Ethiopian Educational Channel


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Inglizcha
Toifa: Ta’lim


እንኳን ደና መጣችሁ
Channel created by @BA1227
በዚህ ቻናል ላይ የሚያገኙት
1. ትምህርታዊ መረጃ መስጠት
2.የሳይኮሎጂ አስተማሪ ምክሮችንና አነቃቂ ንግግሮች
3.መፃህፍቶች በpdf እና የእንግሊዝኛ ንግግር ይለቀቃሉ!!!
በዚህ ቻናል ሀይማኖታዊ እና ፓለቲካ ነክ አይለቀቅበትም !
የቴሌግራሙ ቻናል ሊንክ:👉https://t.me/EEC1227

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Inglizcha
Statistika
Postlar filtri


ከልብ ሞልቶ የፈሰሰው ነው ከአፍ የሚወጣው።
ለቀልድም ቢሆን አንደበትክን ለክፉ ቃል አታሰልጥነው
የሰው ልጅ የሚመዘነው በንግግሩ ነው


ዛሬ Class እንዴት ነበር?


To be #happy in life:

1. Never hate
2. Stop over thinking
3. Live simple
4. Little expectation
5. Always smile
6. Be positive
7. Keep in touch with God.


ደጋግሞ ወድቆ፤ ደጋግሞ ሳይነሳ.....
ከፍ ብሎ የሚበር የለም!!
🎯አውሮኘላን ከመብረሩ በፊት መሬት ላይ ይደፋደፋል። ሯጭ ከውድድሩ በፊት ብዙ ልምምድ እና ጥረት ያደርጋል።

የዛሬ መውደቅና መነሳት ለነገ ስኬት ነውና ሁሌም ቢሆን ጥረት ማድረግ አታቁሙ!!

ውድ ተማሪዎች፦
የላችሁበት ጊዜና እድሜ በጣም ውድ ነው። ስለዚህ በዚህ ወድ ጊዜያችሁና እድሜያችሁ በጥሩ አስተሳሰብ በመጀመሪያ ራሳችሁን፣ ከዚያም ቤተሰብን እና ሀገርን ለመጥቀም ጠንክሮ በማንበብና በመማር ያስፈልጋል።
🎯እናም ተማሪዎች ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ጠንክሮ በማንበብ አላማችሁን አሳኩ!

⭕️ 🎤 ለተማሪዎች (ለእህት ወንድሞቼ) የተላለፈ መልዕክት!!

Join our channel
👇👇👇👇👇👇 👇👇
👉
t.me/EEC1227


Natural or Social ናቹ?


የንስር አሞራ አስገራሚ ባህሪ እና አንተ አንቺ   እና እኔ

🎯ስለ ንስር አሞራ ስነግርህ ከሚገርም መሳጭ ታሪክ ጋር ነው ... እውነት እውነት እልሃለሁ የንስር አሞራ ታሪክ በሁላችንም ህይወት ውስጥ አለና ከራስህ ጋር እያዛመድክ ካነበብከው መጨረሻህን ድል ድል ታሸተዋለህና በፍቅር ተከተለኝ።

ልጀምርልህ

🎯ንስር አሞራ ፀሐይን ቀጥ ብሎ ማየት የሚችል ወደ ጸሐይ አቅጣጫ ጨረሩን እያየ መብረር የሚችል ብቸኛው የአለማችን ፍጥረት ነው ። አንድ ንስር በመብረር ላይ እያለ ቁራወች ጭልፊቶች 100 ወይም 200 ሁነው ከበው ሲጮሁበት ወደጸሐይ እያየ ከፍ ብሎ ይበራል ሌሎቹ ፍጥረቶች ወደ ጸሐይ እያዩ መብረር ስለማይችሉ ይጠፋቸዋል!!

🎯ንስር ከሰው አይን 8 እጥፍ የተሻለ ማየት ይችላል ፣

🎯 ንስር ከ5-7 ኪሜ ያለን ለማደን የሚፈልገውን ነገር በደንብ ለይቶ ማየት ይችላል፣

🎯 ንስር ለአደን እስከ 120 km አካሎ ይበራል፣

🎯 ንስር መመጠለያ ከሌለበት አካባቢ ሁኖ ሃይለኛ ዝናብ ቢመጣ ወደላይ በምጠቅ ከደመና በላይ በሮ ዝናብና ወጀቡን ከስር ያደርጋል እንጂ በዝናብ አይቀጠቀጥም፣

🎯ንስር አድኖ እንጂ ጭራሽ የሞተ አይበላም፣

🎯ንስር ሲታመም ጸሐይን አተኩሮ በማየት ነው ህክምና የሚያገኘው፣

🎯 ንስር 340° ማየት ይችላል። ሰው 180° አካባቢ ነው ማየት የሚችለው፣

🎯ንስር አሞራ እስከ 70 አመት የሚኖር የእድሜ ባለፀጋ ነው ካልክ ልክ ነህ ... ግና 70 አመት ሙሉ በደስታ ከመኖሩ በፊት በእድሜው አጋማሽ ማለትም በ35 - 40 ባለው እድሜው ላይ ከባድ ነገር ይገጥመዋል ...

👉የመጀመሪያው :- ምግቡን ለማደን የሚገለገልበት ጥፍሮቹ ከመጠን በላይ ስለሚያድጉ ምግቡን ከመሬት ላይ ማንሳት ያቅተዋል ...

👉ሁለተኛው :- አጥንትን ሳይቀር መስበር አቅም ያለው አፉ(መንቁሩ) ስለሚታጠፍና ስለሚጣመም ምግቡን እንደወትሮው መመገብ ይሳነዋል ...

👉ሶስተኛው:- ክንፉና በአካሉ ላይ ያሉ ላባዎች ስለሚከብዱት ያ ሰማየ ሰማያትን እየሰነጠቀ ይበር የነበረው ሀይሉ ይክደዋል።

👉እነዚህ ሶስት ከባድ ነገሮች ንስር አሞራ በእድሜው አጋማሽ የሚያጋጥሙት ከባድ ችግሮች ናቸው። አሁን ንስር አሞራ ያለው ምርጫ ሁለት ነው።

👉1ኛ. ካረጀ አካሉ ጋር ዝም ብሎ በመቀመጥ ሞቱን መጠበቅ ?

👉2ኛ. አምስት ወር የሚፈጅ ስቃይና መከራ ያለበት መስዋዕትነትን ከፍሎ ቀሪውን 35 አመት በደስታ ማሳለፍ ?

🖐የመጀመሪያውን ከመረጠ በእድሜው አጋማሽ ይሞታልና ታሪኩ እዛ ጋር ያበቃል። ሁለተኛውን ምርጫ ከመረጠ ግን እነዚህን አምስት መስዋዕትነቶች ማለፍ ይኖርበታል።

👉፩ኛ. ከፍተኛ ተራራ ላይ በመውጣት የብቻውን ጎጆ ይቀልሳል።

👉፪ኛ. ጎጆ ከቀለሰ በኋላ የመጀመርያ ስራዉ የአፉን መንቁር ከአለት ጋር በማጋጨት ነቅሎ ይጥላል።

👉፫ኛ. ይህን ካደረገ በኋላ አዲስ መንቁር ይወጣለታል፡፡ መንቁሩ እስኪያድግ ድረስ ታግሶ በጎጆው ምንም አይነት ምግብ ሳይመገብ መቆየት ግዴታው ይሆናል፡፡

👉፬ኛ. አዲስ መንቁር ከበቀለለት በኋላ በአዲሱ መንቁሩ የገዛ እግሩን አሮጌ ጥፍር ነቃቅሎ ይጥለዋል።

👉፭ኛ. አዲሱ የእግር ጥፍር ከበቀለለት በኋላ ደግሞ ይህንን አዲስ ጥፍር እንደ መሳርያ በመጠቀም በሰዉነቱ የተጣበቁትን እንዳይበር እንቅፋት የሆኑትን የገዘፉና ያረጁ ላባዎችን ነቃቅሎ ይጥላል። በምትኩ አዲስ ላባ ያበቅላል።

👉ይህን 5 ወር በዚህ መልኩ በጀግንነት ከተወጣ በኋላ እንደገና ራሱን በራሱ ወልዶና ወጣት ሆኖ ወደ ንስሮች መንደር ብቅ ይላል፡፡

ወዳጄ ሆይ:-

ችግር ገጠመኝ ብለህ ያዙኝ ልቀቁኝ አትበል ፣ ችግሬ ... ችግሬ ... እያልክም ነጠላ ዜማ አትልቀቅ ፣ ፊትህንም ችግር ፊት አታስመስል ፣ ጥቅም ላይ እያፈጠጠ የሚከተል ሰው በበዛበት አለም ላይ መውደቅህን መጥሪያ ካርድ አታሰራበት ፣ መራብ መጠማትህን ፖስት ለማድረግ አትቸኩል ፣ መገፋትህን እንደ ትልቅ ነገር ቆጥረህ ኡኡኡ አትበል ፣ ስንት ነገር መስራት የምትችልበትን አዕምሮ ለሃሜትና "አሉ ... አለች" መሳሪያ በመጠቀም "የውሸት እየኖርክ - የእውነት አትሙት" ...በቃ! ... ልክ እንደ ንስር አሞራ በህይወትህ አጋማሽ ላይ ምርጫ መቶልሃል ...

፩ኛ. ችግሩን ታቅፎ መሞት ...

፪ኛ. ለችግሩ መስዋትነት ከፍሎ ማለፍ ...

አስተውል

👉ሁለተኛውን ከመረጥክ ልክ እንደ ንስሩ አምስት ዋጋዎችን መክፈል አለብህና ዝግጁ ሁን ...

👉፩ኛ. ራስህን ከመጥፎ ነገሮች አርቀህ በፅሞና ሃሳብህን መግራት ጀምር ...ንስር አሞራው ከፍተኛ ተራራ ላይ የሚወጣው ከሁሉም ንስሮች እርቆ ለህይወቱ ዋጋ ለመክፈል ነው ... ይህን አይነት መላ ምሁራኑ "የስኬት ሱባኤ" ይሉታል።

👉፪ኛ. አንገብጋቢ ችግርህን ለመፍታት ቁርጥ ያለ አቋም ይዘህ እስከ ሞት የሚያደርስ መስዋትነት መክፈል። ንስሩ አፉ ላይ ያለውን ምግብ ማምጫ መንቁሩን እንደሚያስወግደው ሁሉ።

👉፫ኛ. መስዋት የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትዕግስት መጠበቅ ... ይህ ደግሞ ንስሩ መንቁሩ እስኪያድግለት ድረስ ምግብ ሳይበላ እንደሚኖረው ሁሉ አንተም ዋጋ የከፈልክለት ነገር እስኪመጣ በትእግስት እና እምነት መጠበቅ።

👉፬ኛ. በትእግስት ጠብቀህ ያሰብከው ነገር ከመጣ በዋላ ህይወትህን ጠፍንገው የያዙህን ነገሮች መፍታት ... ልክ ንስሩ መንቁሩ እንዳደገለት የእግሩን ጥፍሮች በመንቁሩ እየወጋ እንደሚያስወግዳቸው ሁሉ።

👉፭ኛ. ሁሉን ካሳካህ በዋላ ወደ ህልምህ መብረር ... ይህ ማለት ንስሩ የእግሮቹን ጥፍር አስወግዶ እና አሮጌ ክንፎቹን አስወግዶ ከጠበቀ በኋላ አዲስ ክንፍ ፣ አዲስ መንቁር እና አዲስ ጥፍር ካበቀለ በዋላ እንደ አዲስ ጉልበታም ንስር ቀሪ ዘመኑን ይኖራል።

📷ሲጠቃለል ...

🎯አንተም ፣ አንቺም ፣ እኔም በዚህ ሁሉ መንገድ አልፈን ከባዱን ጊዜ ካለፍን በኋላ በአዲስ የህይወት መንቁር ፣ የተስፋ ጥፍር እና የስኬት ክንፍ ከፍ ብለን እንበር ዘንድ ..... ኑ ንስር አሞራን እንምሰል።

ለዚህ ነው ንስር የጥንካሬ የአይበገሬነት እና የከፍታ የመታደስ የአትኩሮት የሐያልነት ምልክት የሆነ ልዩ ፍጡር በመሆኑ በርካታ ሐገሮች ንስርን ምልክታቸው በማድረግ የሚጠቀሙት!!


ቻናላችን ይህ ነው
👇👇👇👇👇👇
https://t.me/eec1227


የአ/አ ት/ት ቢሮ የሬዲዮ ትምህርት ለማግኘት ከስር ያለው ሊንክ ይጠቀሙ!!!!
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/FM94_7






English proverbs


English proverbs


👉የብርጭቆ ውኃው ነገር

ሶስት አመለካከቶች አሉ፡- 

👉1. ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ሙሉ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚያመሰግኑ፡፡

የሞላው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናመሰግንና ለዚያ ነገር መዋጮ ያደረጉትን ሰዎች እውቅና ስንሰጥ ብሩህና የጠራ ምልከታ ስለሚኖረን የጎደለውን የመሙላት አቅም እናገኛን፡፡

👉2.  ግማሽ ድረስ ውኃ ያለበትን ብርጭቆ በማየት ግማሽ ጎዶሎ መሆኑ ላይ በማተኮር የሚነጫነጩ፡፡

የጎደለው ነገራችን ላይ በማተኮር ፈጣሪን ስናማርርና ለዚያ እንደዳረጉን ያሰብናቸውን ሰዎች ስንወቅስ ያለንን ጋማሹን እንኳን መጠቀም እስከማንችል ድረስ ጨለምተኞች እንሆናለን፡፡ 

👉3  ሙሉ ውኃ ያለው ብርጭ ቢያዩም እንኳን ድንገት አንድ ሰው ይደፋዋል ብለው የሚጨናነቁ፡፡

ሁሉ ነገር ሞልቶልን እንኳን ገና ለገና ይሆንብናል እና ይደርስብናል ብለን ስለምናስባቸው ነገሮች የመጨናነቅ ልማድ ካለን አንዱንም ነገር ሳናጣጥመው እንደፈራንና እንደሰጋን ዘመናችንን እናቃጥላለን፡፡

ዋናው ቁም ነገር ያለንና የሌለን ነገር ሳይሆን ባለንም ሆነ በሌለን ነገር ላይ ያለን አመለካከት መሆኑን አትዘንጉ፡፡

ብሩህ ቀን ተመኘሁ!
https://t.me/eec1227




(E-Library )Eshet Pre-Primary and Primary school dan repost
PREPOSITIONS OF TIME & PLACE




ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል



የዛሬዋ ቀን ሳታልፍ አንድ ነገር ላሳስብ፡- በዚህ አመት የምትሄድበትን አቅጣጫ ወይም ግብህን ጠንቅቀህ ካላወክ በፊትህ ያለው ሁሉም መንገድ ይወስድሃል፡፡

“ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” – Brian Tracy

አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣ “ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡ መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው” በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣ “መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡

ብዙ ሰዎች በደመ-ነፍስ ነው የሚኖሩት፡፡ ከየት ተነስተው ወደ የት መሄድ እንዳለባቸው በቅጡ አያውቁትም፡፡ ወደ የት እንደሚሄዱ ማወቅ በሕይወት ላይ ያለውን ተጽእኖ በፍጹም አስበውት አያውቁም፡፡

የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ! ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው የመጣውን ያስተናግዳል፣ ወደተከፈተለት ይገባል፣ ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡

ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡

“ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” –Henry David Thoreau


“የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” – Nora Roberts


ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አደራረግህን እንጂ” - Unknown Source


https://t.me/eec1227


በአዲስ አበባ በመጪው ዓመት የትምህርት ዘመን ተማሪዎች ለትምህርት ለመመዝገብ ብሄራዊ ዲጂታል መታወቂያ ወይንም ፋይዳ መያዝ አስገዳጅ ሆነባቸው፡፡

የከተማው ትምህርት ቢሮ  የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታ  እንደሆነ ይፋ አድርጓል ተብሏል።ተማሪዎች የፋይዳ ምዝገባ አንዲያካሂዱ በዘመቻ መልክ ለመሰራት የታሰበ ሲሆን እድሜያቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሆናቸው ህፃናትን  ምዘገባ በዘመቻ እንደሚከናወን ተነግሯል።

የፋይዳ ምዝገባ ቁጥር በአዲስ አበባ የመንግስት ተቋማት አገልግሎት ለማግኘት በቅድመ ሁኔታነት የተቀመጠ ሲሆን በከተማው ያሉ የመንግስት ሰራተኞች የቅጥር እና ዝውውር እንዲሁም የደመወዝ አከፋፈል ስርዓት ከምዝገባ ስርዓቱ ጋር እንዲቀናጅ በአስገዳጅ ስርዓትነት መቀመጡን ሰምተናል፡፡የከተማዋ ትምህርት ቢሮ  የልደት እና የፋይዳ ምዝገባ የ2018 ዓ.ም የተማሪዎች የትምህርት ቤት ምዝገባ ቅድመ ሁኔታም እንደሆነ ይፋ አድርጓል።

Via Sheger
@eec1227




Ethiopian Digital Library (EDL) dan repost
English Grade 9 Teacher Guide_b5_Final (1).pdf
2.8Mb
TG for Grade 9

📌Join and share 👇👇👇

➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
✦Join➬ @EthiopiaDigitalLibrary
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖

19 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.