#ለፓስተር_ጻድቁ_የመኪና_ስጦታ_ተሰጣቸው...
ዛሬ 10/5/2017 ለፓስተር ጻድቁ ላለፉት 7 ወራት መኪና ለመግዛት የተቋቋመው ኮሚቴ ዛሬ መኪናውን ለፓስተር አስረክቧል። በሁለት ወር ለመስረከብ የተዋዋለው ሰው በውሉ መስረት ማስረከብ አለመቻሉ ና ኮሚቴውን ያጋጠመው ችግር እንድፈታ የተለያዩ አካላት ባደረጉት ተሳትፎ መፍትሔ አግኝቶ መኪናውን ተቀብለናል።
መኪናው ለማበርከት ሐዋሪያው ቶማስ ምትኩ፣ የኢትዮጵያ የወንጌል አማኞች አብያተክርስቲያናት ካውንስል የጽህፈት ቤት ሐላፊ ፓስተር ጌትነት ለማ፣ የኢትዮጵያ ሙሉ ወንጌል ቤተክርስቲያን ምክትል ፕሬዚዳንት ፓስተር ለውየው፣ የአዲስ አበባ የሐይማኖት ተቋማት ዋና ጸሐፊ ፓስተር ታምራት፣ ኮሚቴውን ያስተባበሩት ፓስተር ግዛቸው ለታና፣ ዘሪሁን ግርማ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በቦታው ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተክርስቲያናት ህብረት ፕሬዚዳንት ፓስተር ጻድቁ አብዶ በበኩላቸው በዚህ ኮሚቴ ውስጥ በዋናነት የነበሩት፣ ፓስተር ግዛቸው ለታን፣ ሐዋሪያው ቶማስ ምትኩን፣ ሐዋሪያው ጆን ግርማና፣ ዘሪሁን ግርማን ያመሰገኑ ሲሆን፣ በተጨማሪም በገንዘባቸውና በተለያየ መንገድ ያገዙትን፣ ድጋፍ ያደረጉ የህግ አካላትም በሙሉ ባርከዋል። ስለ ሁሉም እግዚአብሔር ይመስገን።
ዘገባው የክርስቲያን TUBE የ Facebook ገፅ ነው!
@CHRIST_TUBE@CHRIST_TUBE