Postlar filtri


ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ ቀረበ

የአሜሪካ መንግሥት፣ በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ በመቀጠል ላይ ያለው ግጭት እንዲቆም ጥሪውን በድጋሚ አሰምቷል።

የኤም 23 አማፂያን በርካታ ቦታዎችን በመቆጣጠር ላይ ባሉበት በዚህ ወቅት፣ የአሜሪካንን መንግሥት ጥሪ በድጋሚ ያሰሙት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ታሚ ብሩስ፣ የውጪ ጉዳይ ምኒስትሩ ማርኮ ሩቢዮ ከዚህ በፊት በጉዳዩ ላይ ያሳዩትን አቋም በድጋሚ አንጸባርቀዋል።


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ሊያካሂድ መሆኑ ተሰማ


የኢትዮጵያ አየር መንገድ አለም አቀፉን የሴቶች ቀን አስመልክቶ በሴቶች ብቻ የሚደረግ በረራ ሊያካሂድ መሆኑን አስታውቋል።

በረራው ወደ 6 አገራት የሚደረግ ሲሆን፤ ሁለቱ ዛሬ ማታ የቀሩት አራት በረራዎች ደግሞ ነገ የሚደረጉ ናቸው።
በረራዎቹ  ከካፒፔን እስከ አየር ተቆጣጣሪ እና ቴክኒሻን ድረስ በሴቶች ብቻ የሚደረጉ መሆናቸው ተገልጿል።
ባህርዳር፣ አቴንስ፣ ዴልሂ ፣ዱባይ፣ ሳኦፖሎ እና ዊንድሆክ ከተሞች መዳረሻ ናቸው ተብሏል።

በዓለም ለ114ኛ ጊዜ በአገራችን ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በረራዎቹ መዘጋጀታቸው ነው የተገለፀው።




ጄነራል የተገደሉበት ጥቃት ተሰነዘረ

ደቡብ ሱዳን ውስጥ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሄሊኮፕተር ላይ በተፈጸመ ጥቃት የሱዳን ጦር ጄኔራልን ጨምሮ በርካታ ሰዎች መገደላቸውን ድርጅቱ አስታወቀ።

ሄሊኮፕተሯ በቅርቡ ግጭት በተፋፈመበት የላይኛው ናይል ተፋሰስ ግዛት የአገሪቱን ጦር አባላት ልታስወጣ በምትሞክርበት ወቅት እንደተኮሰባት ተገልጿል።

በጥቃቱም አንድ የሄሊኮፕተሯ ሠራተኛ፣ ቆስለው የነበሩ ጄኔራል እና በርካታ የደቡብ ሱዳን ወታደሮች መገደላቸውን በደቡብ ሱዳን የመንግሥታቱ ድርጅት ተልዕኮ ባወጣው መግለጫ አመልክቷል።

ወታደሮቹን ውጊያ ከተፋፋመበት የላይኛው ናይል ተፋሰስ ግዛት ለማስወጣት በሚሞከርበት ወቅት የተፈጸመው ጥቃት በጦር ወንጀልነት ሊፈረጅ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥታት ገልጿል።


ጀልባዎች ሰጥመው ከ180 በላይ ኢትዮጵያዊን ጠፉ

በጅቡቲ እና በየመን ውቅያኖሶች ላይ በሰጥሙ አራት ጀልባዎች ሁለት ሰው ሲሞት ከ180 በላይ የሚሆኑት መጥፋታቸውን አለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ለኤኤፍፒ አርብ ተናግሯል።

በጅቡቲና የመን ዉቅያኖስ ላይ በጀልባ መስጠም ከጠፉት 181 የሚሆኑት ኢትዮጵያዊያን መሆናቸዉ ዘገባዉ አመላክቷል ።


ኡስታዝ አቡበከርን ላይ እገታ የፈጸሙት ተፈረደባቸው

ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን የተባሉ ግለሰብን በማገት ሊብሬ በመቀየር መኪናቸውን ሊነጥቁ ነበር የተባሉ 5 ተከሳሾች በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ተቀጥተዋል፡፡

የቅጣት ውሳኔውን የወሰነው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ነው።

ተከሳሾቹ ንብረትነቱ የግል ተበዳይ ኡስታዝ አቡበከር ሁሴን መሃመድ የሆነውንና የዋጋ ግምቱ 7 ሚሊየን ብር የሚያወጣ ቪ8 ተሽከርካሪ ሀሰተኛ ሰነዶችን በመጠቀም፣ ማህደሩን በመለወጥና በሽያጭ በማስተላለፍ ለመውሰድ ሲሉ መያዛቸው ተመላክቷል፡፡

በዚህም በዋና ወንጀል አድራጊነት ተካፋይ በመሆን ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል የሙስና ወንጀል ተከሰው እንደነበር ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት የዋለው ችሎት 1ኛ ተከሳሽ ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ4 ዓመት ጽኑ አስራት እና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጣ ውሳኔ አሳልፏል፡፡

በተጨማሪም 2ኛ፣ 3ኛ፣4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ከተያዙበት ቀን ጀምሮ እያንዳንዳቸው በ3 ዓመት ከ3 ወር ጽኑ እስራትና በ2 ሺህ ብር እንዲቀጡ ተወስኗል፡፡


በኢትዮጲያ የአዞ ስጋ ሽያጭ ሊጀመር መሆኑ ተሰማ


የአዞ ስጋን የሚያዘጋጅ እና የሚሸጥ ምግብ ቤት በአርባምንጭ ሊከፈት መሆኑን ተሰምቷል፡፡

የአርባምንጭ አዞ እርባታ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት ዳኜ ለኢትዮ ኤፍ ኤም በሰጡት ማብራሪያ፤ በአርባምንጭ ከተማ የአዞ ስጋ ምግብ ቤት ለመክፈት እንቅስቃሴ መጀመሩን ገልጸዋል።

የውጪ ሃገር ቱሪስቶች የአዞ ስጋ ለመመገብ የሚጠይቁ መሆኑን የገለፁት አቶ ዳዊት፤ ጥናት ተደርጎ ከአንድ ዓመት በኋላ ሬስቶራንቱን ለመክፈት እንደታሰበም ተናግረዋል።

የውጭዎቹ ቱሪስቶች ጋር ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ ዳዊት አንስተው ፤ አሁን ላይ በሃሳብ ደረጃ ነው ያለው ጉዳዩ ወደተግባር አልተገባም ብለዋል፡፡

በአካባቢው አዞዎቹን የሚንከባከቡ ሰዎች የአዞ ስጋ እንደሚመገቡ የሚናገሩት አቶ ዳዊት ይህም በስፋት እንደተለመደ እና አዲስ ነገር እንዳለሆነ አስተውሰዋል፡፡




ፕሬዝዳንቱ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ

የደቡብ ኮሪያ ፍርድ ቤት ከማርሻል ህግ ድንጋጌ ጋር በተያያዘ የተከሰሱት ፕሬዝዳንት ዮን ሱክ ዮል ከእስር እንዲፈቱ አዟል።

ፍርድ ቤቱ ሪፖርቶቹን ወዲያውኑ ባያረጋግጥም ፤የሴኡል ማዕከላዊ አውራጃ ፍርድ ቤት ውሳኔውን አሳልፏል ሲል አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል፡፡

ፕሬዝዳንቱ በጥር ወር ከማርሻል ህግ ድንጋጌው ጋር በተያያዘ መያዛቸዉ ይታወሳል፡፡

አዋጁ አመፅ ነው ሲሉ መርማሪዎች ክስ ያቀረቡ ሲሆን፤ ጥፋተኛ ሆነዉ ከተገኙ የሞት ቅጣት ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ይጠብቃቸዋል ተብሎ ነበር።


በመሬት መንቀጥቀጡ የተፈናቃሉ ወገኖች የድረሱልን ጥሪ አሰሙ

በኦሮሚያ ክልል ፈንታሌ ወረዳ በመሬት መንቀጥቀጥ የተፈናቀሉ አርብቶ ዐደሮች፣ በድርቅ ምክንያት ችግር ላይ እንደኾኑ ተናግረዋል።

ከፈንታሌ ተራራ አቅራቢያ በተከሠተው የመሬት መንቀጥቀጥ እንደተፈናቀሉ ያወሱት አርብቶ ዐደሮቹ፣ አኹን ደግሞ በተጠለሉባቸው አካባቢዎች ድርቅ መታየት በመጀመሩ የቁም እንስሶቻቸው እየሞቱባቸው እንደኾነ አሜሪካ ድምፅ ዘግቧል።


ኦነግና ኦፌኮ ያራመዱት አቋም ተቃወሞ ገጠመው

እናት፣ ኢሕአፓ፣ መኢአድ እና ዐማራ ግዮናዊ ንቅናቄ፤ ኦነግ እና ኦፌኮ ከሳምንታት በፊት በኦሮሚያ ክልል የጋራ "ሽግግር መንግሥት" እንዲመሠረት ከተለያዩ አካላት አደራ መቀበላቸውን በሚመለከት ያራመዱትን አቋም ተቃውመዋል።

አራቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ዛሬ በጋራ ባወጡት መግለጫ "የሽግግር መንግሥት በተናጠል በክልል ደረጃ ሊመሠረት አይችልም" ብለዋል።

የሁለቱን ፓርቲዎች አቋም ክልሎችን ከክልሎች የሚያጋጭ እና ለኢትዮጵያ አደጋ የሚያስከትል ነው ያሉት አራቱ የፖለቲካ ድርጅቶች ሁኔታው "እሳት ላይ ቤንዚን እንደማርከፍከፍ የሚቆጠር ነው" ሲሉ ነቅፈዋል።

አራቱ የፖለቲካ ድርጅቶች የታሰበው "የሽግግር መንግሥት" ጥያቄ ችግሮችን የሚያባብስ እንጂ መፍትሔ የሚያመጣ እንዳልሆነም በመግለጫቸው ጠቅሰዋል።


የጄኔራሉ መታሰር የሰላም ስምምነቱን የሚጥስ እንደሆነ ተገለጸ


የደቡብ ሱዳን ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲ ወታደራዊ ክንፍ የጦር አዛዥ ጄነራል መታሰር ለአምስት ዓመታት የዘለቀውን የእርስ በርስ ጦርነት የቋጨውን የሰላም ስምምነት "የጣሰ ነው" ሲሉ የተቃዋሚው ቃለ አቀባይ ተናገሩ።

ጄኔራል ጋብርኤል ዲዮፕ ላም እንዲሁም በተቃውሞ ላይ ያለው የሱዳን ህዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ (ኤስፒኤልኤም-አይኦ) ከፍተኛ ባለስልጣናት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለእስር መዳረጋቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።




አሜሪካ ከዩክሬን ጋር ስታደርግ የቆየችውን የወታደራዊ ደህንነት መረጃ ልውውጥ ማቋረጧን አስታወቀች

አሜሪካ ከዩክሬን ጋር ስታደርግ የቆየችውን የወታደራዊ ደህንነት መረጃ ልውውጥ ማቋረጧን አስታወቀች። ዋሽንግተን እና ኬቭ የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የወታደራዊ ደህንነት መረጃዎችን ሲለዋወጡ መቆየታቸው ተነግሯል። የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር የሁለቱ ሀገራት የደህንነት መረጃ ልውውጥ እንዲቋረጥ ውሳኔ ማሳለፉን የአሜሪካ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ማይክ ዋልዝ አረጋግጠዋል።


''ስጋት ላይ ነን'' ነዋሪዎች

በምስራቅ ትግራይ በጎረቤት ሀገር በሚደረግ ጥቃት በአካባቢው ባሉ ስምንት ወረዳዎች ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎችን ስጋት ላይ መጣሉ ተገልጿል።

በተደጋጋሚ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች የጸጥታ ችግር እየፈጠሩ መሆኑ የተገለጸም ሲሆን፤ በተለይም በዛላንበሳና አካባቢው ያሉ ማኅበረሰቦች የኤሌክትሪክ እና የሕክምና አገልግሎትን ጨምሮ አስፈላጊ አገልግሎቶችን እንደተቋረጠባቸው ተጠቁሟል፡፡


ትራምፕ ከዘለንስኪ ደብዳቤ ደርሶኛል አሉ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያ ዩክሬን የሰላም ስምምነትን ከግብ ለማድረስ ወደ ድርድር ጠረጴዛው ለመምጣት ዩክሬን ዝግጁ መሆኗን የሚገልጽ ደብዳቤ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ እንደደረሳቸው ገለጹ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በዋሽንግተን በተካሄደው የጋራ ኮንግረስ ስብሰባ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ይህን ደብዳቤ መላኩን አደንቃለሁ ብለዋል።


የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአልሸባብ ወታደራዊ ይዞታዎች ደበደበ

የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአልሸባብ ወታደራዊ ይዞታዎችን መደብደቡን ሶማሊያን ጋሪዳያን ዘግቧል።

የኢትዮጵያ አየር ሃይል ሶማሊያ ውስጥ ዘልቆ በመግባት በመካከለኛው ሸበሌ የሚገኙ የአልሸባብ ይዞታዎች ላይ ድብደባ መፈፀሙን ዘገባው ጠቅሷል።




ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ለቀናት ያለ ምግብ እና ውሃ ከቆዩ በኋላ በህይወት መገኘታቸው ተሰማ

ሜዲትራኒያን ባሕርን ለመሻገር የሞከሩ ኢትዮጵያዊያን አሊያም ኤርትራዊያንን ጨምሮ 32 ፍልሰተኞች በቱኒዚያ የባህር ዳርቻ ለበርካታ ቀናት ያለ እርዳታ ከቆዩ በኋላ በረድኤት ድርጅት ሕይወታቸው ታደገ።

ፍልሰተኞች ተሳፍረውበት የነበረው ጀልባ አደጋ ከደረሰበት በኋላ "ሴቶች፣ ህፃናት እና ወንዶች" ካለ ምግብ እና ውሃ ለቀናት መቆየታቸውን ሜድትሪና የተሰኘው ረድኤት ድርጅት ገልጿል። አንድ ሰው በነዳጅ ማቀነባበሪያው ውስጥ ሕይወቱ ማለፉንም አስታውቋል።

መንግሥታዊ ያልሆነው ድርጅት ከነዳጅ ማቀነባበሪያው 32ቱንም ፍልሰተኞች ማክሰኞ ከሰዓት እንደታደገ የገለፀ ሲሆን፤ ፍልሰተኞቹ ክትትል እተደረገላቸው ነው ብሏል።


በደቡብ ሱዳን መዲና ጁባ ውጊያ እየተካሄደ ነው

የሀገሪቱ ምክትል መሪ ሬክ ማቻር መኖሪያ ቤት በፕሬዝደንት ሳልቫኪር ጦር ተከቧል።

ከሬክ ማቻር ወገን የጦር መሪዎች መካከል የተገደሉ እና ተይዘው የተወሰዱ መኖራቸውም ተረጋግጧል።

ጁብ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ መሆኗ እየተሰማ ሲሆን፣ ንፁሃን ዜጎችም መገደላቸው ከሀገሪቱ ምንጮች እየተዘገበ ይገኛል።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.