╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗
.......📓መጅኑኑ_ዲያሪ📓......
✎ ፀሐፊ፦𝕞𝕦𝕜𝕖𝕣𝕖𝕞
╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝
┎━─━─━─━─━─━─━─━┒
🌟በ 𝕙𝕒𝕗𝕦 𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕡𝕠𝕤𝕥 የተዘጋጀ🌟
┖━─━─━─━─━─━─━─━┚
╔════•| ✿ |•════╗
#ክፍል_ 2️⃣2⃣
╚════•| ✿ |•════╝
የአፍራህ አባት ለምን እንደፈለገኝ እያሰብኩኝ ፈተናውን ሞልቼ ከሁሉም በስተፊት ወጣሁ።ከጊቢው ውጪ ሆኜ አፍራህን መጠበቅ ጀመርኩ።በአንዱ አቅጣጫ የነአዩብ ጎረቤቶች ተሰባስበው ሲመጡ ተመለከትኩ።ግራ በመጋባት አጠገቤ እስኪደርሱ ጠበቅኩ።
ሳግ እየተናነቃት አንዷ ሴትዮ ጠየቀችኝ።
ደነገጥኩ።
ተደግፌው የቆምኩትን ስልክ እንጨት ታክኬ ከአቧሯው ላይ ተዶልኩኝ።ምንም እንኳን ጎረቤት ባያውቅም ማሚ ለኔ ከእናቴ የማትተናነስ ለይቼም የማላያት ምትክ ነበረች።እነ አዩብን ከጊቢው ሲወጡ ስመለከት ምንም እንዳልተፈጠረ ተነስቼ እምባዬን ጠረግኩ።አዩብ በጎረቤቶቹ መገኘት ጥርጣሬ ገብቶት በቀጥታ ወደኔ መጥቶ
እንደዚህ እንዳልኩት ጎረቤቶቹን ሳያናግራቸው መሮጥ ጀመረ።እኔና አንዳንድ ጎረቤቶች ተከተልነው።በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ገብቶ እናቱ የተኛችበትን ክፍል በርግዶ ገባ።እኛም ኮቴውን ተከትለን ገባን።ማንም አልነበረም።ክፍሉ ጀናዛ እንደወጣበት አፍ አውጥቶ ባይናገርም ነገር ግን ምንም ጥሩ ነገር አይስተዋልበት።አዩብ የአልጋውን የተመሰቃቀለ አንሶላ ሲመለከት ጭንቅላቱን ይዞ ወደ እኛ ዞሮ።
እያለቀሰና እየጮኸ ክፍሉን በአንድ እግሩ አቆመው።
ብላ ከኔ ጋር ተሯሩጣ የመጣችው ሴትዮ ልትይዘው ቀረበችው።ይህን ጊዜ ነበር ነገሮች መስመራቸውን የለቀቁት።አዩብ ሴትየዋን በጥፊ አጋላት።ደንግጣ እኔ ወደቆምኩበት በር ለመውጣት ስትንደረደር ዘሎ ጀርባዋ ላይ ተከምሮ በጥርሱ ዘለዘላት።እኔም ሮጬ አዩብን ያዝኩት።ታግዬ ሴትየዋን አስጣልኳት።ሴትየዋ እሪታዋን እያደራች ክፍሉን ለቃ ወጣች።በሆስፒታሉ የነበረው ሰው ወደ ክፍሉ ጎረፈ።የአዩብ አይን ላይ ያልተለመደ የአውሬነት ባህሪይ ይነበብበታል።ከአልጋው ላይ ቁጭ ብሎ ሲያለቅስ ለተመለከተው ደግሞ እናቱ ለሱ ምን ማለት እንደነበረች ቃላትን ሳያዥጎደጉድ የሚገባው ሀቅ ነበር።አዩብ ገና በልጅነቱ መከራዎች ተፈራረቁበት።የአባቱን ናፍቆትና ፍቅር ሳይጠግብ የአባቱን ከፊልድ መምጣት ሲጠባበቅ ጀናዛውን ተቀብሎ ቀብሮ የልቡን ስብራት ለመጠገንና የእናቱን ህመም ለማስታመም ሲለፋ የልጅነት መቦረቂያ ጊዜውን ከእህቱ ጋር ሰውቶ በስተመጨረሻ የእናቱን ሞት ሲያረዱት አራስ ነብር ሆነ።ቁጣው ወሰን አጣ።የእናቱን ሞት ልታረዳውና ልታረጋጋው ከፊቱ የተሰየመችውን እናት በጥፊ አላግቶና በጥርሱ ነክሶ ልትናገር የዘረጋቻቸውን ምላሷን ለዋይታዋ አመቻችቶ ሸኛት።የትናንቱን ዶክተር ጨምሮ ሌሎች በሆስፒታሉ የሚሰሩ ሰራተኞች ተንጋግተው ከክፍሉ ገቡ።በዚህ መሃል ትናንት ከቢሮ አስገብቶ ያነጋገረን ድክተር
ብሎ ሲጠጋው አዩብ ከአልጋው አጠገብ ተቀምጦ የነበረውን ብርጭቆ አንስቶ ከሰውየው ራሰ በረሃ ላይ ከሰከሰው።በቦታው የነበሩ ነርሶችና የጥበቃ ባለሙያዎች ግማሾቹ ዘለው አዩብን ያዙት።ገሚሱ የተፈነከተውንና ከረባዳ ጭንቅላቱ ላይ ደም የሚንጮረጮረውን ዶክተር ይዘው ወጡ።እኔም አዩብን ከያዙት ጋር ተጋፍቼ ወጣሁ።ከክፍሉ ስወጣ ቀስዋ በጎረቤቶቿ ግራና ቀኝ ተጠፍንጋ ተይዛ እያለቀሰች ነበር።ለማን ቅድሚያ መድረስ እንዳለብኝ ማወቅ ታከተኝ።እኔም እንደ ቀስዋ ተጠፍንጌ እየጮህኩ ማልቀስ ፈለግኩ።ሆስፒታሉ ውስጥ ግር ግርና ጩኸት ነገሰ።አዩብን እየጎተቱና እያንፏቀቁ ሲታገላቸው ደግሞ ጥበቃዎቹ በዱላ እያሽመደመዱ ይዘውት ከአንድ መጋዘን ከምትመስል ባዶ ክፍል አሽቀንጥረው ወረወሩና ከተቱት።
ይቀጥላል .....❤️🔥
Like 1⃣0⃣0⃣+♥️ካልሆነ ቀጣዩ ክፍል አይለቀቅም🚫
★
@Hafu_posts🪄 || ★ 𝖍𝖆𝖋𝖚 𝖕𝖔𝖘𝖙🌙 ★