እዚህ ቻናል ላይ የሚለቀቁት ነገሮች የተለያዩ ሰዎች ጥቅሶችና ከመጽሐፍ ላይ የተቀነጨቡ ሃሳቦች ናቸው።ለምሳሌ ሶቅራጥስ፤ኒቼ፤አርተር ዋርከር፤አሌክስ አብርሃም፤ሀይለጊዮርጊስ ማሞ፤ምህረት ደበበ እና ሌሎች ደራሲያንና አሳቢያን የሚያስቡትንና የሚያውቁትን በተለያየ መንገድ ይናገራሉ።
እኛ በተናገሩት ንግግር ላይ አዎ ወይም አይደለም ብለን የየራሳችንን ሀሳብ ወይም መልስ መስጠት እንችላለን።ነገር ግን ማመንና አለማመን፤መቀበልና አለመቀበል፤እውነት ነውና ውሸት ነው ማለት የየራሳችን ምርጫና ውሳኔ መሆኑን ማወቅ አለብን።
እኛ ይሄን ሀሳብ ተቀበሉ ወይም እመኑ ብለን ምንም አይነት ፖስት አንፖስትም።ምክንያቱም ሁላችሁም በየራሳችሁ የመረዳት ልክ ነገሮችን መለየትና ማስቀመጥ ትችላላችሁ።ሌላው ሀሳብ ስሰጡም ራሳችሁን ችላችሁ መስጠት አለባችሁ።ምክንያቱም ለእናንተ ትክክል የሆነ ነገር ለሌላ ሰው ትክክል ላይሆን ይችላል።ስለዚህ ሁላችንም በየየራሳችን መንገድ ሃሳብ ብንሰጥ፤ጥያቄ ብንጠይቅ ወይም የምናስበውን ብንመልስ አሪፍ ነው ብዬ አስባለሁ።በተረፈ መልካም ጊዜ ይሁንላችሁ።
📚
@Bemnet_Library