Addis Admass


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የአዲስ አድማስ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ
=====
አዲስ አድማስ https://bit.ly/2V1zyZQ
ፌስቡክ↠ https://bit.ly/2V0I6jx
ትዊተር↠ https://bit.ly/33fDhaP
ቴሌግራም↠ https://bit.ly/2JgeCvG
ዩቲዩብ ↠ https://bit.ly/3q2hXiv
የእርስዎና የቤተሰብዎ

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ቲክቶክ የራስ ፈጠራን ለማዳበርና ገቢን ለማመንጨት ከፍተኛ አቅም ቢኖረውም፣ ለማህበረሰብ ጤናማ ኑሮና ዘላቂ ግንኙነት ጠንቅ የሆኑ ሃሰተኛ መረጃዎችን የማሰራጫ መድረክ በመሆንም ለአገርና ለህዝብ አደጋ ይደቅናል፡፡ በህዝቦች መካከል ግጭትና ጦርነት ይቀሰቅሳል፡፡ ግለሰቦችንና ቡድኖችን ለጥቃት ያጋልጣል፡፡

ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ብሔር ብሔረሰቦች ሀገር ናት፡፡ ልዩ ልዩ ማንነቶችና ባህሎች እንዲሁም ሃይማኖቶች ተከባብረውና ደምቀው የዘለቁባት ውብ ምድር ናት፡፡ ቲክቶክም ሆነ ሌሎች ማህበራዊ ሚዲያዎች ይህን ለዘመናት የተሻገረ የህዝቦች ተቻችሎ በጋራ የመኖር ወግና ልማድ በሚያዛባና በሚያፈርስ መልኩ ጥቅም ላይ ከዋሉ ከጥቅማቸው ይልቅ ጉዳታቸው የሚያመዝን ይሆናል፡፡

ቲክቶክ እንደ ፈጠራ ማሳያና ጎጂ ንግግሮች ማስተላለፊያ መድረክ፤ ከዲጂታል ምህዳር ጎን ለጎን ሊዳብሩ የሚገባቸው የቁጥጥር ማዕቀፎችን አጣዳፊ አስፈላጊነት ያጎላል። በቂ ቁጥጥር ካልተተገበረ ቲክቶክ በመዝናኛና በአደገኛ ባህሪ መካከል ያለው መስመር የሚደበዝዝበት፣ ለአሉታዊነት አመቺ የመራቢያ ስፍራ መሆኑ አይቀሬ ነው። ፖሊሲ አውጪዎች ከቴክኖሎጂ ባለሙያዎች፣ ሶሺዮሎጂስቶች እና የማህበረሰብ መሪዎች ጋር በአጫጭር የቪዲዮ ይዘቶች የሚስተዋሉ ልዩ ተግዳሮቶችን የሚፈቱ አጠቃላይ መመሪያዎችን ማዘጋጀት አለባቸው።

በተጨማሪም መንግሥት፣ በዚህ ፈጣን የዲጂታላይዜሽን ዘመን፣ የማህበራዊ ሚዲያ ቁጥጥርን ችላ ማለት የሚያስከትለውን አደጋ በቅጡ መገንዘብ ይኖርበታል። የተሳሳቱ መረጃዎችና የጥላቻ ንግግሮች ሁከትና ግጭት ለመቀስቀስ መቻላቸው የቴክኖሎጂ ኩባንያዎችን፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችንና ሰፊውን ተጠቃሚ ማህበረሰብ ጨምሮ ቁልፍ በሆኑ ባለድርሻ አካላት መካከል ውይይትና ምክክር የማድረግ አስፈላጊነትን ያጠናክረዋል። ውጤታማ የምላሽ ስልቶች፤ የተሻሻለ የዲጂታል መስተጋብር ክትትልን፣ ጎጂ ይዘቶችን በተሻለ ለማወቅና ለማስተዳደር በቴክኖሎጂ ላይ ኢንቨስት ማድረግና በመድረኩ ላይ አላግባብ መጠቀምን በተመለከተ የሚነሱ ቅሬታዎችን ሪፖርት ለማድረግና ለመፍታት ግልፅ ሥርዓቶችን መዘርጋትን ሊያጠቃልል ይችላል። ኢትዮጵያ ለደህንነትና የስነምግባር ደረጃዎች ቅድሚያ በመስጠት፣ ልዩነትንና ክፍፍልን ከማጠናከር ይልቅ ገንቢ የሆኑ የሰለጠኑ ውይይቶችንና ንግግሮችን የሚደግፍ የዲጂታል ስነ-ምህዳር ለመፍጠር መትጋት ይጠበቅባታል፡፡

ቲክቶክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ውስጥ ስላለው ሚና ውይይት መደረጉ ስለ ዲጂታል እውቀትና ተደራሽነት ሰፊ የውይይት መድረክን ይከፍታል። ቴክኖሎጂ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ውስጥ እጅጉን እየተቆራኘን በመጣበት በዚህ ዘመን፣ ወጣት ተጠቃሚዎች፣ በዲጂታል ሚዲያዎች ውስጥ በኃላፊነት እንዲንቀሳቀሱ ማስተማር አስፈላጊ ነው።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአራችን የተጀመረው የቲክቶክ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ሽልማት ደረጃውን በጠበቀና ግልጽነትን በተላበሰ መልኩ መቀጠሉ የማህበራዊ ሚዲያውን ለበጎና ማህበረሰቡን ለሚጠቅሙ ተግባራት ለማዋል መንገድ ከፋች እንደሚሆን ይታመናል፡፡ ወጥና ተቋማዊ መሆን ግን ይጠበቅበታል፡፡

በማጠቃለያም ቲክቶክ በኢትዮጵያ ማህበረሰብ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ፣ በዲጂታል ፈጠራና በማህበረሰብ ተግዳሮቶች መካከል ያለውን ውስብስብ መስተጋብር ያካትታል። ተጠያቂነትን በማጉላት ጤናማ የዲጂታል ልማዶችን ማሳደግ፣ የማህበራዊ ሚዲያ ጥቅማ ጥቅሞችን ለማግኘትና ተያያዥ ስጋቶችን ለመቀነስ ልዩ እድል ይፈጥራል። ሚዛናዊ የዲጂታል ምህዳርን ለመፍጠር የሚደረገው ጥረት በፈተናዎች የተሞላ ሊሆን ይችላል፣ነገር ግን ከሁሉም የህብረተሰብ ክፍል በሚደረጉ የትብብር ጥረቶች፣ ፈጠራን የሚያበረታታና የጋራ ደህንነትን የሚደግፍ የማህበራዊ ሚዲያ ገጽታን ማዳበር ይቻላል።


በታሪክ ለንጉሣዊ ቤተሰብ፣ ለጦር ጀግኖችና ልዩ ችሎታ ላላቸው ግለሰቦችና ቡድኖች የሚሰጠው ማህበረሰባዊ ደረጃ (social status)፣ የቲክ ቶክ መምጣትን ተከትሎ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ መገልበጡን እያየን ነው፡፡ በዚህ ዘመን ለታዋቂነትና ለተፅዕኖ ፈጣሪነት የሚሰጠው ቦታ በከፍተኛ ደረጃ እየተለወጠ መጥቷል፡፡ ታዋቂም ሆነ ተጽዕኖ ፈጣሪ ለመሆንም ሆነ ለመሰኘት እንደቀድሞው ጊዜ ብዙም ጥረትና ልፋት ወይም ብቃትና ትጋት የማያስፈልግበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡ ዕድሜ ለቲክቶክና ሌሎች መሰል የማህበራዊ መድረኮች ዝነኝነት የአንድ ጀንበር ክስተት መሆኑን እያየን ነው፡፡

ዛሬ ማንኛውም በእጁ ላይ ስማርት ስልክ ያለው ሰው፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ታዋቂ መሆን ይችላል፡፡ ግለሰቦች በፈጠራ ችሎታቸውም ይሁን በማራኪነታቸው፣ አሊያም በኮማኪነታቸው አንዳንዴም በአጋጣሚ ተወዳጅነትንና ታዋቂነትን በቀላሉ መቀዳጀት ይችላሉ፡፡

በኢትዮጵያ የቲክቶክ መስፋፋት ወጣቶች የፈጠራ አቅማቸውንና ተሰጥኦዋቸውን እንዲያሳዩ፣ ከእኩዮቻቸው ጋር ትስስር እንዲፈጥሩና አዳዲስ የገቢ ማግኛ ሥልቶችን እንዲተልሙ ዕድል መክፈቱ የሚታበል አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ አሉታዊ ጎኖችና ተጽዕኖዎች እንዳለውም ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ ቲክቶክ የተሳሳተና የተጋነነ የግለሰቦች ምስልና ገጽታ ከመፍጠርም ባሻገር የተዛቡ መረጃዎችን በማሰራጨትም፣ በህብረተሰብ ጤናማ አኗኗር ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል፡፡

እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 2025 በተደረገ ጥናት፤ ቲክ ቶክ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወደ 1.59 ቢሊዮን የሚጠጉ ተጠቃሚዎች እንዳሉት የተረጋገጠ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥም 27.5 በመቶ ያህሉ ዕድሜያቸው 18 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው። ቲክቶክ እ.ኤ.አ. በ2016 ዓ.ም በባይትዳንስ ከተመሠረተበት ጊዜ ወዲህ እጅግ በአጭር ጊዜ ውስጥ መጠነ ሰፊ ታዋቂነትን መቀዳጀት ችሏል፡፡ ይህም በማህበራዊ ሚዲያ መድረክ ከፍተኛ ተቀባይነትን ለማግኘት አስችሎታል። የአሰራር ስርዓቱም አጫጭር ቪዲዮዎችን የሚያበረታታ ከመሆኑ አንጻር ተጠቃሚዎች ፈጣን፣ ስሜት ቀስቃሽና አዝናኝ ቪዲዮዎችን ሰርተው በመልቀቅ በአጭር ጊዜ ውስጥ በርካታ ተመልካቾችንና ዕውቅናን እንዲያገኙ አድርጓቸዋል።

በሀገራችን ቲክቶክ በተለያዩ የዕድሜ ክልል ውስጥ በሚገኙ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት በማግኘቱ ከብዙዎች የዕለት ተዕለት ኑሮ ጋር በከፍተኛ ደረጃ ተቆራኝቷል ማለት ይቻላል፡፡ የቲክቶክ ፈጣን እድገት፣ በአንድ በኩል አዲሱ ትውልድ የዲጂታል ተሳትፎው እንዲጨምር፣ በሌላ በኩል በመላው ዓለም ከሚገኙ የቲክቶክ ተጠቃሚዎች ጋር ግንኙነትና ትስስር በመፍጠር፣ አዳዲስ ዕድሎችና አጋጣሚዎችን እንዲያስስ በር ከፍቶለታል፡፡

በተደጋጋሚ ለአሜሪካ ብሔራዊ ደህንነት ስጋት ደቅኗል እየተባለ ሲወነጀል የቆየውና ከአገሪቱ ሙሉ ለሙሉ ሊታደግ አንደ-አሙስ ቀርቶት የነበረው የቻይናው ቲክቶክ፣ በትራምፕ አስተዳደር የእገዳ ጊዜው ተራዝሞለት በአሜሪካዊ ኩባንያ እንዲገዛ ጥረት እየተደረገ ያለው ያለምክንያት አይደለም፡፡ በብዙ ሺ የሚቆጠሩ የአሜሪካ ትናንሽ ቢዝነሶች የገቢ ምንጫቸው የተመሰረተው በዚህ ዲጂታል መድረክ ላይ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ቲክቶክ ለአገራችን ኢኮኖሚ ሊያበረክት የሚችለው አስተዋጽኦ ቀላል አይሆንም፡፡ ግን አያያዙን ካወቅንበት ብቻ ነው፡፡

በኢትዮጵያ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ምርቶችንና አገልግሎቶችን ለተከታዮቻቸው ማስተዋወቅን ጨምሮ የተለያዩ ሚናዎችን ለመወጣት ቲክቶክን መጠቀም ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡ ይህ ታዳጊ የኢኮኖሚ ገጽታ የአገር ውስጥ ቲክቶከሮች ከዚህ መድረክ ገቢ እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። ብዙ ቲክቶከሮች ምርቶችን ማራኪና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስተዋወቅና ለማሻሻጥ ከድርጅቶች ጋር በትብብርና በአጋርነት እየሰሩ ነው፡፡ ይሄ በጎ ገጽታው ነው፡፡ ይሁን እንጂ አሉታዊ ገጽታዎችም አሉት - ለማንወጣው ማህበረሰባዊ ቀውስ የሚዳርግ፡፡

ሰሞኑን የፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ ሚዲያ ከማሕበረሰቡ ባህልና ልማድ ያፈነገጠ ድርጊት ሲፈጽም የነበረን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር አውሎ፣ ምርመራ እያደረገበት እንደሚገኝ ማስታወቁን ልብ ይሏል፡፡

ሌላው አሳሳቢው የቲክ ቶክ ተጽእኖ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በቀላሉ ሁከት ለመቀስቀስና የተሳሳተ መረጃ ለማሰራጨት ምቹ መድረክ መሆኑ ነው። መድረኩ የተሳሳቱ መረጃዎች በማይታመን ፍጥነት እንዲሰራጩ ያደርጋል፡፡ በቲክቶክ የዘር ግጭቶች የሚቆሰቁሱ የጥላቻ ንግግሮችን በቀጥታ ሥርጭት ማስተዋል እየተስፋፋና እየተለመደ መጥቷል፡፡ ሥር በሰደደ የዘረኝነት አባዜ እየተናጠች ለምትገኝ አገር፣ከወዲሁ ልጓም ካልተበጀለት እንዲህ ዓይነቱ ይዘት በማህበረሰቦች መካከል የከፋ ጥላቻና ግጭት መፍጠሩ አይቀሬ ነው፤ አገርንና ህዝብን ለደም መፋሰስ እልቂት የሚጋብዝ፡፡ የእነዚህ ከቲክቶክ ጋር የተገናኙ የጥላቻ ንግግሮች መስፋፋት የሚያሳየው፣ እነዚህን አይነት ጠብ አጫሪ ይዘቶች ለመቆጣጠር፣ ጠንካራ ፖሊሲ መቅረጽ እንደሚያስፈልግ ነው፡፡

ቲክቶክን ጨምሮ በብዙ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ የሚስተዋሉ የቁጥጥር ክፍተቶች፣ ችግሮቹን ይበልጥ እያወሳሰባቸው መጥቷል፡፡ የጥላቻ ንግግርን ለመቅረፍ እመርታ ካደረጉ ሌሎች መድረኮች በተለየ ቲክቶክ ለጎጂ ይዘት ፈጣን ምላሽ የመስጠት አቅሙ ደካማ ይመስላል። የማህበራዊ ሚዲያ ኩባንያዎች ፈጠራን በማሳደግና የተጠቃሚን ደህንነት በማረጋገጥ መሃል ያለውን ሚዛን እንዴት መጠበቅ አለባቸው የሚለው ጉዳይ ብዙ የሚያነጋግር ነው፡፡ ጎጂ ይዘቶችን ለመጠቆምና ለማጣራት ብሎም ለማስወገድ ጠንካራ የዲጂታል ሥርዓት አለመኖሩ፣ የጥላቻ ንግግሮችና የተሳሳቱ መረጃዎች ቁጥጥር ሳይደረግባቸው የሚያድጉበትን ሁኔታ ይፈጥራል፤ ይህም በግለሰብ ደህንነት ላይ ብቻ ሳይሆን በጋራ ማህበረሰቡ ላይ አደጋን ይፈጥራል፡፡

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በመጋቢት 2020 ዓ.ም፣ የጥላቻ ንግግርና የሀሰት መረጃ መከላከል አዋጅን የመሳሰሉ የጥላቻ ንግግሮችንና የተሳሳቱ መረጃዎችን ለመግታት ያለመ ህግ ማጽደቋ ይታወቃል፡፡ ይህ ህግ የማህበራዊ ሚዲያ አገልግሎት አቅራቢዎች፣ ጎጂ ይዘት ያላቸውን ዘገባዎች በተወሰነ የጊዜ ገደብ ውስጥ እንዲያስወግዱ ያስገድዳል። ነገር ግን፣ በአተገባበር ላይ በታዩ ክፍተቶች ሳቢያ ውጤታማ ሳይሆን ቀርቷል፡፡ በኢትዮጵያ የማህበራዊ ሚዲያ እንቅስቃሴዎች ቁጥጥር ላይ ያለው አሻሚነት፣ የተሳሳተ መረጃ ከቁጥጥር ውጭ በሆነ መልኩ ሊስፋፋ በሚችልበት መልክዓ ምድር ላይ ትልቅ ተግዳሮት ሆኖ ተጋርጧል፡፡

የዘርፉ ባለሙያዎች በተሳሳተ መረጃ ስጋት ላይ የሚያተኩሩና ከማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ጋር ኃላፊነት የሚሰማውን ተሳትፎ የሚያበረታቱ የተሻሻሉ የህብረተሰብ ትምህርት መርሃ ግብሮችን ያበረታታሉ። በዲጂታል ምህዳሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን ለመፍጠር ከትምህርት ተቋማት፣ ከሲቪል ማህበራትና ከሚዲያ ባለሙያዎች ጋር የሚደረጉ የትብብር ጥምረቶች አስፈላጊ ናቸው። ያልተረጋገጡ መረጃዎችን ማሰራጨት ስለሚያስከትሏቸው ችግሮች ግንዛቤን በማሳደግና ጎጂ ይዘቶችን የሚከለክል መመሪያ በማውጣት፣ በህብረተሰቡ ንቁ ተሳትፎ፣ የተሳሳቱ መረጃዎችን አሉታዊ ተጽእኖ መቀነስ እንደሚቻል ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡


የቲክቶክ መንታ ገጽታ በኢትዮጵያ



-በቴዎድሮስ ታደሰ አየለ-
⬇️⬇️




ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ባሸነፉበት በቤጂንግ የተካሔደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ቻይና ሰው መሰል ሮቦቶች አወዳደረች።

በቤጂንግ ዛሬ ቅዳሜ የተካሔደው ኢ-ታውን ሒውማኖይድ ሮቦት ግማሽ ማራቶን በዓለም የመጀመሪያው እንደሆነ ተነግሮለታል። በውድድሩ 10,000 ሰዎችና 21 ሰው መሰል ሮቦቶች ተሳትፈዋል።

በውድድሩ የተሳተፉት ሮቦቶች በቻይና የቴክኖሎጂና የምርምር ኩባንያዎች የተሠሩ ናቸው። ሮቦቶቹ የተለያየ ቅርጽና ቁመት ያላቸው ሲሆን፤ከተሳተፉት ሮቦቶች መካከል አጭሩ 120 ሴንቲሜትር ሲረዝም፣ ረዥሙ 1.8 ሜትር ርዝመት አለው።

ሮቦቶቹን የሚቆጣጠሩ ኢንጂነሮች በተለያየ ርቀት በሩጫው ሒደት ማስተካከያዎች ሲያደርጉ ታይተዋል። ሮቦቶቹ 21 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውን የግማሽ ማራቶን የተሳተፉት ለሰዎች ከተበጀ መሮጫ ጎን ለጎን በመከለያ በተለየ መንገድ ላይ ነው።

የሩጫ ውድድሩ ግን ለሁሉም ሮቦቶች ቀላል አልሆነም። አንድ ሮቦት ሩጫው በተጀመረ በደቂቃዎች ልዩነት መሬት ላይ ወድቆ ለመነሳት በርከት ያሉ ደቂቃዎች ወስደውበታል። ሌላ ሮቦት ከመከለያ ሲጋጭ ታይቷል። ከተሳተፉት መካከል የተወሰኑት ከሰዎች እጅግ ዘግይተውም ቢሆን ውድድሩን ማጠናቀቅ ችለዋል።

በቤጂንግ ሮቦቲክስ ፈጠራ ማዕከል (Beijing Innovation Centre of Human Robotics) የተሠራው ቲያንጎንግ አልትራ፣ የግማሽ ማራቶን ሩጫውን ለማጠናቀቅ 2 ሰዓት ከ40 ደቂቃዎች ፈጅቶበታል።

ኢትዮጵያዊው ኤልያስ ደስታ በአንጻሩ ውድድሩን በአንድ ሰዓት ቀድሞ አጠናቋል። ኤልያስ የግማሽ ማራቶን ውድድሩን በአንድ ሰዓት ከ02 ደቂቃ ከ36 ሰከንዶች አጠናቋል።

በሴቶች ኢትዮጵያዊቷ ሐዊ ጉደታ አሸናፊ ሆናለች። ሐዊ ውድድሩን በአንድ ሰዓት ከ11 ደቂቃ ከ7 ሰከንዶች ስትጨርስ፣ ሌላዋ ኢትዮጵያዊት ትነበብ ነጋ ሁለተኛ ሆና አጠናቃለች።

(DW)


ኢትዮጵያውያን ባሸነፉበት የግማሽ ማራቶን የሩጫ
ውድድር ቻይና ሮቦቶችን አወዳደረች


• በውድድሩ 10,000 ሰዎችና 21 ሰው መሰል ሮቦቶች ተሳትፈዋል



⬇️⬇️


የፊልሙ አዘጋጅ ሜል ጊብሰን፣ አራቱ ወንጌላውያን ማርቆስ፣ ማቲዎስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ ያቀረቡትን ትረካ መሠረት አድርጌ ነው ያሰናዳሁት ቢልም፣ ከፊልሙ ተቺዎች መሃል አንዳንዶቹ በፊልሙ ላይ የሚስተዋሉ አንዳንድ ትዕይንቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልተጠቀሱ ናቸው ይላሉ፡፡ ለምሣሌም ገና ፊልሙ ሲጀምር ኢየሱስ በጌቴሰማኒ ሲጸልይ ሠይጣን በእባብ ተመስሎ ሲፈታተነው መታየቱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያልሰፈረ ነው፤ በተጨማሪም ወደ ጎልጎታ ተራራ ሲጓዝ መስቀል ተሸክሞ መታየቱ ልክ አይደለም ባይ ናቸው፡፡ በአይሁድ ልማድ መሠረት፣ የሚሰቀል ሰው ከመሰቀያው እንጨቶች መሃል አንዱ ግንድ በገመድ ታስሮበት ይኼዳል እንጂ ሙሉ መስቀሉን አይሸከምም ነው የሚሉት፡፡
በወዲህ ደግሞ አይሁዳውያኑ አሉ፡፡ የፊልሙ ትዕይንት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ የደረሰው ሥቃይን ያስመለከተበት መንገድ አዘጋጁ ለጽዮናውያን ያለውን ጥላቻ ያሳያል ይላሉ፡፡ ለዚህ ማሥረጃ እንዲሆናቸውም ሜል ጊብሰን በተደጋጋሚ በመጠጥ ሞቅታ ውስጥ ሆኖ ስለ ጽዮናውያን የተናገረው የሚሉትን ያቀርባሉ፡፡ ይህኛው ክስ እንዲህ ከላይ እንደሚታየው ቀለል ብሎ ብቻ አላለፈም፡፡ ተዋናዩ ጂም ካቫይዘልም የጽዮናውያን ጥላቻ አለበት ተብሎ ተከስሷል፡፡ መሰል የአይሑድ ክስ ጠንከር ብሎ መጥቶ በተለይ ካቫይዘል የሚሠራባቸውን ፊልሞች ያለማየት ዘመቻ ተከፈተ፡፡ ያንን ዘመቻ ፍራቻ ይመስላል የአሜሪካው ፊልም አምራች ተቋም ሆሊውድ ፊልም አዘጋጆች፣ ተዋናዩን ማሣተፍ ሊያመጣባቸው የሚችለውን ተቃውሞ በመስጋት እርሱን ላለማሰራት የወሰኑት፡፡
ከ"ፓሽን ኦፍ ክራይስት" በኋላ ባሉት 21 ዓመታት ውስጥ እርሱ የተወነባቸው ፊልሞች ብዛት 3 ብቻ ነው፡፡ ከዚህም ውስጥ ሁለቱ ተቃውሞው ጋብ ካለ ከዓመታት በኋላ በ2023 ዓ.ም የተለቀቁ ናቸው፡፡ ያም ቢኾም በ3ቱም ፊልሞች ላይ እርሱ የሚተውንባቸው ደቂቃዎች ርዝማኔ፣ አንድ ፊልም ያህል እንኳ አይሆኑም፡፡ ለነገሩ እርሱም የዝናው ነገር ግድ የሰጠው አይመስልም፡፡ "በቅድሚያ ለፊልሙ መታጨቴ ሲነገረኝ ያንን ገጸ-ባሕርይ መጫወት ከምወደው ሥራዬ ሊያፈናቅለኝ እንደሚችል አስቤ ለመቀበል አመነታሁ፡፡ በኋላ ግን የትወና ችሎታዬን የሰጠኝ ፈጣሪ የሚያደርገኝን ያድርገኝ ብዬ ገባሁበት፡፡ በውጤቱም አሁን ያ ፊልም ከስምና ሥራዬ ይልቅ በሃይማኖቴ ላይ እንዳተኩር አድርጎኛል" የሚለው ካቫይዘል፤ ወደ ካቶሊክ ሃይማኖቱ ይበልጥ አተኩሮ ሰባኪም ሆኗል፡፡
አብዛኛው የፊልሙ ቀረጻ በተደረገባት የኢጣሊያዋ ሮም ከተማ ለወራት መቀመጣቸውን የሚያወሳው ካቫይዘል፤ በትወናው ላይ ሳለ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት እንደደረሰበት፣ ለሞት ሊያበቃው የደረሰ ክሥተት እንዳስተናገደም ይናገራል፡፡ በዚያ ከባድ ቅዝቀዜ ውስጥ ለፊልሙ ቀረጻ ተብሎ ለአምስት ወራት ሲቆዩ በሳንባ ምች በሽታ መጠቃቱንና ልቡ ላይም ባጋጠመው ሕመም ከአንድም ሁለት ጊዜ ቀዶ-ጥገና ለማድረግ መገደዱን ማለቱ ነው፡፡
የኢየሱስ እናት ቅድሥት ድንግል ማርያም ወደ እርሱ እየሮጠች ስትመጣ በሚታይበት ቅጽበት የገጠመው ቀላሉ ጉዳት እንደሆነ የሚገልጸው ተዋናዩ፤ በርከክ ብሎ ሊያቅፋት ሲዘጋጅ የገዛ ምላሱን ቀርጥፎት መጎዳቱን ያስታውሳል፡፡ ሌላኛው ጉዳቱ ደግሞ ኢየሱስ የተራራውን ስብከት እንዳሰማ የሚነገርበት ትዕይንት ነው፡፡ "አደጋው ከመድረሱ አፍታ በፊት አንዳች ኃይል ያ እንደሚደርስብኝ ነግሮኝ ነበር" ይላል ካቫይዘል፡፡ የፊልሙ አዘጋጆች ቀረጻውን እያቀላጠፉ ሳለ ድንገት መብረቅ ይወድቃል፡፡ መብረቁ ደግሞ ተዋናዩ ካቫይዘልን መቶታል፡፡ ግራና ቀኝ ትከሻው ላይ ልብሱ በእሳት መንደድ ጀምሯል፡፡ በዚህ ተደናግጠው እሳቱን ሲያጠፉለት ትከሻው ላይ ካጋጠመው መጠነኛ ውልቃት በቀር የከፋ ጉዳት ሳይደርስበት አለፈው፡፡
የ2 ሰዓታት ርዝማኔ ያለው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክራይስት" ፊልም ቀጣይ ክፍል ሊሠራለት እንደሆነ ሲወራ ቆይቶ፣ በመጨረሻ አዘጋጁ ሜል ጊብሰን፣ ነገርየው ከወሬም በላይ ዕውነታ ወደ መሆን መቃረቡን የጠቆመ ሲሆን፤ በቀጣዩ የምዕራባውያን ዘመን 2026 "ሪሰሬክሽን" ወይም ትንሣኤ በሚል ርዕስ ለዕይታ እንደሚበቃ አስታውቋል፡፡ በዚህኛው ፊልም ላይ በቀዳሚው ፊልም ላይ የተወነው ጂም ካቫይዘል እንደማይሳተፍ መታወቁ ደግሞ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ታሪክ በፊልም የመሰናዳት ጉዳይ ላይ የሃይማኖት መምሕራን፣ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አጥኚዎች፣ ምዕመናን ጭምር የተለያየ አቋም ይዘው ሲደግፉም ሲቃወሙም ይስተዋላል፡፡ የኢየሱስ ሕይወት ላይ ለሚያጠነጥኑ ፊልሞች የጸና ድጋፍ በመስጠት ረገድ በተለይ የኢቫንጀሊካን ቤተዕምነት ቀዳሚዋ ሆና ትነሳለች፡፡ ቤተ-ዕምነቲቱ በተለያየ ጊዜ ለዕይታ የበቁ ፊልሞችን ዕውቅና ሰጥታ በምታወጣቸው መግለጫዎች፣ ዘመን በተቀየረ ቁጥር በሚገኙ አማራጮች በኩል ሁሉ ዕምነትን መስበክ ተገቢ ነው የሚል አቋሟን ስታንጸባርቅ፣ ሌሎች በክርስትና ዕምነት ማዕቀፍ ውስጥ የሚገኙ ሃይማኖቶች መሪዎች ደግሞ "የለም፣ ኢየሱስን ያህል አምላክ በሰው መወከል ተገቢ አይሆንም፣ ከታሰበው የማስተማር አገልግሎት አልፎ ሰዎች እንዲመለኩ ያደርጋል" በሚል ይቃወሙታል፡፡ በወዲህ ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ አጥኚዎች አሉ፡፡ በአብዛኛዎቹ በሚሠሩ ፊልሞች ላይ የታሪክ መዛባት፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ከሰፈረው ውጪ ያሉ ትረካዎች ተስተውለዋል ሲሉ ይተቻሉ፡፡


ለአፍታ ወደ ሆሊውድ መንደር እንሂድ፡፡
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ዕለተ ዓርብ ጥቅምት 8 ቀን 1972 ዓ.ም አንድ ታሪክ ሠሪ ፊልም ለሕዝብ ዕይታ ቀረበ፡፡
ፒተር ሳይክስ እና ጆን ክሪሽ ያዘጋጁትና በዋርነር ብሮስ ፊልም አምራች ድርጅት በኩል የቀረበው ይህ ፊልም ርዕሱ "Jesus" የሚል ነው፡፡ የፊልሙ አዘጋጆች ያኔ የፊልሙን መለቀቅ አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ፣ ፊልሙ ላይ የአዘጋጅ ወይም ጸሐፊ ሥም እንዲጠቀስ ያላደረጉበት ምክንያት፣ ታሪኩን በቅርብ ጊዜ ከታተመው የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂ፣ "ጉድ ኒውስ ባይብል" ዕትም ላይ የሉቃስ ወንጌልን ተጠቀምን እንጂ ሌላ አዲስ ፈጠራ ስላልተጠቀምን ነው ብለው ነበር፡፡ ወደ 6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ወጪ እንደተደረገበት፣ የቀረጻ ሥራውም በእሥራኤል መከናወኑን አብራርተዋል፡፡ እስካሁን ባሉ መረጃዎች፣ በፊልም ታሪክ በርካታ ሰዎች ካዩዋቸው ፊልሞች አንዱ ሆኗል፡፡ በጣም ካነሰ 6 ቢሊዮን ሰዎች ተመልክተውታል፡፡ መመልከት ብቻ አይደለም፡፡ ፊልሙን ካዩት ውስጥ አብዛኛዎቹ ኢየሱስ ክርስቶስን ሲያስቡ ወደ ኅሊናቸው የሚመጣው በፊልሙ ላይ በመሪ ተዋናይነት የተሳተፈው እንግሊዛዊው ብሪያን ዲያኮን ገጽታ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከ200 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ይህን ፊልም ካዩ በኋላ ሕይወታቸውን ወደ ሃይማኖተኛነት መስመር እንዳስገቡ መስክረዋል፡፡ የ1979 ዓ.ም ጂሰስ ፊልም ሌላም የማይረሳ ታሪክ አለው፡፡ በዓለም ዙሪያ በሁለት ሺህ ቋንቋዎች ተተርጉሞ ተሠራጭቷል፡፡ በፊልሞች ታሪክ በብዙ ቋንቋዎች በመተርጎም ከፍተኛውን ቦታ ከያዙት አንዱ ሆኖ ይወሳል፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ሕይወት ይበልጥም የሥቅለቱ ነገር በተለያዩ ዘመናት በተንቀሳቃሽ ምሥል እየተቀናበረ፣ ተዋንያን እየተመረጡ ለተመልካች ቀርቧል፡፡ በዚህ ረገድ ቀዳሚ ሆኖ የሚቀርበው ከወደ ፈረንሣይ የቀረበው ፊልም ነው፡፡
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ1889 "ለ ፓሽን ዱ ክራይስት/ ዘ ፓሽን ኦፍ ክራይስት" ወይም "የክርስቶስ ሕማም" በሚል ርዕስ የቀረበውና አልበርት ኪርችነር የተባለ ፈረንሣዊ ያሰናዳው ይህ ፊልም፣ ከዚያ ቀደም በማንም ያልተሞከረ የተባለ ነገረ-ኢየሱስን በፊልም ያሳየ የመጀመሪያው ሆኖ ታሪክ ላይ ሠፍሯል፡፡ ሶሺየት ሊየር የተሰኘ የትወና ቡድን አባላት የተሳተፉበት ፊልሙ፣ በ12 ገቢር ተከፍሎ የአምስት ደቂቃ ርዝማኔ ያለው እንደነበረ የሚያወሱለት የፊልም አጥኚዎች፤ "አሁን ላይ የዚያ ከ128 ዓመታት በፊት የተሠራ ፊልም ኮፒዎች በመጥፋታቸው እያየን ለመገምገም ባንችልም፣ ዐይተው ትውስታው ከቀረላቸው ሰዎች የሰሙ ከነገሩን ተነስተን ለማስረዳት ያህል ግን፣ እጅግ ተወዳጅነትን ያተረፈ ትዕይንት እንደነበር መመስከር እንችላለን" ብለውለታል፡፡ አባባላቸው ልክ መሆኑን ለመረዳት ብዙ ርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም፡፡ መቼቱን በሀገረ ፈረንሣይ መዲና ፓሪስ ላይ ያደረገው ‹ለ ፓሽን ዱ ክራይስት›፤ የኢየሱስን ሥቅለት ያስመለከተ ቀዳሚው ፊልም ቢሆንም፣ የታሪክ ነገራው የፈጠረው መነቃቃት፣ ለዕይታ በበቃ ዓመት በማይሞላ ጊዜ ውስጥ ከአንድም አራት ፊልሞች እንዲሠሩ ሰበብ ሆኗል፡፡
በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ዕለተ እሑድ ኅዳር 14 ቀን 1890 ዓ.ም በሰሜን አሜሪካዋ ፊላዴልፊያ መታየት የጀመረው "The Horitz Passion Play"፤ ከይሁዳ ከተሞች አንዷ በነበረችው ቤተልሔም በከብቶች በረት የተወለደውን ሕጻን ለማየት ከተጓዙት ሰብዓ ሰገል ተነስቶ እስከ ትንሣኤው ያለው የኢየሱስ ሕይወት፣ ከብሉይና ሐዲስ ኪዳን በተመረጡ ታሪኮች፣ በ45 ገቢራት የተቀነባበሩበት፣ በዛሬዋ ቼክ ሪፑብሊክ የተቀረጸ ፊልም ነበር፡፡
ከዚህ ፊልም ተከትሎ ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ ሌላ ፊልም ለተመልካች ቀረበ፡፡
"The Passion Play of Oberammergau" በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር ዕለተ ሠኞ ጥር 24 ቀን 1890 ዓ.ም ለዕይታ የበቃው ፊልም ርዕስ ነው፡፡ ይህኛው ፊልም ለመሠራት የበቃበት መነሻ ደግሞ 300 ዓመታት ወደ ኋላ የሚቆጠርለት ልማድ ነው፡፡
በጀርመኗ ባቫርያ ግዛት የምትገኘው ኡበርአማጋው ከተማ ነዋሪዎች ከ1625 ዘመን ጀምሮ ያስቀጠሉት ልማድ አላቸው፡፡ በ1346 የተከሰተውና በአውሮጳ ብቻ 50 ሚሊየን ገደማ ሰዎችን ጨርሶ የነበረው ቡቦኒክ ወረርሽኝ ወይም ጸሊም ሞት፣ ዓለምን ሁሉ ሲያስፈራራ ቆይቶ፣ በ1625 ተራራማዋ ኡበርአማጋው ከተማን ተቆጣጠራት፡፡ በዚያ ማንም ማንንም ማዳን በማይችልበት ዘመን፣ የሚያደርጉትን ቢያጡ ፈጣሪ ያመጣውን ቁጣ እንዲያበርድላቸው ሥዕለት ገቡ፡፡ "ጌታ ሆይ፤ ይህን መቅሰፍት ካሳለፍህልን ዘመናችንን ሁሉ አንተን የምናከብርበት በዓል እናዘጋጃለን" አሉ፡፡ ጸሎታቸው ሰምሮ መቅሰፍቱ ሲበርድም ሥዕለታቸውን ለማድረስ በየአሥር ዓመቱ ትልቅ የኢየሱስን ሕማም የሚያወሳ ትዕይንት ያዘጋጃሉ፡፡ እዚህ ጋ ነው እንግዲህ "The Passion Play of Oberammergau" ፊልም የሚመጣው፡፡
የኢየሱስ ክርስቶስ ከውልደቱ እስከ ዕርገቱ ያለው ታሪክ በ23 ገቢራት፣ በ19 ደቂቃ ርዝማኔ የቀረበበት ይህ ፊልም፣ በወቅቱ ዘ ኒውዮርክ ሄራልድ ጋዜጣ እንደዘገበው፣ በማንሃተን ከተማ ከሚገኘው ግራንድ ሴንትራል ፓላስ ሆቴል በረንዳ ጣሪያ ላይ የተደረገው ቀረጻ ሥንፍና ነው ቢያስብለውም፣ የትዕይንቱን ትረካ ለማቅረብ የተደረገው ጥረት ግን ተደንቆ ተወርቶለታል፡፡ እንደ አሁን ዘመን በትዕይንት ሊገለጽ የማይችል ታሪክ፣ በጽሑፍ ለማስገባት የማይቻልበት ነበርና፣ ፊልሙ በሚታይበት ወቅት በሲኒማ ቤቶች አንድ ሰው ከመድረክ ጀርባ ቆሞ በድምጹ መተረክ ነበረበት፡፡
እንዲህ እንዲያ እያለ እስከዛሬ ድረስ በተለያዩ ቋንቋዎች ከ140 በላይ የኢየሱስን ሕይወት የሚያስቃኙ ፊልሞች ለዕይታ በቅተዋል፡፡ ከእነዚህ ፊልሞች መሃል ደግሞ አንዳንዶቹ እጅግ አነጋጋሪ ሆነው ቀጥለዋል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመሠቀሉ በፊት የነበሩትን 12 ሰዓታት መነሻ አድርጎ የተሠራውና በሜል ጊብሰን ተሰናድቶ በጂም ካቫይዘል ትወና የቀረበው "ዘ ፓሽን ኦፍ ክራይስት" (የክርስቶስ ሕማም) ፊልም፣ ከ21 ዓመታት በፊት ዕለተ ረቡዕ የካቲት 17 ቀን 1996 ለዕይታ ከበቃ ጀምሮ በመላው ዓለም ታይቶ ባስገባው ገቢ ከምንጊዜውም ከፍተኛ ገንዘብ አስገኚ ምርጥ 10 ፊልሞች አንዱ ያደርገዋል፡፡ አስገራሚው ነገር ይህ አይደለም፡፡ ያንን ፊልም ከተመለከቱ ሰዎች ውስጥ አብዛኛዎቹ ፊልሙን ከማየታቸው በፊት የነበራቸውን አቋም እንዲቀይሩ አድርጓል፡፡ ይህም ማለት ፊልሙን ከማየታቸው በፊት አማኝ ያልነበሩ ወይም ለዕምነት ብዙ ግምት የማይሰጡ እንደነበሩ ከተናገሩ ሰዎች መሃከል 69 በመቶዎቹ ፊልሙን ከተመለከቱ በኋላ ወደ ቤተ-ዕምነት ተስበናል ብለዋል፡፡
በአሜሪካ በተደረገ ጥናት ከተሳተፉ ስድስት ሰዎች አንዳቸው "ዘ ፓሽን" ፊልምን ካየን በኋላ ለራሳችን፣ ለቤተሰባችን፣ ለጎረቤቶቻችን ወይም ለሰው ልጅ ሁሉ የነበረን ምልከታ ተቀይሯል ሲሉ፣ ፊልሙን ካዩ በኋላ ይበልጥ ወደ ቤተ-ዕምነቶች መሄድ፣ መጸለይና መሰል ሃይማኖታዊ ተግባራትን ማዘውተር እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡ የዚህ ፊልም ነገር ሲነሳ በርካታ የክርስትና ዕምነት ቤተ-ክርስትያናት መሪዎችና ተመልካቾች አድናቆት ያጀበውን ያህል ተቃውሞም አላጣውም፡፡ በተለይም ከአይሁዳውያን ወገን፡፡


ኢየሱስ እና የሆሊውድ ፊልሞች



-በዮሴፍ ዳሪዮስ ሞዲ-
⬇️⬇️




በድንገት መብረቅ የቀላቀለ ሀይለኛ የነጎድጓድ ድምጽ አስተጋባ፡፡ እኔም ሆንኩ ሌሎቻችንስ ከደሙ ንጹህ እንሆን ይሆን፣ ስል ራሴን ጠየቅኩ ?

የመጨረሻ ተማጽኖ

"በመንግስትህ አስበኝ"
ምስማሮቹ መዳፎቼን እንደ እሳት እያቃጠሉት ነው፡፡ እጆቼ የሰውነቴን ሸክም መቋቋም ተስኗቸው እያንዳንዱን ሰከንድ በብርቱ ስቃይ እያሳለፍኩ ነው፡፡ በስተግራዬ የተሰቀለው ጓደኛዬ፣ የተሰበሰበውን ህዝብ እየተራገመና እየተሳደበ ያቃስታል፡፡ በስተቀኜ የተሰቀለው እሱ ነው፡፡ ናዝራዊው፡፡

እንደ ጎርፍ የሚፈስ ደም ፊቱን ሸፍኖታል፡፡ አይኖቹ ስቃይ እንጂ ጥላቻ አይነበብባቸውም፡፡ ህዝቡ ሲሰድበውና ሲያንቋሽሸው በዝምታ ይመለከታል፡፡ ወታደሮቹ በእጀጠባቡ እጣ ሲጣጣሉም አንዳች ተቃውሞ ከአፉ አልወጣም፡፡

ጓደኛዬ በስቃይ እያጓራ፤ "አንተ መሲህ አይደለህምን? ራስህንም እኛንም አድን!" አለው፡፡
ውስጤ ሌባና ወንበዴ ሆነህ ብትኖርም፣ እንደ ሞኝ መሞት የለብህም የሚል አንዳች ስሜት ተጫነኝ፡፡
"ትንሽ እግዚአብሄርን አትፈራም? እኛስ በስራችን ነው እሱ ምን በደለ!" ስል ገሰጽኩት፡፡
ቀጠልኩና በፍርሀትና በአክብሮት ወደ እርሱ ዞሬ፤ "ኢየሱስ ሆይ፤ በመንግሥትህ አስበኝ" አልኩት፡፡
ድምጹ ደካማ ቢሆንም በውስጤ የነበረውን ስቃይ የማሸነፍ ጉልበት ነበረው፡፡
"እውነት እልሀለው፤ ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" አለኝ፡፡

የተስፋ ቃሉ እንደ ቀዝቃዛ ነፋስ በላዬ ላይ ሲያልፍ ታወቀኝ፡፡ በፈተናና በድንጋጤ በተሞላው የህይወት ዘመኔ ለመጀመሪያ ጊዜ ፍርሀት ሲርቀኝ ተሰማኝ፡፡ ጨለማ ምድሩን ዋጠው፡፡ መሬት ተንቀጠቀጠች፡፡ እስትንፋሴ ከመዘጋቱ በፊት ግን ደግሜ እንደማገኘው እርግጠኛ ነበርኩ፡፡


መቶ አለቃው

በወታደርነት ብዙ ዘመን እንደማገልገሌ በርካታ ሰዎች ሲሞቱ ያየሁ ቢሆንም፣ የዚህ ሰው ግን በጣም የተለየ ነው፡፡ ወደ ጎልጎታ ሲያመጡት ጊዜው ከሰአት በኋላ ነበር፡፡ ማንነቱን ለመለየት እስኪያዳግት ድረስ ደብድበው አጎሳቁለውታል፡፡ ህዝቡ እየዘለፈውና እየዘበተበት፣ ቀሳውስቱ እየተፉበትና እያላገጡበት፣ ወታደሮቼ መስቀሉ ላይ አስተኝተው በካበተ ልምዳቸው ታግዘው ምስማሮቹን እጆቹ ላይ በቅልጥፍና ቸነከሩበት፡፡ መስቀሉን ለመትከል ሲያነሱትም ጸለየ እንጂ እንደ ሌሎች አልጮኸም፡፡

"አባት ሆይ፤ የሚሰሩትን አያውቁምና ይቅር በላቸው" ሲል ተማጸነ፡፡
"ይቅርታ??" እስከዛሬ ከሚሞቱ ሰዎች አንደበት እርግማን፣ ለቅሶና ስድብ እንጂ ይቅርታ የሚለውን ቃል ፍጹም ሰምቼ አላውቅም፡፡

ሰአታት አለፉ፡፡ እኩለቀን ገደማ ላይም ባልተለመደ ሁኔታ ጸሀይ ጨለመች፤ ምድርም በጥቁር ደመና ተሸፈነች፡፡ ከግራና ቀኙ የተሰቀሉት ወንበዴዎች የተለያየ ነገር ሲናገሩት አየሁ፤ እሱ ግን ለአንዱ ብቻ "ዛሬ ከእኔ ጋር በገነት ትሆናለህ" ሲል ሰማሁት፡፡

ከቆይታ በኋላ የሞቱ ሰአት ሲቃረብም ከስቃይ ሳይሆን ከጭንቀት በመነጨ ድምጽ፤ "አባት ሆይ፤ አባት ሆይ ለምን ተውከኝ ?" ሲል ጮኸ፡፡ ይኸኔ ምድር ተንቀጠቀጠች ፡፡ የቤተመቅደስ መጋረጃዎችም ለሁለት ተቀደዱ፡፡

ዘጠኝ ሰአት ሲሆንም "ተፈጸመ" ሲል አንሾካሽኮ አንገቱን ደፋ፡፡

ወታደሮቼም ሆነ ሲያውካካ የነበረው ህዝብ በዝምታ ተዋጡ፡፡

በእነዚህ ቃላት ነገስታትና ቀሳውስት ለማየት አሻፈረኝ ያሉትን ለማየት ታደልኩ፡፡

በዚያን ምሽት በደም የጨቀዩ እጆቼን ታጥቤ አጸዳሁ እንጂ ነፍሴ በደሙ እንደተሸፈነ ነበር፡፡ ደሙ የማይረሱ ቃላትን ነፍሴ ላይ አተመ፡፡

እናማ እኔ ግትር የሮም ወታደር የነበርኩት ሰው በመጨረሻ አመንኩ፡፡


መልካም የትንሳኤ በአል!!!


ጥቁር እንግዳና ሌሎች አጫጭር የስቅለት ታሪኮች


-ሣሙኤል እንግዳ-


ባለፉት ጥቂት ሳምንታት በመላው ክርስቲያኖች ዘንድ ከፍተኛ ክብር የሚሰጠውና የክርስቶስ ትንሳኤ የሚበሰርበት ታላቁ የፋሲካ በአል መዳረስን ምክንያት በማድረግ፣ ይህንኑ በአል ይበልጥ የሚያደምቁና ስቅለትን የሚዘክሩ ጽሁፎችን ለማቅረብ ጥረት ሳደርግ ቆይቻለሁ፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የታወቁና ያልታወቁ የስነጽሁፍ ሰዎች፣ በወንጌላት ከተጠቀሱት ታሪኮች ጎን ለጎን ስቅለትና ህማማትን እንዲሁም የክርስቶስን የሦስት አመታት ምድራዊ ቆይታና አስተምህሮዎች ከእውነታው ሳያፈነግጡ፣ ነገር ግን የበለጠ በሚያጠናክርና ስሜት በሚሰጥ አግባብ የሚተርኩ ልብወለዳዊ መልክ ያላቸው ጽሁፎችን ማንበብ በእጅጉ ያስደስተኛል፡፡ በዚህ ጽሁፍም መሰል ይዘቶች ያላቸው ጽሁፎችን በጥቂቱ እየቀነጫጨብኩ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ እነሆ፡-



ጥቁር እንግዳ

ክፍሉ በዳቦ ጠረንና በሰዎች ትንፋሽ ታውዷል፡፡ የተለኮሰው ላምባ ብርሀን በጠረጴዛ ዙሪያ በተሰበሰቡት አስራ ሦስት ሰዎች ፊት ላይ ያንጸባርቃል፡፡ ኢየሱስ ዳቦውን አንስቶ እየቆረሰ በለስላሳ ድምጽ፤ "ይህ ስለ እናንተ የምቆርሰው ስጋዬ ነው" ሲል ተናገረ፡፡

በድንገት በየት እንደገባ የማይታወቅ ቀዝቃዛ የነፋስ ሽውታ ክፍሉን ሞላው፡፡ መስኮቶች ግን ዝግ ነበሩ፡፡ ቀጠለና የእንጨቱ በር በዝግታ ከውጭ ሲንኳኳ ተሰማ፡፡ ደቀመዛሙርቱ የሚጠብቁት ሰው ባለመኖሩ በድንጋጤ እርስ በርስ ተያዩ፡፡

ጴጥሮስ እጆቹን በፍጥነት ጩቤው እጄታ ላይ አሳረፈና ድምጹን ጎላ አድርጎ "ማነው?" አለ፡፡

መልስ የለም፡፡ በሩ ከቀድሞው ጎላ ባለ ድምጽ ተንኳኳ፡፡ በመቀጠልም በሩ የመንሳጠጥ ድምጽ እያሰማ ተከፈተና ረጅም ካባ የደረበ፣ ፊቱ በካባው ኮፍያ ሙሉ በሙሉ የተሸፈነ፣ ዘለግ ያለ ሰው ወደ ውስጥ ገብቶ ቆመ፡፡

እንግዳው፤ "ሰላም ለዚህ ቤት ይሁን" በማለት ሰላምታ አቀረበ፡፡ ድምጹ ግን ቀዝቃዛና ህይወት አልባ ነበር፡፡
ይሁዳ እየተቁነጠነጠ፤ "ጌታ ሆይ፤ ለተጨማሪ ሰው የሚሆን ቦታም ሆነ ምግብ የለንም" ሲል አጉተመተመ፡፡

እንግዳው እንዲገባ ባይፈቀድለትም የማንንም ግብዣ ሳይጠብቅ፣ በተረጋጋ እርምጃ ወደ ውስጥ ዘለቀ፡፡ በሩ ማንም ሳይነካው ከበስተጀርባው የማስተጋባት ድምጽ አሰምቶ ተዘጋ፡፡ የተለኮሱት ላምባዎች ነበልባሎች በፍርሀት ይሰግዱ ይመስል ወደ ሰውዬው አቅጣጫ አዘነበሉ፡፡

ኢየሱስ የእንግዳውን ውስጥ ድረስ ጠልቆ የሚሰረስር የተሰወረ እይታ በአይኖቹ እየመለከተ፤ "ከእኛ አንዱ አይደለህም ለምን መጣህ ?" አለው፡፡

እንግዳው ደረቅ የፌዝ ሳቅ አሰማና፤ "አይደለሁም ብለህ ነው? ክህደት በሚኖርበት ቦታ ሁሉ የምገኝ አይደለሁምን" በማለት ምላሽ ሰጠ፡፡

ቶማስ አቃሰተ፡፡ እንግዳው ሲንቀሳቀስ ባይታይም በጠረጴዛው ዙሪያ በሚገኙት መቀመጫዎች አንደኛው ባዶ ወንበር ላይ ተቀመጠና፣ ረዣዥም እጆቹን ዘርግቶ አንዱን ዋንጫ ከመጠን በላይ በረዘሙ ጥፍራም ጣቶቹ እየጨበጠ፤ "ቀጣይ ስለሚሆነው ነገር ዋንጫችንን እናንሳ?" አለ፡፡

ይኸኔ እንድሪያስ አንዳች ምልክት አሳየና፣ ጳውሎስ ጩቤውን ከአፎቱ ላጥ አድርጎ እንግዳው ላይ ሊሰካ እጆቹ መንገድ በጀመሩበት ቅጽበት ኢየሱስ፤ "በቃ" የሚል ትእዛዝ የተሞላ ድምጽ አሰምቶ፤ "ይህች ምሽት ከላይ የታዘዘች ናትና፣ በዚህ አንዳች ስልጣን የለህም" ሲል ተናገረ፡፡

እንግዳው በፍጹም እርጋታና ያለአንዳች መረበሽ ጽዋውን በዝግታ ወደ አስቆሮቱ ይሁዳ ገፋ እያደረገ፤ "ስልጣን የለኝም እንዴ?" በማለት በተጠየቃዊ እይታ ተመለከተው፡፡

ይሁዳ እጆቹ እየተንቀጠቀጡ ጽዋውን ተቀበለ፡፡ ከውጪ በእየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ የውሾች ዋይታና ለቅሶ ድቅድቁን የምሽት ጨለማ ሰንጥቆ አስተጋባ፡፡

ሰላሳ የብር ማህለቆች

አስቆሮታዊው ይሁዳ ሳንቲሞቹን ጨብጦ ቅዝቃዜያቸውን በመዳፉ በማጣጣም ላይ ነው፡፡ ይህ ናዝራዊው የተሸጠበት ዋጋ ነው፡፡ አይሁድ ሲመጡ ኢየሱስ ጦርነት ያውጃል ብሎ ጠብቆ ነበር፤ ሰማያት ተከፍተው የእሳት ሰይፍ የያዙ መላእክት የሚወርዱም መስሎት ነበር፡፡ እውነተኛ መሲህ ከሆነ ጭቆናን መታገል አልነበረበትም? እሱ ግን በተቃራኒው በአሳዛኝ ስቃይ እየተመለከተው፤ "ወዳጄ ለማድረግ የመጣህበትን አድርግ" አለው፡፡

እነዚህ ቃላት በፍርሀት አራዱት፡፡ ሁሉንም ነገር በተሳሳተ መንገድ ተረድቶት ይሆን? በአእምሮው ከተሰማው ከባድ የጥፋተኝነት ስሜት በላይ በእጆቹ የጨበጣቸው ሳንቲሞች እንደ ፍም እሳት አቃጠሉት፡፡ ሳንቲሞቹን ለመመለስ ወደ ቀሳውስቱ ሲዞር፤ "ዞር በል አንቀበልህም፤ ወደምታደርስበት አድርሰው" በማለት አላገጡበት፡፡

ከትእይንቱ ለመሸሽ በምሽቱ ጨለማ ሲደናበር አደናቅፎት በአፍጢሙ ተደፋና፣ ሳንቲሞቹ ከመዳፉ አፈትልከው አሸዋ ላይ እንደተንጠባጠበ ደም ጭቃ ውስጥ ገብተው ተሰወሩ፡፡ በእርግጥ የሸጠውና የከዳው መምህሩን ብቻ ሳይሆን፣ ወዳጄ ብሎ የጠራውን ብቸኛውን እውነተኛ ሰው ነበር፡፡

በመጨረሻም ይሁዳ በቅጠል አልባ ጨፍራራ ዛፍ ስር ቆሞ አንዳንድ በደሎች ካሳ ሊኖራቸው እንደማይችል ተገነዘበ፡፡ ነገር ግን በጣም አርፍዶ ነበር፡፡

የቀሬናው ሰው

በወቅቱ ለራሴ ጉዳይ በእየሩሳሌም በማለፍ ላይ ነበርኩ፡፡ ድንገት ሳላስበው አንድ የሮማ ወታደር በወፍራም እጆቹ ትከሻዬ ጨምድዶ፣ "አግዘው" ሲለኝ የግል ጉዳዬ እንደ ጉም በኖ ጠፋ፡፡ ከፊት ለፊቴ እንቅፋት ወደሚያደነቃቅፈው ሰው እየገፈተረኝ፤ "አንሳና ተሸከመው" ሲል አዘዘኝ፡፡

ሰውየው ናዝራዊ ነበር፡፡ ጀርባው በግርፋት ተተልትሏል፡፡ ፊቱ በቡጢና በድብደባ ክፉኛ ቆሳስሎ በደም ተለውሷል፡፡ እንደተገፈተረ ከወደቀበት ሽቅብ ሲመለከተኝ አይኖቹ ከአይኔ ተጋጩ፡፡ እይታው ጥልቅ ነበር፡፡ በውስጡም ከቁጣና ሀዘን ይልቅ ምስጋና ይነበብበታል፡፡

ውስጤ ከዚህ ሁሉ ሰው መካከል እኔ ለምን ተመረጥኩ በሚል ቅሬታ ተሞልቶ መስቀሉን አንስቼ ተሸከምኩት፡፡ የጎልጎታን ዳገት መውጣት ስንጀምር ግን ሹክሹክታዎችን መስማት ጀመርኩ፤

"ልጄን ፈውሶልኛል"
"አንዱን ቂጣ ባርኮ ሺዎችን መግቧል"
"አላዛርን ከሞት አስነስቷል"
በመጨረሻም ወታደሮቹ መስቀል ላይ እጆቹን ዘርግተው ሲቸነክሩ አይኖቼን መንቀል ተሳነኝ፡፡
"አባት ሆይ ይቅር በላቸው" ሲል ቃተተ፡፡
በመስቀሉ ሸክም የዛሉት ክንዶቼ አሁን እየተንቀጠቀጡ ነው፡፡
ለግል ጉዳዬ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቼ የእግዚአብሄርን በግ መስዋዕትነት ተመልክቼ ከተማዋን ለቅቄ ወጣሁ፡፡

የክላውዲያ ህልም

"በዚያ ንጹህ ሰው ላይ በሚሆነው ሁሉ እንዳትተባበሪ"

ህልሙ አሁንም ድረስ ግልጽ ሆኖ ይታየኛል፡፡ ያስጠነቀቀኝ ብርሀን የተጎናጸፈ ሰው ነበር፡፡ ባሌ ጲላጦስ ግን እጆቹን ታጥቦ ናዝራዊውን ለህዝቡ ፈቃድ አሳልፎ ሰጠው፡፡ አሁን ብርሀናማው ሰማይ በጨለማ ተጋርዶ ከቤተመንግስቴ ሆኜ በርቀት ስቅለቱ ወደተካሄደበት ከፍታ አሻግሬ እየተመለከትኩ ነው፡፡

በድንገት አንድ አሽከር ሲሮጥ ወደ እኔ መጣና፤ "እመቤቴ መሬት ተንቀጠቀጠች፤ የቤተመቅደስ መጋረጃዎች ለሁለት ተቀደዱ" ሲል እያለከለከ የተፈጠረውን ነገረኝ፡፡

ልቤ ደረቴን ሰንጥቆ ሊወጣ የፈለገ ይመስል ክፉኛ መታ፡፡ ጲላጦስን እንዲለቀው አስጠንቅቄው ነበር፤ ነገር ግን ፍርሀትና ፖለቲካ አሸነፉት፡፡

ትንሽ ቆይቶ ሌላኛው ዜና ተከተለ፤ "በመስቀሉ ስር የነበረው መቶ አለቃ የእግዚያብሄር ልጅ ነው ሲል መሰከረ"

ጉልበቶቼ ሰውነቴን መቋቋም ተስኗቸው ዘፍ ብዬ ተንበረከኩ፡፡ ህልሙ አሁንም ውስጤ ያቃጭላል፡፡
ጲላጦስ፤ "እኔ ከደሙ ንጹህ ነኝ" ያለው ቃል ውስጤ አቃጨለ፡፡


ከሰሞኑ በፌደራል መንግሥት ስልጣን የተሰጣቸው ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች የትግራይን ችግር ሊፈቱ እንደማይችሉ የገለጸው ሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)፤ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት የሚያቅፍ ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቀር አለበት ብሏል፡፡

የሳወት የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ብርሃነ አጽብሃ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ከሰሞኑ በፌደራል መንግሥት ስልጣን ስለተሰጣቸው የቀድሞ የህወሓት ከፍተኛ አመራሮች ምልከታቸውን አጋርተዋል። አቶ ብርሃነ፣ ጉዳዩ የአመራሮቹና የፓርቲው ቢሆንም፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የክልሉን ሕዝብ ሊነካ እንደሚችል ጠቁመዋል።

ከዚህ ቀደም፣ የትግራይ ሕዝብ በተደጋጋሚ መስዋዕትነት እንደከፈለና ይህም ሕዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር ሕገ መንግሥታዊና ተፈጥሯዊ መብቱን ለማረጋገጥ ሲል እንዳደረገው ሃላፊው አብራርተዋል። ይሁንና ህወሓት ለሁለት መሰንጠቁን ተከትሎ፣ በቡድኖቹ መካከል መካረሩ እየተባባሰ መጥቶ፣ አንደኛው ወገን ጊዜያዊ አስተዳደሩን በሃይል ለማስወገድ ጥረት ማድረጉን አውስተዋል።

“የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት በእርሳቸው ስር የነበሩ ባለስልጣናትን ይዘው ወደ አዲስ አበባ ከሄዱ በኋላ፣ ‘የጊዜያዊ አስተዳደሩ የስልጣን ዕድሜ ስላበቃ’ በሚል ምክንያት በፌደራል መንግሥቱ በኩል የዓዋጅ ማሻሻያ ተደርጓል። ይህን ተከትሎ አቶ ጌታቸው ከስልጣናቸው እንደሚወርዱ በበርካቶች ዘንድ ግምት ተወስዶ ነበር።” ያሉት አቶ ብርሃነ፤ አዲስ የጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ከተሾሙ ወዲህ፣ በርካቶች የአቶ ጌታቸው ዕጣፈንታ ምን እንደሚሆን ሲጠይቁ እንደነበር አንስተዋል።

“እንደ ግለሰብ ስራ ከማጣት ወይም የራሳቸውን ፖለቲካዊ ዓላማ ለማሳካት አልመው የተሰጣቸውን ሹመት እንደተቀበሉ እንገምታለን። ነገር ግን የተሰጣቸው ሹመት ለትግራይ አንዳች ጥቅም ሊያስገኝ አይችልም” ብለዋል።

ለዚህም ምክንያታቸውን ሲያስረዱ፣ “የትግራይ ክልል ችግሮች በክልሉ ውስጥና በትግራይ ልሂቃን አማካይነት ነው መፈታት ያለባቸው እንጂ፣ የፌደራል መንግሥቱን ጨምሮ በሌሎች ጣልቃ ገብ አካላት አይፈታም፡፡ ለዚህም ያለፉት ሁለት ዓመታት የጊዜያዊ አስተዳደሩ ሁኔታና ከዚያ ቀደም ህወሓት መንበረ ስልጣኑን በበላይነት በተቆጣጠረባቸው ጊዜያት የነበሩ ሂደቶች ምሳሌ ናቸው” ሲሉ ጠቅሰዋል።

“በህወሓት የተጠመቁና በፌደራል መንግሥቱ ስልጣን የተሰጣቸው ከፍተኛ አመራሮች የትግራይን ችግር በርቀት ‘ይፈታሉ’ የሚል ዕምነት የለንም። እንደ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ የትግራይ ችግር የሚፈታው በትግራይ ተወላጆችና አቅም ነው። የፌደራል መንግሥት በሚያስቀምጣቸው ሰዎች ችግሩ ለዘለቄታው ይፈታል ብለን አናምንም” ብለዋል፡፡

የአሁኑ ፕሬዚዳንት በጊዜያዊ አስተዳደሩ የተመረጡ ሳይሆኑ በህወሓት አንደኛው ክንፍ ተመርጠው በወታደራዊ ሃይል ግፊት ስልጣን የያዙ መሆናቸውን ፓርቲያቸው እንደሚያምን ያመለከቱት አቶ ብርሃነ፤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቀር ያለበት በሲቪል ፕሬዚዳንትና ካቢኔ እንጂ በወታደራዊ አዛዦች መሆን እንደሌለበት አብራርተዋል።

“ባለድርሻ አካላት የሚሳተፉበት ብሔራዊ ጉባዔ ተጠርቶ ሁላችንንም የሚያስማማ ጊዜያዊ አስተዳደር መዋቀር አለበት” ሲሉም መፍትሄ ያሉትን ሃሳብ ሰንዝረዋል።

የመፍትሔ ሃሳቡን ፓርቲያቸው በተደጋጋሚ ሲያንጸባርቅ እንደቆየ ጠቅሰው፣ ክልላዊ ምርጫ ተካሄዶ አዲስ መንግሥት እስኪቋቋም ድረስ ለሚቀጥለው አንድ ዓመት ያህል የሚቆይ ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋም እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ሌተናል ጄኔራል ታደሰ በአመራርነት ቦታ ሆነው ሰራዊቱ “ያሻውን” እንዲፈጽም በር ሲከፍቱ መቆየታቸውን በማውሳት፣ እርሳቸው “ሁለት ቦታ እየረገጡ” ባሉበት ሁኔታ ለትግራይ ለውጥ ሊያመጡ እንደማይችሉ ጠቁመዋል። “ከህወሓት ጥላ ያልወጡ መሪ ናቸው፤ ከድርጅታቸው ተጽዕኖ እንደሚደርስባቸውም የሚገመት ነው።” ሲሉ ተናግረዋል።

የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከሚያዝያ 3 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር ሆኖ ሲሾሙ፣ የቀድሞ የመቐለ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ክንደያ ገብረሕይወት ከሚያዚያ 6 ቀን 2017 ዓ.ም. አንስቶ የትምሕርት ሚኒስቴር አማካሪ ሚኒስትር ደኤታ ሆነ መሾማቸው የሚታወቅ ነው።


በፌደራል መንግሥት የተሾሙ ከፍተኛ
አመራሮች የትግራይን ችግር ሊፈቱ አይችሉም

-ሳልሳይ ወያነ ትግራይ-
⬇️⬇️


የጤና ባለሞያዎች በመንግሥት የተገለሉ ናቸው ተባለ

የጤና ባለሞያዎች በመንግሥት ዘንድ የተገለሉ መሆናቸውን የኢትዮጵያ የጤና ባለሞያዎች ማሕበር ገልጿል። በተለያዩ የሕክምና ዘርፎች ዙሪያ የተሰባሰቡት ማሕበራት ደካማ እንደሆኑም ጠቁሟል፡፡
የኢትዮጵያ የጤና ባለሞያዎች ማሕበር መሥራችና ዋና ስራ አስኪያጅ ነርስ ዮናታን ዳኛው ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት አጭር ቆይታ፤ የጤና ባለሞያዎች እንቅስቃሴ አዲስ አለመሆኑን ጠቅሰው፣ ከ2015 ዓ.ም. አንስቶ የተለያዩ ጥያቄዎች ሲነሱ መቆየታቸውን ተናግረዋል - በተለይም እርሳቸው የሚመሩት ማሕበር ለመንግሥት ብዙ ጥያቄዎችን ማቅረቡን በመግለጽ፡፡
ለአብነትም፣ ለጠ/ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ ለትምሕርት ሚኒስቴር፣ ለጤና ሚኒስቴርና ለሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፣ እንዲሁም ለሌሎች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው መስሪያ ቤቶች የጤና ባለሞያዎች ጥያቄን በዝርዝር የሚያስረዳ ሰነድ እንዲገባ መደረጉን ነርስ ዮናታን ተናግረዋል። ሌሎችም “ሞቅ ያሉ” የተለያዩ እንቅስቃሴዎች በማሕበሩ አማካይነት መደረጋቸውን አመልክተዋል፡፡
ይሁንና ከመንግስት በኩል እስካሁን ድረስ መፍትሄ የተሰጣቸው ችግሮች እንደሌሉ ዋና ስራ አስኪያጁ ጠቁመው፤ የጤና ባለሞያዎች በበርካታ ጫናዎች ውስጥ እየሰሩ እንደሚገኙ አመልክተዋል። አክለውም፤ “የጤና ባለሞያዎች በመንግስት ዘንድ የተገለሉ ናቸው፤ ይህም ሁኔታ በመጪው ትውልድ ላይ በጎ ተጽዕኖ የሚያሳርፍ አይደለም” ብለዋል።
ማሕበሩ ከደመወዝ ጋር የተገናኙ ብዙ ቅሬታዎች እንደሚደርሱት የተናገሩት ነርስ ዮናታን፤ ከዚህ በፊት ከደመወዝ ጋር የተያያዙ ችግሮች እምብዛም እንደነበሩ ጠቅሰዋል። ይሁንና በአሁኑ ወቅት እነዚህ ችግሮች እየተበራከቱ መምጣታቸውን ለአዲስ አድማስ ገልጸዋል።
በጤና ባለሞያዎች ላይ የሚያርፉ የተለያዩ ጫናዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆነው ማሕበረሰብ ላይም የራሳቸውን ተጽዕኖ እንደሚፈጥሩ በማስታወስ፤ “ደስተኛ ያልሆነ ባለሞያ ደስተኛ ሆኖ ሕዝብን ሊያገለግል አይችልም” ብለዋል፡፡ ከደመወዝ ክፍያ ጋር በተያያዘ የሚፈጠረው ችግር በብዛት የሚስተዋለው በዞንና ወረዳ የመንግስት መዋቅር ላይ መሆኑን ያመለከቱት የማህበሩ መሥራች፤ በከተሞችና ሌሎች አካባቢዎች የደመወዝና ተያያዥ ክፍያዎች በአግባቡ ለጤና ባለሞያዎች እንደሚደርሱ ጠቁመዋል፡፡
ከክፍያ ጋር የተያያዙ ችግሮች መነሻቸው በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚስተዋል ብልሹ አሰራር መሆኑን የሚናገሩት ነርስ ዮናታን፤ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ በመንግሥት አመራሮች በኩል የመፍትሔ ስራዎች መሰራት እንዳለባቸው አሳስበዋል። ከዚህም ሌላ ማሕበሩ በጤና ባለሞያዎች ዙሪያ የሚስተዋሉ ሁኔታዎችን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“በጤና ዘርፍ የተቋቋሙ የተለያዩ የሞያ ማሕበራት ደካማ ናቸው” ያሉት ነርስ ዮናታን፤ ምክንያቱን ሲገልጹም፣ በሞያ ዘርፍ የተከፋፈሉ በመሆናቸው ነው ባይ ናቸው፡፡ በዚህም ሳቢያ ለጤና ባለሞያዎች ድምጽ ለመሆን አለመቻላቸውን ነው የገለጹት፡፡
የኢትዮጵያ የጤና ባለሞያዎች ማሕበር በ2015 ዓ.ም. የተቋቋመ ሲሆን፤ ማሕበሩ የተለያዩ በጤናው ዘርፍ የተሰማሩ ባለሞያዎችን በአባልነት ያቀፈ ነው።


በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ተቋቁሞ በሥራ ላይ የሚገኘው የክልሉ ጊዜያዊ ምክር ቤት በኃይል እንዳይፈርስ ስጋት እንዳለ የተገለጸ ሲሆን፤ ምክር ቤቱ ከአዲሱ ፕሬዚዳንት ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ወረደ ጋር ለመወያየት ጥሪ ማቅረቡ ተሰምቷል፡፡

ለተለያዩ የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ባለፈ ማክሰኞ ሚያዚያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም. ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጠው የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት፣ተቀማጭነታቸውን በአዲስ አበባ ካደረጉ የውጭ አገራት አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ጋር ውይይት ማድረጉንና የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑን እንደገለጸ አስታውቋል፡፡

የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አቶ ሞገስ ታፈረ፤ “የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም የተጠበቀውን ያህል አለመሆኑ ላይ የአመለካከት ልዩነት አለ። ይሁንና አፈጻጸሙ አጥጋቢ አለመሆኑን በተመለከተ ሁሉም አካላት ይስማማሉ” ብለዋል።

ከዚህ ቀደም ሌተናል ጄኔራል ታደሰ ከጊዜያዊ ምክር ቤቱ ጋር ይወያዩ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ሞገስ፤ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኋላ ግን የተጀመረ ግንኙነት አለመኖሩን ተናግረዋል፡፡ አዲሱ ፕሬዚዳንት በቀጣይ ጊዜያት በሚሰሩ ስራዎች ዙሪያ ከምክር ቤቱ ጋር እንዲወያዩ ጥሪ መቅረቡን በመግለጽም፣ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ከጊዜያዊ ምክር ቤቱ ጋር በትብብር መስራቱ “አማራጭ የሌለው ጉዳይ” ነው ብለዋል፡፡

ለፕሬዚዳንቱ ጥሪ ከማቅረብ በተጨማሪ፣ በአሁኑ ወቅት እየተቋቋመ ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር - በአቃፊነቱና አሳታፊነቱ ዙሪያ ለመወያየት ጊዜያዊ ምክር ቤቱ ደብዳቤ መጻፉን ገልጸዋል፤ አቶ ሞገስ። በቀጣይ ጊዜያትም ረቂቅ ዓዋጆችን ከማጽደቅ አንስቶ ድጋፍና ክትትል የማድረግ ስራ እስከመስራት ድረስ የሚዘልቁ ስራዎችን ለማከናወን ጊዜያዊ ምክር ቤቱ ዝግጁ መሆኑን አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት በስራ ላይ እንደሚገኝ የገለጹት ደግሞ የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ ዶ/ር ደጀን መዝገቡ ሲሆኑ፤ በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ላይ ከሚመለከታቸው የፌደራል መንግሥት አካላት ጋር ውይይት እንደተካሄደ ተናግረዋል፡፡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንትን በኢሜይል ለመምረጥ በጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ቀርቦ የነበረውን ጥሪ ምክር ቤቱ መቃወሙንም ጠቁመዋል፡፡

“ጊዜያዊ ምክር ቤቱ የዕድሜ ገደቡ ምንም እንኳ አጭር ቢሆንም፣ በዚህ የሽግግር ወቅት አቅም ለመፍጠር ዕድል የሚያመቻች ሃይል ነው። ይህ ምክር ቤት አሳታፊና አቃፊ በመሆኑ፣ ለትግራይ ክልል የዴሞክራሲ መለማመጃ ተቋም ሆኖ ሊቆጠር ይገባል” ብለዋል። ጊዜያዊ ምክር ቤቱ ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ያስገባው ደብዳቤ ተቀባይነትን እንደሚያገኝም ተስፋ እናደርጋለን ብለዋል፤ ምክትል ሰብሳቢው፡፡

“በቀጣይ ጊዜያት ጊዜያዊ ምክር ቤቱ በሕልውናው ላይ ምን ዓይነት ፈተናዎች ሊጋረጡበት ይችላሉ?“ የሚል ጥያቄ ከጋዜጠኞች የቀረበላቸው ዶክተር ደጀን፤ “ከሕግ አንጻር ምንም ዓይነት ፈተና የለብንም። ነገር ግን ምክር ቤቱ በጉልበት ስላለመበተኑ እርግጠኛ አይደለንም” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል። አቶ ሞገስ በበኩላቸው፤ የጊዜያዊ ምክር ቤቱ የስራ ጊዜ ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ተመሳሳይ መሆኑን ጠቁመው፤ ይህም በሕግ ላይ “የተመሰረተ ነው” ብለዋል።

አያይዘውም፤ “ይህ ጊዜያዊ ምክር ቤት በየትኛውም አካል በሆነ ጊዜ የሚፈርስና የሚቋቋም ተቋም አይደለም” ሲሉ አጽንዖት ሰጥተዋል።

የቀድሞ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት በደንብ ቁጥር 10/2016 ዓ.ም. የተቋቋመው ጊዜያዊ ምክር ቤቱ መጀመሪያ ላይ “አማካሪ ካውንስል” በሚል ይጠራ የነበረ ሲሆን፣ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ግን ስያሜውን ወደ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት እንደቀየረ የሚታወስ ነው። ምክር ቤቱ “የህወሓት፣ የጦር ሃይልና ሌሎች ውክልናን ያላካተተ ነው” የሚል ተቃውሞ ሲቀርብበት ቆይቷል።


የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ምክር ቤት
"በኃይል" እንዳይፈርስ ተሰግቷል

• ጊዜያዊ አስተዳደሩ ከጊዜያዊ ምክር ቤቱ ጋር በትብብር መስራት አለበት


⬇️⬇️


እነሆ፣ ዛሬ የፋሲካ በዓል ዋዜማ ላይ እንገኛለን። ዕለቱ በተለይ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አማንያን ዘንድ ቀኑ “ቅዳም ስዑር” ይባላል። “የተሻረች ቅዳሜ” ማለት ነው። በዛሬው ዕለት የዕምነቱ ተከታዮች በግንባራቸው ላይ ቄጤማ በማሰር ቀኑን አስበውት ይውላል። ምዕመኑ በነገው ዕለት ለሚከበረው ታላቁ የትንሳዔ በዓል የሚያስፈልጉ ሸቀጣሸቀጦችን በአብዛኛው የሚሸምቱት በዛሬው ዕለት ነው፡፡ ለመሆኑ የዘንድሮው የበዓል ገበያ ምን ይመስላል? ዋጋውስ እንዴት ነው? ሸማቾችስ ምን ይላሉ?

የአዲስ አድማስ ሪፖርተር በአዲስ አበባ ከሚገኙ የግብይት ስፍራዎች አንዱ በሆነው በሾላ ገበያ ተገኝቶ የአውዳመት ገበያን ቃኝቷል፡፡ በዚህም መሰረት፣ ቀይ ሽንኩርት በኪሎ ከ55 እስከ 70 ብር፣ ነጭ ሽንኩርት 290 ብር፣ ቲማቲም 60 ብር፣ ካሮት 55 ብር፣ ቀይ ስር 50 ብር፣ ጥቅል ጎመን 35 ብር በመሸጥ ላይ ይገኛሉ። ዕንቁላል የፈረንጅ ከ13 እስከ 14 ብር፣ እንዲሁም የሐበሻ በ17 ብር እየተሸጠ ነው።

የዶሮ ዋጋን በተመለከተ የሃበሻ ዶሮ ከ1000 ብር ጀምሮ እስከ 3000 ብር ድረስ ሲሸጥ፣ በልዩ ስሙ “የወላይታ” ተብሎ የሚጠራውና በቁመናው ከሌሎች ዶሮዎች ገዘፍ የሚለው ዶሮ የ1700 ብር ዋጋ ተቆርጦለት እየተሸጠ ይገኛል። በዶሮ ንግድ ላይ ከተሰማሩ ነጋዴዎች አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ነጋዴ ስለገበያው ሁኔታ ጠይቀነው፣በዘንድሮው የበዓል ገበያ ላይ የዶሮ አቅርቦት ከባለፈው ዓመት አንጻር በተወሰነ መጠን መቀነሱን ነግሮናል።

በቅኝታችን ቅቤና ዓይብ ወደሚሸጥበት ጎራ በማለት ዋጋ ጠይቀናል። ነጋዴዎቹ እንደነገሩን ከሆነ፣ ቅቤ እንደየደረጃው ኪሎው ከ900 ብር ጀምሮ እየተሸጠ ነው። ዓይብ ደግሞ፣ በኪሎ 800 ብር እንደሚሸጥ ተገልጾልናል።

ጠላ ለመጥመቅና ጠጅ ለመጣል ከሚያገለግሉ ወሳኝ ግብዓቶች አንዱ የሆነው የጌሾ ቅጠል በኪሎ 250 ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ የስንዴና የገብስ ብቅሎች በተመሳሳይ ዋጋ፣ ማለትም በኪሎ 800 ብር እየተሸጡ ነው። ወደ ቅመማቅመሞች ተራ ጎራ ስንል፣ ኮረሪማ በኪሎ 1300 ብር እንደሚሸጥ ተነግሮናል። ለዋጋው መወደድ ምክንያቱ ምን እንደሆነ ብንጠይቅም፣ ከነጋዴዎቹ የተሰጠን ምላሽ ዝምታ ሆኗል።

ባለፈው ረቡዕና ሐሙስ የሾላ ገበያን ስንቃኝ፣ ድባቡ የተቀዛቀዘ ነበር ማለት ይቻላል፡፡ አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አንድ ሸማች፣ በዘንድሮው የበዓል ገበያ በአንዳንድ ግብዓቶች ላይ የተስተዋለው የዋጋ ጭማሪ፣ ገበያተኛው ሌሎች አማራጮችን እንዲቃኝ እንዳስገደዱትና የገበያ ድባቡን እንዳቀዛቀዘው ገልጸውልናል። በርግጥም፣ እኛ ለመቃኘት እንደቻልነው፣ ከሾላ ገበያ በተወሰኑ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኙ በድንኳን የተዘጋጁ የ“ቅዳሜ ገበያ” ቦታዎች የተለያዩ ምርቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረባቸው ሸማቹ ፊቱን ወደ እነዚህ ድንኳኖች ያዞረ ይመስላል፡፡ ገበያውም በተሻለ ሞቅ ደመቅ ብሎ ይታያል፡፡

የቁም እንስሳት ግብይት ወደሚከናወንበት፣ የካራሎ የቁም እንስሳት ግብይት ማዕከል ጎራ ብለን ዳሰሳችንን ቀጥለናል። በዚህ ማዕከል ለዕርድ የሚቀርቡ ሰንጋዎች እንደየደረጃቸው ለሸማቾች ቀርበዋል። በዳሰሳችን ወቅት የሸማቾች ቁጥር በእጅጉ አነስተኛ የነበረ ሲሆን፣ በብዛት የሚታዩት ነጋዴዎቹ ነበሩ፡፡ እኛም ሰንጋዎች እንደየደረጃቸው በምን ያህል ዋጋ እንደሚሸጡ ጠያይቀናል። ዝቅተኛው መነሻ ዋጋ 78 ሺህ ብር ሲሆን፣ ከፍ ያለ ሰንጋ ደግሞ በ95 ሺህ ብር እንደሚሸጥ ለማወቅ ችለናል።

ከሰሞኑ የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ መጪውን የፋሲካ በዓል በማስመልከት አንድ መልዕክት አስተላልፏል፡፡ በዚህ መልዕክቱም፣ ፍትሃዊና የተረጋጋ የግብይት ስርዓት እንዲኖርና የአቅርቦት ዕጥረት እንዳይከሰት በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጿል። በእንቁላል ገበያ ላይ የሚታየውን ያልተረጋጋ ዋጋና የስርጭት መዋዠቅ ለማስተካከልም ከአቅራቢዎች ጋር የትስስር ስርዓቱን ይበልጥ በማሳለጥ አቅርቦቱን ማሳደግ እንደሚገባ ጠቁሟል፡፡ ቢሮው ከሚያዝያ 4 እስከ 12 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ የሚቆይ የዋጋ ተመን በተለያዩ የግብርና ምርቶች ላይ “አውጥቻለሁ” ብሏል።

በአጠቃላይ፣ ተዘዋውረን ቅኝት ባደረግንባቸው የገበያ ስፍራዎች የተስተዋለው የተቀዛቀዘ የገበያ ድባብ፣ በዛሬው የቅዳም ስዑር ዕለት ይሟሟቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መልካም የትንሳኤ በዓል!


የዘንድሮ የፋሲካ ገበያ ድባብ

• የሃበሻ ዶሮ ከ1000 ብር እስከ 3000 ብር እየተሸጠ ነው
• የሃበሻ እንቁላል በ17 ብር፣ የፈረንጅ በ14 ብር ይሸጣል


⬇️⬇️


የጄነራሎቹ እግድ ተነስቷል!

አዲሱ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት ሌ/ጀኔራል ታደሰ ወረደ፣ በቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕ/ት በአቶ ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ እግድ የተላለፈባቸውን ሦስት ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦችን፣ ከሚያዝያ 7 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እግዱ መነሳቱን ከሦስት ቀን በፊት በተጻፈ ደብዳቤ አሳውቀዋል።

በቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተጣለባቸው ጊዜያዊ እግድ የተነሳላቸው ሦስቱ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ስም ዝርዝር፦

1.ሜጀር ጄነራል ዮወሃንስ ወልደጊዮርጊስ፣
2. ብርጋዴር ጄነራል ምግበይ ሃይለ እና
3. ሜጀር ጄነራል ማሾ በየነ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.