ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮንሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን /2/
ውስተ አፍላገ ባቢሎን ኅየ
ነበርነ ወበከይነ እንዚራቲነ
ሰቀልነ ውስተ ኲሓቲሃ/2/
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ኢትዮጵያን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቆአችንን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ
ፅኑ መከራን ተቀበልን ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዷልና
አሕዛብም ዘበቱብን እንዲህ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ለአምላካችሁ ቢያድናችሁ ከመከራ
እግዚአብሔር ጽዮንን ለመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
የማረኩን በጦራቸው በኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ
እግዚአብሔር ጽዮንን ለመንግስቱ መርጧታል እና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታል እና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ
ስጋችንን ሊገንዘን የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒትነሽ እናታችን
እግዚአብሔር ጽዮንን ለመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ጽዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
ለተዋሕዶ ልጆች👇
•➢ ሼር // SHARE