ጦብያን በታሪክ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Ta’lim


ኖር
— ስለ ኢትዮጵያ የማነባቸውን /አልፎ አልፎም ጉዞዎቼን/ እዚህ አስቀምጣለሁ ደስ ካላችሁ አንብቡ። ሌሎች ከኢትዮጵያ ያልሆኑ ነገሮችን ባጋራም አብዛኛው ከወዲህ ነው፡፡
Predominantly (but not strictly) about Ethiopia and Ethiopian history.

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


እግዚአብሔር ይስጥልኝ!! ደርሶኛል 😍


አሁንም ድጋሚ ላስቸግራችሁ ነው፡፡ የሀዲስ ዓለማየሁን ትዝታ መጽሐፍ በፕዲኤፍ ሳይሆን የታተመው ያላችሁ፡ ገጽ 28ን ፎቶ አንስታችሁ ላኩልኝ? PDF ላይ ብዙ ጽሑፍ ተዛብቷል።

@hewansemon ላይ አለሁ




አመሰግናለሁ፡ ለሌላችሁም ይኸው


የሀዲስ ዓለማየሁ ትዝታ መጽሐፍ አጠገባችሁ ያለ — ገጽ 28ን ፎቶ አንስታችሁ ትልኩልኛላችሁ እባካችሁ?

@hewansemon ላይ አለሁ


ሃምበርግ የሚዘጋጀው ኤትዮፒካ ጆርናል ኢትዮጵያዊ ጸሐፊያን እንዲያሳትሙ፣ ጽሖፎቻቸውን እንዲልኩ እየጠየቀ ነው። አርቲክሎቻችሁን ላኩ እና ይታተምላችሁ እባካችሁ።

https://journals.sub.uni-hamburg.de/aethiopica/index




Also: BOOK Lauch at AAU

ያሁኑ ዓርብ፣ ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ በራስ መኮንን አዳራሽ


ፍልስፍና ተማሪዎች፡ የካንትን 300 ዓመት ልደት በማስመልከት ደግሮይተር ብዙ መጻሕፍትን/አርቲክሎችን በነጻ እያከፋፈለ ነው።
ይኸውላችሁ ሊንኩ ማየት ለምትፈልጉ፡ https://cloud.newsletter.degruyter.com/kant300


የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ የውይይት መድረክ፡ ስለ ቅርስ ጥበቃ


Call_Senior_Researcher_Coordinator_ZEF_University_of_Bonn_Germany.pdf
541.4Kb
PhD ያላችሁ ይሄን ክፍት የሥራ ቦታ እዩ እስቲ


ድጋሚ የቀረበ፡ ስለ አጼ ቴዎድሮስ

«የካሳ ጀግንነት በ1845 ዓ.ም. ሀገር ያረጋገጠው ሀቅ እየሆነ ሲመጣ ሣልሳዊ አጼ ዮሐንስን ከሥልጣን ለማስወገድ ፍላጎት እንዳለው በዘራፍ ግጥም ሐሳቡን አሳወቀ። መሳፍንቱ ወዲያውኑ መልስ ሰጡ፡ እቴጌ መነን

«ይሄ ቅዋርኛ፤
የፍየል እረኛ።»

ሲሉ ገጠሙ።
በደጃዝማች ወንድይራድ ግቢ የነበረ አንድ አዝማሪ ደግሞ እንዲህ ሲል ገጠመ፡

«ሽህ ብረት ከህዋላው ሽህ ብረት ከፊቱ
ሽህ ነፍጥ ከህዋላው ሽህ ነፍጥ ከፊቱ
ይሄን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ
በሸዋ በትግሬ የተቀመጣችሁ
በጎጃም በላስታ የተቀመጣችሁ
አንድ ዛላ በርበሬ መንቀል አቅትዋችሁ
ቆጥቁጦ አንገብግቦ ለብልቦ ይፍጃችሁ።»

እናት፣ ልጅ፣ እና የቤተመንግሥት ባለሟሎች በሙሉ ካሳን በአይሻል ጦርነት ገጠሙት። ድል አደረጋቸው፤ አጼ ዮሐንስም ውጤቱን ተቀብለው ጀግንነቱን አመኑ። በየፉከራቸው የሰደቡትን በሙሉ ታድያ ካሳ ተራ በተራ ቀጣቸው። እቴጌ መነንን እህል እንዲፈጩ፣ ደጃች ወንድይራድን ብዙ ኮሶ እንዲጠጣ ቀጣቸው። የሰደበውንም አዝማሪ አስጠርቶ ምንድን ነው ያልከኝ ብሎ ጠየቀው፡

«አፍ ወዳጁን ያማል የሚሰራው ሲያጣ
ሽመል ይገባዋል ያዝማሪ ቀልብ አጣ» ሲል መለሰ።

የካሳ ጭካኔ በዚህ ጊዜ ታወቀ። አዝማሪው ተስፋ ያደረገው ቀድሞ ስለሚተዋወቁ ይቅርታ የሚደረግለት መስሎት ነበር ነገር ግን እራሱ እንደገጠመው በሽመል ተደብድቦ እንዲሞት ተፈረደበት።

አንዲት ሴት አዝማሪ ግን ይቅር ተብላ ወደሀገሯ እንድትሄድ ተፈቅዶላታል። እንዲህ ስላለች፡

«እርሱ አይሰማም ብየ እንደት በጉድ ወጣሁ
መንጠልጠያ ባገኝ እሰማይ በወጣሁ
መውረጃ ባገኝም እምድር በገባሁ።» »

ከፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት
ገጽ 51




ደስታ ተክለወልድ ላይ «ቋድ» ተብሎ ተገኝቷል።

ላገዛችሁኝ ሁሉ አመሰግናለው እግዚአብሔር ይስጥልኝ።


Friends, ሰላም ብያለሁ፡፡

አንድ የቆየ ጽሑፍ ላይ የመሣሪያ ዝርዝሮች አግኝቼ የሆነ ቦታ ላይ «ባለቃድ» ይላል።

ቃድ ግን ምን እንደሆነ ለማወቅ ያልሄድኩበት የለም፤ ሰዉም፣ መዝገበ ቃላቶቹም ሊያግዙኝ አልቻሉም። ቃድ ምን ማለት እንደሆነ የሚነግረኝ አለ? የሚያውቅ? ወይ ሌላ ቦታ ተጽፎ ያየ? ብትጽፉልኝ ደስ ይለኛል።

አመሰግናለሁ










Video oldindan ko‘rish uchun mavjud emas
Telegram'da ko‘rish

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.