በመጀመሪያ ደረጃ በሚሰጡ ማስጠንቀቂያዎች ላይ የማይታረሙ የንግድ ተቋማት ላይ እስከ መጨረሻው የገንዘብ እርከን ከተቀጡ በኋላ የንግድ ፈቃድን እስከ መሰረዝ የሚደርስ ቅጣት እንዲቀጡ ይደረጋል።
ይህ ከመሆኑ በፊት ደንቡን የማስተዋወቅ ስራ በሁሉም ሚዲያዎች ይሰራል።
ደንቡን ተግባራዊ አድርገናል እዚህ ላይ ምንም አይነት ድርድር አይኖረውም የማስተዋወቁ ስራ ግን በሰፊው ይሰራበታል የቅጣት እርከኖቹን ይፋ ማድረግ ጀምረናል።
ደንቡ ዝርዝር መመሪያ በቢሮው እየተዘጋጀለት ነው በፍጥነት ጨርሰን ግልጽ እናረጋለን።
ህጉ የሚሰራው የኮሪደር ልማቱ ያለባቸውን አካባቢዎች ብቻ ሳይሆን በመላው አዲስ አበባ በ 11 ንዱም ክፍለ ከተሞች ዋና ዋና መንገድ ላይ የሚገኙ ሁሉንም የንግድ ተቋማትን ላይ ነው።
የትራንስፖርት እንቅስቃሴንም በተመለከተ ሁሉንም የግል የትራንስፖርት ሰጪ አካላትን ጨምሮ የሚመለከት ነው ይህንንም መንገድ ትራንስፖርት ባለሥልጣን ጋር በመሆን በጋራ ተፈጻሚ ይሆናል " ብለዋል።
አስተዳደራዊ የመጀመሪያ ደረጃ የገንዘብ ቅጣት እርከን ምን ይመስላል ?
➡️ ከምሽቱ 3፡30 በፊት የንግድ ተቋሙን መዝጋት 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።
➡️ ለተገልጋይ ሊያቀርብ የሚችለው አገልግሎት ወይም ምርት እያለው የለም በማለት ተገልጋይ እንዳይስተናገድ ማድረግ 10 ሺህ ብር ያስቀጣል።
➡️ መንገድ ዳር ያሉ ንግድ ተቋማት እና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከምሽት እስከ ንጋት ድረስ የተቋሙን የውጭ እና የውስጥ መብራት አለማብራት 7 ሺህ ብር ያስቀጣል።
@Ethio_fastnews@Ethio_fastnews