Postlar filtri


19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ውድድር የተሳተፈው አማራ ፖሊስ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቀቀ።

መጋቢት 1/2017 ዓ.ም (አማራ ፖሊስ)፡-ከየካቲት 22 እስከ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው 19ኛው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ውድድር በአዲስ አበባ ስታዲየም የካቲት 30/2017 ዓ.ም በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ተጠናቋል፡፡

በ10 የስፖርት ውድድር ዓይነቶች የፌዴራል ፖሊስን ጨምሮ ሁለቱ ከተማ አስተዳደሮችና 12ቱ ክልል ፖሊስ ተቋማት መካከል ሲካሄድ በቆየው የስፖርት ውድድር የአማራ ፖሊስ በሶስት የስፖርት ዓይነቶች ማለትም የወንዶች እግርኳስ፣አትሌቲክስና ኢላማ ተኩስ በመሳተፍ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቋል።
አማራ ፖሊስም በኢላማ ተኩስ ውድድር ዋንጫ ያስመዘገበ ሲሆን በእግር ኳስ አራተኛ ደረጃ፤ በአትሌቲክስ ሶስት ወርቅ፣ ሁለት ብር፣3 ነሀስና 10 ዲፕሎማ በማምጣት ውድድሩን በአራተኝነት ማጠናቀቅ ችሏል፡፡
116ኛውን የፖሊስ ምስረታን አስመልክቶ የተዘጋጀው 19ኛው ውድድር ተተኪ ስፖርቶኞችን ከማፍራት ባሻገር የፖሊስ ሰራዊቱን ጓዳዊ ዝምድና ማጠናከሩ ተገልጿል።
ውድድሩ ከተቋረጠበት 2004 ዓ.ም 12 ዓመት በኋላ መሰናዳቱ መልካም ቢሆንም ከተጨዋች ተገቢነትና ዝግጅት አንፃር የነበሩ ክፍተቶችን በማረም በሚቀጥለው ዓመት በድሬደዋ ከተማ ለሚዘጋጀው ሀገር አቀፍ የፖሊስ ውድድር ከወዲሁ መዘጋጀት እንደሚገባ ተገልጿል።
በማጠቃለያ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ድሬዳዋ ፖሊስ ቀጣዩ የ20ኛ ሀገር አቀፍ የፖሊስ ሠራዊት ስፖርት ፌስቲቫል አዘጋጅ የተመረጠ ሲሆን የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ተረክቧል።


በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው ተባለ

በአዊ ብሔረሰብ ዞን ዳንግላ ወረዳ በአባድረ ቀበሌ በፅንፈኛ ቡድኑ ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃ ጠናክሮ እንደቀጠለ መሆኑ ተገልጿል።

መከላከያ ሰራዊቱ ባደረገው የተጠና ኦፕሬሽን በአካባቢው የሚገኘው ፅንፈኛ ቡድን ሙትና ቁስኛ የሆነ ሲሆን አብዛኛውም ለሰራዊቱ እጅ እንዲሰጥ ተደርጓል።

በተጨማሪም ቡድኑ ሲጠቀምበት የነበረ በርካታ የነፍስ ወከፍ መሣሪያ ለመከላከያ ሰራዊቱ ገቢ ተደርጓል ተብሏል።

መረጃው የዳንግላ ወረዳ ኮምኒኬሽን ነው።


በምስራቅ በለሳ ወረዳ በጫካ የነበሩ 16 ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመለሱ።

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በምስራቅ በለሳ ወረዳ በጫካ የነበሩ 16 ታጣቂዎች የመንግስትን የሰላም ጥሪ ተቀብለው ወደ ሰላማዊ ህይወት ተመልሰዋል።

ያሳለፍነው የእርስበርስ ጦርነት ተገቢ እንዳልሆነና ችግሮቻችንን ለመፍታት ውይይት ዋነኛ አማራጭ ሆኖ አግኝተነዋል ብለዋል።

በዚህም "የአማራን ህዝብ ጥያቄ በብጥብጥና በጦርነት ሳይሆን በሠላማዊና በዴሞክራሲያዊ አኳኋን ለመፍታት በቂ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ተናግረዋል።

በመሆኑም በቀጣይ ለሰላም ግንባታ ስራ ከመንግሥት ጎን ተሰልፈው የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የተፈጠረላቸውን ግንዛቤ በመጠቀም የተሳሳቱትን ወደ ሰላም እንዲመጡ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉም አክለዋል።

አሁን ላይ በወረዳው በሁሉም አካባቢዎች ህግ የማስከበር ስራዎች እየተሰሩ ሲሆን የሰላም አማራጮችን መርጠው ለሚመጡ በሩ ክፍት መሆኑን የወረዳው አስተዳደር መግለፁን የማዕከላዊ ጎንደር ዞን በኮሙኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል።


በሀገር አቀፍ የፖሊስ ውድድር 6ኛ ቀን ውሎ የአማራ ፖሊስ ስፖርት ቡድን በአትሌቲክስ ውጤት አስመዝግቧል።

በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ ዛሬ የካቲት 27/2017 ዓ/ም በተካሄደው የአትሌቲክስ ውድድር በ10,000 ሜትር ሴቶች ኮንስታብል አስማረች አንለይ የሻነህ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳልያ አስመዝግባለች።




በተሁለደሬ ወረዳ በመግደል ሙከራ ወንጀል ተከሶ በሌለበት የተፈረደበት በቁጥጥር ስር ውሏል።

የካቲት 27 ቀን 2017 ዓ.ም

በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ የመግደል ሙከራ ከተፈፀመ በኋላ በዋስ እንደተፈታ ከህግ ተሰውሮ በሌለበት የተፈረደበት በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ፖሊስ ገለፀ፡፡

ተከሳሹ ሁሴን ታደሰ ኢብራሒም ሊፈረድበት የቻለው ግንቦት 19 ቀን 2015 ዓ.ም በተሁለደሬ ወረዳ 017 ቀበሌ ልዩ ቦታው ሰግለን የተባለው ስፍራ በዕለታዊ ግጭት ተነሳስቶ ጎረቤቱን በያዘው ክላሽንኮቭ ጠመንጃ ተኩሶ ይስተዋል።
የወረዳው ፖሊስም በደረሰው ጥቆማ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ የምርመራ መዝገቡን በሰውና በቴክኒክ ማስረጃ ካጣራ በኋላ ለሚመከተው የፍትህ አካል ልኳል።
ግለሰቡም የክስ ሂደቱን ከስር ውጭ ሆኖ እንዲከታተል የተሰጠውን የዋስትና መብቱን ተጠቅሞ ከማረሚያ ቤት ከወጣ በኋላ ይሰውራል። የደቡብ ወሎ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ በሌለበት ጉዳዩን ሲመረምር ቆይቶ የካቲት 10 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሹ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ 7 ዓመት ፅኑ እስራት ይወስንበታል።
የወረዳው ፖሊስም ተከሳሽን ሲያፈላልግ ከቆዬ በኋላ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም በሐይቅ ከተማ ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት በቁጥጥር ስር አውሎ የእስር ጊዜውን እንዲፈፅም ለሐይቅ ማረሚያ ቤት አስክቧል።
መረጃው ፡- የደ/ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ፖሊስ ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ክፍል ነው።


በሰሜን ጎንደር ዞን ጃናሞራ ወረዳ ራሱን የደጃች ውቤ ሻለቃ ጃናሞራ ዙሪያ በሚል አደራጅቶ ህዝቡን ሲዘርፍና ሲያሰቃይ የነበረው የፅንፈኛ ቡድን አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

በጃናሞራ ወረዳ የዋሰል ንዑስ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት ኃላፊ ምክትል እንስፔክተር ዋካ አስማረ ከወረዳው የፖሊስና የሰላም አስከባሪ እንዲሁም ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመተባበር የወረዳውን ህዝብ ሲያሰቃይ እና ሲዘርፍ የነበረውን ፅንፈኛ ኃይል በቁጥጥር ስር ማዋል ተችሏል ብለዋል፡፡

ምክትል እንስፔክተሩ እንዳሉት ይህ ፅንፈኛ ቡድን በአዝማራው ኮረፍታው መሪነት ከተለያየ አካባቢ ኃይሉን በማሰባሰብ የአካባቢውን ሰላምና ፀጥታ በማደፍረስ ራሱን የደጃች ውቤ ሻለቃ ብሎ ቡድን በመሰየም ለህዝብ እናታገላለን እያለ ህዝቡን በማታለል ከመካነ ብርሃን ከተማ ወደ ዋሰል ሲሄድ የነበረን የህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ በማስቆም ያለአግባብ ብር በመቀል ህዝቡ እንዳይገለገል ችግር ሲፈጥሩ እንደነበር ለፖሊስ ጥቆማ መድረሱን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በመሆኑም የፀጥታ ኃይሉ ባደረገው ክትትል ከገንዝ ቀበሌ ከጥራይና እሉዋ ፅንፈኛ ቡድኑ በመቀሳቀስ ላይ እንዳለ የካቲት 25/2017 ዓ.ም የፅንፈኛ ቡድን መሪ ሲሰዋ ስድስቱ ከ2 ከላሽ ፣ 1 አብራራው ፣ 1 እስኬስ ፣ 1F1 እና 1 የጪስ ቦንብ ከ9 የክላሽ ተተኳሽ ጋር መማረክ ተችሏል፡፡
ምርኮኛ የፅንፈኛ ቡድን አባል እንደተናገሩት እኛ ወደዚህ አሳፋሪ ተግባር የተቀላቀልነው ባለሰብነው ስሜታዊ መንገድ እና በገንዘብ በመታለል ወደ ጫካ ገብተናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ በወረዳው በመሽሃ አጥገባና አካባቢው ከህዝብ ጋር በመመሳል እየኖሩ ነገር ግን በስውር ወይም አሳቻ ስዓትን በመጠቀም ህዝቡን ሳዘርፉና ሲሰቃዩ የነበሩ ሁለት የፖሊስና የፀጥታ አካል እንዲሁም ከማህበረሰቡ ጋር ባድረጉት ክትትል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉን የወረዳውን ፖሊስ ፅ/ቤት ዋቢ አድርጎ የጃናሞራ ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ዘግቧል፡፡


በሀገር አቀፍ የፖሊስ ውድድር እየተሳተፈ የሚገኘው የአማራ ፖሊስ ስፖርት ቡድን ውጤት አስመዝግቧል።

በአምስተኛ ቀን ውሎ ዛሬ ረፋድ 5:00 በአዲስአበባ ስታዲዬም በወንዶች እግርኳስ የመጨረሻው የምድብ ጨዋታ ከሀረር ፖሊስ ጋር ያደረገው የአማራ ፖሊስ 2ለ0 በማሸነፍ በስድስት ነጥብ ጥሎ ማለፍን ተቀላቅሏል።
ግቦችን በመጀመሪያው አጋማሽ ኮን/ል አማኑኤል አማረና ኮን/ል ማስረሻ ተስፋዬ አስቆጥረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በኢትዮጵያ ስፖርት አካዳሚ በተካሄደው የአትሌቲክስ ውድድር በ800 ሜትር በሁለቱም ፆታ፣ 10,000 ሜትር በወንዶች እና 1,500 ሜትር በሁለቱም ፆታ መርሀ ግብሮች ተሳትፎ ያደረገው የአማራ ፖሊስ አትሌቲክስ ቡድን በ10,000 ሜትር ወንዶች ኮን/ል ስማቸው ድሉ ሶስተኛ በመውጣት ነሀስ ሜዳልያ ያስመዘገበ ሲሆን ዋ/ሳጅን ድንቃለም አየለ 5ኛ ሆኖ አጠናቋል።
በ1,500 ሜትር ሴቶች ምክትል ሳጅን ሀብታም ገበየሁ 1ኛ በመውጣት ወርቅ ስታስመዘግብ ዋ/ሳ የኔነሽ ሽመክት በሁለተኝነት የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች። በ100 ሜትር ሴቶች የተወዳደረችው ም/ሳጅን ፋሲካ ዋለ 5ኛ ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቃለች።


የተሻለ ፖሊሳዊ ስነ ምግባር የተላበሱ ብቁ የፖሊስ አባላትን ለማፍራት በጋራ መስራት ይገባል ተባለ።

የካቲት 25/2017 ዓ.ም

በብርሸለቆ መሠረታዊ ዉትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ እያሰለጠነ ባለው የ33ኛ ዙር የመደበኛና አድማ መከላከል ምልምል ፖሊስ ሰልጣኞች ላይ አጠቃላይ ከሰው ሀይል ምልመላና መረጣ የስልጠና ሂደትና በቀጣይ በዉህደት ተግባራት ዙሪያ በተዘጋጀው የዳሰሳ ፅሑፍ መነሻ ውይይት ተደርጓል።

የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮማንደር አብይወት ሽፈራው እንዳሉት በእዉቀቱ፣ በአመለካከትና በክህሎቱ ጠንካራ የፖሊስ አመራርና አባላት በማፍራት ዙሪያ ወደፊት መደረግ ባለባቸው ተግባራት ጉዳይ በርካታ ጠቃሚ ሀሳቦች መነሳታቸውን ገልፀዋል። በቀጣይም ጥራት ያለው ትምህርትና ስልጠና ለመስጠት ትልቅ ተሞክሮ እንደሚሆን ኮማንደር አብይወት ገልፀዋል።

አስተያየታቸዉን የሰጡን የዉይይቱ ተሳታፊዎች የተነሱት ሀሳቦች ጠንካራ የፖሊስ ተቋም ለመገንባት በህዝብ ቅቡሉነት ያለዉና በስልጠና ሂደቱም ጠንካራ የአመራር ቁጥጥርና ድጋፍ መኖር ለሰልጠናው ከፍተኛ አሰተዋጽኦ አበርክቷል በተለይም ስልጠና ወሰደው ምደባ የሚደረግላቸው አባላት ከምድብ ቦታቸው ከደረሱ በኀላ ያለው አቀባበል እና ከነባር የሠው ሀይልና ማህበረሰቡ እንዲሁም አጋር አካላት ጋር ትውውቅ ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር ከተቻለ በተደራጀ ዕቅድ ከተመራ ውጤታማና የሚጠበቀውን ግብ ያሳካ ተግባር መስራትና የሚሠጣቸውን ግዳጅ መፈጸም የሚችል ሰራዊት ለመፍጠር የጎላ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ብለዋል።

ዘገባው ፦የአማራ ፖሊስ ኮሌጅ የህዝብ ግኑኝነት ክፍል ነው።

ከብርሸለቆ



10 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.