ላስ ፓልማስ ከ ባርሴሎና የተጫዋቾች ሬቲንግ!!ዎይዤክ ሼዝኒ 8.0🇵🇱
ይህ ፖላንዳዊ ግብ ጠባቂ ቋሚ ሆኖ መጫወት ከጀመረ ወዲህ ለክለባችን ጥሩ ገድ ነው ይዞ የመጣው። እሱ በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ክለባችን እስካሁን ምንም ሽንፈት ያልገጠመው ሲሆን 6 ክሊንሺቶችን ደሞ ጠብቆ መውጣት ችሏል። ዎይዤክ ካለፉት 5 ጨዋታዎች በ4ቱ ግቡን ሳያስደፍር ወጥቷል። በትላንትናው ጨዋታ ደሞ 100% ኳስ የማቀበል ስኬት ነበረው ይህም ቀስ በቀስ ከቡድኑ ጋር እየተላመደ እንደመጣ የሚያሳይ ነው።
ዡል ኩንዴ 7.1🇫🇷
ኩንዴ በትላንት ምሽቱ ጨዋታ ጥሩ የሚባል አቋምን በድጋሚ አሳይቶ መውጣት ችሏል።በመከላከሉ ረገድ በጣም ጥሩ የሚባል እና ትላንት ሜዳ ውስጥ ከነበሩት 4ቱ ተከላካዮች ውስጥ በእድሜ ትልቁ ልምድ ያካበተው ተጫዋች እንደመሆኑ መጠን በትላንትናው ጨዋታ የተከላካይ ክፍሉን ጥሩ አርጎ ሲመራ ነበር።
ኤሪክ ጋርሺያ 7.9🇪🇸
ኤሪክ 2025 ከገባ በኋላ እያሳየ ያለውን አቋም አለማድነቅ ከባድ ነው። በብላው ግራና ማልያ ምርጡን ጊዜ እያሳለፈ ነው የሚገኘው። በትላንትናው ምሽት ጨዋታም በኦሊምፒክ ላይ አብሮት ተጣምሮ ከነበረው ፓዉ ኩባርሲ ጋር የሚደንቅ መግባባት ነበራቸው። ኤሪክ በትላንትናው ጨዋታ 92% የማቀበል ስኬት የነበረው ሲሆን በጨዋታውም ድንቅ ነበር።
ፓዉ ኩባርሲ 8.1🇪🇸
ውድ የዚህ ቻነል ተከታታዮች እስቲ እራሳቹን ጠይቁ አሁን ላይ ዓለም ላይ ካሉ ተከላካዮች ሁሉ ማነው የ18 ዓመቱን የፓሱን ሊቅ ፓዉ ኩባርሲን ማስቀመጥ የሚችለው? ምን አይነት እርጋታ ነው በእውነት ይህ የ18 ዓመት ታዳጊ ያለው። ምንም ያህል ተጋጣሚዎች እሱን ጫና ውስጥ ለመክተት ቢሞክሩ እሱ ሁልጊዜ በሚገርም መረጋጋት ከእነሱ ፕሬሲንግ ወጥመድ ያመልጣል። ትላንትናም እንደ ሁልጊዜው ድንቅ ነበር።
#ይቀጥላል
@BARCAFANSETHIOPIA