በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነዉ የ3D LED ስክሪን በአዲስአበባ ተመረቀበኢትዬጲያም ሆነ በምስራቅ አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የ3D LED ስክሪን በኤፔክስ ትሬዲንግ ስር በሆነዉ የኔ አድ የማስታወቂያ ድርጅት በቦሌ መንገድ ወደ ጃፓን ኢምባሲ በሚወስደዉ መስቀለኛ መንገድ ላይ ነው የተቀመጠው።
ስክሪኑ በ 1 መቶ 60 ካሬ ሜትር ላይ ያረፈ ሲሆን በግዙፍነቱ እንዲሁም በምስል ጥራቱ ከሚታወቁት ማያ ገጶች እጅግ የላቀ ነዉ ተብሏል ፡፡
የኤፔክስ ትሬዲንግ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሮቤል ደጉ ይህ የ 3 D ስክሪን በአለማችን በጥቂት ትልልቅ ከተሞች ብቻ የሚገኝ ሲሆን እጅግ የረቀቀ ቴክኖሎጂን ይጠቀማል ብለዋል ፡፡
ስራ አስኪያጁ ቴክኖሎጂዉ የከተማን ገፅታ ከማሳደግ አኳያ ሚናዉ ከፍተኛ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በአዲስ አበባ በአራቱም አቅጣጫ ለማስቀመጥ መታቀድን አስታዉቀዋል ፡፡
ይዘትን በተጨባጭ መልኩ ለማሳየት እና በመንገድ ላይ ትላልቅ ማስታወቂያዎችንና መረጃዎችን ሳቢ በሆነ መልኩ ለማሰራጨት የሚረዳ ነው።
ኤፔክስ ትሬዲንግ መቀመጫዉን ቻይና ሃገር ያደረገ ሲሆን በኢትዬጲያ የኔ አድ የተባለ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፍቶ እየሰራ ይገኛል ፡፡
አቤል እስጢፋኖስ
ጥር 9 ቀን 2017 ዓ.ም
via
Ethio FM 107.8 (author: Ethio Admin)