ኢትዮጵያዊ ከሆናችሁ እንደውዴታ ግዴታ ቆጥራችሁ ከዚህ በታች ያለውን ትዊት በተቻላችሁ አዳርሱት።
እንደኢትዮጵያዊ ወጣት አስቀድመን ባነን አገርም የምትባንንበትን አዎንታዊ እንቅስቃሴ ለመጀመር ደፋ ቀና ማለት ያለብን ጊዜ ላይ ነን። ሀሳባችንን አመንክዮ እና እውቀት ላይ መስርተን ከማንፀባረቅ ጀምሮ እንደአንድ ዜጋ የተሰጠንን መብት በመጠቀም ፊርማችንን በማሰባሰብ መንግስት ጉዳዩን በይበልጥ ትኩረት እንዲሰጠው: ተገቢውን ጥናትና ምርምር እንዲያደርግ በጎ ውጤት ካገኘበትም ቢትኮይንን እንደአገር ማተም እንድንጀምር መገፋፋት እንደምንችል እናምናለን።
ከፊርማው የማይተናነስ ድምፅ ይኖረን ዘንድ መንግስትን ማይን እንዲያደርግ የምንጠይቅበትን እንቅስቃሴ እየጀመርን ነውና: በዚህም እኔና እናንተ ብቻ ሳንሆን የልጅ ልጆቻችን ጭምር ተጠቃሚ ናቸውና ... አደራ አደራ አደራ ... ይህንን መልእክት ያያችሁት ቤተሰቦች ሁሉ በቢትኮይን እድገት የምታምኑ እና በኢትዮጵያዊነታችሁ የምትተማመኑ ከሆነ ከታች ያለውን ፖስት share, like and retweet በማድረግ ይህንን ሁነት እንዲሳካ በአለም አቀፍ ደረጃ ደፋ ቀና እያሉ ያሉትን ምንም ጥቅም ያልጠየቁትን Project Manoዎች እንደአንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት አለንላችሁ እንበላቸው።
Honestly speaking በዚህ ልክ አጠንክሬ ጠይቄያችሁ አላቅምና እንደማታሳፍሩኝ ተስፋ አለኝ። ፖስቱ ከ150 በላይ ላይክ እና Repost ካላገኘ ይሄን ኮሚዩኒቲ የለፋሁለት እንዲሁ በከንቱ እንደሆነ ይታሰበኛልና እስቲ ላንቃዬ እስኪሰነጠቅ በነፃ ህዝቤን ላገለገልኩበት ላይክና retweetቱን ክፈሉኝ። Lets go family.✌️🔥 የምርም ቁምነገር ያለው ነውና እናንተም አትቆጩበትም።🙏✌️
https://x.com/CryptotalkEt/status/1897852444429991977?t=vNojbta8ghZvjR-5qv3bXg&s=19