ለቀድሞ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሽኝት ተደረገላቸው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24/2017 ዓ/ም (ኢ.መ.ብ.ባ)
ከሶስት ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲመሩ የቆዩት ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ ከኅዳር 18/2017 ዓ/ም ጀምሮ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ተከትሎ በባለሥልጣኑ የስራ ኃላፊዎች እና ሰራተኞች ሽኝት ተደርጎላቸዋል።
ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ፣ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣንን በዋና ዳይሬክተርነት በመሩበት ወቅት ተቋሙ በተለያዩ ዘርፎች ለውጦችን እንዲያስመዘግብ የሰሩ መሪ ነበሩ።
በሽኝት ፕሮግራሙ ላይ አስተያየት የሰጡ የባለሥልጣኑ ሰራተኞች፤ የነበራቸውን የአመራር ብቃትና ተቋሙ ላይ የሚታዩ ለውጦች እንዲመዘገቡ በማድረጋቸው አመስግነው፤ በተሾሙበት መስሪያ ቤት መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተዋል።
ሽኝት የተደረገላቸው ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ፣ ተቋሙ ያስመዘገበው ለውጥ የሁሉም የጋራ ስራ መሆኑን በመግለጽ፤ በቀጣይም ከባለሥልጣን መስሪያቤቱ ጋር ስራዎችን በትብብር እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ክቡር አቶ መሐመድ እድሪስ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ያስመዘገቡትን ስኬት በይበልጥ በሄዱበት ተቋም ያሳኩ ዘንድ እንመኛለን።
በመገናኛ ብዙኃን እና በማስታወቂያ ይዘቶች ላይ የህግ ጥሰት፣ የሙያ ስነ-ምግባር ግድፈት፣ የጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃ ሲመለከቱ በ9192 ነፃ የስልክ መስመር ደውለው ማሳወቅዎን አይርሱ፡፡
#ብቁ_መገናኛ_ብዙኃን_ለማህበረሰባዊ_ንቃት
#የጥላቻ_ንግግርና_ሐሰተኛ_መረጃን_በጋራ_እንከላከል
የማህበራዊ ትስስር ገፆቻችንን ይጎብኙ፦
ድረ ገጽ
www.ema.gov.etፌስቡክ
https://www.facebook.com/ethiopian.media.authority/