4-3-3 World News


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


ይህ የእርሶ፣ የአንተ፣ የአንቺ፣ የእናንተ፣ የኛ የሁላችንም ድምጽ ነው! ለሃሳብ አስተያየት ለመስጠት @atsbaha12 ይጠቀሙ

Связанные каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ትምህርት ቤቴ “ቀልዶብኛል” ያለችው ተማሪ ክስ መሰረተች

የ19 ዓመቷ ወጣት የቀድሞ ትምህርት ቤቷ ላይ “አጥፍቶኛል” ስትል ክስ መስርታለች።

የፖርቶ ሪኮ ተወላጇ አሌሻ ኦርቲዝ በአሜሪካ ኮኔክቲከት ሃርትፎርድ የህዝብ ትምህርት ቤት የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷን ተከታትላ ተመርቃለች።

ወጣቷ ትምህርት ቤቱ ምንም እውቀት ሳይኖረኝና ማንበብና በትክክል መጻፍ ሳልችል “በማዕረግ” አስመርቆ ሸኝቶኛል ስትል ነው ክስ ያቀረበችው።

በአምሥት ዓመቷ ወደ አሜሪካ የመጣችው ኦርቲዝ ትምህርት ቤቱ በቸልተኝነት የሞራል ስብራት እንዲደርስብኝ አድርጎኛል ስትልም ነው ክስ የከፈተችው።

“ቋንቋውን በአግባቡና በትክክል መጻፍና ማንበብ ሳልችል የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የነፃ ትምህርት እድል ሰጥቶኛል ይህ መሆኑ ደግሞ የስሜትና የመንፈስ መረበሽ ብሎም የሥነ ልቦና ጫና አሳድሮብኛል” ነው የምትለው።

በወቅቱ ትምህርቴን አጠናቀሻል ከተባልኩ በኋላ በወሰድኩት ፈተና አቅሜን አውቄዋለሁ የምትለው ኦርቲዝ፥ ለቀለዱብኝ ጊዜ እኔም እነሱን ተጠያቂ ማድረግ እፈልጋለሁ ብላለች።

አሁን የኮሌጅ ትምህርት እየተከታተለች ያለችው ወጣት በአብዛኛው በዘመናዊ ስልኮች ላይ በሚጫኑ ቋንቋ አስተማሪ መተግበሪያዎችን እንደምትተጠቀም ትናገራለች።

ዘመናዊ ስልኮችን በመጠቀም ንግግሮችን ወደ ፅሁፍ እንዲሁም ፅሁፎቹን ወደ ንግግር እንደምትቀይርም ነው የምታስረዳው።

ሌላው ቀርቶ የኮሌጅ ማመልከቻ ደብዳቤዋን እና የወረቀት ፅሁፏን በዚህ መልኩ ተጠቅማ በመጻፍ ማስገባቷን ጠቅሳ አሁን ላይ ሁሉም ነገር አስቸጋሪ በመሆኑ ለጊዜው አቁሜዋለሁ ብላለች።

ለጊዜው የአዕምሮ ጤና ክትትል አድርጌ በተሻለ ሁኔታ እመለሳለሁም ነው ያለችው ከሲ ኤን ኤን ጋር በነበራት ቆይታ።(አራዳ FM)

@Ethionews433 @Ethionews433


ዩናይትድ ስቴትስ የንግድ ጦርነቱን ከቀጠለች ቻይና እስከ መራሩ ፍጻሜ ድረስ ለመታገል ቃል ገባች

የቻይና የገንዘብ ሚኒስቴር በአሜሪካ የታጣለውን ታሪፍ የአፀፋ ምላሽ በመስጠት ከማርች 10 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን ታሪፍ ከአሜሪካ በሚመጡ ምርቶች ላይ እንደሚጣል አረጋግጧል ። በመግለጫው ውስጥ እንደተገለፀው በዶሮ፣ ስንዴ፣ በቆሎ እና ጥጥ ላይ 15 በመቶ ታሪፍ ይጣልበታል። በማሽላ፣ በአኩሪ አተር፣ በአሳማ ሥጋ፣ በበሬ ሥጋ፣ በውሃ ምርቶች፣ ፍራፍሬዎች፣ አትክልቶች እና የወተት ተዋጽኦዎች ላይ ደግሜ የ10 በመቶ ታሪፍ ይጣልበታል።

መግለጫው አክሎም “ከመጋቢት 10 ቀን 2025 በፊት ከመነሻ ቦታ የተላኩ እና ከመጋቢት 10 ቀን 2025 እስከ ኤፕሪል 12 ቀን 2025 የገቡ ዕቃዎች በዚህ ማስታወቂያ ላይ በተደነገገው ተጨማሪ ታሪፍ አይገደዱም” ሲል ገልጿል። ዩናይትስ ስቴት የንግድ ጦርነት ድርጊቷን ከቀጠለች እስከ “መራር መጨረሻ” ድረስ እንደምትታገል ቻይና ተናግራለች። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ሊን ጂያን ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዩናይትድ ስቴትስ የታሪፍ ጦርነት፣ የንግድ ጦርነት ወይም ሌላ ዓይነት ጦርነት ማካሄድ ከቀጠለች የቻይናው ወገን እስከ መጨረሻው ድረስ ይዋጋቸዋል ሲሉ ተደምጠዋል።

በተለያዩ የአሜሪካ የግብርና እና የምግብ ምርቶች ላይ እስከ 15 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ የሚያጠቃልለው የቤጂንግ አጸፋዊ እርምጃ የቻይናን ጥቅም ለማስጠበቅ ነው ተብሏል። ሊን በተቻለ ፍጥነት ዋሽንግተን ከቤጂንግ ጋር ወደ ውይይት እንድትመለስ አሳስበዋል። የትራምፕ አስተዳደር ለረጅም ጊዜ ስጋት ፈጥሮ የነበረው በካናዳ እና በሜክሲኮ ላይ ይጣላል የተባለው የ25 በመቶ ታሪፍ በዋሽንግተን ዲሲ ሰዓት አቆጣጠር መሰረት እኩለ ሌሊት ላይ ተጀምሯል። በተመሳሳይ በቻይና ምርቶች ላይ 10 በመቶ ቀረጥ ተጥሏል።ቻይና እና ካናዳ የአፀፋ ምላሽ ሰጥተዋል።

በቻይና መንግስት ስር የሚተዳደረው ግሎባል ታይምስ ጋዜጣ ቤጂንግ የአሜሪካን የግብርና እና የምግብ ምርቶች ላይ ያነጣጠረ የመከላከያ እርምጃዋ መሆኗን ዘግቧል። ቻይና እ.ኤ.አ. በ2018 ከአሜሪካ በሚመጡ አኩሪ አተር ፣በሬ ፣አሳማ ፣ስንዴ እና በቆሎ ላይ እስከ 25 በመቶ የሚደርስ ታሪፍ ብትጥልም ለአሜሪካ የግብርና ምርቶች ትልቁ ገበያ ሆና ቆይታለች። በዓለም ከፍተኛ ኢኮኖሚዎች መካከል ሁሉን አቀፍ የንግድ ጦርነት ሊጀመር እንደሚችል የዘርፉ ባለሙያዎች ስጋታቸውን ገልፀዋል።

በስምኦን ደረጄ

@Ethionews433 @Ethionews433


ነፍሰጡር ሴትን በመምታት ፅንስ እንዲጨናገፍ ያደረገችዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣች

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዎ ወረዳ ዉስጥ ነፍሰጡር ሴትን በመምታት ፅንስ እንዲጨናገፍ ያደረገቸዉ ግለሰብ በእስራት መቀጣቷን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታዉቋል።

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የኮሚዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ለገሰ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት ተከሳሽ ስንቄ ተስፋዬ ጥቅምት 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ ከግል ተበዳይ ቅድስት ሁንዴ ጋር በተፈጠረ አለመግባባት በተነሳዉ ድብድብ ፅንስ እንዲጨናገፍ ምክንያት መሆኗ ተገልጿል ።ተበዳይ ቅድስት ሁንዴ የ4 ወር ነፍሰ ጡር ስትሆን ከተከሳሽ ስንቄ ጋር በጉርብትና እየኖሩ ሳለ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ፀብ ተነስቶ ተከሳሻ የተበዳይን ሆድ በመርገጥ መሬት ላይ ከጣለቻት በኋላ ሁለት ጊዜ ሆዷን በመርገጥ ፅንሱ እንዲጨናገፍ ማድረጓ ተገልጿል ።

የግል ተበዳይ በደረሰባት ድብደባ ከፍተኛ ደም የፈሰሳት ሲሆን የአከባቢው ሰዎች ወዲያውኑ ወደ ሆስፒታል በመዉሰድ ህክምና እንድታገኝ በማድረጋቸዉ ህይወቷ መትረፉ ተገልጿል። ፖሊስ ጥቆማ እንደደረሰዉ ተከሳሿን በቁጥጥር ስር በመዋል የምርመራ መዝገቡን በተከሳሿ ቃል ፣በሰዉና በህክምና ማስረጃ በማደራጀት ለአቃቤ ህግ ልኳል ።

አቃቤ ህግም በወንጀል ህግ ቁጥር 540 እና 543 በፅንስ ላይ በሚደረግ ወንጀል ፅንስን ማስወረድ በሚል ክስ መስርቶባታል ። ክሱ የቀረበለት የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ተከሳሿ በፈፀመችዉ ድርጊት ጥፋተኛ ሆና በመገኘቷ የካቲት 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በአራት ዓመት እስራት እንድትቀጣ የወሰነባት መሆኑን ምክትል ኢንስፔክተር ትግሉ ጨምረዉ ለብስራት ተናግረዋል፡፡

በመባ ወርቅነህ

@Ethionews433 @Ethionews433


በምዕራባዊት የጀርመን ከተማ ማንሃይም የጀርመን ካርኒቫል በማክበር ላይ በነበሩ በርካታ የበዓሉ ታዳሚዎች ላይ አንድ ግለሰብ መኪናውን በፍጥነት በማሽከርከር በፈጸመው ጥቃት በርካቶች መጎዳታቸውን ፖሊስ አስታወቀ።
በዓሉ ከመካሄዱ በፊት እስላማዊ መንግስት ወይም አይ ኤስ እየተባለ የሚጠራው ፅንፈኛ ቡድን በተለይ በኮለንና በኑረምበርግ ጥቃት እንደሚፈጽም በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አስጠንቅቆ ነበረ። በመሆኑም በዓሉ በሚከበርባቸው ከተሞች ጠንካራ የጸጥታ ጥበቃ የነበረ ቢሆንም ግለሰቡ መኪናውን በፍጥነት በማሽከርከር ጉዳት ሊያደርስ መቻሉን የአካባቢው ፖሊስ አስታውቋል።
ስለደረሰው የጉዳት መጠንና ስለጥቃት አድራሹ ማንነት ፖሊስ የሰጠው ዝርዝር መረጃ እንደሌለ ሮይተርስ ዘግቧል። አሁን በደረሰን መረጃ ደግሞ በጥቃቱ 1 ሰው ሞቷል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የትራምፕ አጋሮች ዜለንስኪ አካሄዳቸውን እንዲቀይሩ ወይም ስልጣን እንዲለቁ ግፊት እያደረጉ መሆኑ ተነገረ

ከዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ቅርርብ ያላቸዉ ከፍተኛ የሪፐብሊካን ባለስልጣናት የዩክሬኑን ፕሬዝዳንት ቮልዲሚር ዘለንስኪን ከሩሲያ ጋር በሚያደርጉት ጦርነት ላይ ያላቸውን አቋም እንዲቀይሩ ወይም ወደ ስልጣን እንዲለቁ በመገፋፋታቸዉ ባለፈው ሳምንት አወዛጋቢው የዋይት ሀውስ ስብሰባ በዩክሬን መሪ ላይ ጫና ፈጥሯል።

የአውሮፓ መሪዎች እሁድ እለት በለንደን በተካሄደው ስብሰባ ላይ ለዘለንስኪ አጋርነታቸዉን ያሳዩ ሲሆን የብሪታኒያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኬይር ስታርመር አጋሮቻቸው የመከላከያ ጥረታቸውን እንዲያጠናክሩ አሳስበዋል፡፡ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ በሞላላዉ የዋይት ሀዉስ ጽህፈት ቤታቸዉ ውስጥ ከዘሌንስኪ ጋር ከተጋጩ በኋላ የታቀደዉን የማዕድን ውል ሳይፈርሙ ቀደም ብሎ እንዲሄድ ምክንያት ሆኗል፡፡

ዘሌንስኪ በስብሰባው ላይ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እ.ኤ.አ. በ 2019 የተኩስ አቁም ስምምነትን አላከበሩም እና ገዳይ እና አሸባሪ ናቸዉ ሲሉ ተከራክረዋል ።የትራምፕ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልትዝ ዘለንስኪ ጦርነቱን ለማቆም ለመደራደር ዝግጁ መሆናቸዉን ለዋሽንግተን አስተዳደር ግልፅ አይደለም ብለዋል። ዋልትዝ የትራምፕን ግብ በሞስኮ እና በኪየቭ መካከል የግዛት ስምምነትን በማካተት በአውሮፓ የሚመራ የደህንነት ዋስትናን በመተካት ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን አጽንኦት ሰጥተዋል።

ትራምፕ ዘለንስኪ ከስልጣን እንዲለቁ ይፈልጉ እንደሆነ የተጠየቁት ዋልትዝ "ከእኛ ጋር የሚመክር፣ በመጨረሻም ከሩሲያውያን ጋር እና ይህን ጦርነት የሚያቆም መሪ እንፈልጋለን" ብለዋል።"የፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ግላዊ ወይም ፖለቲካዊ ተነሳሽነት በሀገራቸው ውስጥ ያለውን ውጊያ ከማስቆም የተለየ መሆኑ ከታወቀ፣ በእጃችን ላይ እውነተኛ ጉዳይ ያለን ይመስለኛል" ሲሉ ዋልትዝ አክለዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ የትራምፕ አጋር እና የዩክሬን ተሟጋች የሆኑት የደቡብ ካሮላይና ሴናተር ሊንሴይ ግራሃም ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት የዋይት ሀውስ ግጭትን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ ከዘለንስኪ ጋር መስራት ትችል እንደሆነ ጥያቄ እንደፈጠረባቸዉ ተናግረዋል፡፡

በስምኦን ደረጄ


@Ethionews433 @Ethionews433


በሳዑዲ ዓረቢያና በኦማን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 470 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በዚህ ሳምንት ውስጥ 180 ወንዶች፣ 109 ሴቶች እና 13 ጨቅላ ህፃናት በድምሩ 302 ኢትዮጵያውያን ከሳዑዲ ዓረቢያ ወደ ሀገር የተመለሱ ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 56 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

በተያያዘ ዜና በሳምንቱ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 157 ወንዶች 11 ሴቶች በድምሩ 168 ኢትዮጵያውያን ከኦማን ወደ ሀገራቸው የተመለሱ መሆኑ ታውቋል።

ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ ይገኛል፡፡

ከሚያዚያ 04 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ በሚገኘው ከሳዑዲ ዓረቢያ ዜጎችን የመመለስ ስራ እስካሁን 91 ሺህ 420 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ ተችሏል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የ2.4 ሚሊዮን ሕፃናትን ሕይወት የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
***

በዓለማችን ከከፍተኛ ደም ለጋሾች አንዱ የሆኑት እና በደማቸው በሚገኘው ፕላዝማ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሕፃናትን የታደጉት አውስትራሊያዊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ጄምስ ሃሪሰን ሕይወታቸው ያለፈው በአውስትራሊያ፣ ኒው ሳውዝ ዌልስ በሚገኝ የእንክብካቤ ማዕከል በእንቅልፍ ላይ ሳሉ መሆኑን ቤተሰቦቻቸው አስታውቀዋል።

ሃሪሰን የ88 ዓመት አዛውንት ነበሩ።

‘ባለ ወርቃማ ክንዱ' በሚል በአውስትራሊያ የሚታወቁት ሃሪሰን፣ ደማቸው ውስጥ የሚገኘው ፕላዝማ እምብዛም የማይገኘውንና በደም ውስጥ በሽታ የመከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበትን ‘አንቲ ዲ’ን የያዘ ነበር። ይህ ‘አንቲ ዲ’ የሚለገሰው የገዛ ራሳቸው ደም ፅንሳቸውን ለሚያጠቃባቸው ነፍሰ ጡር ሴቶች ነው።

ፕላዝማ የሰውነት የበሽታ መከላከያ ሥርዓት (አንቲ ቦዲ) የሚዘጋጅበት በደም ውስጥ የሚገኝ ፈሳሽ ክፍል ነው።

ሃሪሰን ደም ለመለገስ ቃል የገቡት የ14 ዓመት ታዳጊ ሳሉ ቀዶ ሕክምና ሲያደርጉ ደም ከተለገሰላቸው በኋላ እንደነበር የአውስትራሊያ ቀይ መስቀል የደም አገልግሎት ሃሪሰንን ለመዘከር ባጋራው ጽሑፍ ጠቅሷል።

ከዚያም የ18 ዓመት ወጣት ሳሉ ጀምረው ፕላዝማ መለገስ የጀመሩ ሲሆን፤ እስከ 81 ዓመታቸው ድረስ በየሁለት ሳምንቱ ደማቸውን ሲለግሱ ቆይተዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ በ2015 ፕላዝማ በመለገስ የዓለምን ክብረ ወሰን ይዘው እስከ 2022 ቆይተዋል። ከዚያ ግን ይህን ክብረ ወሰን በአሜሪካዊ ግለሰብ መነጠቃቸውን የቢቢሲ ዘገባ አስታውሷል።

የሃሪሰን ሴት ልጅ ትሬሲይ ሜሎውሽፕ፣ አባቷ ያለምንም ክፍያ እና ህመም የበርካቶችን ሕይወት ስለታደገ ኩራት እንደሚሰማት ገልጻለች።

"ሁልጊዜም ይህን ማድረጉ ምንም እንደማይጎዳው ይናገር እና ‘የምትታደጊው ሕይወት ያንችም ሊሆን ይችላል' ይል ነበር" ብላለች።

ሜሎውሽፕ እና የሃሪሰን ሁለት የልጅ ልጆች የአንቲ ዲ ተቀባይ ናቸው።

"ይህም ሃሪሰንን ልክ እንደኛ ሁሉ በርካታ ቤተሰቦች በእርሱ ደግነት መኖር በመቻላቸው ደስተኛ ያደርገው ነበር" ብላለች።

@Ethionews433 @Ethionews433


ኢትዮጲያዊቷ የእግር ኳስ ተጫዋች ወንድ ነሽ ቢሉኝም እኔ ግን ሴት ነኝ መገለሉ ይቁም ስትል ተናገረች

(ከአራት ዓመት በፊት የተሰራ ዘገባ)

ለሀዋሳ ከተማ የምትጫወተዉ መሳይ ተመስገን በተያዘዉ የዉድድር ዓመት የሴቶች ፕርሚየር ሊግ በኮከብ ግብ አግቢነት እየመራች ትገኛለች፡፡

ጾታዋን በተመለከተ በርካቶች ጥያቄን ያነሳሉ አንዳንዶችም ከፍተኛ የመገለል በደል እንደሚያደርሱባት ከጋዜጠኛ ምህረት ተስፋዬ ጋር በነበራት ቆይታ ተናግራለች፡፡

ተጫዋቿ በ2006 ዓመት ባህር ዳር ላይ ተዘጋጅቶ በነበረ የክልሎች ሻምፒዮና ጨዋታ ላይ በአንድ ጨዋታ አራት ግቦችን ታስቆጥራለች፡፡ይህ ግን መደነቅ አልነበረም ያተረፈላት ይልቁኑ ይህ ተጫዋች ወንድ ነዉ፤አብሮን ሊጫወት አይገባም የሚሉ ዘለፋና የደጋፊዎች ስድብ ከምቆጣጠረዉ በላይ ስሜቴን የጎዳ ክስተት ነበር ስትል መሳይ ተመስገን ተናግራለች፡፡

በእንዲህ ዓይነት ጫና እና ወከባ የተነሳ ከሶስት ዓመታት በላይ ከዉድድር ራሷ እንድታገል አስገድዷታል፡፡በድጋሚ ወደምትመደዉ ስፖርት እንድትመለስ አሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ ትልቁን ድጋፍ እንዳደረገላትም ታነሳለች፡፡

እግር ኳስ ፌደሬሽኑ በጠየቀዉ መሰረት ምርመራዉን አከናዉና በምርመራዉ ሴት መሆኗ ተረጋግጦላታል፡፡ምም እንኳን መሳይ በምርመራዉ ሴት መሆኗ ቢረጋገጥም በሜዳና ከሜዳ ዉጪ ስሜቷን የሚጎዱ ዘለፋና መገለል ደርሶባታል፡፡

የሰዉነቴ አቋም እኔ ፈልጌ ያመጣሁት አይደለም፡፡ፈጣሪ የሰዉ ልጆችን ሲፈጥር በምክንያት ነዉ፡፡ ስለ እኔ ብዙ የሚሉ ሰዎች ግጭታቸዉ ከእኔ ጋር ሳይሆን ከፈጣሪ ጋር ነው፡፡

መሳይ የማንችስተር ዩናይትድ ደጋፊ መሆኗን የምትናገር ሲሆን ከወጪ የክርስቲያኖ ሮናልዶ አድናቂ ከሀገር ዉስጥ ደግሞ የሽታዬ ሲሳይ አድናቂ መሆኗን የብስራት ሬዲዮ የቀድሞ ዘጋቢ ምህረት ተስፋዬ ተናግራለች፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


እስራኤል የሙስሊም ረመዳን እና የአይሁዶች የፋሲካ በዓል እስኪያልፍ ድረስ በሚል ለቀጣይ ስድስት ሳምንታት የጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነትን በጊዜያዊነት ለማራዘም ወሰነች

የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጽሕፈት ቤት ይህንን ያስታወቀው ቀደም ሲል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ቅዳሜ እኩለ ሌሊት ላይ ካበቃ በኋላ ብዙም ሳይዘገይ ነበር።

@Ethionews433 @Ethionews433


ልጆቼ ይቅርታ!

ለልጆቼ የማወርሰው የለኝም፣ የምኖረው በቤት ኪራይ ነው የምሰራው የመንግስት መስሪያ ቤት በሹፌርነት ነው!

ለበርካታ ዓመታት ያጠራቀምኳትን የልጆቼን ውርስ ለመቄዶንያ ለመስጠት ነው የመጣውት!

አካውንቴ ላይ 107ሺህ ብር አለ ያሉት አቶ አብርሃም 100 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጎልናል!

አቶ አብርሃም ልጆቼ ይቅርታ የማወርሳችሁ ገንዘብ አይደለም
ለእናንተ የሚጠቅማችሁ መቄዶንያን ባወርሳችሁ ነው ብለዋል!

@Ethionews433 @Ethionews433


እስራኤል ምንም አይነት የሰብአዊ እርዳታዎች ወደ ጋዛ ሰርጥ እንዳይገቡ ማስቆሟ ተነገረ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በእስራኤልና በሀማስ መካከል ሲተገበር የቆየዉ የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያ ምዕራፍ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ ለመቀጠል ስምምነት ላይ ሳይደረስ መጠናቀቁ ይታወቃል። ይንንም ተከትሎ ነዉ እስራኤል የሰብአዊ እርዳታዎችን ያስቆመችዉ።

ቀደም ሲል እስራኤል የተኩስ አቁም ስምምነቱ በጋዛ የረመዳን እና የፋሲካ ወቅቶች እስኪያልቁ እንዲራዘም በአሜሪካ የቀረበዉን ሃሳብ እንደምትቀበል አስታውቃ ነበር።

ሃማስ በጋዛ ቋሚ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ለመድረስ እስራኤል የተፈራረመችውን ስምምነት ምዕራፍ ሁለት ተግባራዊ ለማድረግ ያለዉን ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል።

በሌላ በኩል በጋዛ የሚገኙ ፍልስጤማውያን በግዛቲቱ የተከሰተዉን ውድመት ተከትሎ ወደ ጦርነት ሊመልሰን ይችላል የሚል ፍራቻ እንዳላቸው በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ የተቀደሰዉ የረመዳን ወር የፆም የመጀመሪያ ቀናቸውን በያዙበት ቀን ገልፀዋል።

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በጦርነቱ እስካሁን 48,388 ፍልስጤማውያን መሞታቸውን ሲያረጋግጥ 111,803 ሰዎች ቆስለዋል ብሏል። እ.ኤ.አ. በጥቅምት 7 ቀን 2023 በተጀመረዉ የእስራኤል ሀማስ ጦርነት ቢያንስ 1,139 እስራኤላዉያን ህይወታቸዉ ያለፈ ሲሆን ከ200 በላይ በምርኮ ተወስደዋል። ዘገባዉ የአልጀዚራ ነዉ

በ- ሊያ ክብሮም

@Ethionews433 @Ethionews433


#alert

በትግራይ ክልል አብዛኛው ቦታዎች ዛሬ የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበረ መረጃዎች ደርሰውኛል። መቀለ ፣ ዓድዋ ፣ አክሱም ፣ ውቅሮ እና ሌሎች አከባቢዎች ተሰምቷል።

@Ethionews433 @Ethionews433


የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል...

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ እና መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡

@Ethionews433 @Ethionews433


“ዘለንስኪ ይቅርታ ይጠይቀኝ“ ትራምፕ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩኬሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በዋይት ሃውስ ያደረጉት ዱላቀረሽ እሰጣገባ አሁንም የዓለምን ትኩረተ እንደሳበ ነዉ።

ይህን ተከትሎ ፕሬዚዳንት ትራምፕ የዩኬሬኑ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ በዋይት ሃውስ ላሳየው የማይገባ ድርጊት በይፋ ይቅርታ እንዲጠይቃቸው እንደሚፈልጉ ብሉምበርግ አስነብቧል። ፕሬዝዳንቱ ይህን ማለታቸው ደግሞ በበርካቶች ዘንድ ግርምትን እያጫረ ነዉ።

ዘለንስኪ በኋይት ሀዉስ ባደረገዉ ዉይይት ሰብዓዊ ክብር ተነፍጎታል የቃላት ዉረፋና ጊዜዉን ያልጠበቁ ጥያቄዎች ማስተናገዱ አግባብ አደለም በሚል በርካቶች የሶሻል ሚዲያ ርዕስ አድርገዉታል። ይህ ባልረገበበት ሁኔታ የትራንፕ ጥያቄ ደግሞ ተአምር ማሰኘቱ ተደምጧል።

ዘለንስኪ ከዋይት ሀውስ ከወጡ በኋላ በቀጥታ ያመሩት ወደ እንግሊዝ ሲሆን 2.6 ቢሊዮን ዶላር ተበድረው መመለሳቸውም ተሰምቷል።

የአውሮፓ ህብረት ደግሞ በመጪው አርብ የ100 ቢሊዮን ዶላር ለዩክሬን ድጋፍ ለማድረግ አቅዷል ሲሉ የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ተናግረዋል።

በ-ማህሌት ግርማ

@Ethionews433 @Ethionews433


ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀመጡ

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አፅቀ ሥላሴ የ129ኛው የዓድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ በዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት ስር የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በመርሐ ግብሩ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በዓሉ “ዓድዋ የጥቁር ሕዝቦች ድል” በሚል መሪ ሃሳብ ነው ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮችን ጨምሮ በተቋማት፣ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጽ/ቤቶች እየተከበረ የሚገኘው።

በዚህ መሰረትም በዓሉ በአዲስ አበባ ከተማ ዳግማዊ አፄ ሚኒሊክ ሐውልት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ተጀምሯል፡፡

በአርበኞች እና በአሁኑ ትውልድ መካከል የሰንደቅ ዓላማ ርክክብ እንደሚደረግ እና የዓድዋ ድል በዓልን የተመለከተ ጥናታዊ ጽሑፍ እንደሚቀርብም ተመላክቷል፡፡

@Ethionews433 @Ethionews433


4-3-3 ስፖርት በኢትዮጵያ™ dan repost
የተሰጠኝ ህይወት ዛሬ በነፃነት ፣ ደም ተከፍሎበታል ከደም እና ከአጥንት ...ምስጋና ለነሱ ለአደዋ ጀግኖች ፤ ትናገር አደዋ ትናገር ትመስክር...!!!!!⚔️🎶

እንኳን ለ129ነኛው የአድዋ ድል መታሰቢያ ዕለት አደረሳቹ 🇪🇹

@Bisrat_Sport_433et @Bisrat_Sport_433et


የአውሮፓ ሀገራት መሪዎች ለዩክሬን ያላቸዉን ድጋፍ እየገለፁ ነዉ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር በዋይት ሀውስ የነበራቸዉን ፍጥጫ ተከትሎ አዉሮፓዉያኑ ከዩክሬን ጎን መሠለፋቸዉን ተናግረዋል።

የጀርመን ፣ የፈረንሳይ ፣ የስፔን ፣ የፖላንድ እና የኔዘርላንድስ መሪዎች ዩክሬንን የሚደግፉ የማህበራዊ ሚዲያ መልዕክቶችን ካስተላለፉት መካከል ሲሆኑ ዘለንስኪም ለእያንዳንዳቸው
ድጋፍ በቀጥታ የምስጋና ምላሽ ሰጥተዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ከኋይት ሀውስ መልስ በእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ኪር ስታርመር በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለንደን መግባታቸውም ተገልጿል።

ለዩክሬን ድጋፋቸዉን እያሳዩ ከሚገኙት መካከል የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን "አጥቂ ሩሲያ፤ ተጎጂ ዩክሬን ዩክሬንን መርዳት እና በሩሲያ ላይ ከሶስት አመት በፊት ማዕቀብ መጣላችን ትክክል ነበር" ማለታቸዉ ተሰምቷል።

ለዩክሬን የድጋፍ መልእክቶች ከላኩ ሀገራት ኦስትሪያ፣ ቤልጂየም፣ ክሮሺያ፣ ዴንማርክ፣ ኢስቶኒያ፣ ፊንላንድ፣ አየርላንድ፣ ላትቪያ፣ ሊትዌኒያ፣ ሉክሰምበርግ፣ ሞልዶቫ፣ ሮማኒያ፣ ስዊድን እና ስሎቬንያ ተጠቃሽ ናቸዉ።

በዛሬዉ ዕለት የኔቶ ዋና ፀሃፊ ማርክ ሩት ከዋይት ሀውስ ስብሰባ በኋላ ከዘለንስኪ ጋር ሁለት ጊዜ መነጋገራቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል። ዘገባዉ የቢቢሲ ነዉ።

በ- ሊያ ክብሮም

@Ethionews433 @Ethionews433


ግብ ጠባቂዎች ከ8 ሰከንድ በላይ ኳስ ማቆየት የማይችሉበት አዲስ ህግ ጸደቀ
****

የአለም አቀፉ እግር ኳስ ማህበር ቦርድ (IFAB) ግብ ጠባቂዎችን በተመለከተ አዲስ ህግ አውጥቷል።

ግብ ጠባቂዎች ኳስን እጃቸው ላይ ከ8 ሰከንድ በላይ ካቆዩ ዳኞች ለተቃራኒ ቡድን ማዕዘን (ኮርና) መስጠት የሚችሉበትን ህግ ማጽደቁን ይፋ አድርጓል።

ህጉ ከቀጣይ የውድድር ዓመት ጀምሮ የሚተገበር እንደሆነም ነው የተገለጸው።

አሁን በትግበራ ላይ ያለው ህግ ግብ ጠባቂዎች ኳስን ከ6 ሰከንድ በላይ የሚያቆዩ ከሆነ ማስጠንቀቂያ ካርድ የሚሰጥበትና እንደ ሁኔታው ቀጥተኛ ያልሆነ ቅጣት ምት (indirect free kick ) የሚሰጥበት ነው።

በአንተነህ ሲሳይ

@Ethionews433 @Ethionews433


ዶናልድ ትራምፕ እና ምክትል ፕሬዝደንት jd ቫንስ ፡ የዩክሬኑን ፕሬዝደንት ወደ ዋይት ሀውስ ሲጋብዙት ይህን ያህል ይገዳደረናል ብለው አላሰቡም ነበር ።

እና የዩክሬንን ሀብት ለመዝረፍ የሚያስችላቸው ሰነድ ላይ ለመፈረም እንዳልፈቀደ ሲያውቁ ፡ ሰውየው ምንም ይሁን ምን የዩክሬን ፕሬዝደንት ሆኖ እስከመጣ በክብር እንደማናገር እሱንም ሀገሩንም ፡ መሳደብ እና በዛ መልኩ ማናገር ሲጀምሩ. . በርቀት ሆና ማስታወሻ ትይዝ የነበረች አንድ ሴት በተፈጠረው ነገር አዝና አንገቷን ደፋች ።
......
የሀገሯ እንዲህ በአደባባይ መዋረድ ስሜቷን ነክቶት ጉንጮቿ ቀልተው እንባ ተናነቃት ፡
ይህች ሴት Oksana Markarova ትባላለች በአሜሪካ የዩክሬን አምባሳደር ናት ።
ሀገር ስትዋረድ ፡ ሀገር ስትጠፋ ፕሬዝደንቷ በዚህ መልኩ ክብር ሲያጣ ምን ታርግ ?(ዋሲሁን ተስፋዬ)

@Ethionews433 @Ethionews433


Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish
ባለመግባባት የተጠናቀቀው የፕሬዚደንት ትራምፕና የዩክሬኑ ፕሬዚደንት ዘለንስኪ የዋይት ሀውስ ቆይታ።

@Ethionews433 @Ethionews433

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.