በንግድ ማጭበርበር እና ኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣ የነበረ ከ107 ቢሊዮን ብር በላይ ማዳን ተችሏል
ጥር 05/2017 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እንደቀጠለ ነው።
በግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ ባለፉት ስድስት ወራት በጉምሩክ ኮሚሽን በሁሉም ዘርፎች ተጨባጭ ውጤቶች መመዝገባቸው ተመላክቷል።
በተለይም ኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበርን በመከላከል እና መቆጣጠር ዙሪያ ስኬቶች ተመዝገበዋል::
በግምገማው ወቅት ባለፉት ስድስት ወራት 7.38 ቢሊዮን ብር የሚገመቱ የገቢ ኮንትሮባንድ እና 1.57 ቢሊዮን ብር የወጭ ኮንትሮባንድ በድምሩ 8.95 ቢሊዮን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል።
በኮንትሮባንድ ዝውውር የተጠረጠሩ 708 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር ውለው አስፈላጊው ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው እየተደረገ ነውም ስለመሆኑ ተጠቅሷል።
በተጨማሪም በንግድ ማጭበርበር ማለትም በኢንተለጀንስ ስራዎች ፣ በድንገተኛ ፍተሻ፣ በቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ቁጥጥር፣ በድህረ ዕቃ አወጣጥ ኦዲት ፣ በመደበኛ እቃ ፍተሻ እና ሰነድ ምርመራ 98.29 ቢሊዮን ብር ገቢ መገኘቱ ተመላክቷል።
በመድረኩ በጠቅላላ በ2017 የበጀት ዓመት የመጀመሪያው ግማሽ ዓመት በንግድ ማጭበርበር እና በኮንትሮባንድ መንግስት ሊያጣው የነበረ 107.24 ቢሊዮን ብር ማዳን መቻሉን ተገልጿል፡፡
ኮንትሮባንድና ንግድ ማጭበርበርን በመከላከልና በመቆጣጠር ረገድ የኮሚሽኑ አቅም ከጊዜ ወደጊዜ እየጎለበተ መሆኑንም በመድረኩ ተጠቅሷል።