ሰበር ዜና ET🇪🇹


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


መረጃዎች በትኩሱ ና ሳይዉሉ እንዲሁም ሳያድሩ በቻናሉ በኩል ይደርሳሉ
ለአስተያየት እና ለማስታወቂያ ስራዎች 👇👇

@Akiyas21bot

የyoutube ቻናላችን ይቀላቀሉ👇👇

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


አሁንም ቢሆን ወንድም በወንድሙ፤ ወገን በወገኑ ላይ በመተኮስ የሚወሳሰብ እንጂ የሚፈታ ችግር የለም፡፡ በመንግሥት በተለይም በፌዴራል መንግሥት በኩል መሠረታዊዎቹን የአማራ ሕዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ ከመመለስ ውጭ የኃይል አማራጭ መከተል አደጋው የከፋ ነው፡፡ ከግጭት አዙሪት መውጣት የሚቻለው መሠረታዊውን የሕዝብ ጥያቄ በሰከነ መንገድ፣ ከልብ በመመለስ ብቻና ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም፡-
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ ብቻ ሳይሆን፤ የትግሉ አስኳልና የ2010ሩ የፖለቲካ ለውጥ መነሻ በመሆኑ፤ ገዥው ብልጽግና ፓርቲና የሚመራው የኢፌዴሪ መንግሥት ጉዳዩን በከፍተኛ ጥንቃቄ እንዲያየው በድጋሚ እናሳስባለን!
ምንጊዜም ቢሆን ትግላችን ሕዝባዊ መሰረት ያለው እንጅ በመዋቅር ላይ የሚንጠለጠል አይደለም፡፡ መዋቅር የሚያስፈልገው የሕዝብን የትግል ዓላማ በተሰናሰለ መልኩ ለማስፈጸም ነው፡፡ አሁንም ቢሆን መዋቅር በማፈረስ የሚጣል የማንነት ትግል አጀንዳ የለንም፡፡ ለአማራዊ ማንነታችን በዘላቂነት መከበር እንደቀደመው ጊዜ ሁሉ ሕዝባችን ኃይላችን፤ ጉልበታችን ሕዝባዊነታችን ሆኖ ይቀጥላል፡፡በመሆኑም ትግላችን ሕዝባዊ ሆኖ እንደሚዘልቅ እናረጋግጣለን!!
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት ጥያቄ ፍትሐዊ እና ሕጋዊ መሆኑን በመጣንባቸው የትግል ምዕራፎች አስመስክረናል፡፡ ለዚህ እልፎችን በሰማዕትነት ለገበርንበት፣ የአማራ ሕዝብ የትግል አስኳል ሆኖ ለቀጠለው የወሰንና ማንነት ጥያቄያችን በዘላቂነት መመለስ እስከመጨረሻው ፀንተን እንቆማለን!! ‹ወልቃይት ሆይ ብረሳሽ ቀኜ ትርሳኝ› በሚል በመላ አማራ ዋጋ የከፈሉ ወገኖቻችን ሁሉ ሰማዕትነታቸውን እንዘክራለን፤ ቃላቸውን እንፈጽማለን፤ መቼውንም ቢሆን የትግል አደራ አይታጠፍም; ዳግም በጅምላ አንገደልም!!
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የትግል አደራ አይታጠፍም፤ ዳግም በጅምላ አንገደልም‼️
(ከወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ)

የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ የማንነት እና ወሰን ጥያቄ ቀን ጠብቀን፤ ሒሳብ ሰርተን ብቅ ያደረግነው የዘር ካርድ ሳይሆን በመራር የፈተና እና የመከራ ወቅት ሳይቀር እስከ ኢያሪኮ ጎልቶ የተሰማ እውነተኛ የሕዝብ ድምጽ ነው፡፡ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ግፈኞች ቀን ሰጣቸው ብሎ ሳይፈራ፤ በጀምላ ተገደልኩ ብሎ ለነፍሱ እና ለቤተሰቡ ሳይራራ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ በጽናት እና በብርታት ፊት ለፊት እንደተጋፈጣቸው ታሪክ ህያው ምስክር ነው፡፡
የወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ጀግንነት እና ጽናት ራሳቸውን ግፈኞቹን መልሶ እስኪገርማቸው ድረስ ታንኩንም ባንኩንም ጠቅልለው በያዙበት ፈርጣማ ዘመናቸው ሳይቀር በእውነት እና በእውቀት፤ በመርህ እና በእልህ ታግሏቸዋል፡፡ “ማን ከገፋኝ ወደኩ” እንዲሉ ኢትዮጵያዊያን በብሂላቸው የትህነግ አፋኝ አገዛዝ እና ቆሞ ቀር ፖለቲካ ከመሀል ሀገር ተገፍቶ በአንድ ቦታ ብቻ እንዲወሸቅ ያደረገውም እውነተኛ የሕዝብ ትግል ውጤት ነበር፡፡  
የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ ሕግ እና ሥርዓትን መርዂ አድርጎ በሰላማዊ የትግል መንገድ የወከለውን ሕዝብ የአማራ ማንነት ጥያቄ ለማስመለስ ከፍተኛ ትግል ሲያደርግ መቆየቱ ይታወሳል፡፡
ኮሚቴው ሕግ እና ሥርዓትን በተከተለበት በሰላማዊ ትግሉ ሂደት የተሰጠው ምላሽ ግድያ እና አፈና ሆኖ በርካታ አይተኬ አባሎቹንና ወገኖቹን ሕይወት ገብሯል፡፡ እውነትና መርኽ በእጁ የሌለው አፋኙ እና ግፈኛው የትሕነግ አገዛዝ በሰላም የቀረበለትን ጥያቄ በጉልበት ለመቀልበስ ቃታ ስቦብናል፤ ከጅምላ ፍጅት እስከ ጅምላ እስር ድረስ የዘር ማጥፋትና የዘር ማጽዳት ተመጋጋቢ ወንጀሎችን ያለአንዳች ምህረት ፈጽሞብናል፡፡ ይሁን እንጂ ትግላችን እውነተኛ እና ፍትሐዊ በመሆኑ በርካታ ፈተናዎችን በጽናት ያለፈው የወልቃይት-ጠገዴ የአማራ ማንነት እና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ፣ የአማራ ማንነት ትግላችን አጋር የሆኑ ፍትሕ ወዳድ ኢትዮጵያዊያንን በመያዝ መከራውን በብርታት፤ ችግሩን በጽናት፤ ሴራውን በትግል አሸንፈን አሁን ላለንበት ወሳኝ እና ታሪካዊ ጊዜ ላይ ደርሰናል፡፡
ከዚህ እስክንደርስ የተከፈለው መስዋዕትነት ግን እንኳን በወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ ቀርቶ በጎረቤቶቻችን የትግራይ ሕዝቦች ላይ እንኳ እንዲፈጸም አንፈልግም፡፡ ዛሬ እውነተኛ ማንነታችን፣ ሰላማችን አና መብቶቻችን ተከብረው እንደ ሰው መኖር ከጀመርን ሦስት ዓመታት ቢቆጠሩም ትናንት የሆነብንን እና የተፈጸመብንን ግፍ እና መከራ ግን ፈጽሞ ለአፍታ አንዘነጋም፡፡ እንዘንጋ ብንልስ ግህንብ፣ ማይካድራ፣ ጭና፣ተከዜና ሌሎች ሕያው ምስክሮች እያሉ እንዴት መዘንጋት ይቻለናል፡፡
ኮሚቴው፣ ባሳለፋቸው የሰላማዊ ትግል ጊዜያትም ሆነ ከነጻነት በኋላ ባሉ ወሳኝ የትግል ምዕራፎች ውስጥ የአማራ ሕዝብ ለዘመናት ዋጋ የከፈለበት የማንነት እና የወሰን ጥያቄው በዘላቂነት በሕግ ለማጽናት የመንግስትን አቅጣጫና የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት እየተከታተለና  እየተጠባበቀ ባለበት በዚህ ወቅት ወያኔ-ህወሕት የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ እና ከስምምነቱ በማፈንገጥ ዛሬም እንደ ትናንቱ ከስህተቱ የማይማር የደም ነጋዴ መሆኑን በግላጭ ለዓለም ሕዝብ አሳይቷል፡፡
እንደ ወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነትና ወሰን አስመላሽ ኮሚቴ፣ ትሕነግ ለአራተኛ ዙር በከፈተው የጦር ወረራ የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በኃይል መውረሩን፣ በዚህም የደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት አጠቃላይ ሁኔታውን በአንክሮ እየተከታተልን ነው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህ ሕገ-ወጥ የጦር ወረራ በትሕነግ መከፈቱን ተከትሎ በራያ እና አካባቢው አመራሮችና የጸጥታ መዋቅሩ አባላት ላይ በደረሰው ህልፈተ ሕይወት ኮሚቴው ሐዘኑን ይገልጻል፡፡
ትህነግ አሁን የጀመረውን አደገኛ ጠብ-አጫሪነት አደብ ማስያዝ ካልተቻለ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ሕዝብ ዳግም ላለመወረር አስፈላጊውን የትግል አማራጮችን በመጠቀም ያገኘውን ነፃነት በዘላቂነት ለማጽናት ሞት አይቀርም፤ሥም አይቀበርም!! ብሎ ለእውነት፣ ለነጻነት እና ለማንነት እስከ ወዲያኛው ለማለፍ ዝግጁ መሆኑን ኮሚቴው ያሳስባል፡፡
ትሕነግ ራሱ በለኮሰው እሳት ተለብልቦ የፕሪቶሪያውን የሠላም ስምምነት ሳይወድ በግድ የተቀበለ ቢሆንም፣ በስምምነቱ መሠረት የተቀመጡትን ከእሱ የሚጠበቁ ኃላፊቶችና ግዴታዎች ተግባራዊ እንዳላደረገ የሚታወቅ ነው፡፡ ድርጅቱ ሁልጊዜም በቅጥፈትና በማታለል ዓላማዬን አሳካለሁ ብሎ የሚያምን፣ ለራሱ የተጋነነ ግምት የሚሰጥ፤ በየትኛውም የሕግ፣ የሞራልና የፖለቲካ መርሆ የማይታጠር በየትም ፍጭው ዱቄቱን አምጭው ፈሊጥ የሚጓዝ ኃይል ነውና እርሱ ያላከበረውን ስምምነት እንዲከበርለት ሲወተውት ቆይቶ፣ ሲገዘግዘው የቆየውን የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት ዛሬ በግላጭ ራሱ ጥሶታል፡፡
የትሕነግ የዘመናት ባሕርይ ‹ጅራፍ ራሱ ገርፎ ራሱ ይጮሃል› በሚለው የአበው ብሂል የሚገለጽ ነው፡፡ ሁልጊዜም ጩኸት በመቀማት የታወቀ ቡድን በመሆኑ የሰላም ስምምነቱን ከምር ተቀብሎ የታጠቀውን መሣሪያ ማስረከብ፣ ያደራጀውን ሠራዊት መሸኘት እና ቀጠናው ወደተሟላ ሰላም እንዲመለስ የሚጠበቅበትን መፈፀም ሲገባው እንደለመደበት ማጭበርበር ሲብስ ደግሞ ኃይል በመጠቀም ዳግም ወረራ በመፈጸም ፍላጎቱን በጉልበት ሊያሳካ በመሞከር ላይ ነው፡፡ ትሕነግ ዛሬም እንደትናንቱ ከስሌት ይልቅ በስሜትና በማን-አህሎኝነት አስተሳሰብ የሚመራ በመሆኑ ወልቃይት ጠገዴ በእኔ ሥር ይሁን፣ ካልሆነ በኃይል ለመውረር ተከዜን እንደሚሻገር በወንድም የራያ አማራ ሕዝብ ላይ የጦር ወረራ በመፈጸም ቀጣይ አቅጣጫውን ከወዲሁ እያሳየን ነው፤ በርግጥ በዚህ ድርጊቱ ፀረ-ሰላምነቱን ለመላ ኢትዮጵያዊያንና ለዓለማቀፉ ማኀበረሰብ ለአራተኛ ጊዜ  አረጋግጧል፡፡
ዓለም በአደባባይ እንደሚመለከተው እኛ ጥያቄያችን ተፈጥሯዊ የሆነ የእውነት እና የፍትሕ ጥያቄ ነውና የዘመናት ጥያቄያችን ሕጋዊ ምላሽ እንዲያገኝ መንግሥት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እየሠራን እንገኛለን፡፡ በሌላ በኩል እብሪት ከሚነዳው ወራሪ ቡድን ራሳችን ለመከላከል ሁልጊዜም ሁላችንም ዝግጁዎች ሆነን መገኘት እንዳለብን ኮሚቴው በአጽንዖት ያሳስባል፡፡ የወልቃይት ጠገዴ አማራ ማንነት ትግል የሁሉም፣የሁልጊዜምና በሁሉም ቦታ ሁሌም ዝግጁ ሆኖ መገኘት ነው ብሎ ኮሚቴው ያምናል፡፡
እንደሚታወቀው የወልቃይት-ጠገዴ የማንነት እና የወሰን ጥያቄ ታሪክን፣ ፖለቲካን እና ነባራዊውን ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በሕግ አግባብ ለባለቤቶቹ እንዲጸና አለመደረጉ በመንግሥትና በሕዝብ መካከል ሊኖር የሚገባውን መተማመን ሸርሽሯል፡፡ ጤናማ ግንኙነት እንዳይኖር ይልቁንም የሀገረ-መንግሥቱ ጠላቶች በሚፈልጉት መንገድ ግጭት እንዲፈጠር አድርጓል፡፡ ይህ ለኢትዮጵያ የውስጥና የውጭ ጠላቶች የደስታ ምንጭ፤ ለገዛ ሕዝቧና ለወዳጆቿ ደግሞ አሳዛኝ፣ የታሪክ ጠባሳ የሚያሳርፍ ታሪካዊ ስህተት በመሆኑ በፍጥነት ሊታረም ይገባል፡፡




#Update #ራያ❗❗
በራያ አላማጣ ወረዳ እንዲሁም ራያ ኦፍላ ወረዳ ኮረም  ገብተው የነበሩ የህወሓት ታጣቂዎች ወደ መጡበት እንዲመለሱ እየተደረገ ነው። የህወሓት ታጣቂዎች የሰሞኑ እንቅስቃሴ በዋናነት የፀጥታ ስራውን እኛ እንረከባለን በሚል እንቅስቃሴ ወደ አላማጣ ከተማ ለመግባት የሞከሩ ቢሆንም ይሄ ሊሆን እንደማይችል ተነግሯቸው ተመልሰዋል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል። ታጣቂዎቹ ገብተው በነበሩባቸው ገጠራማ አካባቢዎች ሲመለሱ ጭምር ዝርፊያ ፈፅመዋል፣በተለይ የቲማቲም እርሻ በብዛት አውድመዋል ብለውኛል። በርተክላይ አሁንም የሀገር መከላከያ ሰራዊት መኖሩን ገልፀውልኛል።
የአላማጣ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ወደ ቆቦ በመሻሻቸው አሁን ላይ ከተማዋን የፌደራል ፖሊስ እያስተዳደረ ነው ብለዋል። የህወሓት ታጣቂ አላማጣ አልገባም ብለዋል።
የአላማጣ ከተማ ነዋሪ ግሉኮስ ተሳክቶለት የነበረ ታካሚ ሳይቀር ወደ ቆቦ  እንዲሸሹ ዋነኛውን ችግር የፈጠረው የአላማጣ  ከተማ አመራሮች ናቸው ይላሉ ያነጋገርኳቸው ተፈናቃዮች እንዲሁም የፌደራል የፀጥታ አካላት።
መጋቢት 6 በመኪና እየዞሩ  አዋጅ እያወጁ ውጡ ተዋጉ እያሉ ቆይተዉ፣በማግስቱ መጋቢት 7 ግን ካቅም በላይ ነው እያሉ እራሳቸው ሲሸሹ በአይናችን አየን ከዛም የአላማጣ ህዝብ የዕለት ልብስ እንኳን ሳይዝ ወደ ቆቦ መሸሽ የጀመረው ብለዋል።
አሁን ላይ የህወሓት ታጣቂዎች በብዛት የት ነው ያሉት❓
የህወሓት ታጣቂዎች በብዛት የሚገኙት በራያ ባላ መሆኒ ገጠራማ አካባቢዎች ላይ ነው ብለውኛል።
========================
iለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ኢትዮጵያ ከፍተኛ የተባለ የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች መሆኗን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ‼️
ኢትዮጵያ በታሪኳ ከፍተኛ የተባለ የኮሌራ ወረርሽኝ እያስተናገደች እንደምትገኝ የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ ለሚያካሂደው ሥራ አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልገውም ገልጿል።

የድርጅቱ ዳይሬክተር ቴድሮስ አድሐኖም ድጋፉ የማይገኝ ከሆነ ድርጅታቸው በሀገሪቷ የሚያከናውነውን ከጤና ጋር የተገናኝ ሥራ ለመቀጠል እንደሚቸገር ተናግረዋል።

ዶክተር ቴድሮስ የተስፋፋ ድርቅና በሽታ በሚሊየን የሚቆጠሩ አትዮጵያውያንን ሕይወት አደጋ ላይ መጣሉንም አስረድተዋል።

በተለይም በትግራይ፣ አማራ፣ ኦሮሚያና ሌሎች አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት እና ጦርነት የከፋ ጉዳት አድርሷል ነው ያሉት።

በርካታ የጤና ተቋማት እና መሰረተ ልማቶች ላይ ውድመት መከሰቱን አስታውሰው የተለያዩ ወረርሽኞች መከሰታቸውንም ጠቅሰዋል።


የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ በሥምንት ክልሎች 41 ሺህ ሰዎች በኮሌራ በሽታ መያዛቸውንም ገልጿል።

በሽታው በዚህ ልክ በኢትዮጵያ ሲከሰት በታሪኳ ከፍተኛው እንደሆነም ነው ድርጅቱ የገለጸው።

ወባና ኩፍኝም ሌሎቹ ወረርሽኞች መሆናቸውን የጠቀሰው ድርጅቱ፥ በኢትዮጵያ ለሚያከናውነው የበሽታ መከላከልና ጤና አጠባበቅ ሥራ አፋጣኝ የገንዘብ ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቅርቧል።
========================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ በጅምላ እና ችርቻሮ እንዲሳተፉ ተፈቀደ

ከዚህ ቀደም ለአገር ውስጥ ባለሃብቶች ብቻ ተከልለው የቆዩ የወጪ፣ የገቢ፣ የጅምላ እና የችርቻሮ ንግድ ዘርፎች ለውጭ ባለሃብቶች ከፍት እንዲሆኑ ተደረገ፡፡ 

በዚህም መሰረት የውጭ ባለሀብቶች በጥሬ ቡና፣ በቅባት እህሎች፣ ጫት፣ ጥራጥሬ፣ ቆዳ እና ሌጦ፣ የደን ውጤቶች እና የቁም እንስሳት የመላከ የወጪ ንግድ ላይ እንዲሳተፉ ተፈቅዷል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሸን እና የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በጉዳዩ ዙሪያ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በመግለጫው ላይ እንደተገለፀው፤ የተቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎችን የሚያሟሉ የውጭ ባለሃብቶች ከማዳበሪያ እና ነዳጅ በስተቀር በሁሉም የገቢ ንግድ ኢንቨስትመንት ዘርፎች መሰማራት ይችላሉ፡፡

የጅምላ ንግድን በተመለከተ ከማዳበሪያ ጅምላ ንግድ በስተቀር በሁሉም አይነት የጅምላ ንግድ መስኮች መሰማራት ይችላል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም የውጭ ባለሀብቶች ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያሟሉ ለአገር ውስጥ ባለሃብት በተከለሉ ሁሉም የችርቻሮ ንግድ ስራዎች መሳተፍ እንዲችሉ መፈቀዱም ተጠቅሷል። 

በጉዳዩ ላይ በባለድርሻ አካላት የተካሄዱ ዝርዝር ጥናቶች ላይ በመመርኮዝ መሠረታዊ የፖሊሲ ለውጥ ያደረገው የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድም አዲስ የአፈፃፀም መመሪያ አፅድቋል።
Via:ኢቢሲ
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ዱባይ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች‼

በዱባይ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መጠን ነፋስ የቀላቀለ ከባድ ዝናብ መዝነቡን ተከትሎ ከተማዋ በጎርፍ ተጥለቅልቃለች።

ጎርፉን ተከትሎ የዱባይ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ጣቢያን ጨምሮ የከተማዋ ዋና ዋና ጎዳናዎች ከባድ ጎርፍ እያስተናገዱ መሆኑ ተገልጿል።

በተለይም ከዚህ ቀደም በርከታ በረራዎችን ሲያስተናግድ በነበረው የዱባይ አየር መንገድ በረራዎች ተስተጓጉለዋል።

ነፋስ የቀላቀለው ከባድ ዝናብ በኦማን ተከስቶ 18 ሰዎች ህይወታቸው ካለፈ በኋላ አሁን ደግሞ በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ እና በባህሬን ጉዳት እያስከተለ እንደሚገኝ የአልጀዚራ ዘገባ ያመለክታል።
========================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ራያ❗ #ኮረም #አላማጣ❗
በአማራ ክልል ዋግኸምራ ዞን ራያ ኦፍላ ወረዳ ኮረም ከተማ በርካታ የህወሓት ታጣቂዎች መግባታቸውን ተከትሎ ትናንት የአማራ ሚሊሻ ናችሁ ተብለው ስድስት ሰዎችን ገድለዋል። ትናንት በፒካፕ መኪና ከባድ መሳሪያዎችን ጭነው ፓትሮል ሲያደርጉ እና ሲጨፍሩ ነው ያደሩት ብለዋል። በርካታ የኮረም ነዋሪዎች ወደ ሰቆጣ ተፈናቅለዋል ብለዋል።
👉አላማጣ ከተማ አሁን ላይ የተለወጠ ነገር ባይኖርም በከተመዋ በአብዛኛው የሚታዩት የመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች ሲሆኑ ማታ ማታ አልፎ አልፎ የህወሓት ሚሊሻዎች ይታያሉ ብለዋል። የህወሃት ታጣቂዎች በገቡባቸው ቦታዎች የብልፅግና ደጋፊ ናቸው በሚል ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደው ያሰሯቸው ሰዎች አሉ ተብሏል። አላማጣ ዙሪያ በአራት ፒካፕ መኪና የሚንቀሳቀሱ የህወሓት ታጣቂዎችን መመልከታቸውን የመረጃ ምንጮቹ ገልጸዋል።
ትናንት የአፍሪካ ህብረት ተወካዮች በአላማጣ ሪዞርት ሆቴሌ ስብሰባ አድርገው የሰሞኑን ክስተት በተመለከተ ሪፖርት ለማሰባሰብ ጥረት እንደሚያደርጉ በስብሰባው ላይ አንስተዋል ተብሏል።
========================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የተሰጠ መግለጫ‼️
ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናብቦና ተቀናጅቶ በርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ  የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈጸም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈጸመባቸው አካባቢዎች  ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ኾነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ተቸንካሪነት ዋና መለያ የኾነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ኹኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይኾን ከኾነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመኾን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መኾኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመኾኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ኾኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመኾን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈጸመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈጽሟል፡፡ በመኾኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሐሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት  በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ኾኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ኅብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመኾኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ  ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ኾነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡

ኾኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ኹኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
የፓርላማው ድብድብ‼

የጆርጂያ ሕግ አውጭዎች ሰኞ ዕለት በተሰበሰበው ፓርላማ ውስጥ ተደባድበዋል።

የፓርላማ አባላቱ አወዛጋቢ በሆነው የውጭ ወኪሎች ረቂቅ ህግ ላይ በፓርላማ በተካሄደው ክርክር ወቅት የተቃዋሚው ፓርላማ አባል አሌኮ ኤሊሳሽቪሊ የገዥውን የጆርጂያ ድሪም ፓርቲ መሪ ማሙካ ምዲናራዜን በንግግራቸው ፊት ለፊት በቡጢ ከመቱ በኋላ ነው። 

በውጭ አገር ገንዘቦችን የሚቀበሉ ድርጅቶች እንደ የውጭ ወኪልነት እንዲመዘገቡ ወይም ሊቀጡ የሚችሉበት ሂሳቡ፣ ጆርጂያን ፖላራይዝድ አድርጓል እና በ2023 መጀመሪያ ላይ የጅምላ ሰልፎችን አድርጓል።
========================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የኢራን ፕሬዝዳንት ከእስራኤል በኩል ለሚሰነዘር ጥቃት 'ከባድ' ምላሽ እንሰጣለን ሲሉ ቃል ገቡ‼️
የኢራን ፕሬዝዳንት ኢብራሂም ራይሲ ከኳታር አሚር ጋር ሀገራቸዉ በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን የአየር ላይ ጥቃት ስኬታማ እንደሆነ ገልፀው ኢራን ወደፊት በጥቅሟ ላይ ስጋት ካለባት የበለጠ “አሳማሚ” ጉዳት እንደምታደርስ በነበራቸዉ የስልክ ቆይታ ተናግረዋል፡፡

የኢራን የዜና ወኪል እንደዘገበው  በኢራን ፍላጎት ላይ የሚወሰደው ትንሹ እርምጃ በእርግጠኝነት በሁሉም አጥፊዎቹ ላይ ከባድ ፣የተስፋፋ እና የሚያሰቃይ ምላሽ ይጠብቀዋል ስንል በግልፅ እንናገራለን” ብለዋል።
የኢራን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ባገሪ ካኒ ለመንግስት የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደተናገሩት ቴህራን ማንኛውንም የእስራኤል አጸፋ ተከትሎ የምትወስደው እርምጃ እንዳሁኑ ኢራን ተጨማሪ 12 ቀናት ምላሽ ለመስጠት ስለማትጠብቅ በጥቂት ሰከንዶች ልዩነት መልስ እንሰጣለን ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢዝራኤል ካትስ በበኩላቸዉ ሀገራት ኢራን ላይ ማዕቀብ እንዲጥሉ አሳስበዋል፡፡የእስራኤል ከፍተኛ ዲፕሎማት "በኢራን ላይ የፖለቲካ ጥቃትን" እየመራሁ እገኛለሁ ሲሉ ተደምጠዋል፡፡በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ዛሬ ማክሰኞ ጠዋት ወደ 32 ለሚሆኑ ሀገራት ደብዳቤ ልኬያለሁ እናም በኢራን ሚሳኤል ጥቃት ላይ ማዕቀብ እንዲጣል እና የኢራን አብዮታዊ ጥበቃ ጓድ በአሸባሪነት እንዲፈረጅ ለመጠየቅ በደርዘን የሚቆጠሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮችን እና የአለም መሪዎችን አነጋግሬያለሁ ብለዋል።
የእስራኤል ወታደራዊ አዛዥ ሄርዚ ሃሌቪ በኢራን ጥቃት ቀላል ጉዳት በደረሰበት ወታደራዊ ጣቢያ በመገኘት ለወታደሮች እንደተናገሩት የኢራን ድርጊት የአጸፋ ምላሹን ያገኛል ሲሉ ተናግረዋል።

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የኤርትራ መግለጫ‼️
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚንስቴር፣ በኤርትራ እና ኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር "ፈጽሞ ሊቀየር በማይችል ኹኔታ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተሠምሯል" ሲል ከሁለት ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ ገልጿል‼️
መግለጫው፣ ባኹኑ ወቅት በኹለቱ አገሮች መካከል ያለው ድንበር፣ በዓለማቀፉ የድንበር ኮሚሽኑ ውሳኔ መሠረት "ባግባቡ የሚታወቅ እና በሕግ የተረጋገጠ ድንበር" መኾኑን ጠቅሷል። በኤርትራ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች ወይም በኤርትራ እና ትግራይ ሕዝቦች መካከል የሕግ ጥሰት ካልኾነ በስተቀር ሌላ ምንም ዓይነት ግጭት የሚያስነሳ ጉዳይ እንደሌለ በመግለጫዋ የጠቀሰችው ኤርትራ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብም ከፍተኛ ውድመት ካስከተለው የኹለቱ አገሮች የድንበር ጦርነት ትልቅ ትምህርት ወስዷል ብላለች።
ሰሞኑን የኤርትራ ጦር የኢሮብ ተወላጆችን ማንነታቸውን ኤርትራዊ ብለው እንዲቀይሩ እና በኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት እንዲሳተፉ እያስገደዱ መሆኑንና ወደ ብሄራዊ ግዳጅ አንሄድም ያሉ ሰዎችንም መሆኑ ነዉ
========================
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ እንዳሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችና ግለሰቦች በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለባቸው የተባሉ ናቸው ብለዋል።

በተለይም በመጋቢት 26/2016 ዓመተ ምህረት በጆር ወረዳ ለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለባቸው የተባሉ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና አምስት የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሆኑ ሰባት የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በተለያዩ መድረኮች በጋምቤላ ከተማ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሞክር አንድ ግለሰብ ከአመራሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።

በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኮሚሽነር ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል።
መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ብዙዎችን ስጋት ላይ የጣለው የኢራን እና እስራኤል ፍጥጫ‼️‼️
ኢራን በእስራኤል ላይ ጥቃት ትፈጽማለች በሚል ስጋት አሜሪካ ለዜጎቿ ማስጠንቀቂያ አወጣች‼️
አሜሪካ በኢራን ሊቃጣ በሚችል ጥቃት ስጋት ምክንያት ዜጎቿ በእስራኤል እንቅስቃሴ ከማድረግ እንዲቆጠቡ አስጠነቀቀች።
የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኞቹ ከኢየሩሳሌም፣ ቴል አቪቭ ወይም ቤርሳቤህ ከተሞች ውጪ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ አሳስቧል።
በተመሳሳይ የዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) መንግሥት ከኢራን ሊፈጸም የሚችል ጥቃት መኖሩን በመግለጽ በጉዞ ማሳሰቢያው ላይ ማስጠንቀቂያ አውጥቷል።
የጀርመን አየር መንገድ የሆነው ሉፍታንዛ ወደ ኢራን መዲና ቴህራን የሚያደርገውን በረራ እስከ ዛሬ ድረስ ሰርዟል።

ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


ኢትዮጵያ ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን ከሥራ እና ከማኅበራዊ ግልጋሎቶች የሚያገል ምዝገባ ልትጀምር ነው‼️
የኢትዮጵያ መንግሥት ፆታዊ ጥቃት ፈጻሚዎችን የሚመዘግብ ሥርዓት ሊጀምር መሆኑን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።
ምዝገባው ፆታን መሠረት አድርገው የሚፈጸሙ ጥቃቶችን ለመከላከል እና ለመቀነስ ያለመ ነው የተባለ ሲሆን፣ በተለይ “ወሲባዊ ጥቃቶች ላይ ትኩረት” እንደሚያደርግ ተነግሯል።
በሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የሴቶች መብት እና ጥበቃ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ስለሺ ታደሰ፣ የምዝገባ ሥርዓቱን ለመጀመር 10 ሚሊዮን ብር እንደሚፈጅ ለቢቢሲ የተናገሩ ሲሆን፣ ይህ በጀት በተለያዩ አካላት መዋጮ እንደሚሸፈንም ጠቁመዋል።
ይህ ‘ብሔራዊ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል ምዝገባ ሥርዓት’ በሚቀጥለው ዓመት ወደ ሥራ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።
በኢትዮጵያ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተደረገ ጥናት ከጠቅላላ የአገሪቱ ሴቶች 35 በመቶዎቹ የተለያዩ ዓይነት ፆታዊ ጥቃቶች እንደሚደርሱባቸው ያሳያል።
‘ብሔራዊ የፆታዊ ጥቃት ወንጀል ምዝገባ ሥርዓት’ የተሰኘው ሥርዓቱ፣ ጥቃት ፈጻሚዎች በሕግ ከታሰሩ እና ቅጣት ከተላለፈባቸው በኋላም ለዘለዓለም ተጠያቂ የሚያደርግ እና “ከተመረጡ” ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ግልጋሎቶች የሚያገል መሆኑ ታውቋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


አቶ በቴ ኡርጌሳ በበርካታ ጥይት ተደብድበዉ ህይወታቸዉን እንዳጡ የህክምና ባለሙያ ተናገሩ‼️

👉🏼 በአስክሬናቸዉም ላይ የፎረንሲክ ምርመራ አልተካሄደም ተብሏል

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ውስጥ በምትገኘው የትውልድ ከተማቸው መቂ ረቡዕ ሚያዝያ 3/2016 ዓ.ም. ተገድለው የተገኙት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር አቶ በቴ ኡርጌሳ በበርካታ ጥይት መመታታቸውን የሕክምና ባለሙያ እና የቤተሰብ አባላት ለቢቢሲ ገለጹ።

አስከሬናቸው ከመቂ ከተማ ወጣ ብሎ በሚገኝ ቆሻሻ መጣያ አካባቢ የተገኘው አቶ በቴ ኡርጌሳ፣ ጭንቅላት ላይ አምስት በጥይት ምት የተፈጠሩ ጉዳቶችን መመልከታቸውን ለደኅንነታቸው ሲሉ ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ የሕክምና ባለሙያ ተናግረዋል።

“ጭንቅላቱ ላይ አምስት ቁስለት፣ ወገቡ ላይ ሦስት ቦታ፣ በግራ ጎኑ አንድ ትልቅ ጉዳት፣ ከወገቡ ወደታች እና ታፋው ላይም ተጨማሪ አንዳንድ ጉዳት በአጠቃላይ 11 የሚሆኑ ቁስለቶች ታይተዋል።”

የሕክምና ባለሙያው ሁሉም ጉዳቶች በጥይት የተፈጠሩ መሆን አለመሆናቸውን የተጠየቁ ሲሆን፣ “ለእኛ እንደዚያ ይመስላሉ። ገሚሶቹ ጥይቱ በገባበት የተፈጠሩ፣ ገሚሶቹ ደግሞ ጥይቱ የወጣበት ቦታዎች ላይ የሚገኙ ሊሆኑ ይችላሉ። ሁሉም ጥይት የገባበት ነው ማለት አይደለም” ብለዋል።

እኚሁ ባለሙያ አቶ በቴ ጭንቅላታቸው ላይ አምስት ጉዳቶች ቢኖሩም፣ ፊታቸው ላይ ግን ምንም ዓይነት ጉዳት አለመመልከታቸውን ተናግረዋል።

በአቶ በቴ አስከሬን ላይ የፎረንሲክ ምርመራ እንዳልተካሄደ ገልጸውም “በሰውነታቸው ላይ የቀረ ጥይት መኖር አለመኖሩን መለየት ይከብዳል” ሲሉ ለቢቢሲ መናገራቸውን ዳገጀ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። የህክምና ባለሙያው ጨምረውም “ጭንቅላታቸው ላይ የታየው አምስት ጉዳት ግን ሰውነታቸው ውስጥ የቀረ ጥይት መኖሩን ጥርጣሬ ይፈጥራል” ብለዋል።

የፖለቲከኛውን ግድያ ተከትሎ የተለያዩ መላምቶች የተሰነዘሩ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል በፖለቲከኛው ግድያ ላይ የመንግሥት ኃይሎች አሉበት መባሉን ውድቅ አድርጓል።

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ግድያ ላይ ገለልተኛ ዓለም አቀፍ አካል ምርመራ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት እንዲፈቅዱ አሜሪካ ጠይቃለች። የኦሮምያ ክልል መንግሥት በመቂ ከተማ አስከሬናቸው ተጥሎ የተገኙት ፖለቲከኛ የተገደሉት “ባልታወቁ ጥቃት አድራሾች” እንደሆነ ገልጿል።

የአቶ በቴ ኡርጌሳ ቤተሰብ አባል የሆኑ ሌላ ግለሰብ በበኩላቸው ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ረቡዕ ጠዋት ከነዋሪዎች ባገኙት መረጃ መሠረት፣ ሁለት ሰዓት አካባቢ አስከሬኑን ማግኘታቸውን ተናግረዋል። እኚሁ የቤተሰብ አባል አስከሬኑን ሲያገኙት አካሉ ብዙ ቦታዎች ላይ ቆስሎ መመልከታቸውንም ገልጸዋል።

“አካሉ ላይ የተገኙትን ጉዳቶች ትክክለኛ ቁጥር የአስከሬን ምርመራ ውጤት ነው የሚያሳየው። ቢያንስ በስድስት ጥይቶች መመታቱን ግን ፎቶዎች ተነስተው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ከተለቀቁት ማየት ችለናል።

የመቂ ከተማ ከንቲባ አቶ ዲልቦ ኡርጌሳ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃለ ምልልስ ግድያው የተፈጸመው ቤተሰብ መካከል በተፈጠረ አለመግባባት መሆኑን ገልጸው፣ ጉዳዩን ለማጣራት ምርመራ እንደሚያደረግ ተናግረው ነበር።

የአቶ በቴ የቤተሰብ አባል ግን ምንም ዓይነት የቤተሰብ አለመግባባት እንደሌለ ተናግረው “ሐቁ እንዳይወጣ መንገድ ለማሳት፣ ሕዝብ መሃልም መደናገር ለመፍጠር ያለመ ነው” ሲሉ አስተባብለዋል። “እርሱን ገድለው ያልጠገቡ፣ እውነቱን ለማጥፋት የፈለጉ” ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA




በተሽከርካሪ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ።

አደጋው የደረሰው ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ከቀኑ 8፡00 ላይ ከአክሱም ከተማ ወደ ውቅሮ ማራይ በሚወስደው መንገድ ላይ ነው። በአንድ ሚኒባስ እና ባጃጅ መካከል በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰምቷል።ለግጭቱ መከሰት ያልተገባ ፍጥነት መሆኑን ፖሊስ ጠቁሟል።
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA


የኢትዮጵያ እና ሶማሊያን ውጥረት ለማርገብ ኬንያ የባሕር ጠረፍ ስምምነት ሃሳብ አቀረበች!

ኬንያ በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረው ውጥረት ለማርገብ ያስችላል ያለችውን ቀጠናዊ የባሕር ጠረፍ አገልግሎት አጠቃቀም ስምምነት አማራጭ አቀረበች።ይህ ኬንያ ያቀረበችው አማራጭ በቀጠናው የሚገኙ የባሕር በር የሌላቸው አገራት በንግድ ስምምነት መሠረት የባሕር መተላለፊያ አገልግሎት እና ጥቅም የሚያገኙበትን ዕድል የሚፈጥር ነው ተብሏል።

ከጥቂት ወራት በፊት ኢትዮጵያ እና ከሶማሊያ ተገንጥላ ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የባሕር በር ለማግኘት የመግባቢያ ሠነደ መፈረሟ በአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ መካከል ከፍተኛ ውጥረትን ፈጥሯል።ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ ታኅሣሥ 22/2016 ዓ.ም. አዲስ አበባ ላይ በመሪዎቻቸው መካከል የተፈራረሙት የመግባቢያ ሠነድ ኢትዮጵያ ነጻ አገር መሆኗን ላወጀችው ሶማሊላንድ ዕውቅናን ለመስጠት፣ ሶማሊላንድ በምላሹ ለኢትዮጵያ የባሕር በር ለመፍቀድ ከስምምነት መድረሳቸው መዘገቡ ይታወሳል።

ይህንንም ሶማሊላንድን የግዛቱ አንድ አካል እንደሆነች የሚገልጸው የሶማሊያ መንግሥት ስምምነቱን አጥብቆ በመቃወም፣ የአገሪቱን ሉዓላዊነት የሚጥስ ድርጊት ነው በማለት አጥብቆ ተቃውሞታል።ይህን ተከትሎ ሶማሊያ በሞቃዲሾ የሚገኘቱን የኢትዮጵያን አምባሳደር ከአገር አስወጥታ በአዲስ አበባ የሚገኙትን አምባሳደሯን ባለፈው ሳምንት ጠርታለች።

በሁለቱ የአፍሪካ ቀንድ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውዝግብ ለማርገብ ኬንያ አሁን አማራጭ ያለችውን ሐሳብ ወደ ጠረጴዛ አምጥታለች።የኬንያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና ፀሐፊ ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት በቀጠናው ያሉ የባሕር በር የሌላቸው አገራት በንግድ ስምምነት መሠረት የባሕር በር የሚያገኙበትን አማራጭ የሚሰጥ ነው ብለዋል።

ኮሪር ሲንጋኦኢ እንደሚሉት ከጂቡቲ እና ከምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ጋር በሚደረገው ምክክር ቀጠናዊ የባሕር አገልግሎት አጠቃቀም ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል ብለዋል።“ኢጋድ የባሕር በር አገልግሎት አጠቃቀም የሚደነግግ ሕግ ማርቀቅ ይችላል” ያሉት ባለሥልጣኑ፣ ናይሮቢ የምታቀርበው አማራጭ ተቀባይነትን የሚያገኝ ከሆነ ኢትዮጵያ “አስተማማኝ የባሕር በር አማራጭ ይኖራታል” ሲሉ ኮሪር ተናግረዋል።

እኒህ የኬንያ የውጭ ጉዳይ ከፍተኛ ባለሥልጣን ኬንያ ያቀረበችው አማራጭ ከኢትዮጵያ በተጨማሪ የሶማሊያን ሉዓላዊ አንድነት የሚያረጋግጥ ይሆናል ብለዋል።ኬንያ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለማርገብ ከመጋረጃ ጀርባ ሁለቱን አገራት ስታደራድር ስለመቆየቷ ሲገለጽ ቆይቷል።
Via BBC
ለጥቆማና ማስታወቂያ ለማሰራት
    👉 @Akiyas21bot
  

@ET_SEBER_ZENA
@ET_SEBER_ZENA



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.