እንጠንቀቅ! ነገ እኛው ላይ መሞከሩ አይቀርም‼️ ዛሬ እንዲህ ሆነ...አራት ኪሎ መንበረጸባዎት ቅድስት ሥላሴ ተሳልሜ ወደ ስራ ለማቅናት ረፋድ አካባቢ ከቤት ወጣሁ።
ወደታክሲ ተራ እያቀናሁ እያለ አንድ አጠር ጠቆር ያለ ነጠላ ላዩ ላይ ጣል ያደረገ ልጅ "እናት እናት እባክሽ ቦታ ጠፍቶብኝ ነው ወደዚህ አካባቢ ጫላ ህንጻን ታቂዋለሽ?" አለኝ። እንደማላውቀው ነገርኩት።
"ወይኔ ወዴት ሄጀ ልፈልገው ባለቤቴ እመጫት ናት ቤት ብቻዋን ስለሆነች ቶሎ መመለስ ነበረብ ምን ይሻለኛል"እያለ አብሮኝ እየተራመደ ያወራል። የኔ ምላሽም ባውቀው እጠቁምህ ነበር ነገር ግን አላቀውም ብየው መንገዴን ቀጠልኩ።
በዚህ መሀል አንዲት እንደሱ ነጠላ የለበሰች ጥላ የያዘች ሴት ጠጋ ብላ ምን ልርዳህ አለችው... የሚፈልገውን ነገራት። እሱ በቀኝ እርሷ በግራ ሆነው እኔን መሀል አድርገው ማውራታቸውን ቀጠሉ። ቀደም ቀደም ብየ ስራመድ አንድ መነጸር የለበሰ በእጁ አጀንዳ የያዘ ሰው ተቀላቀለን።
ከዚያ በኋላ ሴቷ አፍጫሽ ላይ ጥቁር ነገር አየሁ ብላ ወደአፍንጫየ ተጠግታ ነካችኝ....ያኔ መደንዘዝ ጀመርኩ። አስፓልቱን አሻግረው ብር የሚመስል ቀለም ወዳላት ቪትስ መኪና ውስጥ አስገቡኝ።
መኪና ውስጥ ብዙ ያወራሉ ግን አይሰማኝም ድንዝዝ ብያለው። ማውራት አልችልም። የሚያወሩት ነገር ልክ እንዳልሆነ ተረድቻለሁ ግን መናገር አልችልም...
በመጨረሻም በውስጡ በሶፍት የተጠቀለለ ጠጠር መሰል ድንጋይ የያዘ የተፈረመበት ለማለት ይከብዳል የተሞነጫጨረበት ፖስታ እና የመታወቂያየን ኮፒ ይዜ ኮዬ ፈጨ ክፍለከተማ ራሴን አገኘሁት።
ብዙ ሲጠይቀኝ ቆይቶ ኖሯል በቁጣ የጥበቃ ባለሙያው ምን ልርዳሽ እያልኩሽኮ ነው የት መሄድ ፈልገሽ ነው ሲለኝ ነቃው😭ልገልፀው በማልችለው በከፍተኛ የራስ ምታት ውስ ሆኜ ነበር።
ቦርሳዬና ስልኬ አለ፣ የቃልኪዳንና የጋብቻ ቀለበቴን ግን ወስደውታል። እንዴት እንደምንጠብቅ ባላቅም በተቻላችሁ ራሳችሁን ጠብቁ!! ሿሿ እንዲህ ነው ለካ!
አንድ እህታችን ለAb Bella እንደነገረችው!!
@Ethiopian_Digital_Library@Ethiopian_Digital_Library