እንማር


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
    Ads - @Kiya988
https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የማያውቁት ሀገር አይናፍቅም ነው ያሉት?! የማያውቁት ሰውስ?! ለምን አትለኝም?! ስለናፈቀከኝ እኮ ነው

"ሆ ሆ መልኩን እንኳን የማያውቁትን ሰው መናፈቅ አይከብድም?!" ይሉ ይሆናል የሰሙን ሰዎች

እኮ ና እና ንገራቸው ጠይም ሆንክ የቀይ ዳማ ረዘምክ አጠርክ ጉዳዬ እንዳልሆነ ንገራቸው

አንተ ብቻ ና እና በቅጡም ቢሆን የፈዘዘ ህይወታችንን ለርስ በርሳችን ቅመም ሆነን ቤታችንን እናሙቀው። ምንም አንጨምር ምንም አንቀንስ እንደሆንነው ሆነን እንዋደድ። አንዳችን ለሌላችን ድርብ ደስታ ብለን ራሳችንን እናሻሽል።

ስንሰስት የነበረውን ልባችንን አሳልፈን እንሰጣጥ። ያለ ገደብ ያለ ልክ እንዋደድ "ለካ እንደዚህም መሆን ይቻላል" እስኪሉ ድረስ

ከሁሉም በላይ ግን በእድሜያችን ካገኘናቸው ጓደኞች በሙሉ በላይ ጓደኛሞች እንሁን ስለድብርቴ እና ጭንቀቴ ላልቅስብህ መጥተህ ስራ ቦታ ስላናደዱህ ሰዎች ንገረኝ ከዛ ሁሉንም ረስተነው ስንስቅ እናምሽ

በፊልም ምርጫ አልስማማ ብለን አንተ በቲቪ እኔ በስልኬ የተለያየ ፊልም ተቃቅፈን እንይ በዘፈን ምርጫችን እንበሻሸቅ ባነበብነው መፅሀፍ እንጨቃጨቅ

አብረን ቤተክርስቲያን እንሂድ ከዛ አብረን ጂም እንስራ አብረን እናብስል አብረን እንብላ

አንዳንድ ቀን ደግሞ እኔ ስፅፍ አንተ ስትስል ሙሉ እሁዳችንን የተለያየ ክፍል ውስጥ ሳንተያይ እንዋል

በአል ማንኛችን ቤተሰቦች ጋር እንደምናሳልፍ ለመወሰን ለአስረኛ ጊዜ እጣ እንጣል።

"ዛሬ እራት ውጪ ነን ምንም እንዳታበስዪ" ብለህ ድንገት አስቦርቀኝ ከመንገድ ያገኘሁት ነው ብለህ እንደቀልድ አስፈንጥዘኝ እንቅልፍ እንቢ ሲለን በጃኬት ተጀቡነን በእኩለ ለሊት ለወክ እንውጣ ስለጨረቃ እንራቀቅ ብዙ ኮከብ በቆጠረ እንሽቀዳደም

አውቃለሁ ሁሌ እንደዚህ አይኮንም አይደል?! እሺ ይሁን ብቻ አንተ ና እንጂ ፀቡም ቢሆን አይቅርብን እንጣላ ግን ተዘጋግተን እንኳን አንጨካከን ከእንቅልፍህ ባንነህ አልጋ ልብሱን አልብሰኝ ስራ ቦታህ ደውዬ ጓደኞችህን "ሰላም ስላልሆንን ምሳ አብራችሁት ሆናችሁ መብላቱን ቼክ አድርጉ" ልበላቸው

ራት አዘጋጅቼ ቀድሜህ ተኝቼ ስጠብቅህ ቀስቅሰኸኝ ካልታረቅን አንድ ቀን ማደር እንደማትችል ንገረኝ በእፎይታ እኔም ልነፋረቅብህ

ሲላፋ ሲጃጃል እንዳልነበረ ሰው ስለወደፊታችን እንደ ባለስልጣን እንወያይ የአስር አመት የአምስት አመት እቅድ እናቅድ

ብቻ አንተ ና እንጂ...



✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss

3.2k 0 36 12 88

Thoughts dan repost


ገጠራማ እርሻ ቦታ ነው

ባል እና ሚስት የሆኑ ገበሬዎች አዲስ ስለገዙት እቃ እያወሩ ነው - ትልቅ የአይጥ ወጥመድ ገዝተው እያወሩ ነው።

ይህንን ሲያወሩ ደግሞ አይጥ ትሰማለች...

የወጥመዱ መገዛት ያሳሰባት አይጥ ዶሮ ጋር ሄዳ ትነግራታለች..

"ታዲያ እኔ ስለ አይጥ ወጥመድ ምን አገባኝ" ብላ ፊት ነሳቻት

ከዚያም ፍየል ጋር ሄዳ ስትነግራት "የአይጥ ወጥመድ እኔን አያሰጋኝም አትነዝንዢኝ" ብላ አባረረቻት

አይጧ ተስፋ ሳትቆርጥ ላም ጋር ሄዳ ስጋቷን ስታስረዳት "የአይጥ ወጥመድ ላምን አይዛት ምን ጨነቀኝ" አለቻት

አይጧ በመልሳቸው አዝና ልጆቿን እና ዘመዶቿን ሰብስባ ከጎሬዋ ገብታ ተደበቀች

ማታ ላይ ወጥመዱ የተጠመደበት ቦታ ላይ ከፍተኛ ጩኸት ተሰማ

የቤት እመቤቲቱ ወጥመዱ ያዘልኝ ብላ ስትሄድ ለካንስ ወጥመዱ የአንድ መርዛማ እባብ ጭራ ይዟል አላየችውምና እባቡ ነደፋት

ባልየውም አካባቢው ያለ ሐኪም ቤት ወስዶ አሳክሟት ሐኪሙ የዶሮ ሾርባ ብትመገብ መልካም ነው አለ

ዶሮዋ ለሾርባ ታረደች

ቤተ ዘመድ ሚስትየውን ሊጠይቅ ሲመጣ ለመስተንግዶ ፍየሏ ታረደች

ሴትዮዋ አልሆነላትም ሕይወቷ አለፈ

ባልየው ቀብር ማስፈፀሚያ አልነበረውም እና ላሚቷን ለቄራ ሸጣት...

አይመለከተኝም አትበል !!

4.2k 0 42 7 177

#6

«በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት!»

    ልጄን እና ባለቤቴ ለኔ አለሞቼ ናቸው።ልጄም ብቸኛ ልጄ በመሆኗ እኔን የሚመስል ነገር እንዲኖራት ብመኝም ምኞቴ በምናብ ብቻ ቀረ።ለነሱ ነፍስህን ስጥ እንኳ ብባል ያለማመንታት ነው የማደርገው ፤ እነሱም ይወዱኛል ፤ ልጄ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ነበረች በጣም ጥሩ በሚባል ውጤት ነው ያለፈችው ፤ ቀጣይ ሁኔታዎችን ለልጄ  ለመወሰን ከባለቤቴ ጋር ውይይት ላይ ብንሆንም ልንስማማ አልቻልንም።የማውቃት የምሣሣላት ባለቤቴ የማላቃት እስኪመስለኝ ድረስ•••

    ዛሬ የመጨረሻ ስምምነት ላይ ለመድረስ አስቤ ልጄን የእናቷ እናት ( አያቷ) ጋር አድርሼ መኪናዬን ደጅ ላይ እንዳቆምኩ ወደ ግቢ ገባሁ። ዳንቴሏን እየጠለፈች ነበር ፤ ግንባሯን ስሜ ፊትለፊቷ ያለው ሶፋ ላይ ዘፍ አልኩ ።የባጥ የቆጡን ስናወራ ከቆየን በኋላ ትዝ ሲለኝ አስቤ ወደ መጣሁበት ጉዳይ ተሸጋገርኩ።

      “ ••• እኔ ምልሽ እማቲ የልዕልቷን ጉዳይ ሳንወስን ቆየን •••”

      “ እኔ ባለፈው እንዳልኩህ ነው ••• ወደ ጀርመን እንድትበር ነው ምፈልገው ፤ ሂደቱን ከሆነ ደግሞ እኔ ጨርሼላታለሁ ••• ስለዚህ አባት አትከራከረኝ ! ” አለች አይኔን ማየት የከበዳት ይመስል ከኪሮሿ ላይ አይኗን ሳትነቅል።

“ አይሆንም እማቲ ስንት ነገር አውርተን ተመልሰሽ እዛው ••• እኔ እዚህ ካለ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ጋር ተዋውዬ ገንዘቡንም  ከፍያለሁ፤ ደግሞ  እዚህ ኮሌጅ ለመግባት ያላትን የረጅም ጊዜ ፍላጎት እና ህልም ተውቂያለሽ ፤ ሰርፕራይዝ ላደርጋት በማሰቤ ነው ••• እንደምታይው ውጤቷም ከፍተኛ ነው ••• መሔዷንም አልከለከልኩም  ትንሽ ይራዘም ነው ያልኩሽ ••• ”

     ብዙ ተነጋገርን ፣ ተጨቃጨቅን ፣ ተከራከርን ግን ስምምነት ላይ ለመድረስ ዳገት ሆነብን ፤ ይበልጥ የተጋጋለ ክርክር ውስጥ ገባን ትግዕስቴም አልቋል ።

     “ ••• ቆይ ይህን ያህል አጣድፈሽ ልጄን ጀርመን ለመላክ እንድትቆርጭ ያደረገሽ የእውነት ጎብኝታ እና ተዝናንታ እንድትመለስ ብቻ ነው ። ”

“ አዎን ••• ይህው ነው ። ” አለች። ያለፍቃዷ እንባዋ ክልብስ እያለ መውረድ ሲጀምር ደነገጥኩ፤ ለቅሶዋ የተደበቀ እውነት እንዳለ ጠቆመኝ።

  “ አይደለም አላምንሽም ••• ብዬ ሌላ ምክንያት አለሽ እውነቱን ንገሪኝ ”
“እውነቱን ማወቅ ትፈልጋለህ ብርታቱ አለህ ••• ”


      “አዎን ንገሪኝ እስከማልቀስ ያደረሰሽማ ለጉብኝቷ ብቻ አይደለም ምንድነው? ” አልኩ በንዴቴ ላይ የማወቅ ጉጉቴ ተጨምሮ

   ሁለት ፎቶዎች አምጥታ ሰጠችኝ እና ከኔ ሶስት እርምጃ ርቃ ቆመች ። ብዙም አልገባኝም ሁለት አፍላ ወጣቶች አብረው የተነሱት ፎቶ እሱ ፀጉሩን በአጭሩ ተቆርጦ ተበጥሯል፤ የሷ አፍሮ ነው አፈ ድስት ሱሪ ለብሰዋል። ሁለተኛው ፎቶ ላይም ራሳቸው ወጣቶቹ ግን እሷ አርግዛለች እሱ ደግሞ እጁ ሆዷ ላይ አድርጎ የተነሱት ፎቶ ። አሁን ደነዘዝኩ ፤ እሱን አላወኩትም ልጅቷ ግን ባለቤቴ ናት ያኔ የልጃችን የ6 ወር ነፍሰጡር እያለች፤ ቀና ብዬ አየሗት “ አልገባኝም ምንድነው?”

   “ አዝናለሁ ሽፈራው •••አንተ የልጄ አባት አይደለህም ••• ይህን ፎቶው ላይ የምታየው ፍቃዱ ልጄን ባረገዝኩ በወሩ ከ 5 ወራት በኋላ ወደ ውጭ እንደሚበር የሚያረዳ መርዶ ከቤተሰቦቹ ደረሰን ፤ ከዛም ያኔ ካንተ ጋር ጥሩ ግንኙነት እንዳለን ስነግረው ቤተሰቦቼ አንተን እንዳገባ ወትውተውኝ ስለነበር አንተን አግብቼ ካንተ እንዳረገዝኩ በማስመሰል ወለድኳት ፤ እሱም በተመቸው ግዜ ሁኔታዎችን አመቻችቶ እኔን ና ልጄን እንደሚወስደኝ ቃል ገባልኝ ••• ይኸው አሁን ከድፍን 17 ዐመታት በኋላ ያ ግዜ ደርሶ ወደ ምወደው የልጅነት ፍቅሬ ልጄን ይዤ ልበር ነው ። ለዛ ቅድሚያ እንዳትደነግጥ አስቤልህ ነው ልጄን ለጉብኝት በሚል ልኬ እኔ በሳምንቱ ልበር ያሠብኩት ለእስከዛሬው እንክብካቤ እና ፍቅር ግን በጣም አመሰግናለሁ ••• አዝናለሁ ።”

   አናቴን በፍልጥ የተመታሁ ያህል ደነገጥኩ ፤ ምን ልበል ምላሴ ተሳሰረ ፤ ቆይ ይህን ከመርዶ የከፋ ነገር ስታረዳኝ ለስነልቦናዬ እንኳ አልተጨነቀችም ፤ ብዥ አለብኝ ከዛ ትዝ አይለኝም።
ስነቃ ማንም አጠገቤ የለም ወድቄ የነበርኩበት ቦታ ላይ ነኝ ተጣራሁ ማንም ቤት ውስጥ የለም ፤ እንደምወዳቸው እና እንደማፈቅራቸው ያህል ያፈቅሩኛል ብዬ ማስባቸው እና በነፍሴ ጭምር ምወራረድላቸው ልጄ እና ባለቤቴ የኔ አለመሆናቸውን ተረዳሁ። እውነታውን ለመቀበል ተቸገርኩ ፤ ግን ይኸው ነው ።

   በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት ግዜ አደረሰኝ፤ ግን ምን ዋጋ አለው አሠባበሬ የከፋ ሆነ።

       ✍️ መቅደስ



https://t.me/justhoughtsss


ሮበርት ዳውኒ ጁኒየር (Robert Downey Jr)

"በመውደቅ ጽንሰ-ሐሳብ አላምንም"

"ወደ ኋላ ተመልሰህ ጅምርን መቀየር አትችልም ነገር ግን ካለህበት መጀመር እና መጨረሻውን መቀየር ትችላለህ"

"ስለ ትወና የማውቀው በጣም ትንሽ ነው። እኔ በሚያስደንቅ ሁኔታ የማስመሰል ችሎታ ያለው ሰው ነኝ"

"
እኔ እንደማስበው መጥፎ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርጉት ነገሮች ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ የሚያደርጉ ነገሮች ናቸው"

"ከወላጆቼ ጋር ጥሩ ግንኙነት አለኝ ለዚህም በጣም አመስጋኝ ነኝ"

"እኔ ማድረግ የምችለው ብቸኛው ነገር በራሴ ላይ መስራቴን መቀጠል ብቻ ነው"

"እኔ ልዕለ ኃያል አይደለሁም እኔ ብዙ ደስታ ያለው ሰው ብቻ ነኝ"

"ህይወታችሁን ለመለወጥ መቼም አልረፈደም"

"ኮከብ የመሆን ፍላጎት የለኝም ታላቅ ተዋናይ የመሆን ፍላጎት አለኝ"

"በአዎንታዊ አስተሳሰብ ሃይል ውስጥ ትልቅ እምነት አለኝ"

"ትልቅነትን ለማግኘት ከፈለክ Risk ለመውሰድ ፈቃደኛ መሆን አለብህ"

"
ለመሻሻል ሁልጊዜ ቦታ አለ"

"ሕይወት ስህተት መሥራት እና ከእነሱ መማር ነው"

"ታላቅ ስራ ለመስራት ብቸኛው መንገድ አንተ የምትሰራውን መውደድ ነው"

"ፍርሃት ህይወታችሁን እንዲመራው መፍቀድ የለባችሁም"

"ስኬት ምን ያህል ገንዘብ እንዳገኘህ ሳይሆን በምትሠራው ነገር ምን ያህል እንደምትደሰት ነው"

"እራስህን በጥሩ ሰዎች መክበብ አስፈላጊ መሆኑን ተምሬያለሁ"

"ቂም ለመያዝ ህይወት በጣም አጭር ናት"


በምድር ላይ......

የዘላለም ሀብት የለም ፣የዘላለም ትምህርት የለም ፣የዘላለም ብሄር የለም ፣የዘላለም ትዳር የለም፣የዘላለም በሽታ የለም፣የዘላለም ስኬት የለም፣ የዘላለም ጓደኝነት የለም

ሁሉም ነገር ከጥቂት አመታት በኋላ እዚሁ ያበቃል!! ይራገፋል .....

እኛ ያየነው ነው ላይ ብቻ ሳይሆን እግዚአብሄር ያየልን ጋር እንኖር ዘንድ አይናችንን ይግለጥልን...
በንቃት በሙላት እና በኩራት ኖረን መሞት እንድንችል ይርዳን!

"የዘላለም አምላክ እንጂ የዘላለም ችግር የለም" ይኸው ነዉ...

6.9k 0 50 10 250

✅አንድ ቀን ቅዳሜ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ... በስሜት እየቃተተች "በደንብ አባልገኝ አለችኝ" ቃሉ ቀፈፈኝ ... አባልገኝ! ... ፈፅሞ ከእሷ አንደበት የወጣ አይመስልም፤ የእሷ ቃላት ጠያይሞች ናቸው። ይሄኛው የተቃጠለ የመኪና ዘይት የመሰለ ጥቁር የከተማ ቃል ነበር።

"እንደዚያ አትበይ ማሂ" አልኳት።

"ለምን?"

"ይደብራል!"

"ይደብርህ! አባልገኝ!!" ዝም አልኳት። ከብዙ ግርምት ጋር ።

✅በአራት አመት ቆይታችን አልጋ ላይ ከስሬ ተኝታ ከሚቆራረጥ ትንፋሿ ውጭ አንድ ቃል ስትተነፍስ ሰምቻት አላውቅም ነበር፣ የዚያን ቀን ግን ምርር ባለ ድምፅ ብዙ ብዙ ነገር አለች ... አልሰማም ብል እንኳ አስገድዶ በጆሮዬ የሚፈስ ነገር... "እንደማታገባኝ እያወቅሁ አብሬህ መተኛት ብልግና ነው ... ለመባለግ፣ ለመርከስ ፈቅጄ ነው ... ይሄ ፍቅር አይደለም፤ አባልገኝ! ... ሳሎን ውስጥ አባልገኝ፣ ሶፋህ ላይ አባልገኝ፣ ምንጣፍህ ላይ አባልገኝ፣ ኩሽናህ ውስጥ አባልገኝ..."

7k 0 21 25 117

ገና በ13 አመቱ ትምህርቱን አቁሞ ፡ ዳይመንድ ነጋዴ ከሆነው አጎቱ ጋር ተቀጥሮ መስራት የጀመረው savji dolakia ያኔ በችግር ምክንያት የተወውን ትምህርት ደግሞ አልተመለሰበትም ፡ በዛው ቀረ ።
......
ከቀለም ትምህርት ይልቅ ፡ የዳይመንድ ፈርጦች ነፀብራቅ ማረከው ፡ እና ቀስ በቀስ ከዚህ ቢዝነስ ጋር እየተዋወቀ አድጎ
ከአመታት በፊት የራሱን የዳይመድ ማምረቻ ከፍቶ መስራት ጀመረ ።
...
አሁን ህንድ ውስጥ ያለው የመጨረሻ ግዙፍ የዳይመንድ ካምፓኒ የዚህ ሰው ነው ።
.....
ህንዳዊው savji dolakia በችግር ምክንያት የትምህርቱ ነገር ባይሆንለትም በቢዝነሱ አለም ተሳክቶለታል ። ቢሊየነር ነው ። በዛ ላይ ሲበዛ ቅን እና ደግ ።
ስለደግነቱ ትንሽ ይወራለት ....
............
2016 ላይ ነው ።
የሱ ንብረት የሆነውን የHari Krishna ካምፓኒ ሰራተኞችን በሙሉ ሰበሰበ ፡ እና እንኳን ደስ አላችሁ አላቸው ።
በእናንተ ጥረት ኩባንያችን በሚገርም ሁኔታ አትርፏል ፡ እና ይህን በማስመልከት ትንሽ ስጦታ አዘጋጅተናል አለና. ..
ለአራት መቶ ሰራተኞች መኖሪያ ቤት. ... ለ 1260 ሰራተኞች ደግሞ የመኪና ስጦታ አበረከተ ።
ይህችን ነገር እንድገማት. . ለ 400 ሰራተኞች የቤት እና ፡ ለ1260 ሰራተኞች ነው መኪና የሸለመው !

ይህን ከማድረጉ ከአመት በፊትም ለ 491 ሰራተኞቹ መኪና ፡ ለሁለት መቶው ደግሞ ቤት ገዝቶ ሰጥቶ ነበር ።
.....
የሱ ስኬት የተገኘው በሰራተኞቹ ጥረት እና ጉልበት መሆኑን ሁሌም የማይረሳው savji dolakia በ2018 እንደዚሁ ለስድስት መቶ ሰራተኞች መኪና ሸልሟል ፡ እና እንዲህ እንዲህ እያለ በአጠቃላይ ካሉት 5,500 ሰራተኞች እስካሁን ድረስ ፡ አራት ሺህ የሚሆኑትን ሸልሟል ።
በቀጣይ ደግሞ የተቀሩት 1,500 ዎችም እስከጎበዙና ውጤታቸውን እስካሻሻሉ ድረስ እነሱም ይሸለማሉ ።
.....
የ savji dolakia ደግነት ይህ ብቻ አይደለም ፡ በመቶ የሚቆጠሩ ሰራተኞቹን ሰርጋቸውን ደግሶ ድሯል ። የጎጆ መውጫ ብሎ የገንዘብ ስጦታ ሰጥቷል ።
..........
በቤተሰባዊ ህይወቱ እጅግ ደስተኛ የሆነው ፡ ይህ መልካም ሰው ከወራት በፊት ደግሞ ወንድ ልጁን ፡ ሀገር ጉድ ባሰኘ ሀይለኛ ሰርግ ደግሶ ድሮታል ።
እና በዚህ ሰርግ ላይ መጥተው ቡራኬ ወይም ምርቃት የሰጡት ደግሞ የህንዱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ናቸው

6k 0 17 7 130



ለመኖር ስትል ..ላለመውደቅ ስትል ..ላለመሸነፍ ስትል
በአንድ ወይም በሌላ መንገድ የሚገጥሙህን ፈትናዎች ተቋቁመህ ለማለፍ ስትል ...

.በጥረትህ.....በልፋትህ...በድካምህ ...በጥንካሬህ....ተጣመህም ቢሆን ተጨራምተህ .ራስህን ሰው ለማድረግ ችግሮችን ሁሉ በጥሩ ሁኔታ የምትቋቋምባት ናት ህይወት በቃ ምን ልበልህ ህይወት እንደዚህ ናት!

መልካም ቀን ይሁንላችሁ
!

7.4k 0 47 1 176

ልጅ እናቱን ጠየቃት
ልጅ:- "እማዬ ለምን ታለቅሻለሽ?"
እናት:- "ሴት ስለሆንኩ ነው ልጄ።"
ልጅ:- "አልገባኝም እማዬ?"
እናቱ አቀፈችውና :-"በፍፁም አትረዳውም" አለችው።
ከዚያም ልጁ አባቱን ጠየቀ:- "እናቴ ለምን ያለምክንያት ታለቅሳለች?"
አባቱ እንዲህ ሲል መለሰ:- "ልጄ ሁሉም ሴቶች ያለምክንያት ያለቅሳሉ።"

ልጁ ጥያቄው ሳይመለስለት ....

ካደገ በኋላ ያ እናቱ ምታለቅስለት የነበረውን ነገር ለማወቅ አንድ ጠቢብ ጋ ሄዶ ጠየቀ።
"ሴቶች ለምን ያለቅሳሉ?"

ጠቢቡም መለሰለት።
❤ፈጣሪ ሴትን ሲፈጥራት ምድር ላይ ያለውን ሸክም እንድትሸከም ትከሻዋን ጠንካራ አድርጎ ነው የፈጠራት።

❤መዳፎቿንም ለስላሳ እና እረፍት የሚሰጡ አድርጎ ፈጠራት።

❤9ወር ተሸክማ አምጣ ለመውለድም ውስጣዊ ጥንካሬን ሰጣት።

❤ልጆቿ አድገው ሲያስቸግሯትም የማይጨክን አንጀት ሰጣት።

❤የቤተሰቧን ሸክም እንድትሸከም, እንድትንከባከብ, አስቸጋሪ ልጆቿንም እንደየአመላቸው ልትችል, አድገውም ቢሆን ቢያስከፏት ላትጨክንባቸው ሰፊ ልብ ሰጣት።

❤ለልጆቿም የማያልቅና የማይተመን ፍቅር እንዲኖራት አድርጎ ፈጠራት።

❤በመጨረሻ ...
እፎይ ማለት በፈለገች ሰአት እንባ የማፍሰስ አቅሙን ፈጣሪ ሰጣት።

👉ይህ የእሷ ደካማ ጎኗ ነው ያለምክንያት ቢሆንም እንኳን የሴቶችን እንባ ማክበር አለብህ።

👉አንተን ስትወልድህ እትብትህ ከእሷ ጋር ሲቆረጥ የቀረ አካል መኖሩን አትዘንጋ።
በማለት መለሰለት።

ክብር ለሴቶች ክብር ለእናቶች❤❤❤!!

8.4k 0 91 1 444

የሆነ ቀን ይመጣል: አንድ የማይቀር ቀን አለ

👇🏾

የሆነ ቀን የእናትህ የስልክ ጥሪ ናፍቆት ብቻ ይሆናል
.
"ምን አለበት ብዙ ጊዜ አብሬያት አሳልፌ በነበረ!" የምትልበት ቀን ይመጣል
.
ቀልዷ ቀርቶ ቁጣዋ የሚናፍቅህ ቀን ይመጣል
.
ትኩስ ቡናዋን እና እንጀራ በሚጥሚጣዋ ከብርንዶ እና ጠጅ በልጦ የሚናፍቅህ ቀን ይመጣል
.
ድምጿ ሁሉ ከአእምሮህ ትውስታ ጠፍቶ ይናፍቅሃል

👇🏾

በል ለእናትህ ደውልላት አሁን: ከቻልክ ሄደህ ዘይራት
.
በህይወት ከሌለች ደግሞ እረፍት ተመኝላት እና በርታ !!

መልካም ቀን !!

❤️🙌🏼

8.5k 0 44 16 316

ናታሊያ - "የእናትነት እና የሃዘን ጥግ" ይሏታል

👇🏾

ለሰባት ወራት ያህል የሞተ ልጇን ይዛ የኖረችው ቺምፓዚ የእናትነት: የሃዘኔታ እና የርህራሄ ምልክት ናት ይሏታል

ቫሌንሲያ ውስጥ ባዮፓርክ የተባለ የእንስሳት መጠበቂያ ውስጥ ናታሊያ የታቀፈችው ልጅ ሞተባት: ሆኖም ግን መልቀቅ አልፈለገችም

የፓርኩ ባለስልጣናት ልጇን ከመቀማት ይልቅ ሃዘኗን እንድትወጣ ፈቀዱላት: የሞተው ልጇን አቅፋ ሰባት ወራትን ቆየች

በስተመጨረሻ የልጇ ስጋ ከአጥንቱ ተላቅቆ ቆዳ እና አፅም የሆነባት ናታሊያ ልጇን ለመጣል ተገደደች: ለሰባት ወራት የቆየው የሃዘን ሂደቷም አለም እንዲህ መዘገበው

🙌🏼❤️

9.5k 0 42 9 283

አባቴ ሁሉ ነገርን መጋፈጥ ይሰብራል ይላል ።

...ጀግና ሁኔታን የሚረዳ ነውም ይላል ።

እኔ የምጋፈጠው ለማሸነፍ ጀግናም ለመሆን አይደለም ሲደርሱብኝ ነበር።

አፈግፍጌ አውቃለሁ።

ያፈገፈኩኝ ግዜ የሚሰማኝ ስሜት መጥፎ ነው።

አባቴ "የማያፈገፍግ ታጋይ በቶሎ ይሞታል" እያለ የውትድርና ገጠመኙን ያጣቅስልኛል።

በሕይወቱ ምድር ላይ እንደኔ የሚጨነቅበት ጉዳይ ያለ አይመስለኝም...

"እሱ ማስረዳት አይችልም... በዛ ላይ ያፈጣል ....ችግር የሚፈታው አንገት ለአንገት በመተናነቅ ይመስለዋል" ይላል ስለ እኔ ሲናገር...

"አንዱ ይገለዋል አጉል ቦታ ይመቱታል የሰው ሰው እጁ ላይ ይጠፋል" ሲል ይሰጋል።

"እኔ በሕይወት የኖርኩት እጅ ሰጥቼ ነው...ይሄው ከዛ በኃላ ያገኘሁት መዓረግ እና ደስታ ይቆጠራል ...?? "

አባቴ ትኩረቱ ስለሆንኩ መሰለኝ...
ልጁ ስለሆንኩ መሰለኝ ...
ስላሳደገኝ መሰለኝ ...
ስለሚያስብልኝ መሰለኝ ...

ከኔ በተሻለ እኔን ያውቀኛል።

ስለእኔ ገምቶ የተሳሳተበት ግዜ አላስታውስም...

"በጠበል አልወጣ ያለ ጂኒ አለበት..." ይላል።

የሆነ ቀን ተሳካልኝ ልጄ ልብ ገዛልኝ ስለቴ ሰመረልኝ ብሎ በመሃበርተኛው ፊት ተናዞ ስለቱን እንዳስገባ የመሃበርተኛው ልጅ አዲሱ ነገረኝ...

ስለት ካስገባበት ቀን ጀምሮ ሳሰላስል ልብ ገዛ እንዳለው አይነት ሰው ሆኛለሁ ።

ደርሰውብኝ ያለፍኳቸው ቀምተውኝ የተውኳቸው ትተውኝ ያለቀስኩበት ሥፍራ ብዙ ነው ።

ምን ብሎ ተስሎ ይሆን ስለቱ የሰመረው...??

ምን አለ አሁን ትልቅ ሕልም እና ሕልሙን መተግበርያ ጥንካሬ ስጠው ብሎ ቢሳልልኝ...

(በአድኃኖም ምትኩ)
(ወግ ብቻ)

9.6k 0 42 4 169

#5


"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት"......አልኳቸው...


ከዶርም ልጆች ጋር  "ረጅም ጊዜ እምነታችንን ያገኙ ግን ደሞ ውሸት የነበሩ ነገሮች" በሚል ርዕስ ዙሪያ ያጋጠመንን በየተራ ለመናገር ተስማምተን ንግግሩ ከኔ ተጀምሮ ነው.....



ከሴት ጋር አንድ አልጋ ውስጥ አጊንቼው እህቴ ናት ቢለኝ አምነው ነበር....ቤቲ ደውላ፣ ኮኪ ጠርታኝ፣ ማሂ ፈልጋኝ እያለ የሴት ስም በዝርዝር ሲጠራልኝ በአንዲቷም እንደማይቀይረኝ በሰአቱ ፍቅሩ  አረጋግጦልኛል.....


የhighschool የመጀመሪያ አመት ተማሪ እያለን ነበር ፍቅሩን መግለፅ የጀመረው....ከረጅም የእንቢታ ጊዜ በኋላ በሀሳቡ ተስማማሁ።

የሌላ ፆታ ፍቅርን ሀ ብዬ የተማርኩት በሱ ነው....ወንድሜ፣ ጓደኛዬ፣ ሚስጥረኛዬ እና ወደፊቴን አቃጄ ሆነ....24 ሰአት ልቡ እኔ ጋ ነበር....ታጋሽ፣ ትሁት፣ እኔን ደሞ እንደትልቅ ሰው አክባሪ ለኔ ከሱ በላይ አልነበረም።  እኔም ፀሎቴ ውስጥ ሳይቀር ቅድሚያ ተሰላፊ አደረኩት


የህይወታችን ወሳኙ እድሜ  ፣ አዲስ ነገር ሁሉ ሚፈጠርበት እድሜ ላይ ተገናኘንና አብሮነታችን ላይ ጥገኛ ሆንን....

ለፍቅር ያለኝ ትርጉም በዚ ግንኙነት ተመሰረተ....ማንም ፍቅረኛውን ወዶና መርጦ ካገባ በኋላ ሊከዳት ወይም ልትከዳው አትችልም, መጀመሪያም ያላፈቀረው ጋር ካልተጣመረ በቀር.....

ኮካዬን ጎንጨት ብዬ ወሬዬኔ ቀጠልኩ...

የሆነ ቀን እንደለመድነው ፍቅርሽን ለምን አትገልጪም በሚል ተጣልተን ሁለት ወይም ሶስት ቀን ተኮራረፍን( እውነቱን ነው ፍቅርን በቃል መግለፅ ላይ ጎበዝ አደለሁም😁...ተደጋጋሚ የመጣያ ርዕሳችን ነበር)።

ከዛም በሶስተኛው ቀን  እንደለመድነው ብዙ አመት ተለያይቶ እንደቆየ ሰው ስናወራ ዋልን። በዙሪያ ያሉት ጎደኞቼ ሁሉ በኛ የ24 ሰአት ወሬ እንደተማረሩ ነው...ከልጅነት እስከ እውቀት ምታወሩት አያልቅባችሁም? የሁሉም ጥያቄ ነበር


መጨረሻ ላይም ያስጨነቀው ጉዳይ እንዳለና ልነግርሽ ፈልጋለሁ አለኝ...ህመሙና ጭንቀቱን ሳልሰማው ቢያልፍ ደስታዬ....ብዙጊዜ የሱን ችግር ሰምቼ እኔ እየታመምኩ ለሱም ፈተና ሁኜበታለሁ.....  ምነው አልኩት

እንደቀላል ነገር በተደጋጋሚ ስሟን ይጠራው የነበረችው ልጅ ከሱ አረገዝኩ እንዳለችና እንዴት ልጁን እንደሚያሳድግ እንዳማክረው ጠየቀኝ.....ግራ ገባኝ...ለሱ የሴትነት ልኩ እኔ ነበረኩ....እህቱም፣ እናቱም፣ ፍቅረኛውም.....ምንም አላልኩም "እኔስ" ብቻ ነበር ያወጣሁት ቃል....
እሱም,  በፈለገው ጊዜ በአካል ስለማያገኘኝ እና ፍቅሬን ስለማልገፅ
በፍቅር ቃል ልቡን እንዳሸፈተችና ሁሌም አጠገቡ እንደነበረች ነገረኝ( እኔ የት ሂጄ ማለት ፈልጌ ስላልቻልኩ ዝም አልኩ).....እንደሰው በክብር ተጣልተን ቢሆን ለዚ የበቃነው ደስ ባለኝ ....የሱ እርጋታ ደሞ እኔን እብድ ሊያደርገኝ ደረሰ....

እንደምንም እራሴን አረጋግቼ "መቼ ነው  ኢኼ የሆነው" አልኩት... የሆነ የተለመደው ፀባችን ምሽት ላይ ከቆንጆ ወይን ጋር አጠገቡ ያገኛት እሷን ስለሆነ የኔ ክፍተት እንደሆነ በድጋሜ ነገረኝ....ሶስት ቀን ራሴን ታመምኩ

የቱ ጋር ፍዝዝ ብዬ እንደሆነ አላቅም አንቺ ጋ ነኝ እያለ እሷ ጋር የተገኘው.....

ኢኸው በመጨረሻም እስከዛሬ ያመንኩት ሁሉ ውሸት መሆኑን ደረስኩበት.....በርግጥ የትኛው እምነቴ እንደተሳሳተ አላረጋገጥኩም..... "የእውነት አፍቃሪ ሊክድ አይችልም" ያልኩት ወይስ "እሱን እራሴን ከማምነው በላይ ማመኔ"....

ቶሎ ለመፅናናቴ ትልቁን ቦታ የወሰደው ግን ኢኼ ፅሁፍ ነው "ታምኖ የተገኘ ብቻ ሳይሆን አምኖ የተገኘንም ፈጣሪ ይክሳል" ....ብዬ ታሪኬን ጨረስኩ

ሁሉም አሳዘንኳቸው መሰለኝ ዝም ብለው ቀሩ

✍ሚሚ


https://t.me/justhoughtsss

8.3k 0 25 1 105

✅''ማድረግ ያለብህ ሁሉ''እያደረክ በቀኑ መጨረሻ ላይ ባዶነትና የመንፈስ ጭንቀት እየተሰማህ ከሆነ ፣ምን አልባት ሌላ ሰው ለራሱ ደስታ የጻፈውን እየሰራህ እንጂ ማድረግ የምትፈልገውን እያደረክ አይደለም ማለት ነው። ''

✍️ ''Brianna wiest ′′📖

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988


የኢትዮጵያውያን አንድነት ዳግም የታየበት የካራማራ ድል !

የካቲት 26 ቀን 1970 ዓ/ም የሱማሊያን ዚያድባሬ ጦር ለመመከት በካራማራ ጀግኖች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የህይወት መሰዋዕትነት ከፍለው ወራሪውን ጦር ከሀገር ያባረሩበት እና የሀገራቸውን ሰንደቅ ያውለበለቡበት ቀን ነው።

በሶቪየት ህብረት ከፍተኛ የሆነ ድጋፍ የመጣው የዚአድባሪ ጦር የእናት ሀገር ጥሪ እያለ በተሰበሰበው የኢትዮጵያ ጦረኛ " ካራማራ " ላይ ድባቅ ተመትቶ ወደ መጣበት ተመልሷል።

በጦርነቱ መጀመሪያ ሶቪየት ህብረት ሶማሊያን ስትደግፍ ነበር በኃላ ላይ ወደ ኢትዮጵያ አዘንብላ ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እገዛ አድርጋለች ፤ ከኢትዮጵያ ጋር ጥሩ ግንኙነት የነበራት አሜሪካ ደግሞ ወደ ሶማሊያ ፊቷን አዙራ ነበር።

በጦርነቱ ኩባ፣ ሰሜን ኮሪያ፣ የመን እና ምሥራቅ ጀርመንን ጨምሮ ሌሎች አገራት አጋርነታቸውን ለኢትዮጵያ አሳይተዋል።

ከ16,000 በላይ የኩባ ወታደሮች በውጊያው እንደተሳተፉ መዛግብት ያሳያሉ። ደቡብ የመንም ጦሯን
#ለኢትዮጵያ አሰልፋ ነበር።

በተለያየ የፖለቲካ የትግል ሁኔታ፣ በተለያየ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ የኢትዮጵያ ሀይሎች ሁሉ ስለ ሀገር አንድ ሆነው የዚያድባሬን ጦር የመከቱበት የካራማራ ጦርነት የኢትዮጵያ አንድነት ዳግም በጉልህ የታየበት ስለመሆኑ ይነገርለታል፡፡

በየአመቱ የካቲት 26 ቀን የሚታሰበው የ " ካራማራ ድል " ዘንድሮም ለ47ኛ ጊዜ እየታሰበ ይገኛል
፡፡


#4

"በመጨረሻም ያመንኩት ሁሉ ዉሸት መሆኑን ደረስኩበት "
አለች ከተቀመጠችበት አግዳሚ ወንበር ላይ ፈንጠር ብላ በመነሳት ። አይኖች ሁሉ ወደሷ ሆኑ ። አበደች እንዴ በሚል አይነት አየናት ። ሰንበት ነው አጥቢያችን በሚገኘው ደብር የእለቱን የቤተ-ክርስቲያን ስርአት ካከናወንን ቡሃላ የንስሀ አባታችንን ለማግኘት ልጆቻቸው ሰብሰብ ብለን እየጠበቅናቸው በዚ መሀል ነበር ግቢ ውስጥ ማትጠፋው ፀይም ቆንጅዬ ልጅ ጮክ ብላ ማውራት የጀመረችው (በዝምተኝነቷ ስለምናቃት ደነገጥን)
    "አልደከማችሁም ? ሁሉንም ነገር እርግፍ አድርጎ
     መተው አላማራችሁም ? አለች ሁላችንንም እያየች
ምን እንደሆነች ስለማናቅ ሁላችንም ግራ ተጋባን !
     "እግዜሩም ደሀ ላይ ይበረታል በችግር ላይ ችግር          
      መደራረብ ያውቅበታል " አለች ወደ ሰማይ አንጋጣ
       በትዝበት እያየች
ንሰሀ አባታችን "ደህና አረፈዳችሁ ?" ብለው ወደ አዳራሹ ሲገቡ አንጋጣ ስታነባ አዩዋት
        "ወለተ ጊዮርጊስ ምነው ልጄ ምን ነካሽ ?"
         "አባ ተዉኝ ዛሬ እንኳን ይውጣልኝ "አለች
ወደኛ ዞር ብላ "እብድ መሰልኳቹ አደል ?(በጥልቅ ሀዘን ማውራት ጀመረች) በውሸት አለም ምኖር ሰው አደለም ፈጣሪ የረሳኝ በሁሉ የተገፋው ነኝ ታዲያ ማበድ ይነሰኝ ? "
         "የሆንሽውን ንገሪን እስኪ ልጄ" አሉ በእድሜ ገፋ ያሉ እናት ። በስስት ና በጉጉት ሄዳ እግራቸው ስር ቁጭ አለች ። "እውነት እማማ ይሰሙኛል ?" አለቻቸው እያነባች ። አሳዘነችኝ ለካ ጆሮም ይናፍቃል....ሴትዮዋ አንገታቸውን ነቀነቁላት ። አደለም እሳችው እኛ ሁላችንም  ለመስማት ጆሮዋችን አሹለን እየጠበቅናት ነው ።
            "እየውሎትማ እማማ...አንድ ጨካኝ ወንድም ነበረኝ በጣም ቁማርተኛ ነበር ቤት ውስጥ ምንም ነገር እስከማይቀር ድረስ እየሸጠ ተጫውቶበታል ። ከሁሉም የከፋው ግን የቤታችን ነበር....የሆነ ጥቁር ጠዋት ሱፍ የለበሱ ሰዎች ብጣሽ ወረቀት ይዘው መተው ቤቱን በቁማር እዳ እንደወሰዱት አረዱን ። እናቴ ላቧን ልጅነቷን ደሟን የጨረሰችበት ቤት ያንቺ አደለም ስትባል ልቧ ቀጥ ብሎ በዛው አሸለበች...ታሳዝናለች አይደል ?! በቃ ከዛ የኔን ነገር ተዉት ህይወቴ ግራ ገባው እዛ ና እዚ መባዘን ተግባሬ ሆነ....ከብዙ መባዘኖቼ መሀል አንድ ሰው ተዋወኩ ችግሬን ነገርኩት አለውልሽ አለኝ ትከሻውን ሰጠኝ ሳላመነታ ተደገፍኩት (የንዴት የበቀል እና የእልህ ፈገግታ ፊቷ ላይ በግልፅ ይታያል) ጥሩ ኑሮ መኖር ጀመርኩ " ብላ ጸጥ አለች ፋታ የመውሰድ አይነት ዝምታ ። ሁላችንም በጉጉት እጠበቅናት ነው ። (እኔ በበኩሌ ስንቱን አሰብኩት)

እንባዋን ጠራርጋ ተረኳን ቀጠለች "ከጊዜያት በኋላ ጸነስኩ ደስታ ምሆነውን አሳጣኝ አለም የኔ መሰለችኝ ፈጣሪዬን በብዙ አመሰገንኩ ። ስወልድ ግን ደስታዬ ተሻረ። የሞተ ነው የወለድሽው ብለው ሬሳ አስታቀፉኝ" (እንባዋ እንደጅረት ይወርዳል) ንግሯሯ በጣም ስለሰቀጠጠኝ አይኖቼን በህመም ጨፈንኳቸው እናትነት ሚገባቸው ሴቶች ፊታቸውን በነጠላ ሸፍነው ያነባሉ ።

"ይሄ ይገርሞታል እማማ....ይባስ ብሎ ባሌ ሸጠኝ ።!"
"ሸጠኝ ?!" አሉ እማማ በድንጋጤ
"አዎ ሸጠኝ " አለች ቃላቱን ረገጥ አርጋ
"ለማን ? "
"ለሴተኛ አዳሪነት " አለች ስብር ብላ
እማማ በስመአብ ብለው አማተቡ !

"ለካ ያገባውት ሰው ወንጀለኛ ቁማርተኛ ከህገ ወጥ ስራ ውስጥ ማይጠፋ ሰይጣን ነበር ። ለብዙ ጊዜ ገላዬን እየቸበቸቡ ተጫወቱብኝ እሱም ልጃችን ሲሞት ብቻዬን ጥላኝ ምንም ሳይጎልባት ሽርሙጥና ገባች እያለ ስሜን አጠፋው።"
"ኧረ በዲማው" አሉ እማማ እኛም ብንሆን ምንሰማው ነገር ክብድ ብሎናል ።

" ደሞ እኮ ልጄ ሞቶ አደለም እሱንም ሽጦት ነው። (ፊቷ ትንሽም ቢሆን ተስፋ ተነበበት) ለነፍሴ ያለች ነርስ ናት አሳዘንሽኝ ብላ የነገረችኝ ። አሳየኝ እያልኩ ብዙ ለምንኩት አስለመንኩት ጭራስ አበደች ለየላት የሞተ ልጅ ከየት ላምጣ የኔንስ ሀዘን ለምን ተቀሰቅሳለች እያለ ራሱን እንደ ፃድቅ አስቆጠረ ። እሱ ምስኪን የተገፋ አባት እኔ ግን ( ሳግ ተናነቃት) እኔ ግን እብድ ሱሰኛ ሴተኛ አዳሪ ብዙ ብዙ ተባልኩ። በጣም ስታምም ገላዬ እንደ ድሮ ተፈላጊነት ሲያጣ አውጥተው ጎዳና ጣሉኝ አባ ናቸው ከምንም አንስተው ለዚ እንኳን ያበቁኝ።" ብላ ተነፈሰች

ሁላችንም ወደ አባ ዞርን አቀርቅረው እንባቸውን ያፈሳሉ።

"በቃ እኔ ማለት እቺ ነኝ አለኝ ምለው ወንድሜ የተደገፍኩት ባሌ የፈጠረኝ አምላኬ ተባብረው ያረገፉኝ ማያቁኝ የገፉኝ ያምንኩት ሁሉ የኖርኩት ሁሉ ውሸት የሆነብኝ ሰሚ እንኳን የሌለኝ ብቸኛ " ብላ ተንሰቀሰቀሰች ። አብረናት አነባን....

ስንቶቻችን ነን የኑሮዋችንን ዉሸት ማመን ሳንፈልግ እዛው በሀሰት ምንቦራጨቅ ብናምንም መውጫው የጠፋን....ለካ አንዳንዴ ኑሮ ሀሰት መሆኑን አምኖ መቀበል እረፍት አለው....

ከቤተ መቅደስ የተከፈተው "ከንቱ ነኝ ከንቱ ከንቱ ነኝ ዋስትና መከታ እግዚአብሔር ካልሆነኝ " ሚለው መዝሙር እንባችንን አገዘው ።

                                   ✍️ ወርቅ_አለማው

https://t.me/justhoughtsss

9k 0 19 1 116

"...አንድ ሰው የሚያጋጥመው ትልቁ ህመም ረሃብ፣ድህነት አልፎ ተርፎም ሞት ሳይሆን ፍቅሩን በማይቀበል አለም ውስጥ ማፍቀርን ነው -ልብን ሙሉ በሙሉ መስጠት እና በምላሹ ባዶነትን እና ዝምታን ብቻ መቀበል ታላቁ ህመም ነው።

በውስጣችን የሚያስፈራ ተቃርኖን ተሸክመናል፡ ፍቅርን እንፈልጋለን ግን እንፈራዋለን። መቀራረብን እንናፍቃለን ግን መልሰን እንሸሻለን; እነዛን ሰዎች እንወዳቸዋለን ግን እንጠራጠራቸዋለን። ከሄዱት ጋር እንድንጣበቅ የሚያደርገን እና ከጎናችን ያሉትን ችላ እንድንል የሚያደርገን ይህ ምን አይነት እርባና ቢስነት ነው?

እኔ የሚገርመኝ፡ ፍቅር የጥንካሬያችን ፈተና ነው ወይስ የድክመታችን መገለጫ? እና ከምንም ነገር ለማምለጥ የምንገባበት ብቸኝነች የፍቅር ተፈጥሯዊ ውጤት ብቻ ነውን?

"The Brothers Karamazov" ከተሰኘው ልብወለድ የተወሰደ


አንድ ቪዲዮ እያየሁኝ ነበር

👇🏾

አንድ ማየት የተሳነው ወጣት የእግር ኳስ ስቴዲየም ከጏደኛው ጋር ገብቶ ጏደኛው ጨዋታውን እየተከታተለ ይተርክለታል

………………

አንድ የረጅም ጊዜ Best Friend አለኝ: like a Brother to me

እንደ አጋጣሚ ሆኖ አንድ የስራ አጋሩ የመስማት ችግር ያጋጥመዋል

ምን ቢያደርግ አሪፍ ነው?

👇🏾

የምልክት ቋንቋ ትምህርት መማር ጀመረ: ወዳጁን ለመርዳት እና ግንኙነታቸውን ለማስቀጠል ሲል ከስራ ሰአቱ ቀንሶ የምልክት ቋንቋ መማር👏🏼

ፈጣሪ ረድቶት ወዳጁንም ፈጣሪ ማረለት እንጂ🙏

❤️🙌🏼

9.3k 0 11 4 231

የኮርማ ፍልሚያው ሜዳ በደጋፊዎች ጩኸት እየተናጠ ነው

ተወዳዳሪው ደግሞ የምንም ጊዜው ድንቅ የኮርማ ተፋላሚው ማታዶር አልቫሮ ሙኔራ ነው

👇🏾

ኮርማው በቁጣ እየተንደረደረ ተፋላሚውን ገንድሶ ሊጥለው አረፋ እያደፈቀ ሲደነፋ ህዝቡ ማታዶር አልቫሮ ምን ሊያደርግ ይሆን ብለው በጉጉት ይጠብቃሉ

ማታዶር አልቫሮ ግን መፋለሙን አቁሙ ከስታዲየሙ ግድግዳ ጥግ ሄዶ ቁጭ አለ

ሊወጋው የመጣው ኮርማ አጠገቡ ሲደርስ አዋራውን አቡንኖ ቆመ: ስቴድየሙ ፀጥ ረጭ አለ

ማታዶር አልቫሮ ሁኔታውን እንዲህ ሲል ይገልፀዋል

👇🏾

“በዚያች ቅፅበት የኮርማው ቀንድ ላይ ያለውን ገዳይ ሃይል ረሳሁት: አይኖቹን ሳያቸው ከቁጣ ይልቅ ንፁህነቱን ተመለከትኩኝ:: ሊያጠቃኝ አልነበረም የመጣው: የህዝቡ ጩኸት እና የተገራበት መንገድ ለጠብ በመሆኑ ብቻ ነበር ሲደነፋ የነበረው: ኮርማውን ጨካኝ እንዲሆን ያደረግነው ተፋላሚዎቹ እና ህዝብ ነው" አልኩኝ

ማታዶር አልቫዶር ወዲያው ለፍልሚያ የሚጠቀምበትን ሻሞላ ጥሎ ለመጨረሻ ጊዜ የኮርማ ፍልሚያ ሜዳን ተሰናበተ

አለም ያጨበጨበለት እና ዝነኛው የኮርማ ተፋላሚ ቀንዱን አሹሎ እየደነፋ የመጣውን ኮርማ በጥቂት ርህራሄ እና ቁጭ በማለት አበረደው

ህይወቱም ተቀየረ!!

👇🏾

ምናልባትም ሃይለኛ እና ቁጡ የምንላቸው ሰዎች የሚፈልጉት ርህራሄ እና ቁጭ ማለትን ቢሆንስ እላለሁኝ

ሃይለኛ እና ቁጡ የሆኑ ሰዎች አይናቸውን ብናይ ርህራሄ እና ህመም የሞላባቸው ሊሆኑ ይችላሉ: ማየት ብቻ በቂ ነው

❤️🙌🏼

8.4k 0 40 2 168
20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.