ልሣነ አምሐራ ሚዲያ


Kanal geosi va tili: Efiopiya, Amharcha
Toifa: Siyosat


በዚህ ቻናል ፈጣንና ወቅታዊ የአማራ ፋኖ እለታዊ ዘገባዎች እንድሁም ፈጣን ዜናዎች ይቀርባሉ።
ለማንኛውም ጥቆማ በ @lisaneamhara ያናግሩን‼️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Kanal geosi va tili
Efiopiya, Amharcha
Toifa
Siyosat
Statistika
Postlar filtri


በዛሬው እለት የስናን አባጅሜ ብርጌድ እና የንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ ፋኖዎች በጥምረት ጀብድ ፈፅመዋል‼

የአማራ ፋኖ በጎጃም በቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ክፍለጦር  አባል ብርጌዶች የስናኑ ስናን አባጅሜ ብርጌድ እና የደብረ-ማርቆሱ ንጉስ ተክለሃይማኖት ብርጌድ በጋራ በመሆን ከደብረማርቆስ ተነስቶ ወደ ረቡ ገበያ ባለስልጣናቱና ለመሸኘት እና ሬሽን ለማቀበል የተንቀሳቀሰዉን ጠላት አፈር ደቼ አብልተውታል::

በዚህም:

12 ክላሽ
1 ስናይፐር
ከ8 በላይ የወገብ ትጥቅ ከነሙሉ ሎዱ መማረክ የተቻለ ሲሆን 1 ፓትሮል ተቃጥሏል::

በርካታ ቁጥር ያከው የጠላት ሀይል ሲሸኝ የቆሰለውም ብዛት ያለው ነው ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።




#በአዋጅ_ቀን_ጀብድ‼

ልማደኛው #ዘንገና_ብርጌድና #ግዮን_ሰከላ ብርጌድ መብረቁ ሻለቃ ሁለቱ ተናባቢ ነብሮች ጠላትን ምርኮኛ ሙትና ቁስለኛ በማድረግ ታላቅ ድልን ተቀዳጅተዋል። ቀኑ አንድነት የተበሰረበት የጠላትን ቅስም የሰበርንበት ድማማ ዲክላሬሽን በመባል የሚታወቅና እየተከበረ ያለበት ታሪካዊ እለት ነዉ።

በዚህ ቀን ነዉ እንግዲህ ከሰከላ ወደ ቲሊሊ ተንቀሳቅሶ ሬሽን ለመቀባበል በማሰብ እንደቄጣማ ሲያረግድ ሲጨነቅ ሲጠበብ ቢዉልም በተያዘበት ደፈጣ ሰተት ብሎ ገብቶ ምርኮኛ ሙትና ቁስለኛ ሁኗል።
ከቀኑ 8:00 የጀመረዉ ዉጊያ አድማሱን እያሰፋ ከአሽፋ መገንጠያ እስከ አምቢሲ ዘልቋል።

የኔ ጠላት ያንተ ጠላት ምንለዉ የለንም፤እንደ አማራ ወጠን እንደ አማራ እናሸንፋለን።
በአንድነት ስንሆን እንዲህ ድል በድል ሁነን እንደምቃለን💪

ዝርዝር ምርኮ ከቆጠራ በኋላ የምናደርስ ይሆናል።

ኢትዮ 251 ሚዲያ




የቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የመጀመሪያ ጉባኤውን ማካሄዱ ተገለፀ::

በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የአማራ ፋኖ በወሎ (ቤተ አምሓራ) ቅርንጫፍ የሆነው ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር የምዕራብ ወሎ ቀጠና ውስጥ ባሉ 11 ወረዳዎች ውስጥ የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከጃማ እስከ ሳይንት እንድሁም ለጋምቦ እና ከላላ ድረስ ሌሎች ወረዳዎችንም አካሎ ከየአቅጣጫው በተውጣጡ ፋኖዎች የተዋቀረ ክፍለ ጦር ነው ተብሏል::

ክፍለ ጦሩ በኮማንዶዎች እንደሚመራም ነው ለማወቅ የቻልነው::

የጀግኖች ስብስብ የሆነውና በንፁሁ ታጋይ ስም የተሰየመው የዚህ ክፍለ ጦር አንዱ ከፍተኛ አመራር ጥር 6 ቀን 2017 ዓ/ም በርካቶችን ጥሎ መስዋዕትነት ሲከፍል ከ4 ወረዳዎች በውጭጩ የመጣው ጠላት ከ60 በላይ ኃይሉ ተደምስሶበታል::

በጥር ስድስቱ ውጊያ የተወርዋሪ ክፍለ ጦሩ ወታደራዊ አዛዥ ኮማንዶ ተመስገን አለምነው መስዋዕትነት የከፈለው ከበባ ሰብሮ እና በርካቶችን በመጣል ጀብዱ ፈጽሞ መሆኑን የምዕራብ ወሎ ኮር ባወጣው የሀዘን መግለጫ ላይ አስታውቋል::

የምዕራብ ወሎ ኮር አዛዥ አርበኛ አደም አሊ በተገኘበት ጉባኤውን ያካሄደው ተወርዋሪ ክፍለ ጦሩ በጎደሉ አመራሮች ቦታ አዳዲሶችን ተክቷል::

ጎርጎራ ቲቪ - ከእውነት ጋር
የጠብመንጃ አንጋቾች ድምጽ


የመብረቁ ተፈራ ኮማንዶና አንደኛ ሻለቃ ጥምር ጦር አራጢ (ወይንውሀ መገንጠያ) ላይ ጠላትን እየረፈረፉት ነው።


የደብረ ኤልያስ ቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች በጠላት ላይ ድልን ተቀዳጁ!
==============================================

ራሱን መከላከያ እያለ የሚጠራው የፋሽስታዊው አብይ አህመድ ወንበር አስጠባቂ የሽብር ቡድን ደብረ ኤልያስ ከተማ ገብቶ በጀግኖቹ የአማራ የቁርጥ ቀን ልጆች መገረፍ ከጀመረ ድፍን ሁለት ወራት አልፈዋል።በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ በርካታ የወራሪው ጦር እስከ ወዲያኛው ተሸኝቷል።በርካቶችም ቆስለዋል።
ቀደም ብሎ ካስገባው የጠላት ኃይል በተጨማሪ ከሰሞኑ በርካታ ሰራዊት ማስገባቱ ይታወቃል።ይህም የወረዳውን ገጠራማ አካባቢ ለመቆጣጠርና በዋናነት ግን የብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ስላሴ አንድነት ገዳምን በድጋሚ ለማውደም እየተደረገ ያለ እንቅስቃሴ ነው።

ዛሬም ከደብረ ኤልያስ ከተማ ሙሉ ጦሩንና መሳርያዎቹን ጭኖ ወደ ጓይ መገንጠያ በተንቀሳቀሰው የጠላት ኃይል ላይ ጀግኖቹ የቀስተ ደመና ብርጌድ ፋኖዎች ከፍተኛ የሆነ ውጊያን በመክፈት ታላቅ ኪሳራን አድርሰውበታል።በአርበኛ ድረስ አለማየሁና አርበኛ ነጋ መኮንን የተመራው ይህ ውጊያ የጠላትን ቅስም የሰበረ ነበር።ጠላት በዙ-23ና በሞርተር የታገዘ ውጊያ ቢያደርግም ቀስተኞቹ ግን ከምሽጋቸው ፍንክች ሊሉ አልቻሉም።

በዚህ ውጊያ በወገን በኩል ቀላል ቁስለኛ ከሆኑ ጥቂት ፋኖዎቻችን ውጭ የተከፈለ መስዋዕትነት የሌለ ሲሆን በጠላት በኩል ግን 16 አምቡላንስና ፓትሮል በቁጠር ደረጃ ከ112 በላይ ቁስለኛ የተነሳ ሲሆን የሟቹን መጠን ግን በተረጋገጠ መረጃ ማወቅ አልተቻለም።ምክንያቱም በየቦታውና ምሽግ ባደረጉት የሳሰር ቤተ ክርስቲያን ይቀብሩት ስለነበር ነው።ይሁን እንጅ ከቁስለኛው በላይ ሊሆን እንደሚችል ግን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸውልናል።

ጠላት በአሁኑ ሰዓት በጎፍጭማ ታዳጊ ከተማና የቀጋት ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚገኝ ሲሆን የትኩረት አቅጣጫውም የብሔረ ብጹዓን አጼ መልክዓ ሥላሴ አንድነት ገዳምን በድጋሚ ለማውደም እንደሆነ ይታወቃል።

ደብረ ኤልያስ ግን ጠላትን ውጣ ማስቀረቷን ቀጥላለች ትቀጥላለችም።

ድል ለሕዝባችን!
ክብር ለሰማዕቶቻችን!
አዲስ ትውልድ፣አዲስ ተሰፋ፣አዲስ አስተሳሰብ!

ፋኖ ኢ/ር ዘመን ባሳዝነው
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ 6ኛ ክፍለ ጦር
የቀስተደመና ብርጌድ ፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ

ጥር 19/2017 ዓ.ም




ጀግናው ተሰውቷል:: እኔም የሰማሁት ዘግይቼ ነው!!

ለነገሩ እሱ ቢሰዋም የልቡን ሰርቶ ነው:: በአጠቃላይ ሰሞኑን በአማራ ሳይንት ቀጠና በሰፊው የምዕራብ ወሎ ግንባር ነገሮች በፍጥነት ተቀይረዋል::

2 መከላከያ እና ሚሊሻዎች የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይንት መቅደላ ክፍለ ጦር አትሮንስ ብርጌድን በመሀል ሳይንት ወረዳ ግንባር ተቀላቅለው ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል የሚል መረጃ አሁን ደርሶኛል:: የአትሮንስ ብርጌድ አዛዥ ፋኖ ጎሹ ታረቀኝ የጠላትን አቅም እያሽመደመደው ነው:: ቁልፍ አዋጊዎችን አምጥቶበታል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ በዚሁ በአማራ ሳይንት ቀጠና በለጋምቦ ወረዳ ግንባር ገነቴ አቅራቢያ ሰሞኑን ታሪክ ሲሰራ ሰንብቶ ኖሯል:: ጥር 6 ለ7 ሌሊት በተደረገ ጦርነት የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር አደራጅ ኮሚቴ አባል እና የክፍለ ጦሩ ስራ አስፈጻሚ የሆነው ኮማንዶ ተመስገን ሳይንቴው ጀብዱ ፈፅሞ በጀግንነት ተሰውቷል::

የኮሩ ጊዜያዊ ኮሚቴው ተሰባስቦ አዳዲስ ስራ አስፈጻሚዎችን በመሰየም በሰራዊቱ ሊያፀድቅ ከየቦታው ተሰባስቦ ለጋምቦ ወረዳ እና ወግዲ ወረዳ ድንበር አቅራቢያ የምትገኝ ብስቁልል የምትባል መንደር ውስጥ ከኮሩ አዛዥ አርበኛ አደም አሊ ጋር ውይይት ላይ ሳሉ የኮሩ አዛዥ አጃቢ የነበረና ከቀናት በፊት ከድቶ ወደ መንግስት የገባ የየሹም አካባቢ ተወላጅ ባንዳ ከወግዲ ወረዳ በኩል ጠላትን እየመራ መጥቶ ከሌሎች የጎረቤት ወረዳዎችም ተጨማሪ ኃይል በቦታው በመድረስ ሌሊት ከባባ ቢፈፅምም ጀግኖች በታትነውታል::

ሞት አይፈሬው ሳይንቴ ከ4 ወረዳዎች የጥምር ጦሩ ጊዜያዊ ካምፓች ተውጣጥቶ በመጣ ከ400 የማያንስ መከላከያ እና እልቆ የለሽ አ.ሚ.ፓ. (አጥቦ አይለብሴ ሚሊሻ...አድማ ብተና እና ፓሊስ) ድብልቅ ሰራዊት ጋር በነበረው ትንቅንቅ በርካታ ጠላት ደምስሶ ተሰውቷል::

የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አዛዥ አርበኛ አደም አሊ ጋር ውጊያን በመምራት ላይ ሳለ ነው ኮማንዶ ተመስገን የተሰዋው:: ፊት ለፊት ሲዋጋ ቆይቶ ከበባ ሰብረው እና ጠላትን ከምሽጉ ነቅለው በማስፈርጠጥ ታላቅ ገድል እየፈፀሙ ባሉበት ቅጽበት ነው በድንገት የተመታው::

በዚህ አውደ ውጊያ ከወግዲ በኩል ከመጣው ጥምር ጦር ብቻ 30 በጥይት ቀምሶ 17ቱ ሙት ሲሆን ቀሪው ቆስሏል::

በለጋምቦ በኩልም ከዚህ ያላነሰ ቁጥር ያለው ጠላት ተደምስሶ 20ዎቹ ጊምባ ተቀብረዋል:: ከ5 ቀናት በኋላ ከትናንት በስቲያ አስከሬን ለቀማ ወደ ውጊያው ቀጠና የተጓዘው ጠላት አርሶአደሮችን አፋልጉኝ ብሎ አስገድዶ ሲፈልግ ቆይቶ የ6 ወታደሮችን እግር አግኝቷል::

በብስቁልሉ ኦፕሬሽን በድምሩ ከ60 በላይ ጠላት እንደተመታ ነው መረጃዎች የሚያሳዩት:: የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር ቀኝ አዝማች ይታገሱ አረጋው ተወርዋሪ ክፍለ ጦር ኦርዲናንስ ኃላፊን ጨምሮ አንድ የንጉሥ ሚካኤል አሊ ክፍለ ጦር ፋኖ መቁሰሉ የተገለፀ ሲሆን ከኮማንዶ ተመስገን ሳይንቴው ጋር መስዋዕትነት የከፈለም ሳይኖር እንዳልቀረ ነው የሰማሁት::

በጥቂት መስዋዕትነት አስገራሚ የሚባል ጀብዱ ተፈፅሟል ኮማንዶ ተመስገን እንደተሰዋም አንቆጥረውም ሲሉ ነው ጓዶቹ የገለፁት:: ሞት አይፈሬው ጀግና የሳይንቴይቱ ልጅ ከአዲስ አበባ ድረስ ወደ ግንባር ከገባ ሁለት ወር አልሆነውም:: የቀኝ አዝማች ይታገሱን ደም የምንመልሰው ህዝባችን ነጻ ሲወጣ ነው ብሎ የወንድሙን ደም ሊመልስ ገብቶ የልቡን ሰርቶ ተሰውቷል:: ለቃሉ ታምኖ የወንድሙንም አደራ ተሸክሞ እስከ ሞት ድረስ በሀቅ ታግሎ አርፏል:: ይህ ወርቃማ ዕድል ነው:: የዚህ ታሪክ ባለቤት ሆኖ ስም አስሮ መሰዋት መታደል ነው እንጅ ሞት አይባልም!!

ለወዳጅ ዘመድ እና ለጓዶቹ በሙሉ መጽናናትን እመኛለሁ!! ነፍስ ይማር!!


የጎንደር ፋኖ አንድ ሆነ✊




ምዕራብ ጎጃም ከቡሬ ከተማ ወጣ ብሎ ደረቋ ላይ ሀይለኛ ጦርነት በመካሄድ ላይ ሲሆን ከቡሬ ከተማ ታንክ እዬሄደ ይገኛል አስፈላጊው ጥንቃቄ እንዲደረግ መረጃው በአስቸኳይ ይዛመት።


የጣናው መብረቅ ብርጌድ ከባህር ዳር አፍጫ ስር በምትገኘው መሸንቲ ከተማ ውስጥ ትናትን 8 ሰአት ላይ የተሰካ ኦፕሬሽን ሰርቷል::




🔥🔥የዞዝ አምባ ንጉስ ክ/ጦር አስደናቂ የደፈጣ ኦፕሬሽን🔥🔥

👉የአማራ ፋኖ በጎንደር፦ የዞዝ አምባ ንጉሥ ክ/ጦር ትንታጎች ጥር 01/2017 ዓ.ም በሁለት ግንባሮች በተጠና ደፈጣ ወራሪ ሠራዊቱ ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል።

👉 የመጀመሪያ ግንባር ከእብናት በአራት ኦራል ተጭኖ ቋሊሳን ለመያዝ የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊት ልዩ ቦታው ገላ ማጠቢያ የተባለ ቦታ ላይ ደፈጣ የጣሉት የዞዝ አምባ ንጉሥ ክ/ጦር፣ ተከዜ ግንባር ናደው ብርጌድ ባለ ልዩ ተልዕኮ መብረቆች አማካይነት በተወሰደ መብረቃዊ ጥቃት በርካታ ሙትና ቁስለኛውን እያዝረከረከ ፈርጥጦ ወደ እብናት ገብቷል።

👉 ሁለተኛው  ግንባር በተመሳሳይ ከእብናት በአራት ኦራል ተጭኖ ቆላ መልዛ ኒቋራ ከተማን ለመያዝ የተንቀሳቀሰን ወራሪ ሠራዊት በሌላኛዋ አግኝቸው ቢተዋ ብርጌድ በተጣለ ደፈጣ ከ20 በላይና በርካታ ቁስለኛውን እያዝረከረከ ፈርጥጦ እንደለመደው እብናት ከተማ ገብቷል።

     ኅልውናችን በተባበረ ክንዳችን!!!

የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕ/ግንኙነት መምሪያ


ወሎ ቤተ አምራ ውስጥ አስደናቂ ድል ተመዘገበ:-

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ታሪካዊ ድል አስመዝግቧል::
-
ትናንት ታህሳስ 30 ቀን 2017 ዓመተ ምህረት ከወረዳው መቀመጫ ማሻ ከተማ ወደ ኮሬብ በሲኖትራክ ሲንቀሳቀስ የነበረ አድማ ብተና ላይ በተፈፀመ ድንገተኛ ጥቃት ሲኖትራኩ ላይ ያሉት አድማ ብተናዎችን እሳት በልቷቸዋል::
-
ደምወዝ ተቀብለው ሲገሰግሱ ድስም የምትባል ቦታ ላይ ነው ጭዳ የተደረጉት:: የአማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ምክትል አዛዥ ፋኖ ሙሀመድ አሊ (ጭንቅየለሽ) እና የሼህ ሁሴን ጅብሪል ብርጌድ ዋና አዛዥ ፋኖ በለጠ ምትክ (ድሮን) በመሩት በዚህ ኦፕሬሽን አስደናቂ ድል ሊመዘገብ መቻሉን የአማራ ፋኖ በወሎ ምዕራብ ወሎ ኮር አማራ ሳይት መቅደላ ክፍለ ጦር ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ፋኖ ቃለአብ ወርቅዬ አስታውቋል::
-
በዚሁ በመቅደላ ወረዳ ውስጥ ታህሳስ 28 ቀን አቶ ኢብራሂም የተባለ ግለሰብ ከኮሬብ ወደ ማሻ ከተማ የቤተሰቡን እና የጎረቤቹን የሴፍቲኔት ገንዘብ ለመቀበል እንደመጣ መነሀሪያ ፊት ለፊት ህይወቱን በግፍ ተነጥቋል::

ይህ ግለሰብ ከፋኖ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት የሌለው ሲሆን ከዚህ ቀደምም አንድ የባጃጅ ሾፌርን ሙዚቃ ለምን ከፈትክ ብለው ህይወቱን ተነጥቋል ተብሏል::

ጥምር ጦሩ በንፁሀን ላይ አሰቃቂ ግፍ መፈፀሙን ቀጥሏል ያለው ፋኖ ቃለአብ ይህን ግፍ የሚፈፅም ጠላት ጋር ንግግር ስለሌለን በምክክር ኮሚሽን ስም ደሴ ተሰባስቦ የሚመክር አካል ወደ እኛ ቢመጣ ቅጣታችን የከበደ እና እስከ ሞት የሚደርስ ነው ብሏል::




ፋኖ ጋዜጠኛ ወግደረስ ጤናው የአማራ ፋኖ በጎጃም የህዝብ ግንኙነት ክፍል ስራ አስፈፃሚ አባል በመሆን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና ሀላፊ በመሆን ተሹሟል!


ሰበር~ የድል ዜና

ጣርማበር፣ ደብረሲና ፣ ሸዋሮቢትና ራሳ !!

ሳምንት ያስቆጠረው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ተጋድሎ

ታህሳስ 25/2017 ዓ.ም

ከሳምንት በላይ በሸዋ ወደ ራሳ ያለ የሌለ ሀይሉን ለቃቅሞ ወደ ራሳ ለመግባት የሞከረው የምርኮኛው ብርሃኑ ጁላ ሰራዊት መውጫ ጠፍቶት በራሳ ሸለቆዎች ላይ እየረገፈ ይገኛል። በረሃብና በውሃ ጥም የተዝለፈለፈው ወራሪው ሴት ደፋሪ የአብይ አህመድ ስልጣን ጠባቂ ቅጥረኛ ሰራዊት ወደ አልሞ ተኳሾቹ ቀዬ ዘው ብሎ ገብቶ መውጫ ጠፍቶት እየተገረፈ ይገኛል።

ድሽቃን እንደክላሽ የሚተኩሱት የመከታው ማሞ ልጆች ዛሬ አድማሱን ባሰፋው አውደ ውጊያ በጣርማበር ፣ደብረሲና ሾላሜዳ ላይ በሞርተር የታገዘ ትልቅ ትንቅንቅ እያደረጉ ይገኛሉ። አርበኛ ስንታየሁ ማሞ(ራንቦ) ክፍለጦር ፤ማንበግር ንጉስ ሻለቃ ከደብረሲና ጣርማበርና ሻላሜዳ የጠላትን ሀይል እየገረፈችው ትገኛለች። በተጨማሪ የአፄ ዘረያዕቆብ ክፍለጦር ጣይቱ ብርጌድ አንድ ሻለቃ በራሳው አውደውጊያ እየተሳተፈች ነው።

በሌላ ግንባር ደጃዝማች ተሳማ አርገጤ ክፍለጦርና 7ለ70 ክፍለጦሮች በሸዋሮቢት ዙሪያ ማፉድና ገደባ የጠላትን ጦር እያረገፉት ይገኛሉ። በአውደውጊያው የጠላት ዙ-23 ከጥቅም ውጪ ሲሆን ከሸዋሮቢት አካባቢ ያለው የጠላት ሀይል መድፍ እያስወነጨፈ ይገኛል። በተመሳሳይ ገደባ ጊዮርጊስ ላይ የጠላት አንድ ኦራል ሲማረክ ከአንድ ሻለቃ በላይ ሀይል ተደምስሷል። 

ድል ለአማራ ህዝብ !!
ድል ለአማራ ፋኖ !!



20 ta oxirgi post ko‘rsatilgan.