🌹 ፍቅሬን በ ግጥም 🌷


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


➣ Express love without reciprocation !
➣ Swimming with a pure heart !
➣ Where trust and empathy prevail !
➣ Thinking about people more than your !
➣ Preach love until her last breath !
= +251931374891
= t.me/Abate_Hiwote

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


ተማሪ ነህ 🤗


የ1000 ብር ካርድ ሊለቀቅ ነው 9 ደቂቃ ብቻ ነው የቀራው። ቶሎ ከስር JOIN ሚለውን ነክታቹ JOIN REQUEST ላኩ 🏃‍♀️🏃‍♂️




አድዋ ማለት.....
አድዋ!  የጥቁር ህዝብ ሁሉ ድል ነው።
አድዋ!  የኢትዮጵያ ክብር ነው።
አድዋ!  የእኩልኑት ማህተም ነው።
አድዋ!  የጥቁር ህዝብ ትንሳዔ ነው።
አድዋ!  የሉአላዊነት አዋጅ ነው።
አድዋ!  የነፃነት ፀሐይ ነው።
አድዋ!  የቱሪዝም መሥህብ ነው።
አድዋ!  የትውልድ መቅረጫ ነው።
አድዋ!  ከድህነት መውጫ ነው።
አድዋ!  አንድነት መፍጠሪያ ነው።
አድዋ!  ግርማ ሞገስ ነው።
አድዋ!  የእኩያን ማሳፈሪያ ነው።
አድዋ!  የግፉአን ጠበቃ ነው።
አድዋ!  አገር አድን ነው። ጸሃፊያን
እንኳን ለ127ኛዉ የአድዋ ድል በዓል አደረሰን!


የአፍሪካ  ኩራት💪🔥


https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ሁሉም ትውልድ አድዋ አለው
የኔም አድዋ ልቤ ላይ ነው
ጀግና ማለት ይቅር ባይ ነው
ሚኒሊክ ዛሬም ንጉስ ነው 🤝

#አድዋ 💚💛❤️
#ምኒልክ 💚💛❤

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


🔪🛠 #የቋራው_ማዓበል 🛠🔪

ሰርቲፋይድ ሰርቬ--ኮተም ሜካኒካል፣
ድሮዊንግ ዲዛይነር--ሲቪል አርክቲካል፤
ምናምን ምናምን፥ ምናምን እያልን፣
ምንጠራው ኢንጂነር፥ መድገም ያቃተውን፤
ሶፎመር ቦርቡሮ፥ ጀጎልን ያጠረ፣
ላሊበላን ቀርፆ፥ አክሱም የወቀረ፤
ጠቢብ ቅመ አያቱ፥ ተጠቦ ያቆማት፣
ሀገሩን ሺ ቦታ፥ ከፋፍሎ ሊጥላት፤
ያሰበው ከበርቴ
መሳፍንት ጠራርጎ፥ እየገሰገሠ፣
የቋራው ማዓበል፥ እንግሊዝ ደረሠ።

#በጅላሉ_ወርቁ

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


😍😍ህልማለሜ😍😍



ተንተርሼ ካልጋ ቀትር በለሊቱ🌙
ውጥርጥር በሃሳብ አያልፍም እለቱ
       በህልሜ እንደትመጪ አይኖቼን ከደንኩኝ
        አንቺግን የለሽም🫣
        ላፍታ እንኩአን እንዲወስደኝ ከሃሳብ አልሸሽም
ይቅር አልፈልግም አለይሽ ከእቅፌ 🫤
ልዙር ልገላበጥ ትራሴን ታቅፌ
      አወይ የኔ ምናብ በትራሴ ፈናታ አንቺን እያለመ
      ሲፈካ ሲከስም መች አንቺ አገኘ  😨
ከንፈሩን በቁጭት ሲያመነዥክ ያድራል 
አይኔ በርበሩን በስስት ይቃኛል 🙁
ልቤ እንደ ክራር ትዝታን ይቃኛል
          አንቺግን የለሽም ከሃሳብ አልሸሽም አንቺ ግን አትመጭም
        አለሜ ህልም እልም ሕልም እልም
       ናፍቆትሽ ገደለኝ ልክ እንዴ ውሃ ጥም
ስልኬን አነሳለው መልክሽን በ ፎቶ ላፍታ እቃኛለው 📱
ሰዓቴን ደገምኩት አይነጋ ይህ ምሽት🕒
        ህልማለሜ አስታወስሽ ያንን እለት
        ተቃቅፈን ባንድ አልጋ ፍቅር ስንሰራበት🥰
እቀፈኝ አጥብቀህ ትይኝ ነበር ስርቅ
ዛሬ ግን የለሽም ከሃሳብ አልሸሽም
            ናፈቀኝ ከንፈርሽ እሱም ብቻው አይደለም ነገር ሁለመናሽ
          እኔ ግን ታደልኩት አፈስኩኝ ፍቅርሽን
         ይኸው አሁን ደሞ አሰብኩ ፈገግታሽን 😁
         አቅፎ የሚውሉ እንያን ጉንቾችሽን 😘
ጠጋ በይ ልንገርሽ ማንም እንዳይሰማኝ ላሾክሹክ በጆሮሽ
እኔ ማለት ማነኝ የሷ ብቻ እኮ ነኝ ማንን እንዳትይኝ
          ስሟን እንድነግርሽ ነይ አንዴ ልቀፈሽ 👩‍❤️‍👨
         ስሟ እኮ ሲጀምር አ ፊደል ከፊቱ
         ላፍታ ነየ ብቅ በይ አይሄድም ሰዓቱ🕢
         በናፍኮትሽ ደጋን ታመመኩልሽ እቱ
ስላንቺ መናገር ከቶ አይሰለቸኝም
ብራና ወጠርኩኝ ላቅልምሽ በብእር ✍
አልገባኝም ውሉ ስደምር ስቀንስ ደግሞም ሳጭበረብር 🤔
          ስንቱ ተከፈለ ለመውደድ ለፍቅር 🥰
          ደስ እያለኝ ልሙት የታባቱ ማሰብ
         ከልጆቼ እናትጋ ሳስብ ሳብሰለስል 👩‍❤️‍👨
         ቃሌን እሰጣለው አልረሳሽም ፍፁም🥹

          ✍✍✍ተፃፈ በዳዊት✍✍✍
@davunin


​​⊶⊷⊶⊷❍ የእብደት ሚስጥሬ ❍⊶⊷⊶⊷


ፍቅሬን በቃላቶች ~ ደርድሬ ባልገልፀው
የኔ ነሽ የምልሽ ~ ያንቺ ነኝ የምለው
ድምፅሽ መዳኒቴ ~ የህይወት እጣዬ
አካልሽ ጉልበቴ ~ የስኬት ማማዬ
ሌላ ማንም የለም ~ ባንቺ ነው ማማሬ
እውነት እልሻለሁ ~ የእብደት ሚስጥሬ
  
    ━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━

ድንቅ ተውቦሽን
ከቅኔዬ ዜማ
ከቀለሙ ውህደት
በጥበብ ምትሐት
             
                ተቀምጦ አገኘሁት
መቼም አይጠፋኝም
እንዲሄ ያለ  ስዕል      እንዲህ ያለ ግጥም
ቀልብ የሚያተራምስ    ነፍስ የሚቆረጥም
ሳይዘራ አይበቅልም
ዘሩ ደግሞ አንቺ ነሽ
ምስቅልቅል መሳቴን ዜማ የሰጠሺው
ሻጋታ ብሩሼን ቀለም የነከርሺው
ምናቤን ለኩሰሽ ውበት ያዘመርሺው
ዘሩ ደግሞ አንቺ ነሽ
እና ይኸውልሽ.....................
ግጥሜን እያነበብኩ ስዕሌን እያየሁ
አንቺን አስባለው
ከአዘቦት ነፍሴ
ከእውቀቴ በላይ
ከእምነቴ በላይ
ከተፈጥሮም በላይ
እንደ ኢየሱስ ተአምር
ያልተጠበቀ እለት ወርዶ እንደሚታይ
ከምናቤ ሸራ ትንሳኤ አግኝተሽ
እስክትሳይ ድረስ እውነት ውበት ሆነሽ
በከርቤ ፣ በስግደት ፣ በብቻ ጉባኤ እንደሚገኝ ቅኔ
እስከዚያ ድረስ ነው የምወድሽ እኔ

ለካ እወድሻለው!!"


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።

#ተፃፈ_በዳዊት
@Davunin

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


የባከነ ከአብ


ሰከን እንበል እስቲ እንቁም አጢነን፣
እሳቶች ቢንቁን እናጥፋቸው ቀጥነን።
የባዘነ ድባብ፣
የባከነ ከአብ፣
ያም ያም ጊዚያዊ ነው ቢቆጠር ቢለካ፣
ያካበትሽው ገንዘብ ያቆምሽው ፋብሪካ፣
የሰፈርሽው በእጅሽ ንብረትሽ ሀገሬ፣
አእላፍ ትዝታ ቁራሽ እንጀራ እና አምስት ጥማድ በሬ፣


#ገጣሚ አብረሀም ደመቀ
ጥቅምት መባቻ 2017


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እና ለቻናላችን ቤቸሰቦች በሙሉ
እንኳን ለታላቁ ጾመ ኢየሱስ (የዐብይ ጾም) በሰላም አደረሳቹ።

ጾሙ የሰላም ፣ የበረከት ፣ እንዲሁም የፀሎታችን ምላሽ የምናገኝበት ይሁሉን።

ልመናችንን ፣ ሱባኤአችንን ፣ ፀሎታችንን ፈጣሪ ይቀበልልን ።

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


የፈሪ ፍቅር .. . . .

በተኮላተፈ ፥ ስርዝ ድልዝ ድምፆች፣
ሲለማመድ ከርሞ ፥ ካንደበቱ ገፆች።
ደፈር ብሎ ልቤ ፥ ላይነግራት መውደዱን፣
ቃላት ያማርጣል ፥ እያሰባት ውዱን።

ተስፋ አፈር በላው ፥ ተስባብሯል መቅኔው፣
ፍራት ሰንጥቆታል ፥ ውስጡ ሲሸሽ ወኔው።
እንኳን አንገት አቅፎ ፥ እቤቷ ሊሸኛት፣
ከንፈር እየሳመ ፥ ባ'ንድ አልጋ ሊተኛት።
ስንት ጊዜ ጥሮ ፥ ወግ ደርሶት ሊያገኛት
የቁም ቅዠት ሆኖ ፥ ቀረ እንደተመኛት።

ባ'አንድ ቀን ለሊት ፥ ያየዋት በደና፣
ህልሜ ነበረች ፥ ገሀድ ያለች መና።
ልብ የሌለው ወዶ ፥ ለመግለፅ ሲዳፈር፣
መሽኮርመሙ ቀርቶ ፥ ቀና ሲል አይናፋር።
አንደበት ሲገራ ፥ ልቧን አርጎ ፈራጅ፣
ቀን እየቆጠረ ፥ እራሱን ሲያዘጋጅ ።

ከዛሬ ነገ ቀጥሮ ፥ ሊነግራት እያለ፣
አንዱ ጠልፎ ጥሏት ፥ ይዟት ኮበለለ።
ውሀ በላው ቅስሙን ፥ ሀሞቱ እረገፈ፣
በእምባ ተጨማልቆ ፥ በፀፀት አለፈ።
ሀዘን አጠላበት ፥ ብሶት ቤቱን ሰራ፣
ነፍሱ ነዶ ጋየ ፥ እብደት ስሙን ጠራ።

እናም እንዲህ አለ. . . .

ለጎኔ ማክዳ ፥ የዘላለም ቅምሻ፣
ስመኛት ዘመኔን ፥ ለህይወቴ ማምሻ።
ፍርሃት ልቤን አስሮ ፥ ጊዜ እየጠየቀኝ፣
ህልሜን አሰርቆ ፥ ባዶ እጁን ጠበቀኝ።

ገጣሚ፦ keyso✍

@getembate


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


💔የማያሽር...ጠባሳ💔
፨።።።💘💘💘።።።፨

ቀኑም አይመሽልኝ ለሊቱም አይነጋ
ልቤ እየተቀጣ በሀሳብ አለንጋ
ከልብ ውስጥ የማይጠፋ ከቶ ማይረሳ
ህመሙ የማይድን የማይሽር ጠባሳ
ቁስሉ የሚቆጠቁጥ የህሊናን ዕዳ
አሸክማኝ ሄደች በሰውፊት አዋርዳ
ሀዘን ድንኳ ጥሎ ጎጆውን ቀልሶ
ልቤውስጥ ይኖራል ጎኔን ተንተርሶ
ልቤ ፍቅርን ብሎ ለፍቅር ባደረ
ሀዘን ቤቴን ወርሶት ቅስሜ ተሰበረ
.
.
.
ያላረኩት የለም ልቤን ለማሳመን
በደልሽን ችዬ ካንቺ ጋር ለመሆን
ግን አንቺ አልገባሽም ባንቺ መጎዳቴ
በብርሀን ጭለማ መሆኗን ህይወቴ።።።።


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


🔥ስልክ ቁጥር በማስገባት ብቻ ሰዎች ያሉበትን ቦታ ማወቅ የሚያስችለን አሪፍ አፕልኬሽን, በተለይም ልጆቻችን  እና የቤተሰባችን አባል ከኛ በሚርቁበት ጊዜ ያሉበትን ሁኔታ ለመከታተል ሁነኛ መፍትሄ ነው

አፑን ለማውረድ 👇👇👇
               
https://play.google.com/store/apps/details?id=net.brighttechnology.ethiotech&hl=en

10k 0 13 1 10



ያቺን ቀን....
ምነው በሰረዛት
  ከህይዎቴ መዝገብ፣
ተገብቶሽ አይደለም
  ዘለፋ እና ስድብ፣
ተደፍቼ ላልቅስ
  ከደጀሰላሙ፣
መቅለሌን ባየና
  በሰጠልኝ ላንቺ
    የይቅርታ ልቡን።

ይህቀረን የምለው
  እንደሌለ አውቃለው፣
ከልቤ ነው ማማ
  መልካሙን መልካሙን
    በሄድሽበት ሁሉ
      እመኝልሻለው፣
ዳግም ከሕይዎትሽ
  ላልገባብሽ ፍፁም
    እምልልሻለው።

#ተፃፈ_በዳዊት
@Davunin

https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA

16k 0 61 3 64

ሌሎችም ውስጥ...
(ሳሙኤል አለሙ)


መች ኑር ብለሽኝ...
አልኖርም አልኩ፤
መች ሙት ብለሽኝ...
አልሞትም አልኩ፤
በክቡራን'ና ክቡራት
አልታይሽም እየተቀደምኩ።


እንደው...
ታክቶሽ እንጂ ለምስጋናው
ዝለሽ እንጂ ለፍለጋው፤
አታጭኝም ነበር...
ሌሎችም ውስጥ እየተጠጋጋው።

ሳሙኤል አለሙ
    
@Samuelalemuu

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━


#ተከታይ_የሌለው_አንድ

መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።
መውደድ....
ባርባ...ባርባው፤
ማፍቀር.....
ባርባ...ባርባው፤
ለተገዢው ልቤ
ክዳው ለማትገባው።
ለታዛዡ ልቤ
ዋሽታ ለማትገባው።

ቀርበው ሲጠይቁኝ...
አንዱን ልቤን
እያስለካው፤
አንዴ ልየው ሲሉኝ...
አንዱን ልቤን
እያስጠጋው፤

ስኖር...አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
ላንዴ...ስኖር...ስኖር...ስኖር...ስኖር
ስኖር..አንዴ...አንዴ...አንዴ...አንዴ
በስንቱ አንዴ-ዎች
አንዱን ልቤን፥ ላንዴ ሳስሞክረው፤
አለሁኝ በተስፋ
ገዢ እንደቸገረው።

ሳሙኤል አለሙ
@Samuelalemuu

━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
https://t.me/joinchat/AAAAAE-H14mYFGMHTdYugA


☀️☀️ ለወዳጅ ዘመድ እንዲሁም ለጓደኛ ምን አይነት ስጦታ ልስጥ ብለው አይጨነቁ !

የ ስዕል ( Art ) ስራወችን በስጦታ መስጠት ለምትፈልጉ ከታላቅ  ቅናሽ ጋር አሁኑኑ ይዘዙን ።
ጥራት ያላቸውን ስራወች ሰርተን በፍጠነት እናስረክባለን ።
  

order ለማረግ 👇👇👇

☎️ 
+251912453800
☎️ 
+251931374891
     ይደውሉ 👆👆👆

በቴሌግራም
@Abate_Hiwote ላይ ያናግሩን።

20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.