❖ጥር 1️⃣8️⃣
https://youtu.be/n_cvi9wKGxo?si=LYxCZ7t63VD8Rli9☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
ሙሉው ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስን ያድምጡ
ዝርወተ አጽሙ ለቅዱስ ጊዮርጊስ #የንግሥ በዓል እንኳን አደረሰን
❖ጥር 18 ቀን"ዝርወተ አጽሙ"ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ነው፡፡ይህች ዕለት ለሰማዕቱ በቁሙ አጥንቱ የተበተነበት እንደ ማለት ነው፡፡
❖ቅዱስ ጊዮርጊስን ለዘመናት በብዙ ስቃያት ሲያስጨንቁት ኖረው በጽናቱ አሸነፋቸው፡፡70 ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ከማሳፈሩ ባሻገርም በርካታ በመቶ ሺ የሚቆጠሩ አሕዛብን ማርኮ ለሰማዕትነት አበቃ፡፡በዚህ የተበሳጨው #ዱድያኖስም ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስን እንዲቆራርጡት አዘዘ፡፡ወታደሮቹም ቅዱሱን ቆራርጠው በብረት ምጣድ ላይ ጠበሱት ያለርህራሔም አካሉን አሳረሩት ቀጥለውም ፈጭተው አመድ አደረጉት በአከባቢው ወደነበረው ትልቅ ተራራ #ደብረ ይድራስ ወጥተው በነፋስ በተኑት፡፡
❖እነርሱም ይሀንን ፈጽመው ዞር ስሉ ግን የቅዱሱ አጽም ባረፈባቸው #ዛፎች #ቅጠሎችና #ድንጋዮች ሁሉ"#ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት"የሚል ጽሐፍ ተገኘ፡፡
❖ስለዚህ ይህች ዕለት ቅዱሱ የሰማዕትነት አለቅነት የተሾመባት ዕለት ነች ማለት ነው፡፡
❖ወዲያው ግን ኃያል ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከተበተነበት ተነስቶ ወታደሮችን አገኛቸው" #በክርስቶስ እመኑ"ብሎ አስደንቆ ወደ ሕይወት መራቸው፡፡70ው ነገሥትም አፈሩ፡፡
❖የሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ አማላጅነት ጸሎት በረከት ይደርብን፡፡
❖አሜን ❖አሜን ❖አሜን