አዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት በዲጂታላይዜሽን ቴክኖሎጂ የወረቀት አልባ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አደረገ።
አዘና ጥር 22/2017 ዓ.ም (አየሁ ጓ/ኮሙኒኬሽን)
በአዊ ብሔ/አስ/አየሁ ጓ/ወ/የአዘና ከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት የከተማ መሬት መረጃ አያያዝና አስተዳደር ስርዓትን በማዘመን የካይዘን ፍልስፍናን ተግባራዊ በማድረግ ለተጠቃሚው/ለደንበኛው ማህበረሰብ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በራሱ አቅም ሶፍት ዌር በማበልጸግ በቅርብ ጊዜ ማስመረቁ የሚታወቅ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ተቋሙ በዲጂታላይዜሽን ስርዓት አገልግሎት ለመስጠት አጠቃላይ ስራው አጠናቆ የወረቀት አልባ አገልግሎት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ አድርጓል።
የተቋሙ ዋና ስራአስኪያጅ አቶ ወንድም ምህረት የወረቀት አልባ አገልግሎትን ለመስጠት በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረጉ ሲሆን ይህ ቴክኖሎጂ ከአደጋ ስጋት ነፃ፣ ለአገልግሎቱ ፈጣን፣ የባለይዞታውን የፋይል ደህንነት የሚጠብቅ፣ ዋስትናው የተረጋገጠ፣ ተጠቃሚው ማህበረሰብ ከተቋሙ በተሠጠው መለያ ኮድ መሠረት ፈጣን፣ ቀልጣፋና ከሐሜት የፀዳ አገልግሎት የሚያገኝበት መሆኑን አብራርተዋል።
ከተቋሙ አገልግሎት ተጠቃሚው ማህበረሰብ በያዘው መለያ ኮድ መሠረት ከዛሬው ቀን ጀምሮ የወረቀት አልባ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችል ይፋ ያደረጉት አቶ ወንድም ይህ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ እውን በመሆን በሲስተም የወረቀት አልባ አገልግሎት በመጀመሩ እንኳን ደስ አላችሁ/አለን ብለዋል።
የአዘና ከተማ መሪ ማ/ቤት የወረቀት አልባ ሲስተም ይፋ ባደረገበት በዛሬው ዕለት በቦታው የተገኙት የወረዳው ከተማና መሠረተ ልማት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ አየነው ዋሲሁን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት በማስተላለፍ ይህ ቴክኖሎጂ እውን እንዲሆን ለስኬት እስከሚደርስ የተሳተፉ ለአቶ መሀመድ አሚን፣ ለተቋሙ ስራአስኪያጅና መላ ሠራተኞች፣ ለከተማው ማህበረሰብና የድርሻውን ለተወጡ ሁሉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።