Jafer Books 📚


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha


የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !!

አድራሻችን
ለገሃር ተወልደ ህንጻ ስር
አብርሆት ቤተመጻሕፍት ግቢ ውስጥ
ጥቁር አንበሳ ትምህርት ቤት ፊት ለፊት
ሜክሲኮ ደብረወርቅ ህንጻ ስር
ሳሪስ አዲሱ ሰፈር
ጀሞ
ለቴሌግራም https://t.me/Jafbok
ለፌስቡክ https://www.facebook.com/jaferbookshop?mibextid=ZbWKwL
ለዌብሳይት www.jaferbooks.com

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Statistika
Postlar filtri


የዓለማየሁ ደመቀ " ዮቶር ፪ " ለንባብ በቅቷል ::


" ማማ በሰማይ " ስድስተኛ ዕትም ለንባብ በቃ ::

አንዲት የአስራስምንት ዓመት ጉብል ከአንድ ዐይታው የማታውቅ ወጣት ጋር ልትገናኝ ትወጣለች ::

ከዚህ ቀን ጀምሮ ያጋጠሟትና ያለፈችባቸው ተከታታይ ክስተቶች በሕልሟም ፣ በዕውኗም አይታው / አስባው በማታውቀው ሁኔታ ሕይወቷን ግልብጥብጡን አውጥተው ይለውጡታል :: 

ማማ በሰማይ የፍቅር ታሪክ ነው :: የአብዮትም ፣ የተስፋም ፣ ሕልምም ፣ የአመጽም ፣ የሽብርም ፣ የመተማመንም ፣ የመከዳዳትም ፣ የሰቆቃም ፣ የሰቀቀንም ፣ ራስን በራስ የመለወጥም ፣ የድል አድራጊነትም የነዚህ ሁሉ ሰብዓዊ ረቂቅ ባሕሪያት ታሪክ ነው ::


ሁለት ፍሬ ብቻ አለን ::


#ሰውና_ተፈጥሮው
አዲስ መጽሐፍ

👉5ት ድንቅ ትምህርቶችን እነሆ ለቅምሻ፦

The Laws of Human Nature የተሰኘው የሮበርት ግሪን ድንቅ መጽሐፍ #ሰውና_ተፈጥሮው በሚል ርእስ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ዋለ ።

ታዋቂውን 48 Laws of POWER የተሰኘውን መጽሐፍ 48ቱ የኃያልነት ሕጎችን በሚል በተረጎመችው #ሃኒም_ኤልያስ የተተረጎመ ሲሆን፣ ልክ እንደ #የኃያልነት_ሕጎች_መጽሐፍ ጥፍጥ ብሎ ከተዘጋጀው #ሰውና_ተፈጥሮው አዲስ መጽሐፍ ላይ ለቅምሻ 5ቱን ድንቅ ትምህርቶች እነሆ ብለናል፦


#አንድ
#መርዛማ_ሰዎችን_አስወግድ

ከመርዛማ ሰዎች ጋር አብዝተን የምንገናኝ ከሆነ በአካልም ሆነ በአእምሮ ሊጎዱን ይችላሉ ይለናል። እነዚህ ከልክ ያለፈ ትችት የሚሰጡ፣ ምቀኛ፣ ትዕቢተኛ፣ ጠበኛ ወይም ራስ ወዳድ የሆኑ ሰዎችን ያጠቃልላል።  እነዚህን ባህሪያት በራሳችን እና በሌሎች እንዴት መለየት እንዳለብን እና ራሳችንን ከእነሱ እንዴት ማራቅ እንዳለብን ያስተምረናል።

#ሁለት
#ስሜታዊነትህን_ተቆጣጠር

ስሜታችን ምን ያህል በጥልቅ እንደሚገዛን እና ውሳኔዎቻችንን እና ድርጊቶቻችንን እንዴት እንደሚነካ አናውቅም። ምክንያታዊነትን በማዳበር እነዚህን ስሜታዊ ተፅእኖዎች እንዴት መቋቋም እንደምንችል ማወቅ የግድ ይለናል። እራሳችንን ጠንቅቆ ማወቅ፣ ስሜቶቻችንን ከሥሮቻቸው መፈተሽ፣ የምላሽ ጊዜያችንን ማዘግየት፣ የአስተሳሰብ እና የስሜታዊነት ሚዛንን ማግኘትን የመሳሰሉ ስልቶችንም ሮበርት ግሪን በመጽሐፉ ይጠቁመናል።

#ሶስት
#ከጓደኞችህ_ጋር_አብረህ_ወደ_ገደል_አትግባ

ከሌሎች ጋር ለመስማማትና ብቻችንን ላለመሆን ብለን የሌሎችን አስተያየት ወይም ግምት ከልክ በላይ እንዳንቀበል ያስጠነቅቀናል።  ይህ ግለሰባዊ አቅማችንን እንድናጣ እና ለቡድን አስተሳሰብ እንድንጋለጥ ሊያደርገን ይችላል።

#አራት
#ሳታቋርጥ_የተሻለ_ነገርን_ፈልግ

ባለን ነገር እንዳንረካ እና ሌላ ቦታ ያለን የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ነገር እንድንፈልግ ይገፋናል። ከመጠን በላይ የሆነ ምሬትም ወደ ብስጭት፣ ጭንቀት፣ መሰላቸት ወይም ሱስ እንደሚመራን፣ ከዚህ ይልቅም እስካሁን ያገኘነውን በምስጋና ተቀብለን፣  ራሳችንን በማሻሻል ላይ ማተኮር እንዳለብን ያሳየናል።

#አምስት
#በሰዎች_ጭምብል_ስር_ምን_እንዳለ_ተመልከት

ሮበርት ግሪን፣ ሰዎች ብዙውን ጊዜ እውነተኛ ሀሳባቸውን እና ስሜታቸውን ከራስ መተማመናቸውና ከአካላዊ ውበታቸው ስር  እንዴት እንደሚደብቁ ያሳየናል።  በሌሎች ቃላት እና ድርጊቶች ውስጥ ያሉ የማታለል ምልክቶችን እንዴት መለየት እንደሚቻል ያብራራልናል። እንዲሁም በሰዎች ፊት ሀቀኝነታችንን እና ታማኝነታችንን ሳናጣ እንዴት መጫወት እንዳለብንም ያስረዳናል።

#ሰውና_ተፈጥሮው መጽሐፍ በቅርብ ቀን በገበያ ላይ ይውላል።

👉ሌሎች የሮበርት ግሪን ምርጥ የእንግሊዝኛ መጽሐፍት እጅግ በጥራት ታትመው በገበያ ላይ፦

👇👇👇

#The_Laws_of_Human_Nature

📕📕📕




Classics Fiction , Philosophy and Self Help ORGINAL books ትንሽ ቅጂዎችን አስገብተናል ::


የ ROBIN SHARMA በ 2024 ተጽፎ ለንባብ የበቃው መጽሐፍ ለሀገር ውስጥ ገበያ በቅርቡ ይገባል ::


Nomadic Poems dan repost
⭕️ የመጻሕፍት ወግ | አፍሮጋዳ

“አፍሮጋዳ” የሌሊሳ ግርማ የወግ ስብስብ ድርሳን ነው። በይዘቱም ባሕላዊ፣ ኪነ ጥበባዊ፣ ፖለቲካዊ ጉዳዮችን ይዳስሳል። ጸሐፊው ከዚህ ሥራው በፊት “የነፋስ ሕልም” የተሰኘ የአጫጭር ልብ ወለዶች ስብስብ አሳትሟል። በኋላም “መሬት - አየር - ሰማይ”፣ “የሰከረ እውነታ”፣ “እስቲ ሙዚቃ”፣ “ነጸብራቅ” እና “ይመስላል ዘላለም” የሚሉ የወግና የአጫጭር ልብ ወለድ መጻሕፍትን ለአንባቢያን አድርሷል።


📌 “የመጻሕፍት ወግ” ቆይታውን በሌሊሳ ግርማ “አፍሮጋዳ” ድርሳን ላይ አድርጓል።


የቪዲዮው አድራሻ👇




⭕️ https://youtu.be/MwBTJPMY0dc?si=pFSDz409J3U1ZjQN


ስትሄድ የጠለሸው ገጿ ፈክቷል፡፡
ያከሰመው ሕይወቷ አብቧል፡፡

እንደአዲስ የታደሰችበትን ምክንያት ይረዳ ዘንድ ብዙ አልቆየም፡፡
የሸራረፈው ልቧን ይጠግንላት ዘንድ ፈጣሪ የላከላት ካሳ እንደሆነ አምናለች፡፡

ከድብልቅልቅ የኀዘን ስሜቱ ይወጣ ጊዜ ሳያገኝ ይድህበት የቀረውን እንጥፍጣፊ ጉልበቱን የሚያሟጥጥበት መርዶ ሰማ፡፡

ልትሞሸር ነው፡፡

እሱን ከልቧ አውጥታ ልታገባ ነው፡፡
ያጠፋውን ያርም ፣ ስህተቱን ያቀና እድል ይኖረው አጥብቆ ተመኘ፡፡
ፍቅርን አይመለከት በሀብት የታወረ የቤተሰቦቿን ማስፈራሪያ አይቀበል ዘንድ ወኔ ማጣቱ በቂ ምክንያት አይሆን ይሆናል፡፡

ለዛቻቸው እጅ መስጠቱ ፣ ፍቅሩን መሰዋቱ ዘላለም ይቀጣበት ዘንድ ሳይፈረድበት የሚታቀፈው ቅጣቱ ይሆን ይገባው ይሆናል፡፡

"ዛሬ ቅዳሜ አይደለም"


እነዚህ ተወዳጅ በእንግሊዝኛ የተጻፉ መጻሕፍት አስገብተናል ::


እነዚህ ቢዝነስ ላይ የሚያተኩሩ መጻሕፍት አሉን :: ከእያንዳንዳቸው አንድ አንድ ፍሬ ነው ያለን ::

ለማዘዝ  @abumame  ያውሩን ::

11 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.