Postlar filtri




Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


በየክፍሉ የነበረውን ጽሑፍና ችግር እዚህ ላይ ለማሳዬት የሚያሳፍር በመሆኑ ትተነዋል።




ጥር 30 ቀን 2017 ዓ.ም

ለት/ቤታችን ተማሪዎች በሙሉ


እንደምታውቁት በየመማሪያ ክፍላችሁ ያለው ግድግዳ የተቆፋፈረና የተላላጠ፣ የተጻፈው ጽሑፍ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ ይጽፈዋል ተብሎ የማይጠበቅ፣ ነውር የበዛበት ሲሆን አሁን ያላችሁትና ቀደም ሲል የተማሩበት ተማሪዎች በየጊዜው ጽሑፍ እየጨመራችሁበት ክፍሉ ለእናንተም ሆነ ለመምህራን ክብር የማይመጥን፣  ለመማር ማስተማር ምቹ ያልሆነና የሚያሳቅቅ ሆኖ ቆይቷል።

ይህ ሁኔታ እንዳይቀጥል ለማድረግ ሁሉም ክፍሎች ተጠግነው ቀለም እንዲቀቡ የተደረገ መሆኑን እያሳወቅን ከሁለተኛው ሴሚስተር ጀምሮ ሁሉም ተማሪ የክፍሉን ንጽሕና ጠብቆ መማር ያለበትና ለዚህም ከክፍሉ ንጽሕና ጀምሮ በምትማሩበት ክፍል ስላሉት የትምህርት ቁሳቁሶች በየክፍላችሁ ፈርማችሁ የምትረከቡና ጉድለትና ጥፋት ቢከሰት በግልም ሆነ በጋራ የምትጠየቁ መሆኑን እናስገነዝባለን። ከሁሉም በላይ ክፍላችሁንና የትምህርት ግብአታችሁን በንጽሕና እና በጥንቃቄ መያዝ የሚጠቅመው ራሳችሁን መሆኑን በመረዳት ራሳችሁን አክብራችሁ በመልካም ሥነ ምግባር እንድትጠብቁ እናሳውቃለን።

                                 ት/ቤቱ


ከዚህ በታች የተቀመጠው ሊንክ የእንግሊዘኛ ትምህርት አጋዥ ሰለሆነ ተማሪዎችና መምህራን እንዲጠቀሙ እንዲደረግ እናሳስባለን።

https://learn-english.moe.gov.et


Bulbula GSS Since 2000 E.C student dan repost
ጥር 26/2017ዓ.ም

በቡልቡላ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ባህልና ኪነ ጥበብ ክበብ አባል የሆናችሁ ተማሪዎች በሙሉ

በባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የተዘጋጀ የኪነ ጥበብ ውድድር እና የመዝናኛ መርኀ ግብር ስለተዘጋጀ ለውድድር የሚሆኑ የኪነ ጥበብ ስራዎች ያሏችሁ እና በተሳታፊነትም መገኘት የምትፈልጉ ነገ ማለት 27/05/2017ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00' (ሦስት ሰዓት) በት/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ።

መርኀ ግብሩ የሚከናወነው ነገ ከ 7:00' ወይም ሰባት ሰዓት ጀምሮ በኤር ጃቢ ሆቴል ስለሆነ ለቤተሰብ አሳውቃችሁ ፍቃድ ማግኘት ይኖርባችኋል።

ት/ቤቱ!!!

Amajjii 26/2017A.L.I

Barattoota Miseensa Gumii Aadaafi Aartii Mana Barumsaa Sadarkaa Lammaffaa Waliigalaa Bulbulaa taatan hundaaf

Sagantaan dorgommii aartii fi bashannanaa Waajjira Aadaa fi Tuurizimii qopheesse waan jiruuf, warri hojii aartii dorgommichaaf qabdaniifi hirmaachuu barbaaddan, guyyaa boruu, 27/05/2017 ganama sa'aatii 3:00 (sa'atii sadii)tti galma walga’ii mana barumsichaa keessatti akka argamtan isin hubachiifna.

Sagantaan kun boru sa'a 7:00 ykn sa'a torba irraa eegalee Hoteela Air Jabitti kan gaggeeffamu waan ta'eef maatii keessan beeksiftanii hayyama argachuu qabdu.

Mana Barumsaarraa!!!


የመ/ር ገብሩ ደበበ ቀብር የሚፈጸመው በትውልድ ቦታው (ጅማ) መሆኑን ስለሰማንና ቤተሰቦቹ አስከሬን ይዘው አሁን ጉዞ ስለጀመሩ በያዝነው ቀጠሮ መሠረት ወደ ቤቱ መሄድና መቅበር አለመቻላችንን በከፍተኛ ሀዘን እናሳውቃለን።😭




😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭

ጥር 25/2017 ዓ.ም

ለትምህርት ቤታችን ማኅበረሰብ በሙሉ፤

የትምህርት ቤታችን የአማርኛ ቋንቋ መምህር የሆኑት መ/ር ገብሩ ደበበ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
እኚህ አንጋፋና ሥራ ወዳድ መምህር  እስከ ቅርብ ሳምንታት ድረስ የማስተማር ኃላፊነታቸውን  በፍጹም ቅንነት እየተወጡ የቆዩ ሲሆን በቅርቡ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም ዛሬ ምሽት ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። በት/ቤታችን የእንግሊዝኛ መምህርት የሆኑት መ/ርት ፀሐይ ሙሉነህ ባለቤታቸው ናቸው።

እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማር!!

ባለቤታቸውን መ/ርት ፀሐይን፣ ልጆቻቸውን፣ ቤተሰቦቻቸውን፣ ሁሉንም የሥራ ባልደረቦችና ተማሪዎቻቸውን እግዚአብሔር ያጽናናልን!!

😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭😭


ጥር 25 ቀን 2017ዓ.ም

                       ማስታወሻ

                  ለተማሪዎች በሙሉ፤

የመጀመሪያው ሴሚስተር ማጠቃለያ የፈተና ወረቀት ለተማሪዎች የሚመለሰው ሰኞ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ.ም በጠዋቱ ፈረቃ ብቻ መሆኑን ቀደም ሲል ገልጸንላችኋል።

በዚሁ መሠረት ሁላችሁም ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያላችሁ ተማሪዎች ነገ በጠዋት በየመማሪያ ክፍላችሁ ተገኝታችሁ የፈተና ወረቀታችሁን ከመምህራን እንድትቀበሉ፤  የእርማት ወይም ሌሎች ችግሮች ካሉ በዕለቱ ብቻ እንድታስተካክሉ እና በሁሉም የትምህርት አይነቶች ያላችሁን የተሟላ ውጤታችሁን ማወቅ የሚገባችሁ መሆኑን እንገልጻለን።

ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ስትመጡ የተማሪ የደንብ ልብስ (Uniform) እና መታወቂያ አሟልቶ መምጣት ያስፈልጋል።

                                     ት/ቤቱ


2017 Grade 12 History Model Examinations.pdf
361.1Kb
CHEMISTRY G12 MODEL EXAM1 2017.pdf
292.8Kb
ECONOMICS MODEL EXAM1 2017.pdf
730.1Kb
G12 1st Model English 2017.pdf
738.3Kb
GEOGRAPHYGRADE 12 MODEL.pdf
194.9Kb
GRADE -12- BIOLOGY MODEL 2017.pdf
464.6Kb
MATHS G-12 FOR SOCIAL 2017R.pdf
507.4Kb
Maths Model for Grade 12 (NS) 2017.pdf
370.3Kb
Physics G12 MODEL -Exam 2017 .pdf
593.0Kb
SAT model exam1 2017.pdf
546.9Kb
🔥የ12ኛ ክፍል ሞዴል ፈተና

✅አዘጋጅ
👉አራዳ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት

⛔️መንፈቀ አመት
👉የመጀመሪያ መንፈቀ አመት 

⭐️የትምህርት አይነት
👉ሁሉም

⭐️አመት 👉2017

⭐️ክፍል 👉1️⃣2️⃣

🪟ለሌሎች ማጋራት አንርሳ‼️


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish


Dear Students, ''Push yourself, because no one else is going to do it for you; but, cheating in exam undermines the purpose of education''






Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish




ጥር 14/2017 ዓ.ም

ለሁሉም የትምህርት ቤታችን ዉድ ተማሪዎች በሙሉ

ጉዳዩ፡ ተማሪው ወደ ት/ቤት ግቢ ለመግባት መሟላት ያለባቸውን መስፈርቶች የማሳወቅ ይሆናል።

ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው ተማሪ ወደ ግቢ ለመግባት ከአንድ ተማሪ የሚጠበቀዉን መስፈርት ማሟላት እንዳለበት ይታወቃል።

በዚህ መሰረት በአሁኑ ወቅት ጥቂት ተማሪዎች ያለመታወቂያ እየገቡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል። ይህ የሆነበት ምክንያት ቀደም ባሉት ጊዜያት አንዳንድ ተማሪዎች የመታወቂያ ካርዶቸዉ ለመምህራን እና ለት/ቤቱ አስተዳደር የተሰጠ እንደ ሆኔ ሀሳብ ሲያቀርቡ ሰለነበረ ነዉ።

ስለሆነም ተማሪዎች ከነገ 15/05/2017ዓ.ም ጀምሮ እንደ ትምህርት ቤት የበር ክትትል በትምህርት ቤቱ ግቢ እና ክፍሎች ውስጥ ሰለሚደረግ:-

1. ማንኛውም ተማሪ ያለመታወቂያ ካርድ መግባት አይችሉም፣

2. ማንኛውም ተማሪ የቆየ ደረሰኝ ይዞ መግባት አይችሉም፣

3. ማንኛውም ተማሪ ፀጉሩን በህጋዊ መንገድ አስተካክሎ መግባት አለበት፣

4. ማንኛውም ተማሪ ፀጉሩን በተለያዩ ስልቶች (styles) ማስተካከል እንደማይቻል በሚገባ በመረዳት ፀጉሩን ማስተካከል መቻል አለበት፣

5. ማንኛውም ተማሪ ዘግይቶ ከመድረስ ነፃ መሆን አለበት፣

6. ማንኛውም ተማሪ ዩኒፎርም ለብሶ መገኘት አለበት፣

7.የሴት ተማሪዎች የወንድ ዩኒፎርም መልበስ የተከለከለ ነዉ፣

8. ማንኛውም ተማሪ ትምህርት ቤቱ ከሰጠው መታወቂያ ውጪ ሌላ ይዞ ወይም ሲያጨበርብር ከተገኘ ትምህርት ቤቱ እርምጃ እንደሚወስድ እናሳስባለን፣

በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት ቅድመ ሁኔታዎች ከፈተና ቀን በፊት መሟላት ስላለባቸው ከነገ 15/05/2017ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ተማሪዎች የትምህርት ቤቱን ህግ እና ደንብ እንዲያሟሉ ትምህርት ቤቱ በጥብቅ ያሳስባል።

ት/ቤቱ

Amajjii 14/05/2017A.L.I

Barattoota Mana Barumsaa Keenyaa Hundaaf

Dhimmi isaa: Dirqama barataan tokko gara mooraa Mana Barumsaatti ol seenuuf guutuu qabu isin beeksisuu taha.

Akkuma mata duree armaan oliitti eeramuuf yaalametti barataan tokko gara mooraa Mana Barumsaatti ol seenuuf wantoota akka barataa tokkootti nama barbaachisuu guutuun dirqama akka tahe ni beekama.

Bu'uuruma kanaan, yeroo ammaa barattootni muraasni waraqaa eeyyummaa malee ol galaa akka jirtan bira gahamee jira. Sababni kun taheefis yeroo darbe barattootni tokko tokko waraqaan eenyummaan keenyaa barsiisota yookaan bulchiinsa mana barumsaa sababeeffachaa turuun keessani ni beekama.

kanaafuu, barattootni guyyaa borii jechuun 15/05/2017 irraan eegalee akka mana barumsaatti hordoffiin balbala mooraa mana barumsaafi kutaa barnootaa keessatti gaggeeffama waan taheef:

1. Barataan kamiyyuu waraqaa eeyyummaa malee ol seenuu akka
hin dandeenye,

2. Barataan kamiyyuu nagahee guyyaan isaa expiry taheen galuun dhorkaa tahuu,

3. Barataan kamiyyuu rifeensa mataa isaa seeraan sirreeffachuun ol seenuu,

4. Barataan kamiyyuu rifeensa mataa isaa style adda addaan sirreeffachuun akka hin dandahamne sirriitti hubachuun of sirreessee dhufuu dandahuu,

5. Barataan kamiyyuu barfatee dhufuurraa bilisa tahuu,

6. Barataan kamiyyuu uffata seeraa mana barumsaa (uniform) sirnaan uffatee argamuu,

7. Barattootni shamarranii tokko tokko uffata seeraa mana barumsaa (uniform) kan dhiiraa uffatanii dhufuurraa of eeggachuu,

8. Barataan kamiyyuu waraqaa eenyummaa manni barumsaa kenneefiin ala waraqaa gosa adda addaa jijjiiranii fiduun yookaan gowwoomsuuf osoo yaaluu yoo argame manni barumsaa tarkaanfii akka fudhatu isin hubachiisuu,

Walumaagalatti, barataan kamiyyuu guyyaan qormaataa osoo hin gahiin dursa haaldureewwan guuttachuu qaban kanneen armaan oliitti eeraman waan taheef guyyaa borii jechuun 15/05/2017 irraan kaastanii barataan hunduu dirqama manni barumsaa isin irraa barbaadu guutuun akka dhuftan manni barumsaa cimsee isin beeksisa.

Mana Barumsaarra!!

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.