አጠቃላይ የክስ ሂደት
🛑🛑🛑🛑🛑🛑🛑♨️
ፍትሐብሔር ማለት ምን ማለት ነው?
የፍትሐብሔር ጉዳይ ከወንጀል ጉዳይ የተለየና በሰዎች መካከል የሚፈጠር መብታዊና ጥቅማዊ ግንኙነቶችን የያዘ ጉዳይ ማለት ነው ብሎ መተርጎም ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፡- የአንድ ሰው የጤፍ ክምር ያለባለቤቱ ፈቃድ ሌላ ሰው ሊጠቀምበት አይችልም፡፡ ይህን ክምር የእኔ ነው የሚል ሌላ ሰው ቢመጣ ከባለቤቱ ጋር የፍትሐብሔር ክርክር ይፈጥራል ማለት ነው፡፡ ክርክሩም በዕርቅ ወይም በፍርድ ቤት መፍትሔ ሊያገኝ ይችላል፡፡
የፍትሐብሔር ክርክር የሚመራዉ በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ በመሆኑ በወስጡ የተደነገጉ አንዳንድ ጉዳዮችን መመለከቱ ጠቀሜታ አለዉ፡፡
ክስ /መልስ/ክርክር/ይግባኝ
ጉዳዮችን በድርድር ስምምነት መፍታት ካልተቻለ ሌላው የመብትና ጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ ክስ ነው፡፡
የክስ ማመልከቻ የክሱን ምክንያትና የሚጠየቀዉን ዳኝነት በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 80 እና 222 መሰረት በዝርዝር የያዘ መሆን ይገባዋል፡፡
ከሳሽ ከክስ ማመልከቻዉ ጋር ስለክሱ የሚያስረዱትን የሰነድ ማስረጃዎች እና የሰዉ ምስክሮች በመዘርዝር እነዚህ ማስረጃዎች የሚያስረዱትን የክስ ምክንያት ጭምር በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 137 እና 223 መሰረት መግለጽ ይኖርበታል፡፡
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 145 መሰረት ደግሞ በእጁ የማይገኙ የሰነድ ማስረጃዎችን ለፍ/ቤት በማስረዳት ማስረጃዉ ከሚገኝበት አስቀርቦ እንዲመረምርለት ማድረግ፡፡ በተጨማሪም የፍርድ ማሰፈፀሚያ የንብረት ተከሳሹ እንዳያሸሽ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 154 መሰረት ለማሳገድ አቤቱታ ማቅረብ፡፡
በመጨረሻም በፍ/ሥ;ሥ/ህ/ቁ 213 መሰረት በሬጅስትራር በኩል ክሱን ማቅረብ ያለበት ሲሆን ሬጅስትራሩም አቤቱታዉ ተሟልቶ የቀረበ መሆን አለመሆኑን በመመርመር አቤቱታዉ ጉድለት ያለበት ከሆነ ለከሳሽ ይመለሰዋል( የፍ/ብ/ሥ/ህ/ቁ 229)፡፡አቤቱታዉ ጉድለት ከሌለበት ደግሞ ተገቢዉ የዳኝነት ክፍያ ተከፍሎበት ፋይል እንዲከፈት ያደርጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ዳኛዉ ከሳሹ የክስ ምክንያት ያለዉ መሆኑንና ጉዳዩም በፍ/ቤቱ የዳኝነት ሥልጣን ዉስጥ ያለ መሆኑን በመመርመር ጉድለት ካለበት ፍ/ቤቱ ተከሳሽን መጥራት ሳያስፈልግ አቤቱታዉን ይሰርዘዋል፡፡ አቤቱታዉ ጉድለት ከሌለበት ግን ተከሳሽ ቀርቦ መልስ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ይሰጣል (የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 231 እና 233)፡፡
በፍ/ቤት መጥሪያ በአግባቡ የደረሰዉ ተከሳሽ እንደከሳሽ የክስ አቀራረብ ሁሉ ህጉ በሚፈቅደዉ ሥነ-ሥርዓት ከሳሽ ያቀረባቸዉን ፍሬ ነገሮች የሚክድበት ወይም የተጠየቀዉን ዳኝነት አይገባም የሚልበትን ምክንያት በመግለጽ መከላከያ መልሱን በቀጠሮዉ ቀነ በጽሁፍ ማቅረብ ::
የመጀመረያ ደረጃ መቃወሚያ
የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያ ማለት ወደ ዋናዉ ፍሬ ነገር ሳይገባ ክሱ ተቀባይነት እንዳይኖረዉ ለማድረግ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244 መሰረትየሚቀርብ ክርክር ማለት ነዉ፡፡
ተከሳሽ ለቀረበበት ከስ መልስ ሲሰጥ የሚከተሉትን የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ማቅረብ ይችላል፡-
ከሳሽ ክሱን በመሰረተዉ ጉዳይ ላይ መብትና ጥቅም እንዲሁም ችሎታ የሌለዉ ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 33 መሰረት በዝርዝር ለፍርድ ቤቱ ማስረዳት፣
በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 244 መሰረት ፍ/ቤቱ ነገሩን ለመስማት ሥልጣን የለዉም በማለት፣ክስ የቀረበበት ጉዳይ አስቀድሞ በፍ/ቤት የተወሰነ መሆኑን፣ ክስ የቀረበበት ጉዳይ በሌላ ፍ/ቤት የክስ
ማመልከቻ ፣መልስ ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን፣አንደኛዉ ተከራካሪ ወገን በነገሩ የማያገባዉ መሆኑን በመግለጽ በጉዳዩ ዉስጥ ገብቶ መከራከር አይገባዉም በማለት፣ ክሱ በይራጋ የተገደ መሆኑን መግለጽ እና ክሱ የተነሳበት ነገር በሽምግልና ታይቶ በስምምነት የተፈፀመ መሆኑን (ለዕርቅ የተቀጠረ መሆኑን) የመገልጹ መቃወሚያዎችን ይመለከታል፡፡ ለእነዘህም ተከሳሽ ምክንያቱን በጹሁፍ ውስጥ መግለጽ ያስፈልጋል (የፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ.234 (1)(ሐ)፡፡ ከዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባዉ ጉዳይ ከላይ የተጠቀሱት የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያዎች ከአንድ በላይ ከሆኑ በአንድ ጊዜ ተጠቃለዉ መቅረብ አለባቸዉ ፡፡ መቅረብ ከሚገባቸዉ መቃወሚያዎች ዉስጥ ሳይቀርቡ የቀሩት ትክክለኛ ፍርድ ለመስጠት የማያሰናክሉ ከሆነ ባለጉዳዩ ራሱ ሆነ ብሎ ለማቅረብ ባለመፈለግ እንደተዋቸዉ ይቆጠራል ስለሚል ቅድመ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል፡፡
ተከሳሽ ከዚህ በላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ሌሎች መቃወሚያዎችንም ማቅረብ የሚችል ሲሆን፡-
• በክሱ ዉስጥ ከከሳሽ ጋር አብሮ መልስ መስጠት የሚገባዉ ወገን ካለ ጣልቃ ገብቶ እንዲከራከርለት በፍ/ብ/ሥ;ሥ/ህ/ቁ 43 መሰረት መጠየቅ፣
• በክሱ ዉስጥ መጨመር የሚገባቸዉ ሌሎች ሰዎች ሰይጣመሩ የቀሩ እንደሆነ እንዲጣመሩ መጠየቅ /የፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 39(2)፣
• የተከሳሽ ከሳሽነት ክስ ወይምመቻቻል ጥያቄ ማቅረብ (የፍ/ብ/ሥ;ሥ/ህ/ቁ 234(1)(ረ) እና 236)
ክስ መስማት
ክስ መስማት ማለት ቀደም ሲል በከሳሽ እና በተከሳሽ የቀረቡትን የክስ ማመልከቻ፣መልስ፣ቀርቦ በክርክር ላይ ያለ መሆኑን የሰነድ ማስረጃ እና የሰዉ ምስክር ዝርዝር መሰረት በማድረግ ፍ/ቤቱ ግራቀኙን ተከራካሪ ወገኖች በቃል እያነጋገረ (እየመረመረ) በክርክሩ ዉስጥ አከራካሪ የሆነዉን ነጥብ ወይም ጭብጥ የሚለይበት ደረጃ በመሆኑ ክስ ለመስማት በተቀጠረበት ቀን ግራቀኝ ተከራካሪ ወገኖች ካልቀረቡ የክስ መዝገቡ መዘጋት ወይም ይግባኝ መዝገቡ መዘጋት ዉጤትን ያስከትላል (የፍ/ብ/ሥሥ/ህ/ቁ 241 እና 269(2)፡፡
በክርክር ወቅት (ክስ በሚሰማበት ወቅት) ተከሰሽ መጥሪያ ደርሶት ያልቀረበ ከሆነ በፍ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 70(ሀ) መሰረት በሌለበት የነገሩ መሰማት የቀጥላል፡፡
በክርክር ወቅት (ክስ በሚሰማበት ወቅት) ከሳሽ ባልቀረበ ጊዜ መዝገቡ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ህ/ቁ 73 መሰረት መዝገቡ ይዘጋል፡፡
ይግባኝ ስለማቅረብና ስለ ይግባኝ ክርክር
ይግባኝ ስለማቅረብ
ከሳሽ ክስ መስርቶ ተከሳሽ መልስ አቅርቦ ሲከራከር በቆየባቸው ጉዳዮች ላይ ፍ/ቤቱ በመዝገቡ ላይ ትዕዛዝ (ብይን) ወይም የመጨረሻ ውሳኔ ሰጥቶ መዝገቡን በሚዘጋበት ወቅት በተሰጠው ብይን
(ውሳኔ) ቅር የተሰኘ ወገን በስነ-ስርዓት ህጉ መሰረት የዉሳኔ ጠይቆ ይግባኝ ቅሬታውን በማዘጋጀት
ከመሸኛ ደብዳቤ ጋር ጉዳዩን ማየት ሥልጣን ላለዉ ፍርድ ቤት አቅርቦ እስከ መጨረሻዉ ይከራከራል፡፡
የግባኝ ባይ ማሟላት የሚገባዉ ነገሮች
የግባኝ ባይ በበታች ፍቤት ቅር የተሰኘበትን የህግና የፍሬ ነገር ክርክሮች (ጉዳዮች) ለይቶ በማዉጣትና ለፍ/ቤት ማስረዳት ይጠበቅበታል፣
መልስ ሰጪ ሲሆን ለተነሱት የጽሁፍ ቅሬታዎች ለእያንዳንዱ መልስ ማዘጋጀት አለበት፡፡
ይግባኝ ሰለ ሚሰማበት ሁኔታ
ይግባኙን ለመስማት በተወሰነዉ ቀነ ቀጠሮ የይግባኙን ምክንያቶች የማስረዳት ግዴታ ያለበት ይግባኝ ባይ ስለሆነ በጽሁፍ ያቀረበዉን ዋኛ ዋኛ ነጥቦች በክርክር በአጭሩ ማስረዳት ያስፈልጋል፣
@Henoktayelawoffice #join