Postlar filtri


































🌿#የህይወት_ፍልስፍና (#Life_Philosophy)

የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ጀምሮ ኑሮን ለመምራት በሚያደርግበት ግዜ የተለያዩ መሰናክሎች ወይም አንቅፋቶች ያጋጥሙታል። ቁልፉ ግን የህይወትን አላማ ግብ መረዳት ነው። ባጋጠሙት እንቅፋቶች ምክንያት የህይወቱን አላማ ከዳር ሳያደርስ በመንገድ ላይ ሊገታ ይችላል። ስለዚህ ለስኬቱ መዳረስ የሚያራምደው የህይወት አመለካከት ወይም ፍልስፍና ቁልፍ ሚና ይጫወታል። አንዳንዴ ግን የህይወትን ፍልስፍና መያዙ ብቻ በቂ አይደለም። ፍልስፍናውን መከተልና መሆን(ዋነኛው የህይወቱ አካል አድርጎ መኖር) በጣም የተለያዩ ነገሮች ናቸው።

የህይወታችንን ግብ ከዳር አንዲደርስ ሁለት ግዙፍ የህይወት አመለካከት ግንባሮች አሉ (የሁለቱም ፍልስፍና አራማጆች በየግላቸው ትክክል ነው ብለው ያምናሉ ለምሳሌ ሁለት የእግር ካስ ቡድ አሉ። ሁለቱም ለማሸነፍ ወደ ሜዳ ይገባሉ። ሁለቱም የአጨዋወት ስልት አላቸው። አንዱ የያዘው ስልት ለራሱ ትክክል ነው ለተጋጣሚው ግን ስህተት ነው ሌላውም በተመሳሳይ):-

1) ፕሮታጎኒስት (Protagonist):- የፕሮታጎኒስት አቀንቃኞች የሰው ልጅ እያንዳንዱን ቀን በታላቅ ትጋት መስራት አለባቸው ፣ በቻሉት መጠን ከራሳቸው አልፈው ለሌላው የሚፈይድ አንዳች መልካም ወይም ቀና የሆነ ተግባር መፈፀም አለባቸው። በህይወት ለሚያጋጥማቸው አያንዳንዱ መልካም ሆነ አሳዛኝ ገጠመኝ ሳይበገሩ ወደ ፊት መቀጠል አለባቸው ምክንያቱም ሁሉም የሰው ልጅ በምድር ላይ የተፈጠረበት ትልቁ ምክንያት በህይወት ዘመኑ መልካም ነገር ለመስራት አንጂ ኖሮ ኖሮ ለመሞት በቻ አይደለም ብለው ያምናሉ።

፨ የፕሮታጎኒስቶችን ፍልስፍና ጠቅለል ስናደርገው:-

• የሰው ልጅ የተፈጠረው ለስራና ለስራ በቻ ነው ፣
• ሁሌም ቢሆን መልካም ነገር መስራት ይኖርብናል ፣
• ተስፋ መቁረጥ በምንም ተዓምር የለበትም ፣
• ዛሬን ሳይሆን ነገን ነው መኖር የሚገባን ፣
• ሁሌም ወደ ኋላ ሳይሆን ወደ ፊት ይሉናል።

2) አንታጎኒስት (Antagonist):- አንታጎኒስቶች ያላቸው የህይወት ፍልስፍና የሰው ልጅ ሞትን ማሸነፍ ካልቻለ አልያም የሰው ልጅ መጨረሻው ሞት ከሆነ ህይወት ነገ ሳትሆን ዛሬ በቻ ናት። ስለዚህ የሰው ልጅ መኖር ያለበተደ ዛሬን ብቻ ባሻው መንገድ መሆን አለበት። ስራ ፣ አላማ ፣ ፅናት ፣ ግብ ፣ ራዕይ ... ወዘተ የሚባል ኮተት ሁሉ ከንቱ ስንቅ ነው። አጅግ መናጢ የሆነው ግለሰብና የናጠጠው ሀብታምም መጨረሻው ሞት ነው። ጠ/ሚኒስትሩው ፣ ኩሊው ፣ የተማረው ፣ ያልተማረው ፣ ስኬታማው ፣ ስኬት አልባው ... ሁሉም ይሞታሉ። ታዲያ ሞት የማይቀርል ዕዳ ከሆነ ምን አስለፋን ፣ አስደከመን ...? ሞት የማይቀር ከሆነ የሰው ልጅ ነገን እያሰበ ሳይሆን ዛሬን ብቻ መኖር አለበት ምክንያቱም የሰው ልጅ ምንም ይሁን ምንም መጨረሻው ሞት ነውና የሚል አመለካከት ያራምዳሉ።

፨ የአንታጎኒስቶችን ፍልስፍና ጠቅለል ሲደረግ:-

• የሰው ልጅ ይሞታል ፣
• ዛሬን ብቻ ነው መኖር ያለብን ፣
• የተፈጠርነው ለደስታ በቻ ነው ፣
• ሁሉም ነገር የተፃፈልን ስለሆነ መለወጥ አይቻለንም።

ስለ ህይወት ፍልስፍና አንዳንድ ጥሬ ሀቆች

#በምድር ላይ ካሉት በቢልዬን የሚቆጠር ህዝብ መካከል ሶስት አራተኛው ወይም 75% የአንታጎኒስት አመለካከትን አስበውበት ይሁን ሳያስቡበት ያራምዳሉ። አንድ አራተኛው ወይም 25% የፕሮታጎኒስት አመለካከት ተከታዮች ናቸው።
አኛስ ከየትኞቹ ወገን ነን ...? ሀሳብና ድርጊት በጣም የተለያዩ ጥሬ ሀቆች ናቸው። አንዳንዴ በሀሳብ ደረጃ ተቀብለን በድርጊት ካልገለፅነው ትርጉም የለሽ ይሆናል። ስለዚህ ስንቶቻችን ነን ሀሳብና ድርጊት ሆድና ጀርባ መሆናቸው ቀርቶ መርፌና ክር የሆኑልን?

#ምንጭ:- "ኦያያ ፣ 2000 ከፓሪስ መልስ" *በአዘርግ


◉ Join us share◉●••






🌿#ችግሮችን_እንደ_ካርታ_ጨዋታ

ትክክለኛ አስተሳሰብ ያለው ሰው ችግር አያስጨንቀውም፡፡ ምክንያቱም በቀላሉ መፍትሄ ከመሻቱም በዘለለ ለሕይወቱ ጣዕም ይጨምርለታል፡፡ ካርታ በምትጫወትበት ወቅት የማይረቡ ካርታዎች ቢደርሱህ እድል ከእኔ ጋር አይደለችም ብለህ በራስህ ማዘን አትጀምርም፡፡

አዎ አታስብም!

እንደ ፈተና አይተኸው ካርታዎቹን በሚገባቸው ቦታ እየሰካካህ ለማሸነፍ ትጥራለህ፡፡ ስታሸንፍ ከፍተኛ ደስታ ይሰማሃል፡፡ችግሮችን በድል ትወጣ ዘንድ የዚህ ዓይነት ብሩህ አመለካከት ይኑርህ፡፡

ለራስህም ይህን በል፦

"ከራሴም ይሁን ከዓለም ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ፡፡ የሚያጋጥሙኝ ችግሮች ያለኝን እውቀትና ኃይል ስለሚፈትኑት መጥፎ አይደሉም፡፡ በተገቢው ጊዜ ተገቢ ነገር ለመስራት እንቀሳቀሳለሁ፡፡"

አዎ ይህንንም አሁኑኑ ማድረግ ትችላለህ!

#አሁኑኑ_አደርገዋለሁ መጽሐፍ

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.