🔻 I ክለባችን ሊቨርፑል በዛሬዉ ጨዋታ ላይ ከ57 አመት በፊት በዛሬዋ ቀን ሙኒክ አየር መንገድ ላይ የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ፣ ስታፎች ፣ ጋዜጠኞች እና የፕሌኑ ሰራተኞች በፕሌን አደጋ ምክንያት ህይወታቹን ላጡ ሲባል ለአንድ ደቂቃ በዝምታ እና በህሊና ፀሎት የምናሳልፍ ይሆናል።
አደጋዉ የተከሰተዉ እ.ኤ.አ በ1958 ሲሆን ማንችስተር ዩናይትድ ሬድ ስታር ቤልግራዴን ከተጫወቱ በኋላ ወደ እንግሊዝ ሲመለሱ ነዉ።
ሬድ ስታር ቤልጋርድ የሰርቢያ ክለብ ሲሆን ተጨዋቾቹ ከሰርቢያ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ አስበዉ ቢሆንም ፕሌኑ ነዳጅ ስላነሰበት በሙኒክ አየር መንገድ በመብረር ነዳጅ ለመቅዳት ያርፋል ፣ አርፎም ነዳጁን ከቀዳ በኋላ በስተመጨረሻ ወደ እንግሊዝ ለመመለስ ፕሌኑ እየተንገዳገደ ለመንሳት ቢሞክርም መንገዱ በበረዶ እና በእርጥበት የተሞላ ነበረ። ለመንደገዳገድ ሁለቴ ሞከሩ አልሳካም አላቸዉ ከዛን በሶስተኛዉ ሙከራ ፕሌኑ ከቁጥጥር ዉጭ በመሆን ከአጥር ጋር ተጋጭቶ አጥሩንም አልፎ አንድ ቤት ጋር ሄዶ ተላተመ በዚህም ምክንያት ፕሌኑ ፈነዳ።
ፕሌኑ ላይ 44 ሰዎች የነበሩ ሲሆን 23 ሰዎች ህይወታቹን ሲያጡ 21 ሰዎች ደግሞ ጉዳት አስተናግደዉ ነበረ። ከ23 ሟቾች 8 የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች ፣ 3 የክለቡ ስታፍ አባላት ፣ 8 ጋዜጠኞች ፣ 2 የፕሌን ሰራተኞች ፣ 2 ተሳፋሪ ነበሩ። ከአደጋዉ ላይ ከተረፉት መካከል አንዱ በቅርቡ ህይወቱ ያለፈዉ እንዲሁም የክለቡ አይረሴዉ ሌጀንድ ቦብ ቻርልተን ይገኝበታል።
WE WILL NEVER FORGET❤️@Ethioliverpool143@Ethioliverpool143