ኒያላ ኢንሹራንስ ከሰራተኞቹ ከፍተኛ ቅሬታ እና ክስ ቀረበበት
- "13.6 ሚልዬን ብር በቦነስ ስም ለድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ብቻ እንዲከፈል ተደርጓል"
ኒያላ ኢንሹራንስ ውስጥ ከፍተኛ የሆነ የህዝብ ሃብት ምዝበራ እና የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለ ሰራተኞች ለብሄራዊ ባንክ እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት በፃፏቸው ደብዳቤ ማሳወቃቸውን ሰምተናል።
በሃገሪቱ ካሉ እና በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ አግኝተው በስራ ላይ ከሚገኙ 17 የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ የሚመደበው ድርጅቱ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ከፍተኛ የሆነ የመልካም አስተዳደር ችግር እና ውንብድና በኩባንያው ከፍተኛ አመራሮች በተደጋጋሚ እየተፈፀመ የህዝብ ሃብት እና
ንብረት በማን አለብኝነት እየተመዘበረ ይገኛል ብለዋል።
ለዚሁ ማሳያ ይሆን ዘንድ ሰራተኞቹ የተለያዩ ማስረጃዎችን ለእነዚህ ሁለት አካላት እንዳሳወቁ መሠረት ሚድያ የደረሰው ሰነድ ያሳያል።
ለምሳሌ ኢትዮጵያ በሂሳብ አያያዝ እና አቀራረብ አዋጅ ቁጥር 847/2006 ዓ.ም መሰረት የአለም አቀፍ የሂሳብ አያያዝ (IFRS) ህግን ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ ተቀብላ እየተገበረች ቢሆንም እ.ኤ.አ በ January 1, 2023 ጀምሮ ድርጅቱ በሂሳብ አመቱ እንዳልተገበረ በውጭ ኦዲተሮች ተረጋግጧል ብለዋል።
በሁለተኛነት የቀረበው አቤቱታ ደግሞ "ይህ በIFRS መርህ መሰረት ያልተዘጋጀ እጅግ የተጋነነ ትርፍ ተገኘ በማለት ባለአክሲዬኖችን እና ባለድርሻ አካላትን በማሳሳት በህገወጥ መንገድ እ.ኤ.አ በ 2023/24 አመት ብቻ የትርፍ ምጣኔ የተሰላ 3% የትርፍ ድርሻ 13.6 ሚልዬን ብር በቦነስ ስም ለድርጅቱ ስራ አስፈፃሚ ብቻ እንዲከፈል ተደርጓል" ይላል።
ከዚህም በተጨማሪ እ.ኤ.አ በ 2021/22 የበጀት አመት ብቻ የብሄራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SB/46/2018 ለኩባንያው የቦርድ አባላት በአመት ሊከፈል የሚገባው ማንኛውም ክፍያ ከብር 150 ሺህ መብለጥ የለበትም ብሎ ቢደነግግም ይህን መመሪያ በሚፃረር መልኩ ከ6 ሚልየን ብር በላይ በቦነስ ስም ለኩባንያው ቦርድ አባል እንዲከፈል ተደርጓል ብለዋል።
ለ20 አመታት በላይ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳንል በሰራንበት የኢንሹራንስ ሴክተር በቂም በቀል በሌሎች የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ውስጥ ሰርተን እንኳን ቤተሰቦቻችንን እንዳናስተዳድር ሆነ ተብሎ የኢንሹራንስ ኩባንያዎቹ እኛን እንዳይቀጥሩ ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ እና ጫና እያሳደሩ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ ህጋዊ ስራ ሰርቶ የመኖር ፣ በየትኛውም ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት እና ንብረት የማፍራት ህገ-መንግስታዊ መብታችንን የሚጋፋ የማን አለብኝነት ድርጊት ነው" በማለት ቅሬታቸውን ለብሄራዊ ባንክ እና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ አስገብተዋል።
Via : Meseret Media
@Addis_Reporter @Addis_Reporter