ዛሬ የ ዉበታችን ቀን ነው እስኪ አንዳንዴ አስተማሪ የሆነ ነገር ለ ባለ ትዳር እህቶቼ 🥰
ጀናባ ትጥበት🛁ይህ ትጥበት እጅግ በጣም ቀላል እና ግዜ የማይፈጅ ኢባዳ ነው።
ሁለት አይነት አስተጣጠብ አለ የመጀመሪያው በሱና መሰረት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ያብቃቃል የሚባለው ነው።
የመጀመሪያውን ዘርዘር አድርገን ስናየው፦
✅ረሱል ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ለጀናባ ትጥበት ከ 2-3ደቂቃ🕒 ብቻ እንደሚወስድባቸው እና በ3-4litter🚰 ውሃ እንደሚታጠቡ ዘገባዎች ያስረዳሉ(ወፍራም እና ረጅም ፀጉር እንደነበራቸው እንዳትረሱ)
➡️ስንታጠብ በሱናው መሰረትም ይሁን በኖርማል አስተጣጠብም ይሁን ውሃ የግድ መንካት ያለባቸው ቦታዎች፦
↪️አፍን መጉመጥመጥ
↪️አፍንጫ ውስጥ ውሃ አስገብቶ ማስወጣት(ይህ ብዙ ግዜ ይረሳል ግን የትጥበቱ አካል ነው)
↪️ከራስ እስከ እግር ያለው ሙሉ የሰውነት አካል ውሃ መንካት አለበት
ሱናው ይህን ይመስላል፦ሰሂህ ቡሃሪ መፅሃፍ 1 ቁጥር 273
0⃣ኒያ ማድረግ እና ቢስሚላህ ብሎ መጀመር
1⃣እጅን 3ግዜ መታጠብ
2⃣እስቲንጃ ማድረግ
3⃣አሁንም እጅን በደንብ መታጠብ
4⃣ውዱእ ማድረግ(እግራችንን ታጥበን ስንጨርስ እንታጠባለን)
5⃣በሁለት እጃችን🤲 ውሃ ሞልተን 3ግዜ(1ግዜም ይቻላል ሱናው ግን 3ነው) ራሳችን ላይ ማፍሰስ እና የፀጉራችንን ስር በጣቶቻችን እያሸን ማዳረስ(ርዝመቱ ላይ ሳይሆን ስሩን ማዳረስ ነው ዋናው)
6⃣ከዚያ ሙሉ ሰውነታችን ላይ ከላይ እስከታች ውሃ ማፍሰስ
7⃣መጨረሻ ላይ እግራችንን ታጥበን እንጨርሳለን
ያብቃቃል የሚባለው አስተጣጠብ ደግሞ፦
0⃣ኒያ
1⃣አፍ እና አፍንጫ ውስጥ ውሃ አስገብቶ ማስወጣት
2⃣ከራስ ጀምሮ ሙሉ አካል ላይ ውሃ ማፍሰስ ....አለቀ....
ይህን ኢባዳ አድካሚ እና አሰልቺ እንዳይሆን፦
✅ሁሌም በውሃ ብቻ መታጠብ ሳሙና እና ሻምፖ አለመጠቀም ልክ ውዱእ ስናደርግ ሳሙና እንደማንጠቀመው።
✅በኖርማል ሻወር የምንወስድበትን እና ፀጉራችንን በደንብ የምንታጠብበትን ጊዜ ከዚህ ትጥበት ጋር አለማድረግ/መለየት
✅ፀጉራችንን እስከጫፍ ድረስ ውሃ ውስጥ አለመንከር(ዋናው የፀጉራችን ስርን ማዳረስ ነው)
✅አነስ ባለ ውሃ መጠቀም (ሱና ነው እንዲሁም ማባከን ደግሞ ኢስራፍም ስለሆነ)
✅በተቻለ መጠን በትንሽ ደቂቃ ውስጥ ታጥቦ መጨረስ
✅በቀዝቃዛ ውሃ መታጠብ ለማትወዱ መብራት ሲጠፋ መጠባበቂ ሚሆን ትንሽዬ ሲሊንደር መግዛት😜😜
@HANIF_TUBE01👍Like share ↗️