ሐኪሞች የአሳማ ኩላሊትን በመውሰድ ለአንድ ግለሰብ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ አከናወኑ
********************************
በማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል የሚገኝ የሐኪሞች ቡድን ፤ በላቦራቶሪ የዘረመል ማስተካከያ የተደረገለት የአሳማ ኩላሊትን በመጠቀም ቲም አንድሪውስ ለተባለ ግለሰብ የተሳካ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረጉ ተነግሯል።
ለ66 ዓመቱ ቲም አንድሪውስ የኩላሊት ንቅለ ተከላ ማድረግ የሕይወት እና የሞት ጉዳይ ነበር። እናም በሐኪሞቹ የቀረበለትን የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላ ጥያቄ ለመቀበል አላመነታም።
ምክንያቱም አንድሪውስ መጨረሻ ደረጃ በደረሰው የኩላሊት በሽታ ምክንያት ለሁለት ዓመታት ያህል በዳያሊሲስ ላይ ቆይቷል።
አዲስ ኩላሊት ለማግኘት ስሙ በመጠባበቂያ ዝርዝር ውስጥ ቢሰፍርም ፤ የደም ዓይነቱ ለጋሽ አካል ለማግኘት አስቸጋሪ አድርጎበት ቆይቷል።
አንድ ኩላሊት ለመተካት በአማካይ ከሦስት እስከ አምስት ዓመታት ይወስዳል ፤ ነገር ግን ጥናቶች እንደሚያሳዩት የደም ዓይነታቸው “O” የሆኑ ሰዎች ኩላሊት ለማግኘት እስከ 10 ዓመታት ሊጠብቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያመላክታሉ።
https://web.facebook.com/EBCzena/posts/pfbid0vL7y2isbJsxp12RRKjhY5mVCfaN2x97EGCxvBvWH1qq4x7jGMqEfSn2fASBWedwrl?cft[0]=AZWxEzqrEzBABEvRz6URRqztKF6GU2Fs6rviXF-rI-DRdI7qLygxWLwTqkt2-zU-RwW8xC2IIyTzuoWXi2-tayqeDeQob-CQv7rIu9udNDm2w3BARKOUdJ0OzP7pZrapUqv-uAwcqMIhTsQMx0i-O-nNVvYj644dG7T6QQY5XZgTPeY2jKHPpi8AYeOouWQm724&
tn=%2CO%2CP-R