‹‹ፍቅርና ወሲብ›› በObjectivism ፍልስፍና
=============================
© Yonas Tadesse Berhe
==================
በObjectivism ‹‹ፍቅር ያዘኝ›› ማለት ‹‹እኔ የራሴ እሴቶች አሉኝ፤ value system አለኝ፤ የምወደውና የማከብረው አለኝ›› ማለት ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ያሉት አእምሯችን ውስጥ ነው፡፡ የሰው ልጅ የሁለት ነገሮች ውህደት ነው ― የነፍስና የአካል፡፡ አየን ራንድ ‹‹ነፍስ›› የምትለው ‹‹የንቃተ ህሊና (Consciousness) የሆኑትን ነገሮች›› ነው፡፡
""""
የሰው ልጅ የራሱ የሆኑ እሴቶች (values) ላይ አንድ ፍላጎት አለው፡፡ ይሄውም፣ ልክ መስታወት አካላዊ ገፅታችንን እንደሚያሳየን ሁሉ፣ የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶችም (abstract values) አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን፡፡ ‹‹አካል መንሳት›› ማለት ከረቂቅነት ወደሚታይ አካላዊ ነገር እንዲቀየሩ መፈለግ ማለት ነው፡፡ ይሄም የሚገለፀው በሌላ ሰው ላይ ነው፡፡ በመሆኑም፣ ‹‹የያዝናቸው ረቂቅ እሴቶች አካል ነስተው ማየት እንፈልጋለን›› ሲባል ‹‹የእኛ እሴቶች በሌላ ሰው ውስጥ ማየት እንፈልጋለን›› ማለት ነው፡፡ ይሄም ማለት፣ ሌላ ሰው የኔን ዓይነት እሴቶች ተላብሶ ሳይ፣ የኔን ነፍስ እሱ ላይ አየዋለሁ፤ እናም በፍቅሩ እወድቃለሁ ማለት ነው፡፡ ይሄ ፍቅር ግን የግድ ፆታዊ ብቻ ሳይሆን ልባዊ ጓደኝነትንም ይጨምራል፡፡
"""""
እናም ያፈቀርኩት ሰው ‹‹የኔ የእሴቶች መስታወት›› ነው፤ በእሱ ውስጥ የእኔን እሴቶች አይበታለሁ፤ መስታወት ይሆነኛል፡፡ ነፍሴ እሱ ላይ መገለፅ ስትጀምር ማድነቅ እጀምራለሁ፡፡ የኔን ዓይነት ‹‹value system›› ሌላ ሰው ሲያደርገው ወይም ስታደርገው ስናይ ማድነቅ እንጀምራለን፡፡ ነገሩ የሚጀምረው በአድናቆት ነው፡፡ አየን ራንድ፣ ‹‹የዚህ አድናቆት የመጨረሻው ደረጃ ‹‹ፍቅር›› ይባላል›› (the highest form admiration is Love) ትላለች፡፡
""""
በObjectivism ፍልስፍና፣ ሰው የሚያፈቅረው በሌላ ሰው ውስጥ የሚገኘውን የራሱን እሴቶች ነው፡፡ ‹‹ባልና ሚስት ከአንድ ወንዝ ይቀዳል›› የሚባለው ዓይነት መሆኑ ነው፡፡ ባል የራሱን values በሚስቱ ውስጥ ያገኛል፤ ሚስቲቱም እንዲሁ፡፡ ይሄ ነገር objectivist ስለሆንክ ምናምን አይደለም፤ ሁሉም የሰው ልጅ experience የሚያደርገው ነገር ነው፡፡ ለምሳሌ፣ ሂትለር አያፈቅርም ማለት አይደለም፡፡ እሱም የራሱ values አሉት፡፡ ይሄም ማለት፣ ሂትለርም የራሱ ዓይነት values ያላትን ሴት ያፈቅራል ማለት ነው፡፡
"""""
በObjectivism ፍልስፍና፣ ፍቅር ስሌት ወይም calculation አይደለም፡፡ ‹‹አፍቃሪ እንድትሆን ወይም ሴቷ እንድታፈቅርህ እንዲህ አድርግ፣ እንዲህ ሁን…›› የሚባል ነገር የለም፡፡ በሰራኸው የነፍስህ ቅርጽ እንደዛ ዓይነት ቅርጽ ያለው ሌላ ሰው ነፍስ ታያለች፡፡ ፍቅር ስሌት አለመሆኑን ለማሳየት አየን ራንድ እንዲህ ትላለች ‹‹አንድ ወንድ አንዲትን ሴት በቀላሉ ዘለላ ፀጉሯን ወደ ኋላ ስትመልሰው አይቶ ነፍሷን ሊለየው ይችላል፡፡ ነፍስ ነፍስን ልታስተውል ትችላለች፡፡
"""""
በሌሎች ውስጥ ያለ የራስን እሴቶች በማድነቅ የሚጀመረው ይሄ ክስተት ወደ ፍቅር ያድግና በስተመጨረሻ በወሲብ Celebrate ይደረጋል፡፡ ‹‹Sex is the Celebration of this Love›› ትላለች አየን ራንድ፡፡ ትክክለኛው ወሲብ ይሄ ነው ትርጉሙ፡፡ አየን ራንድ እንዲህ ትላለች፣
‹‹ከአድናቆት ወደ ፍቅር ያደገውን ግንኙነት Celebrate ለማድረግ ፖስት ካርድ ልሰጥህ እችላለሁ፤ እሱ ግን አያረካኝም፡፡ የአንገት ሐብል ልገዛልህ እችላለሁ፤ እሱም አያረካኝም፡፡ የሚያረካውና የመጨረሻው ውዱ ስጦታዬ ርቃን የሆነውን አካሌን እሰጥሃለሁ፡፡ I am happy to give you this naked body in celebration of that administration and love.››