⚠️🛑🛑ወንድም "ኢሳም ሐበሻ" 🛑🛑
🤲 አላህን ፍራ።
✔️ፊልም ትተህ በመምጣትህ በጣም ተደሰትናል አልሐምዱሊላህ።
🛑"ኢስላማዊ" ብለህ ግን ሰው ስታሳስት ጥፋትህ እጥፍ ድርብ ይሆናል።
⚖ "ኡስታዞች" የሚባሉት ስታጠፋ ዝም ስላሉህ ሐቅ ላይ ነህ ማለት አይደለም። እነሱ ታላቁ ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ቢፈፀምም ዝም ነው የሚሉት።
😀 ፕሮግራምህ ላይ ቶርታ ኬክ ካስቆረስካቸው ሰዎች ውስጥ በአላህ ላይ ማጋራት ያለባቸው የክህደት ጭፈራ ስብስቦች ላይ በደስታ አብሮ የሚጨፍር ሰው ይገኝበታል። እንዲህ አይነት ሰዎች ጋር አብርህ የምትሰራቸው ስራዎች ስህተትህን ይበልጥ ያገዝፉብሀል። ወደ አላህ ተመለስ።
💊 ለነፍስህ ፍራ። "25 አመት ፊልም ኢንዱስትሪ ላይ ነበርኩ።" ትላለህ። 25 አመት የሸሪአ እውቀት መሰብሰብ ላይ እኮ አልነበርክም። እንዴት በጥፋት ዘመን ላይ የኖርክበትን ዛሬ ለመስራት ላሰብከው የጥፋት "x ኢስላማዊ ፊልም" መንደርደሪያ ታደርገዋለህ?
🔑 ይልቁንም ለነፍስህ እዘንላት ሀይማኖትህን ተማር እና ወሎ፣ ሰሜኑ ኢትዮጵያ፣ መላው ኢትዮጵያ ላይ አላህ ንሰሃ ሳይገባ ለሞተ ሰው የማይምረው ወንጀል ሺርክ (በአላህ ላይ ማጋራት) ይሰራል። ሰውን በአላህ ፍቃድ ከዚህ ክህደት እንዲወጣ ተምረህ አስተምር ይህም የነብያት መንገድ ነው።
ወሎ ላይ
📱📱📱📱📱📱📱
1) የቦረናው ደግዬ እርዱኝ አባብዬ ይባላል። ይሄ ክህደት ነው።
2) ሙወከል እየተባለ ለሰይጣን ለነ ሰይፉ ጨንገሬ ይታረዳል። ይሄም ከኢስላም ያስወጣል።
…
📱📱📱📱📱📱📱
ታድያ ይሁ ሁሉ ክህደት እና በአላህ ላይ ማጋራት ያለበትን የኢትዮጵያ ህዝብ ጭራሽ ፊልማቸው ኦርቶጉል ውስጥ ኩፍር የጨመሩትን ቱርኮች አንት ልትሰራ ላሰብከው "ፊልም" ጭራሽ እርዳታ መጠየቅህ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ አይሆንምን?
🛑ወንድሜ መልካም ነገር ማለት አንተ መልካም ያልከው ሳይሆን ኢስላም መልካም ያለው ነው።
🎧 ኢስላምን ለማገዝ ከቁርአን ከሐዲስ ኡለማዎች ከሄዱበት መንገድ ውጭ ያለው ሁሉ የጥፋት መንገድ ነው።
😀 ገንዘብ እና ጊዜህን በጥፋት መንገድ ላይ አታባክን።
⚖ አላህ ፊት ብቻችንን ራቁታችንን የምንቆምበት ቀን አለ።
😀 ለአላህ ብለህ ተወው። አላህ በተሻለ እሱ በሚወደው፣ ወደሱ ለሚያቃርብህ አምልኮ አንተንም እኛንም ይለግሰን።
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem