Advanced Freshman


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


🔔ይህ ቻናል በ2017 freshman ለሚማሩ ተማሪዎች የተዘጋጀ እና በዉስጡ የተለያዩ የዩንቨርስቲ መረጃዎችን, አጋዥ መፅሐፍቶች, ቲቶሪያል, mid እና final ፈተናዎችን ሚያዘጋጅ እና ተማሪዎች ወደ ሚፈልጉበት ዲፓርትመንት እንዲገቡ ሚያግዝ ነው ::
📩For comment and ads :- @EEG12bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


🎙Advice for university students

🗣ሁላችሁም አዳምጡት ይጠቅማቿል😊

©️Credit: Sofoniyas

@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

2.6k 0 32 14 32

የጥንቃቄ መልእክት🏹

🙌አብዛኞቻቹ የጊቢ ተማሪዎች አይደላችሁ(ፍሬሽማን እና remedial) እናላችሁ በተለያየ አጋጣሚ inbox ወይም group ላይ ብዙ ሚያወሯችሁ ሰዎች ያጋጥሟቿል::ከነዚህም ዉስጥ ስራ መስራት ትፈልጋለህ/ሽ ብለዋቹ እናንተን attract ለምድረግ እና በደካማ ጎናችሁ መተው ለማይሆን ፀፀት ይዳርጉአቿል:: በተለይ ከፒራሚድ ስኪም ስራ ጋር የተያያዙ ብዙ ተማሪዎችን ለኪሳራ የዳረጉ ድርጅቶች ብቅ ብቅ እያሉ ነዉ::ምታቁ ታቃላችሁ ማታቁ ደግሞ እንደዚህ አይነት ሰዎች ሲያናግሯቹ ነቃ እንድትሉ እና በቀላሉ እንዳትበሉ ለማለት ያህል ነዉ::

Breakthrough "infinity power'
OMD ምናምን ?? እንዲህ እያሉ እራሳቸውን እያደሱ ያጨበረብሯችኋል " በተለይ በየ groupu የስራ ዕድል ወይም online ስራ ምናምን እያሉ ሚርመሰመሱ ሰዎች አሉ ተጠንቀቁ!!

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

7.8k 0 46 14 121

Freshman ተማሪዎች 1st semester ዉጤት እንዴት ነበር? GPA ስንት አመጣችሁ?
So‘rovnoma
  •   4GPA
  •   Above 3.8
  •   Above 3.5
  •   Above 3
  •   Below 3
  •   Remedial ነኝ😁
126 ta ovoz

8.9k 0 5 42 113

🚨 ALERT

የቴሌግራም ፕርሚየም ስጦታ ብለው ኢንቦክስ የሚልኩላችሁን እንዳትከፍቱ ። አብዛኞቹ አካውንታቸውን እያጡት ይገኛል ይህን መረጃም ለሁሉም ሼር በማድረግ ከጥፋት ራሳችሁን እንድታድኑ እንገልፃለን ።

በብዛት የሚልኩት በምታወሩት ሰው አካውንት ነው!! HACK ካደረጉት በዋላ የማቀው ሰው ነው የላከው ብላቹ እንድታስቡ በምታቁት ሰው አካውንት ይልኩላቹዋል ሊንኩን ስከፍቱት እናንተንም HACK ያረጋሉ ከዛ በእናንተ አካውንት ደግሞ እናንተን ወደሚያውቃቹ ሰው በራሳቹ አካውንት ይልካሉ!!

ACCOUNT Ban እስከመሆን ድረስ ሊደርስ ይችላል:: ስለዚህ ሊንኩን በጭራሽ እንዳትነኩት!!!

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


🥏 የግቢ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ዉስጥ ስትማሩ እልኸኛ ልትሆኑ ይገባል። ለራሳችሁ ስትሉ እንዲሁም በተስፋ ለሚጠብቋችሁ ቤተሰቦቻችሁ ስትሉ በእያንዳንዱ እንቅስቃሴያችሁ መታመን አለባችሁ

#️⃣ከምንም በላይ አዋዋላችሁ ላይ ጥንቃቄ አድርጉ!! ሰው ውሎውን ይመስላል ሲባል ተራ አባባል አይደለም ወደዳድችሁም ጠላችሁም ውሏችሁ ማንነታችሁን ይገነባል::

#️⃣ትክክለኛ መንገድ ላይ ካልሆኑ ተማሪዎች ጋር ገጥማችሁ ከሆነ አሁኑኑ ግንኙነቱን አቋርጡት እና ለነጋቸው ዋጋ ከሚሰጡ እና ሳይኖራቸው ልጆቻቸውን ለማስተማር በሚለፉ ቤተሰባቸው ላብ ላይ ከማይቀልዱ ተማሪዎች ጋር ግጠሙ::

🔗በተለይ ሪሚዲያል እና fresh man ላይ በደንብ ትኩረት ሰጥታችሁ ተዘጋጁ ከዛ በኋላ በሚኖራችሁ ቆይታ ዘና ብላችሁ እየተማራችሁ ጎን ለጎን ቢዝነስ እየሰራችሁ ተመርቃችሁ ስትወጡ ቅጥር ሳትጠብቁ ቤተሰብ ላይም ጥገኛ ሳትሆኑ የራሳችሁን ነገር ራሳችሁን ችላችሁ መስራት ትችላላችሁ

ብልህ ሁኑ !!

ብዙ ነገር እየከበደ እየመጣ ነው እሱን ሁላችሁም በየቤታችሁ አስተውላችሁታል ብለን እናምናለን። ስለዚህ ነገ እዚህ አለም ላይ ከፍ ብላችሁ ለመኖር ከፈለጋችሁ ዝቅ ብላችሁ እራሳችሁ ላይ ምትሰሩበት ሰዐት ላይ መሆናችሁን አስተውሉ

ማድረግ የምትችሉትን በሙሉ አድርጉ ከናንተ ምንም አይቅር የተረፈውን ለፈጣሪ ተዉለት

ከፊት ለሚጠብቃችሁ ፈተና ዝግጅት ያልጀመራችሁ ካሁኑ ጀምሩ በቂ ጊዜ አላችሁ አሁንም አልረፈደም!!


JOIN : @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️

13.4k 0 63 26 200

ዛሬ ለኢትዮጵያውያን የድል ቀን ነው!

አሜሪካም፣ አውሮጳም ድል ባለ ድግስ የነፃነት ቀናቸውን ያከብራሉ። የነፃነት እና የድል ቀን ይለያያል። ኢትዮጵያ የምታከብረው የድል በዓሏን ነው። የድል በዓልን ለማክበር መታደል ያስፈልጋል። መመረጥም ያስፈልጋል።

እንኳን ለ አድዋ የ ድል ቀን አደረሳችሁ።

ሀገራችንን ሰላም ያርግልን🙏


#Ads

የግቢ ተማሪዎች ናችሁ?

💻ዛሬ በጣም ሊጠቅማችሁ የሚችል ነገር ይዘንላችሁ መተናል

🪃እንደሚታወቀው የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ስትሆኑ ገንዘብ በጣም ያስፈልጋቿል::

💴እናም ግዜያቹን በማይጎዳ መልኩ የተለያዩ website ላይ ያሉ ፕሮጀችቶችን እየሰራችሁ ራሳችሁን በገንዘብ ምትችሉበትን መንገድ በነፃ አቅርበንላቿል::

እነዚህን ፕሮጀክቶች ለመስራት ሚያስፈልጋችሁ ነገሮች:-

📞Smart phone or Pc
🌐Internet

🏑እያንዳንዱን step እኛ guide ስለምናደርጋችሁ  በደምብ የሚሰራ ሰው በጣም ተጠቃሚ ይሆናል::

ተቀላቀሉን
👇

@web_projects10
@web_projects10


ውድ የመጀመርያ አመት እና የሬሜዲያል ተማሪዎች የዩንቨርስቲ ቆይታቹ እንዴት ነው ከ10?
So‘rovnoma
  •   9.9
  •   9
  •   8
  •   7
  •   6
  •   5
  •   ከ5 በታች
  •   1
1106 ta ovoz


ፍሬሽማን ተማሪዎች Final exam ተፈተናችሁ? ከየት ግቢ? ዘንድሮ በግብያቹ COC አለ?


የ Senior ተማሪዎች ምክር ጤና ለምትፈልጉ ተማሪዎች

➕ጤና የምትፈልጉ ማለትም Medicine, pharmacy, Anesthesia, Veterinary medicine, Dentist, Optometry እና አሁን ያልጠቀስኳቸውን የጤና Fieldoch መግባት የምትፈልጉ ልጆች 

በጤና ዠርፍ እየተማሩ ያሉ ልጆች እነርሱ ካሳለፋቸው ነገሮች አንፃር በይበልጥ በ 3 ነገሮች ትኩረት እንድታደርጉ ይመክሯቿል


1️⃣ኛ ውጤት መስቀል አለባቹ

#️⃣ውጤት በተለይ ደግሞ ጤና ለመግባት ፍላጎት ያላቹ ልጆች የ First semester ውጤታቹ አሪፍ ሊሆን ይገባል ብቻ ባጭሩ ጤናን ካለ ውጤት ማግኘት ይከብዳል አሁን ላይ ባለው ሁኔታ እንደውም ሁሉም ግቢዎች ከነርስ ጀምሮ እስከ Medicine ድረስ ከፍተኛ ውጤት ይጠይቃሉ ውጤቱም በትንሹ 3.2 በላይ ሊሆን ይችላል Medicine እና ሌሎች የሚፈለጉ ዲፖርትመንቶች ደግሞ የሚጠይቁት ውጤት 3.8 በላይ ሊሆን ይችላል ይሄ ግቢ ከገባቹ በኃላ የምትሰሩት ውጤት ብቻ ነው የ Entrance ውጤታቹ ብዙም ላይረዳቹ ይችላል ቢበዛ ከ 30% ቢይዙት ነው አንዳንድ ግቢዎች ደግሞ እንደውም ላይዙትም ይችላሉ ስለዚህ ጤናን የምትፈልጉ ልጆች ካሁኑ ውጤት መስራት እንዳለባቹ አውቃቹ ትኩረታቹን ትምህርታቹ ላይ ብቻ አድርጉ፤ ይሄን ስንል ደግሞ ተጨናነቁ ማለታችን እንዳልሆነ መቼም ትረዱናላቹ::

🥈ኛ በደንብ አስቡበት

#️⃣ለምን ጤና መግባት ፈለጋቹ ቤተሰብ ስላላቹ ነው ወይስ ጥሩ ገንዘብ አገኝበታለሁ ብላቹ ?? ይሄ ጉዳይ በደንብ ሊታሰብበት ይገባል ያው እንደምታውቁት ከሌሎቹ ፊልዶች አንፃር የጤና ፊልድ ጥረት የሚፈልጉና ብዙ ረዘም ያለ ጊዜ የሚውስዱ ስለሆኑ በግለትና በስሜት እንድትመርጧቸው አይመከርም ምክንያቱም በኃላ ላይ ፍላጎትና ጥረት ከሌላቹ ማማረራቹ አይቀርም ከባሰባቹ ደግሞ ትምህርቱን ጥሎ መውጣትም አለ::

🥉ኛ ማንንም አትስሙ
 
#️⃣አንዳንድ ለጤና ፍላጎት የሌላቸው እና ውጤት መስራት የማይችሉ ጀለሶቻቹ እነርሱ ጤና መግባት ስለማይችሉ ብቻ እናንተ የምትፈልጉትን ጤና የተለያዩ የወረዱ ሀሳቦችን እያነሱ ፍላጎታቹን ሊያጣጥሉባቹ ይችላል ስለዚህ be Wise 😎 አትስሟቸው።

ይቀጥላል ...

©️Race Tutorial

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


😀በነገራችን ላይ ዛሬ ልደቴ ነው! እስኪ መልካም ምኞታችሁን ግለፁልኝ😅


🎓 ፍሬሽማን ተማሪዎች ምን ዲፓርትመንት ለምግባት እያሰባቹ እና እያጠናችሁ ነዉ?
So‘rovnoma
  •   Medicine ➕
  •   Pharmacy, Anesthesia, Radiology
  •   Law ⚖️
  •   Engineering
  •   Other natural
  •   Other social
467 ta ovoz




Freshman exam dan repost
logical fallacies activities.doc
32.0Kb
Students Exercise Logic & Crit Thinking.pptx
169.1Kb
♻️EXERCISE ON INFORMAL FALLACY

❇️ ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎችን ባንድ ላይ የያዘች አጭር ፋይል ናት ተጠቀሙባት

🌐 Like👍 Share 📱📲

𝚓𝚘𝚒𝚗 𝚞𝚜 
@freshman_materials ⭐️
@freshman_materials ⭐️


Take a lesson⚠️
ይህ በወለጋ ዩንቨርስቲ ተማሪዎች ለመውጫ ፈተና ሲገቡ ስልክ ይዘው የተያዙ ናቸው።

ስልክ ለፈተና አትጠቀሙ እሺ😊

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

12.8k 0 75 24 221

#DebreMarkosUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 28 እና 29/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-H የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ የስማችሁ የመጀመሪያ ፊደል ከA-E የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በቡሬ ካምፓስ
➭ ሌሎቻችሁ የማኅበራዊ እና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ካምፓስ

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➭ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➭ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➭ አራት 3×4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➭ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና ትራስ ልብስ፡፡

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


#EthiopianDefenceUniversity

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፥ የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም ጀምሮ የተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ምርጫ ውስጥ እንደሚካተት አሳውቀዋል።

JOIN: @ADVANCED_FRESHMAN ⭐️

13.5k 0 30 18 104

#DebreBerhanUniversity

በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 6 እና 7/2017 ዓ.ም እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

https://tinyurl.com/dbu-rcp-2017 ሊንክ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ቁጥራችሁን በማስገባት የተመደባችሁበትን ግቢ ማወቅ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


ሪሚድያል ተማሪዎቻቸውን ጠርተው የተቀበሉ ዩኒቨርሲቲዎች

1. ጂጅጋ ዩንቨርስቲ (ታህሳስ 14 እና 15)
2. ወልድያ ዩንቨርሲቲ( ጥር  19 እና 20 )
3. ሚዛን ቲፒ ዩንቨርሲቲ (ህዳር 11 እና 12 )
4. ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ (ህዳር 26 እና 27)
5. አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 2 )
6. ዲላ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 14 እና 15)
7. ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 7 እና8 )
8. ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 7 እና 8)
9. ዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 21 እና 22)
10. ሀረማያ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 2,3 እና 4)
11. ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ (ጥር 5,6 እና 7)
12. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
13. ቦረና ዩኒቨርሲቲ (ታህሳስ 22 እና 23)
14. ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 3 እና 4)
15. አዲግራት ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
16. ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ  (ታህሳስ 20 እና 21)
17. ወሎ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 3 እና 4)
18. መቱ  ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 1 እና 2)
19. ራያ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 15 እና 16)
20. መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19 እና 20)
21. አክሱም ዩኒቨርስቲ (15 እና 16)
22. አሶሳ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 22  እና 23)
23. መቅደል አምባ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 13,14 እና 15)
24. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 14 )
25. አርሲ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19 እና 20)
26. ጂንካ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 13  እና 14)
27. ወለጋ ዩኒቨርሲቲ  (ጥር 19  እና 20)
28. ወራቤ ዩንቨርስቲ (ጥር 21 እና 22)

ሪሚዲያል ተማሪዎቻቸውን ጠርተው ግን ያልተቀበሉ ዩንቨርስቲዎች

1. ወልቂጤ ዩኒቨርስቲ (ጥር 26 እና 27)
2. ጋምቤላ ዩንቨርስቲ (ጥር 28 እና 29)
3. አምቦ ዩኒቨርስቲ (ጥር 29 እና 30)
4. ደብረ ታቦር ዩንቨርስቲ (ጥር 29 እና 30)
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 29 እና 30 )
6. መቀሌ ዩኒቨርሲቲ (ጥር 30 እና የካቲት 1)
7. ቦንጋ ዩንቨርስቲ ( የካቲት 1 እና 2)
8. ዴቢ ዶሎ ዩንቨርስቲ (የካቲት 3 እና 4)
9. እንጅባራ ዩንቨርስቲ (ጥር 26 እና 27)
10. ሰላሌ ዩንቨርስቲ (ጥር 28 እና 29)

#️⃣ ሪሜዲያል ተማሪዎቻቸውን እስከ አሁን ድረስ ያልጠሩ ዩኒቨርሲቲዎች

1. ደብረ ብርሃን ዩንቨርስቲ እና
2. ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ

JOIN:@ADVANCED_FRESHMAN⭐️


ስለ አንዳንድ ዲፓርትመንቶች ማብራሪያ የሰጠንበትን post ለማግኘት ከታች ያሉትን ሊንክ ተጠቀሙ

👾Architecture ⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1322

🖊 Management⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1329

💻 Software engineering⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1334

🔨 Law⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1350

💊Radiology⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1354

👨‍⚕️Medicine⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1361
https://t.me/Advanced_Freshman/1384
https://t.me/Advanced_Freshman/1392

💵Economics⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1367

🎙Journalism⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1370

💻Computer science⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1374

💰Accounting and finance⬇️
https://t.me/Advanced_Freshman/1377

ሁሌም ለላቀ ዉጤት

JOIN:
@ADVANCED_FRESHMAN⭐️

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.