ሐሙስ ዕለት የኮሮናቫይረስ ክትባት ሙከራ በሰዎች ላይ ይጀመራል!
የዩናይትድ ኪንግደም የጤና ሚኒስትሩ ማት ሃንኮክ ዛሬ አመሻሽ ላይ በሰጡት መግለጫ ላይ ለኮሮናቫይረስ የተዘጋጀው ክትባት በዚህ ሳምንት ሐሙስ እለት በሰው ላይ ሙከራ ይካሄድበታል ሲሉ አሳውቀዋል። ሚኒስትሩ ጨምረውም መንግሥታቸው ለበሽታው ክትባት ለመስራት በሚያስችሉ ጥረቶች ላይ የሚችለውን ሁሉ ነገር እንደሚያደርግ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።አክለውም ዩናይትድ ኪንግደም ለወረርሽኙ ክትባት ለማግኘት በሚደረጉ ምርምሮች ላይ “ከየትኛውም አገር ክትባት በላይ ከፍተኛ ገንዘብ” መድባ እየሰራች መሆኑን አመልክተዋል።
በዚህ መስክም ሚኒስትሩ ኦክስፎርድን ዩኒቨርስቲንና የለንደኑን ኢምፔሪኣል ኮሌጅን ጠቅሰው “ሁለቱም ፈጣን ውጤትን እያሳዩ ያሉ ተስፋ ሰጪ” ሥራዎችን እያከናወኑ መሆናቸውን አስረድተዋል።