፡" [2ኛጴጥ.3.20 ና 21]፤ አሁንም ከዚሁ ሳንርቅ የመርከቧ መስኮቶች የተከፈቱት በአርባ ቀን መሆኑን ይገልጻል፡፡ "ከአርባ ቀን በኋላ ኖኅ የሠራውን የመርከቢቱን መስኮት ከፈተ" [ዘፍ. 8.6]፡፡ መርከቧ የቤተክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ እስራኤል ወደ ምድረ ርስት ያደረጉት ጉዞ አርባ ዓመት እንደ ፈጀ ተጽፏል፡፡ ይህም መንገድ ደግሞ የአርባ ቀን መንገድ ነበር፤ በእግዚአብሔር ቁጣ ወደ አርባ ዓመታት ተለወጠ እንጂ፡፡ "በሙሴ ተመርተው ከግብጽ የወጡ ሁሉ አይደሉምን? አርባ ዓመትም የተቆጣባቸው እነማን ነበሩ? ሬሳቸው በምድረ በዳ የወደቀ" [ዕብ. 3.7-19] ሲል ቅዱስ ጳውሎስ ጽፎታል፡፡

✓ እስራኤል አርባ ዘመን መና ከደመና እየወረደላቸው ተመግበዋል፤ ውኃ ከዐለት እየፈለቀላቸው ጠጥተዋል፡፡ ሲያምጹም ተቀጥተዋል፡፡ ሙሴ ወንድሞቹን እስራኤልን ለመጎብኘት የመጣው በአርባ ዓመት ነበር "በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ ሙሴ ጎበዝ በሆነ ጊዜ ወንድሞቹ ወጣ የሥራቸውን መከራ ተመለከተ" [ዘጸ. 3:11፤ ሐዋ. 7:23] የተሰደደውም በዚሁ ዕድሜው ነው፡፡ በምድያም በግ በመጠበቅ አርባ ዘመን ኖሯል፡፡ እንደገና እስራኤል ከግብጽ ባርነት ነጻ እንዲያወጣ እግዚአብሔር የላከው በአርባ ዘመን ነበር፡፡ "አርባ ዓመትም ሲሞላ የጌታ መልአክ በሲና ተራራ ምድረ በዳ ታየው፡፡" [ዘጸ. 3:30]፡፡

✓ ይህም ብቻ አይደለም ሙሴ ለዚህ አገልግሎት በተመረጠበት ጊዜ በሲና ተራራ አርባ ቀንና ሌሊት ጾሟል "ሙሴም ወደ ደመናው ውስጥ ገባ ወደ ተራራውም ወጣ ሙሴም በተራራው ላይ አርባ ቀን አርባ ሌሊት ቆየ" [ዘጸ. 24.19] ዝም ብሎ ሥራ ፈትቶ አይደለም የቆየው፤ ሥራውም ጾም ነው፡፡ "እግዚአብሔርም ሙሴን በእነዚህ ቃሎች መጠን ከአንተና ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን አድርጌያለሁና እነዚህን ቃሎች ጻፍ አለው በዚያም አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከእግዚአብሔር ጋር ነበር አልበላም አልጠጣም" [ዘጸ. 34፡27] እየጾመ ነበር ማለት ነው፡፡ በዚህ ጾሙ ሙሴ የቃል ኪዳኑን ጽላቶች ተቀብሎአል፡፡ ከዚህ የምንረዳው ከንቱ ሳይሆን ዋጋ ያለው እንደኾነ ነው፡፡ የኤልያስ ጉዞ አርባ ቀን አርባ ሌሊት እንደ ነበረ ተጽፏል፡፡ "የእግዚአብሔር መልአክ ደግሞ ኹለተኛ ጊዜ መጥቶ ዳሰሰውና የምትሄደበት መንገድ ሩቅ ነውና ተነሥተህ ብላ አለው፤ ተነሥቶም በላ ጠጣ፤ በዚያም ምግብ ኃይል እስከ እግዚአብሔር ተራራ ኮሬብ ድረስ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ሄደ" [ዘጸ.19፡4-8]፡፡

✓ ሕዝቅኤል አርባ ቀን ጾሞ 600 ሙታን አስነሥቷል፡፡ ዕዝራ ሱቱኤል አርባ ቀን ጾሞ የጠፋ መጻሕፍትን መልሷል፤ አብረው የነበሩ ዐምስት ሰዎች ቀን ቀን ይጽፋሉ ማታ ማታ ጥቂት እህል ውኃ ይቀምሱ ነበር፡፡ [ዕዝ.ሱቱ. 13፡23-25] ጌታችን በተወለደ በአርባ ቀኑ ወደ ቤተ መቅደስ ገብቷል፡፡ [ሉቃ. 2፡22]: ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ አርባ መአልትና ሌሊት ጾመ [ማቴ. 4፡2]፡፡ በተነሣ በአርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ [ሐዋ. 11.10]፡፡ ሰው በተፀነሰ በአርባ ቀኑ ተስዕሎተ መልክዕ ይፈጸምለታል፡፡ "በአርባ ቀን ትሾመዋለህ" እንዲል ቅዱስ አትናቴዎስ ወንድ በተወለደ በአርባ ቀኑ ሴት በተወለደች በ80 ቀኗ ኹለት አርባ ክርስትና ይነሣል፡፡ ሰው በአፈር በአርባ ቀኑ ጸሎተ ፍትሐት ይደረስለታል፡፡ ሰው በአርባ ቀኑ ጸሎተ ተክሊል ይደረስለታል፡፡ [ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 24 ገጽ 322]

አርባ ቀን ይህን ያህል ምስጢር ያለው ቀኑ ነው ጌታችን ለምን? አርባ ቀን ጾመ ስንል ከላይ ያየናቸውን አበው ነቢያት ብዙውን ጊዜ የጾሙት አርባ ቀን ነው፡፡ ቢቀንስ አጎደለ ከፍ ቢያደርግ አበዛ ብለው አይሁድ የነቢያትን ሕግ አፈረሰ በማለት ትምህርቱን አንቀበልም ባሉ ነበርና ይህንን ምክንያት በማንሣት አርባ መአልትና ሌሊትን ጾመ፡፡ እስራኤል 40 ዓመት ተጉዘው ምድረ ርስት ገብተዋል፡፡ እናንተም 40 ቀን ብትጾሙ ገነት መንግሥተ ሰማያት ትገባላቹ ሲለን ነው፡፡ ከላይ እንደ ተመለከትነው የጥፋት ውኃ አርባ ቀንና ሌሊት ዘነበ፤ ምድር ጸዳች ሰው አርባ ቀንና ሌሊት ቢጾም ርስት መንግሥተ ሰማያት ይወርሳል ሲለን ነው፡፡ ጾም ሲርስት ለመንግሥተ ሰማያት የሚያበቃ ከኃጢአት የሚያነጻ እንደሆነ ሊያስተምረን በኦሪት በተጾመው ቊጥር ጾም ሥርዓትን ሰጥቶናል፡፡

መልካም ጾም ይሁንላችሁ።

https://t.me/Abalibanos333


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል5⃣

#አዳምጡ መልካም ቆይታ

https://t.me/Abalibanos333
ይቀጥላል


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

🌿#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል4⃣

🌺#አዳምጡ መልካም ቆይታ

https://t.me/Abalibabos333
ይቀጥላል


አንድ ዓሣ አጥማጅ ገና ሳይነጋ በጠዋቱ ወደባህር ዳርቻ ሄደ ነገርግን ይህ ሰው የደረሰበት ሰዓት ጨለማ ነበር በወቅቱም ለሥራው ስላልተመቸው እስኪነጋ ቁጭ ብሎ መጠበቅ ጀመረ ከባህር ዳርቻውም አጠገብ በድንጋይ ጠጠሮች የተሞላ ጆንያ አጋጠመው።

🌚ዓሣ አጥማጁም ከጆንያው ውስጥ ያለውን አንድ ጠጠር አውጥቶ ወደባህሩ ሲወረውረው እንቦጭ የሚል ድምፅ ሰማ። ይህም ድምፅ ስላስደስተው ወድያውኑ ሌሎች ጠጠሮች በየተራ እየወረወረ እንቦጭ እንቦጭ እየደረገ እየተደሰተ መወርወሩን ቀጠለ…

ይህ ዓሣ አጥማጅ በጆንያ ውስጥ የነበሩትን ጠጠሮች ወርውሮ አንዲት ጠጠር ብቻ በቀረው ሰዓት የብርሃን ወገግታ መምጣቱን አስተዋለ።

አጥማጁም የያዛውን ጠጠር ለመወርወር ከመቀመጫው ብድግ ሲል በእጁ የያዛውን ጠጠር በደንብ አገላብጡ ተመለከተ በድንጋጤም ሲያስተውለው ጠጠር ሳይሆን አልማዝ(💎) መሆኑን ተረዳ።

ዓሣ አጥማጁም በንዴት ሲቃ ተናነቀው ምክንያቱም እስኪነጋ ድረስ ሲወረውር የነበረው በጆንያ ሙሉ ጠጠር ሳይሆን አልማዝ መሆኑን አስተዋል።

ብዙ ሰዎች በህይወታቸው እንዲህ ናቸው። በእጃቸው ያለው ጊዜ አልማዝ መሆኑን ሳይረዱ እንቦጭ እንቦጭ የሚል ድምፅ ለመስማት ሲሉ ጊዜያቸውን በእንቅልፍ፣ በምንም፣ በፊልም፣ በማህበራዊ ድህረ-ገፅ፣ በወሬ፣  በክርክር እና በብስጭት ወደ ማይመልሰው ባህር ይወረውሩታል ጥቂቶች እንደ ዓሣ አጥማጁ በመጨረሻ ሰዓት ጊዜያቸው አልማዝ እንደሆነ ሲረዱ አብዛኞቹ ግን ጊዜ ምንም እንዳልሆነ ሳያውቁ በዚያው ይበቃል።

የሰው ልጅ በምድር ላይ የተሰጠው ጊዜ ውስን ነው። ይህን ውስን ጊዜ በወቅቱና በሰዓቱ ካልተጠቀመበት እድሉ ላይመለስ ይወሰድበታል።  ምንም ቢለፋ፣ ቢያለቅስ እና ቢፀፀት ተመልሶ አያገኘውም። ይልቁንም በጊዜው የዘራውን መልካም ይሁን ክፉ በጊዜው ያጭዳል።

https://t.me/Abalibanos333
ምክር ነክ ፁሑፍ..


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል3⃣

#አዳምጡ መልካም ቆይታ

https://t.me/Abalibanos333
ይቀጥላል


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል2⃣

#አዳምጡ መልካም ቆይታ

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል..


⛪️ ዝጎራ# ፀሐፊ አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

🌿#ተራኪ #እዮብ #ዮናስ ክፍል1⃣

🌺#አዳምጡ መልካም ቆይታ

@Abalibanos333
ይቀጥላል


የተወደዳችሁ ውድ  የቤተ ሊባኖስ ቻናል ተከታታይ ቤተስቦች  ወንድሞችና እህቶች እንደምን ከረማችሁ አምላካችን እግዚአብሔር እስከዚች ዕለት ስላደረሰን ስሙ የተመሰገነ ይሁን በቀጣይ ጊዜያት የአለማየሁ ዋሴ እሸቴ ዝጎራ የተሰኘዉን ተወዳጅ መጽሐፍ በተራኪ መልክ በክፍል በክፍል አዘጋጅተን ወደ እናተ በዚህ ሳምንት የምናደርሰ ይሆናል



enatem ezi channl lay sew bemegabez edketatelu adrigu https://t.me/zemsriwochu3

    


ክርስቶስ ሊቀ ካህን ሲባል
መሀሪነቱን ነው የሚገልጸው?
ወይስ አማላጅነትን?

🎙ዮሐንስ🎙

የተሐድሶዎች እና ፕሮቴስታንቶች የዕብራውያን
2 : 17 ን ቃል በቸልታ
ሳይገነዘቡ ማለፍ አደጋ ላይ
ጥሏቸዋል!!!


ጾታዊ ፍቅር.pdf
227.8Kb
ጾታዊ ፍቅር
በ voice ማዳመጥ ያለተመቻችዉ
በpdf

@Abalibanos333


🥀ጾታዊ ፍቅር🥀

🎙አቡ(ወንዴ)🎙
ክፍል 5

፦ጾታዊ ፍቅር ከማን ጋር?
፦ጾታዊ ፍቅር ከማን ጋር ቢሆን አምላክ ይፈቅዳል?ከማንስ ጋር ቢሆን አይፈቅድም?

https://t.me/Abalibanos333


#ጾታዊ ፍቅር

🎙አቡ(ወንዴ)🎙
ክፍል 4

፦እኛ ወጣቶች(ፍቅረኛሞች) ጥምረታችን ምን መምሰል አለበት?
፦ጾታዊ ፍቅር መቼ እንጀምር?
፦ጾታዊ ፍቅር ከእግዚአብሔር ጋር

https://t.me/zemariwochu3
ይቀጥላል.


🌹ጾታዊ ፍቅር🌹

🎙አቡ(ወንዴ)🎙
ክፍል 3

፦የዘመኑ ጥምረት
፦ፍቅረኛ አለህ/ሽ? ምን አይነት ነው ጥምረታችሁ?
፦ፍቅረኛ ልትይዝ ልትጠይቃት ነው? ምክንያትህ ምንድነው? እርግጠኛ ነህ አፍቅረሀት ነው?

https://t.me/zemariwochu3


🌹ጾታዊ ፍቅር🌹

🎙አቡ(ወንዴ)🎙
ክፍል2

፦የመጀመሪያ ፍቅር ሲይዘን ታስታውሳላችሁ?

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል


🌹ጾታዊ ፍቅር🌹

🎙አቡ(ወንዴ)🎙
ክፍል 1

ፍቅር ምንድነው?ለምንድነው የምናፈቅረው?በምንድነው የምናፈቅረው?ለምንድነው ስናፈቅር ልባችን ታምቡር ሚመታው?አንደበታችን ሚቆላለፈው?እጃችን የሚያልበው?...

https://t.me/Abalibanos333

ይቀጥላል

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.